TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዛሬም የድጋፍ ሰልፎች ዛሬም እየተደረጉ ነው...

በዛሬው ዕለት የካቲት 12 ዓ/ም በበደሌ ከተማ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድን የለውጥ አመራር የሚደግፍ ሰልፍ እየተደረገ ይገኛል። የሰልፉ ተሳታፊዎች እንደነገሩን ሀገር በጥላቻ፣ በስድብ እና የሰዎችን ስራ በማሳነስ አይገነባም፤ የተለያዩ አካላት ከስድብ እና ከማንቋሸሽ ይልቅ ለህዝብ ያላቸውን ሀሳብ ያቅርቡ ህዝቡ የሚሆነውን ይመርጣል የሚል መልዕክት በሰልፉ ተላልፏል።

በተመሳሳይ፦

በሻሸመኔ ከተማ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይን የለውጥ አመራር የሚደግፍ ሰልፍ እየተደረገ ይገኛል። በስለፉ የከተማው ነዋሪዎች የትኛውም ወገን ከስድብና ከጥላቻ እንዲቆጠብ መልዕክት ተላልፏል።

በሌላ መረጃ፦

ትላንት ምሽት ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን ቢሮ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ እንደተመለከትነው ነገ ዓርብ የካቲት 13 የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስራ የሚያበረታታ፣ የለውጥ ኃይሉንም የሚደግፍ ሰልፍ ይደረጋል ተብሏል።

[ፎቶ : በደሌ እና ሻሸመኔ ቲክቫህ ቤተሰቦች]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሸገር ዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታ...

በሜድሮክ እህት ኩባንያ ‹‹ሆራይዘን ፕላንቴሽን›› እየተገነባ ያለው የሸገር ዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ ተጠናቆ ሥራ ሊጀምር የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደደረሰ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ።

በሆራይዘን ፕላንቴሽን የእቅድ ቢዝነስ ልማትና ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ ይበልጣል ሽመልስ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት ግንባታው ከተጀመረ ወራትን ያስቆጠረው የሸገር ዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል።

የመሰረት ድንጋይ ከተጣለ ጀምሮ ሥራው በጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እየተመራ እንደነበር የተናገሩት ሥራ አስኪያጁ በቀን 18 ሰዓት በመስራት ግንባታውን ማፋጠን እንደተቻለና ጎን ለጎንም የማሽነሪዎችንና የሌሎች ግብዓቶችን ግዢ ተፈፅሞ ሀገር ውስጥ መግባታቸውን ገልጸዋል።

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን ጋዜጣ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢንጅነር ስመኘው በቀለ የመታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ!

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ የነበሩት የኢንጅነር ስመኘው በቀለ የመታሰቢያ ሐውልት በዛሬው ዕለት ተመረቀ፡፡

በመታሰቢያ ሐውልቱ የምርቃት ሥነ ስርዓት ላይ በኦርቶዶክስ እምነት ስርዓት መሰረት የፍትሃትና የፀሎት ሥነ - ስርዓት ተካሂዷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በሐውልቱ ምርቃት ስነ ስርዓት ላይ የተገኙ የተለያዩ ድርጅቶ፣ ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፡፡

[የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SolveITAccelerator

Icog Labs ከJICA ጋር በመተባበር ከኩዱ ቬንቸር በተገኘ ድጋፍ Solve IT Accelerator በተሰኘ ፕሮግራማቸው ለሥራ ፈጣሪዎችን ለማብቃት ፣ የገንዘብ ድጋፍ እንዲሁም የተለያዩ ስልጠናዎችንና ድጋፎችን ለማድረግ መጨረሳቸውን አዘጋጆቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

Solve IT Accelerator በቅርቡ በይፋ ለሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጥ ሲሆን ወጣት ሥራ ፈጣሪዎችን የሚመዘግብበትና ስለ ፕሮግራሙ የሚገልጽበትን ድረ ገጽ ይፋ አድርጓል፡፡ ቲክቫህ ኢትዮጵያም ቤተሰቦቻችን ይህንን እድል እንዲትጠቀሙ እየጠቆምን ተከታታይ መረጃዎችንም የምናደርሳችሁ ይሆናል፡፡

More https://www.icog-sa.com

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaB
TIKVAH-ETHIOPIA
መንግስት ንብረታችንን እየነጠቀን ነው... መኪና የተነጠቀባቸው የቤተሰባችን አባላት፦ "መንግስት የህዝብ ንብረት መንጠቅ ተያይዞታል። ኮድ 2 ኦሮ VAN መኪኖች የሰጠን ኦሮሚያ መንገድ ትራንስፖርት ስህተት ካለበት የሰጠ አካል ነው መጠየቅ ያለበት ህዝብ ያለጥፋቱ እየተገላታ ነው። ኮድ 2 ኦሮ van መኪኖች እየቀሙ ቃሊቲ ግምሩክ መጋዘን እያስቀምጡ ነው እነሱ የሚሉት ኮድ 3 መሆን ነበረባቸው፤ ኮድ 2…
ከቲክቫህ ቤተሰቦች፦

መኪናቸውን ተይዞ ጉምሩክ እንዲያስገቡ የተጠየቁ ባለንብረቶች የተፈፀመባቸውን አግባብ ያልሆነ ድርጊት በተመለከተ ለሚመለከታቸው አካላት ቅሬታ አሰምተዋል።

ከጥዋት ጀምሮ ስንከራተት ነበር ያሉት የቲክቫህ ቤተሰቦች ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ለማግኘት ሞክረን ነበር ግን ሚኒስትሯ ሰኞ ነው የሚገቡት ተብለን ተመልሰናል ብለዋል። ሌሎች በስፍራው ያገኘናቸው አካላት ደግሞ እየሆነ ያለውን ነገር እውቅና የሌለው ነው ብለውናል ሲሉ ለቲክቫህ መልእክታቸውን ልከዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የኮሮና ቫይረስ ጽኑ ህሙማንን መቀበል የሚያስችለውን የቅድመ ዝግጅት ስራ እያጠናቀቀ መሆኑን አስታወቀ።

ሆስፒታሉ የኮሮና ቫይረስ ድንገት ወደ ሀገር ውስጥ ቢገባ በቫይረሱ የተጠቁ ጽኑ ህሙማንን ተቀብሎ እንዲያስተናግድ በጤና ሚኒስቴር መመረጡ ይታወሳል።

በዚህም የተሟላ የህክምና ማሽን እና አምስት የጽኑ ህሙማን ታካሚዎችን ማስተናገድ የሚችል የጽኑ ህሙማን ማገገሚያ ማዕከል ለይቶ ማዘጋጀቱን ዋና ስራ አስፈጻሚው ዶክተር ታምሩ አሰፋ ገልፀዋል።

ከዚህ ባለፈም በጽኑ ህሙማን ማገገሚያ ማዕከሉ ውስጥ ለሚሰሩ 40 ሰራተኞች በቫይረሱ ህክምና እንዲሁም የቅድመ ጥንቃቄና መከላከያ ስራዎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑንም ተናግረዋል።

በቫይረሱ ዙሪያ ግንዛቤን ለመፍጠር እንዲያስችልም ብሮሸሮችና በራሪ ወረቀቶች በማተም በሆስፒታሉ ለመታከም ለሚመጡትም ሆነ ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም እየተሰራ መሆኑም ነው የተገለፀው።

በአዲስ አበባ ለሚገኙ 13 ሆስፒታሎችም በኢትዮጵያ አየር መንገድና በባቡር ጣቢያዎች ላይ ለሚሰሩ ሰራተኞች 5 ሺህ ለቅድመ መከላከያ የሚያገለግል የአልኮል እጅ ማጽጃ፥ በሆስፒታሉ የፋርማሲ አገልግሎት ክፍል ተመርቶ መሰራጨቱን ከሆስፒታሉ የፌስ ቡክ ገፅ የተገኘነው መረጃ ያመላክታል።

[የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በቤንች ሸኮ ዞን በጉራፈርዳ ወረዳ ከጸጥታ መደፍረስ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 73 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የዞኑ ሠላምና ጸጥታ መምሪያ አስታወቀ።

የመምሪያው ኃላፊ አቶ አድማሱ ባኩስ እንደገለፁት ግለሰቦቹ የተያዙት የካቲት 8/2012 ዓ.ም በወረዳው ከተከሰተ ግጭት ጋር በተያያዘ እጃቸው እንዳለበት በመጠርጠራቸው ነው።

የወረዳውን ጸጥታ ከማስከበር እና ህዝብን ከማረጋጋት አኳያ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ያልተወጡ አመራሮችን ጨምሮ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ተጠርጣሪዎች መካከል 13 የሚሆኑት የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እንደሚገኙበት ይገኙበታል። “ቀሪዎቹ 12 የመንግስት ሠራተኞች ሲሆኑ 48 የሚሆኑት ደግሞ የአካባቢው ነዋሪዎች ናቸው” ብለዋል።

#ENA
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#የካቲት12

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ በየካቲት 12 ሰማዕታት ዕለት!

ከ83 ዓመት በፊት የካቲት 12 በፋሺስት ጣሊያን ጦር የተጨፈጨፉበት ሰማዕታት ለመዘከርና የአበባ ጉንጉን ለማኖር በዛሬው ዕለት ረፋድ ላይ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ የፓለቲካ ፓርቲ ፕሬዝዳንት የሆነው እስክንድር ነጋና የፓርቲው አባላት በቦታው በመገኘት የህሊና ጸሎትና የፎቶ ስነ-ስርዓት በማካሄድ አስበዋል፡፡

#TikvahFamily
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#DrAmirAman

ጤና ሚኒስቴር በሀገሪቱ የጤናው ዘርፍ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ላላቸው የቀድሞው የጤና ሚኒስቴር ዶ/ር አሚር አማን የምስጋና እና የእውቅና ኘሮግራም ተካሂዷል።

[ጤና ሚኒስቴር]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ምንነቱ ባልታወቀ ህመም ሰዎች እየሞቱ ነው...

በሱማሌ ክልል ሰዎች ምንነቱ ባልታወቀ ህመም እየሞቱ እንደሆነ ዘ ጋርዲያን አስነብቧል፡፡ ሟቾች እና ታማሚዎች በአፍ እና አፍንጫቸው ደም ይፈሳቸዋል፤ ከባድ ትኩሳትም ታይቶባቸዋል፡፡

የጤና ችግሩ የተከሰተው በቻይናው የካሉብ ጋዝ ፕሮጀክት አካባቢ ነው፡፡ ነዋሪዎች የሕመማችን ምክንያት የፕሮጀክቱ ኬሜካል የምንጠጣውን ውሃ ስለበከለብን ነው ብለዋል፡፡

https://www.theguardian.com/global-development/2020/feb/20/the-mystery-sickness-bringing-death-and-dismay-to-eastern-ethiopia

#WazemaRadio
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#UPDATE

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ለከፍተኛ ኃላፊነት ሹመት ሰጡ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዐማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ ፈንታ ደጀንን ከየካቲቲ 5/2012 ዓ.ም ጀምሮ በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው እንዲያገለግሉ ሹመዋል፡፡

መቀንጨርን ለመከላከል ለሰቆጣ ቃል -ኪዳን ስምምነት ተፈፃሚነት የትምህርት ቤት ምግብናን በማስጀመር፣ በትምህርትና በዐዕምሮ ልማት ላይ ትኩረት ሰጥተው በመስራታቸው የሚታወቁትን ወ/ሮ ፍሬአለም ሽባባውን ደግሞ ከጥር 28/2012 ዓ.ም ጀምሮ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው እንዲያገለግሉ ዶ/ር ዓብይ ሹመዋቸዋል፡፡ ወ/ሮ ፍሬአለም የታዋቂዋ ድምፃዊ እጅግአየሁ ሽባባው እህት ሲሆኑ በቅርቡም ላስብበት የተሰኘ መጽሐፍም አሳትመዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ከመቂ ቲክቫህ ቤተስቦች፦

ከመቂ ቲክቫህ ቤተሰቦች በደረሰን ጥቆማ ከመቂ 2 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የአንበጣ መንጋ መከሰቱን ገልፀውልና ህብረተሰቡ መንጋውን ለማባረር ጥረት እያደረገ ይገኛል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot