This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዘይንድይቦ ጎቦ...
የቲክቫህ ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ቤተሰቦች የየካቲት 11 45ኛ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በሁሉም ትግራዋይ ልብ ውስጥ ያለውን የትግራይ ህዝብ መዝሙር አድርሰዋል።
"ዘይንድይቦ ጎቦ"
ዘይንድይቦ ጎቦ ዘይንሰግሮ ሩባ ፍፁም ወይከ የለን
መስመር እዩ ሓይልና-ህዝቢ እዩ ሓይልና-ወይከ ኣይንሰዓርን
ሃሩር ፀሓይ ንዳድ ህቦብላ ማይ በረድ
ማይማይ ትበል ነብሲ ኣብ ጀቕጀቕ ትረግረግ
ደንጎላ ንተርኣስ በዓቲ ይኹን ቤትና
ለይትን ቀትርን ጉዕዞ ይድከም ይጥመየና
መስመር እዩ ሓይሊና-ህዘቢ እዩ ሓይሊና-ወይከ ኣንስዓርን
ዘይንድይቦ ጎቦ ዘይንሰግሮ ሩባ ፍፁም ወይከ የለን
መስመር እዩ ሓይልና-ህዝቢ እዩ ሓይልና-ወይከ ኣይንሰዓርን
ንከበብ በዛብእ መሬት ትፅበበና
ኣብ ስጋና ይቀርቀር ኣስናን ፀላእትና
ስጋና ንኣሞራ ደምና ውሑጅ ይኹን
ኣዕፅምትና ይድቀቕ ሕሩጭ ኮይኑ ይበተን
መስመር እዩ ሓይሊና ህዝቢ እዩ ሓይልና
ክባታት ፀላኢ ክንፍንፅሖ ኢና
ዘይንድይቦ ጎቦ ዘይንሰግሮ ሩባ ፍፁም ወይከ የለን
መስመር እዩ ሓይልና-ህዝቢ እዩ ሓይልና-ወይከ ኣይንሰዓርን
ናፓል ምስ መርዛም ጋዝ ፋሽሽታዊ ነዳድ
ሚሊዮን ቁምቡላታት ኣብ ልዕሌና ይንጎድ
መስዋእትን መቑሰልትን ክሳራታት ንክፈል
ዝኸፍአ መከራ ውዲታት ይፍተልተል
መስመር እዩ ሓይሊና-ህዝቢ እዩ ሓይሊና-ተዓወቲ ኢና!
አማርኛ ትርጉም : https://telegra.ph/TIK-02-19
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#UPDATE
የኦሮሞ እና የአማራ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና ምሁራን "በዜጎች ደህንነት ላይ ልዩነትን በማጥበብ የጋራ ጉዳዮችን ይዞ መሄድ" በሚል ሀሳብ ላይ ምክክር ማድረጋቸው ተገለጸ፡፡
ምክክሩ የተደረገው የሁለቱ ብሄር ፖለቲከኞችና ምሁራን በሁለቱ ህዝቦች የጋራ ጉዳዮች ላይ በመወያየት የጋራ ሀሳብ መያዛቸው አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው ተብሏል።
የሁለተኛው የጋራ መድረክ ባለ አምስት (5) ነጥብ የጋራ የአቋም መግለጫ፦
- ኢትዮጵያ የብዙ ብሄሮችና ብሔረሰቦች፣ ሃይማኖቶችና የፖለቲካ አመለካከቶች ሀገር መሆኗን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል፣ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ያለባት እንድትሆን ተስማምተናል፤
- ሁለቱ ህዝቦች ሰፊ የሆነ የጋራ መስተጋብርና ማህበራዊ ትስስር ያላቸው መሆኑን ተገንዝበናል፤
- የሁለቱን ህዝቦች አሰፋፈር እና የጋራ አኗኗር ከግንዛቤ በማስገባት ሰላምና መረጋጋትን እንዲሁም መሰረታዊ መብቶችን ማረጋገጥ የሁላችንም ኃላፊነት መሆኑን ተረድተናል፤
- ዝርዝር ታሪካዊ ጉዳዮችን ለአጥኚዎች በመተው በሚያግባቡን ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ተግባባተናል፤
- ይህን በፖለቲካ ፓርቲዎችና ልሂቃን የተጀመረውን ውይይት ደረጃ በደረጃ እያዳበርን ለመሄድ በውይይታችን ተስማምተናል፡፡
#ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvhahethiopia

የቲክቫህ ቤተሰቦች ጥቆማ ስጡ...
የህጻናት መጫወቻ በትምህርት ቤቶች ውስጥ መኖር ለህጻናት ትልቅ ደስታ ሲሆን የትምህርቱንም አሰጣጥ ቀላልና ውጤታማ ያደርገዋል፡፡
አሁን ላይ የግል ት/ቤቶች ዘመናዊና ጽዱ የመጫወቻ ስፍራ ሲኖራቸው አብዛኛው የመንግስት ትምህርት ቤቶች ደግሞ ለዚህ ብዙም አልታደሉም፡፡
ይህ ደግሞ የመጫወቻ ስፍራዎች በራሳቸው የሀብትን ደረጃ መለኪያ እየሆኑ መምጣታቸው የህጻናቱ አዕምሮ ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ ቀላል የሚባል አይሆንም፡፡
ልዩነቱን ማጥፋት ባይቻል እንኳን ለማጥበብና ህጻናትን ደስተኛ ሆነው እንዲማሩ ለማስቻል ' ኩኩሉ ' በሚል መጠሪያ የተለያዩ የመንግሥት ትምህርት ቤቶችን የህጻናት መጫወቻዎችን በራሳቸው ወጪና ጉልበት በመስራትና በማስዋብ ህጻናት ትምህርት ቤታቸውን እንዲወዱና በቀላሉ ተዝናንተው ለትምህርት የተዘጋጀ አዕምሮ እንዲኖራቸው ለማስቻል እየሰሩ የሚገኙ ወጣቶች ብቅ ብለዋል፡፡
የማህበሩ አባለት እስካሁን አራት ት/ቤቶችን የመጫወቻ ሥፍራዎችን በመስራትና በማደስ ትልቅ አበርክቶ አድርገዋል አሁንም ይህንን ሥራቸውን በስፋት ለመስራት ቢያስቡም የተሻለ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ት/ቤቶች መለየት ፈታኝ እንደሆነባቸው ይናገራሉ፡፡
ለዚህም በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙና የመማሪያ ክፍል ጥገና፣ የወንበር ጥገና፣ የመጫወቻ ስፍራ የሌላቸው ድጋፉ ያስፈልጋቸዋል የሚባሉ ትምህርት ቤቶችን የቲክቫህ ቤተሰቦች በአከባቢያቸው ተመልክተው ቢጠቁሙን እኛ ለመስራት ዝግጁ ነን የሚል ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ጥቆማ መስጠት የምትፈልጉ፦ +251913185145 / +251 91 155 2494
#TIKVAH_ETH

በባህር ዳር ከተማ በለቅሶ ላይ በተተኮሰ ጥይት የአንድ ግለሰብ ህይወት አለፈ!
በባህርዳር ከተማ በለቅሶ ላይ የተተኮሰ ጥይት የሌላ ሰው ህይወት ማጥፋቱን የከተማው ፖሊስ አስታወቀ። ለቅሶ የነበረውም በተመሳሳይ በጥይት ህይወቱ ላለፈው ሰው ነው።
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የሶስተኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር አብርሃም ልየው እንደገለጹት ድርጊቱ የተፈፀመው ትናንት አመሻሽ ላይ ወራሚት ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ ነው።
ድርጊቱም አንድ ግለሰብ በዚሁ ዕለት ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ተኩል አካባቢ በመጠጥ ስሜት ተገፋፍተው በታጠቁት የጦር መሳሪያ ራሳቸውን ሊያጠፋ እንደቻሉ ፖሊስ ባደረገው ማጣራት መረጋገጡን ተናግረዋል።
የአካባቢው ነዋሪዎች የተኩስ ድምፅ ሰምቶ ሲወጣ የግለሰቡ ህይወት ማለፉን ሲመለከቱ በታጠቁት የጦር መሳሪያ ከተጎጂው ቤት ተደጋጋሚ ጥይት ይተኮሳል።
የጥይት ተኩሱን የአካባቢ ምድብተኛ ፖሊሶች እንዲያስቆሙ በወቅቱ ጥረት ቢያደርጉም ከአቅም በላይ በመሆኑ ድርጊቱን መግታት አለመቻሉን አስረድተዋል።
ይተኮስ የነበረ ጥይት የሟች ጎረቤትና የቅርብ ጓደኛ የሆኑ ግለሰብን በመምታት ህይወቱ ማለፉን ዋና ኢንስፔክተር አብርሃም አብራርተዋል። ድርጊቱን ፈፅሟል የተባለው ግለሰብም እስካሁን በቁጥጥር ስር ባለመዋሉ ይዞ ለፍርድ ለማቅረብ የአካባቢው የፀጥታ ኃይል የተጠናከረ የክትትል ስራ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
#ENA

የጌዴኦ ዞን አስቸኳይ ጉባኤ...
የጌዴኦ ዞን ምክር ቤት 4ኛ መደበኛ 4ኛ ዙር አስቸኳይ ጉባኤ የሥራ ዘመን አንደኛ አስቸኳይ ጉባኤ አካሂዷል። ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ጉባኤው ላይ አቶ ሳሙኤል ቦኮን የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አድርጎ ሹሟል። አዲሱ ምክትል አስተዳዳሪም አቶ ሳሙኤል ቦኮ በምክር ቤቱ ፊት በመቆም ቃለ መሐላ ፈጽመዋል።
አቶ ተከተል አበራ የዞኑ ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ፣ አቶ ሽፈራው ቦጋለ ትምህርት መምሪያ አቶ ወርቅነህ ጋሹ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ እና አቶ ኤርምያስ ቸካ የእንስሳት እና አሳ ሀብት መምሪያ ኃላፊ ሆነው እንዲሰሩ አቶ ገዙ አሰፋ በዕጩነት አቅርበው የምክር ቤቱ አባላትም በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል፡፡

የጌዴኦ ህዝብ ክልልነት ጥያቄ...
የጌዴኦ ዞን ምክር ቤት 4ኛ መደበኛ 4ኛ ዙር አስቸኳይ ጉባኤ የሥራ ዘመን አንደኛ አስቸኳይ ጉባኤ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የጌዴኦ ህዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄን ገምግሞ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
በሙሉ ድምፅ ውሳኔውን ያሳለፈው ምክር ቤቱ የጌዴኦን ዞን ክልል ለመሆን የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ሁኔታዎች ያሉ መሆናቸውንም የምክር ቤቱ አባላት ገልጸዋል።
የጌዴኦ ዞን ምክር ቤት አባላት የጌዴኦ ህዝብ በክልልነት ቢደራጅ ለህብረተሰቡ የሚኖረውን ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ፋይዳዎች ላይም ሰፊ ውይይት አድርገዋል ተብሏል።
[የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት]

"መንግሥት ጥያቄዎችን ለመመለስ ባለው አቅም ሁሉ ይሰራል" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከስልጤ ዞን ነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት በርካታ ጥያቄዎች ቀርበውላቸው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
የመሠረተ ልማት፣ የመልካም አስተዳደር እንዲሁም ወቅታዊ አገራዊ ሁኔታዎች ላይ ያተኮሩ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም መንግሥት ባለው አቅም ጥያቄዎችን ለመመለስ መሠራት ያለበትን ሁሉ እንደሚሠራና ኅብረተሰቡም በሚችለው ሁሉ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡
በደቡብ የሚነሱ የክልልነት ጥያቄዎችን በተመለከተ ቀደም ብሎ ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ከተውጣጡ የህብረተሰብ ተወካዮች ጋር መወያየታቸውን አስታውሰው፣ ጥያቄዎችን በጥናት ላይ በተመሠረተ መንገድ እንደሚመለከቱ ገልፀዋል፡፡
በብሄር ብሔረሰቦች ቁጥር ክልል እንደማይመሠረት ፣ ነገር ግን ሕዝቡ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብቱ እንደሚከበርም ተሰምሮበታል፡፡
ምንጭ፡- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

የካቲት 12 የሰማእታት ቀን በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው!
83ኛው የሰማእታት ቀን በአዲስ አበባ የ6 ኪሎ የሰማእታት መታሰቢያ ሀውልት አደባባይ አባት አርበኞችና ሌሎች የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት በመከበር ላይ ነው፡፡
የሀገር መከላከያና የፌደራል ፖሊስ መርሽ ባንድ በቦታው በመገኘት የሰማእታት ቀኑን በተለያዩ ጣእመ ዜማዎች እያሰቡ ይገኛሉ፡፡
የአባት አርበኞች ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ እለቱን አስመልከቶ በሰጡት አስተያየት ቀኑ የዛሬ 83 አመት በፋሺስት ኢጣሊን መሪ በሆነው በግራዚያኒ አማካኝነት ከ30 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን በግፍ የተገደሉበት እለት ነው፡፡
አሁን ያለው ወጣት እለቱን ሲያስብ አባቶቹ በመሰዋትነት ያቆዩለትን ሀገር በአንድነት በመሆን በማበልጸግና ሰላሟን በመጠበቅ ወደፊት ለማስቀጠል መሆን እንዳለበት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መልእክት አስተላልፈዋል።

#የካቲት12
"አሁን ያለው ትውልድ ይቅር መባባልን ከታሪካችን ሊማር ይገባል" - የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች ፕሬዝዳንት
83ኛው የሰማዕታት ቀን አዲስ አበባ 6ኪሎ በሚገኘው የሰማዕታት መታሰቢያ ሐውልት እየተከበረ ይገኛል።
በበዓሉ ላይ የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ ዕለቱን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልእክት፣ ቀኑ የዛሬ 83 ዓመት በፋሺስት ጣሊያን ወራሪ ጦር መሪ በሆነው ግራዚያኒ ከ30 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን በግፍ የተገደሉበት ዕለት ነው ሲሉ አስታውሰዋል።
ሆኖም ይህንን ጭፍጨፋ በይቅርታ ዘግተን ወደፊት በመጓዝ እዚህ ደርሰናል፤ አሁን ያለው ትውልድም ይቅር መባባልን ከዚህ ሊማር ይገባል ብለዋል።
አክለውም፣ ወጣቱ ዕለቱን ሲያስብ አባቶቹ በመሥዋትነት ያቆዩለትን አገር በጋራ ለማሳደግ እና ሰላሟን ለመጠበቅ መነሣት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
ዕለቱ አባት አርበኞች ፣ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ የማኅበራዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ኢንጂነር እንዳወቅ አብጤ ፣ ሌሎች የክብር እንግዶች፣ የከተማዋ ነዋሪዎች እና የውጭ አገራት ቆንስላ ተወካዮች በተገኙበት ነው እየተከበረ የሚገኘው።
#ኢቢሲ

TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE - የሟቾች ቁጥር 2,012 ደርሷል - በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 75,307 በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2,012 የደረሰ ሲሆን 75,307 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 14,942 መድረሳቸውን ተመልክተናል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE
- የሟቾች ቁጥር 2,120 ደርሷል
- በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 75,730
በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2,120 የደረሰ ሲሆን 75,730 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 16,155 መድረሳቸውን ተመልክተናል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
- የሟቾች ቁጥር 2,120 ደርሷል
- በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 75,730
በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2,120 የደረሰ ሲሆን 75,730 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 16,155 መድረሳቸውን ተመልክተናል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#የካቲት12
የካቲት 12 ቀን ጣልያን ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት በጀነራል ግራዚያኒ ትዕዛዝ የተጨፈጨፉ ኢትዮጵያዉያን የሚታሰቡበት ነዉ። የዛሬ 83 ዓመት ግራዚያኒ የተባለዉ የጣሊያን ጀነራል ከሀገሩ ኢጣሊያ ንጉሳዊያን ቤተሰቦች ዘንድ አንድ ልዑል መወለዱን አስመልክቶ ደስታዉን ለማክበር የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በአሁኑ 6 ኪሎ ዩንቨርሲቲ በቀድሞዉ ገነተ ልሎል ቤተመንግሥት ሰበሰበ።
በዚህ ወቅት የፋሽሽት ኢጣሊያ ወረራ ያስቆጫቸዉ ሞገስ አስገዶም እና አብርሃ ደቦጭ የተባሉ ሁለት ወጣቶች ከተሰበሰበዉ ሕዝብ መሀል ወጥተዉ ወደ ግራዚያኒ ቦንብ ወረወሩ። በዚህም ግራዚያን እና በርካታ ባለስልጣናቱ ቆሰሉ። ይህ ያበሳጨዉ የፋሽስት ኢጣሊያ ጀነራል ግራዚያኒ ያለርህራሄ ኢትዮጵያዉያን እንዲጨፈጨፉ አዘዘ።
ኢትዮጵያውያኑ ሰማዕታት በፋሽሽት ኢጣሊያ የተጨረጨፉት በ1929 ዓ/ም የካቲት 12 ቀን ልክ የዛሬ 83 ዓመት ነበር። ወጣት አብርሃ ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶምን ጨምሮ በሦስት ቀናት ብቻ 30 ሺህ ኢትዮጵያዉያን በዕለቱ ተሰውተዋል።
የሰማዕታቱ መታሰቢያ ሀውልት በአዲስ አበባ ከተማ በስድስት ኪሎ አደባባይ ላይ ቆሟል። በሀውልቱ ሥር በየዓመቱ የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ የመታሰቢያ ስነስርዓት ይካሄዳል። ዛሬም በስፍራው ህዝብ በተገኘበት የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ እና በተለያዩ ስነስርዓቶች ዕለቱ ታስቧል።
#DW2011የካቲት12 #ENA2012የካቲት12
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

ዛሬ ማለዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ18ኛ ክፍለ ዘመን ዘውድ ለመመለስ ከመጡት የደች የውጪ ንግድ እና የልማት ትብብር ሚኒስትሯ ሲግሪድ ካግ ጋር ተገናኝተዋል።
ዘውዱ ከ1985 ዓ/ም አንስቶ ጠፍቶ የቆየ ሲሆን፣ በጥቅምት 2011 ዓ.ም. በኔዘርላንዷ ሮተርዳም ተገኝቷል።
የኔዘርላንድ መንግሥት ይህንን ቅርስ ለኢትዮጵያ መመለስ ጠቃሚ እንደ ሆነ በማመን ዘውዱ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ሁኔታዎችን አመቻችቷል።
#PMOEthiopia

አዲስ የመንግሥት ሠራተኞች ውሎ አበል ደንብ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀረበ!
የኢፌዴሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አዲስ የመንግሥት ሠራተኞች ውሎ አበል ደንብ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ማቅረቡን አስታውቋል።
በኮሚሽኑ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አለባቸው ዓለሙ፣ ረቂቅ ደንቡ ካለው ነባራዊ ሁኔታ በመነሣት በጥናት ላይ ተመሥርቶ መዘጋጀቱን አመልክተዋል።
ደንቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተመርምሮ ማስተካከያ ከተደረገበት በኋላ፣ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመርቶ ተግባር ላይ እንዲውል የሚደረግ መሆኑም ተጠቁሟል።
#ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢፌዴሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አዲስ የመንግሥት ሠራተኞች ውሎ አበል ደንብ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ማቅረቡን አስታውቋል።
በኮሚሽኑ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አለባቸው ዓለሙ፣ ረቂቅ ደንቡ ካለው ነባራዊ ሁኔታ በመነሣት በጥናት ላይ ተመሥርቶ መዘጋጀቱን አመልክተዋል።
ደንቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተመርምሮ ማስተካከያ ከተደረገበት በኋላ፣ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመርቶ ተግባር ላይ እንዲውል የሚደረግ መሆኑም ተጠቁሟል።
#ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከሐምሌ 1 ቀን 2004 ዓ/ም ጀምሮ ስራ ላይ የዋለው የመንግስት ሠራተኞች የቀን ውሎ አበል መመሪያ፦
የመንግሥት ሠራተኛ በየትኛውም ክልል ሄዶ ቢሰራ ከፍተኛ ደመወዝ አለው የሚባለው 225 ብር የሚታሰብለት ሲሆን፤ አነስተኛ ደመወዝ ተከፋይ ነው የሚባለው ደግሞ በቀን የሚያገኘው 111 ብር ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የመንግሥት ሠራተኛ በየትኛውም ክልል ሄዶ ቢሰራ ከፍተኛ ደመወዝ አለው የሚባለው 225 ብር የሚታሰብለት ሲሆን፤ አነስተኛ ደመወዝ ተከፋይ ነው የሚባለው ደግሞ በቀን የሚያገኘው 111 ብር ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬም የድጋፍ ሰልፎች ዛሬም እየተደረጉ ነው...
በዛሬው ዕለት የካቲት 12 ዓ/ም በበደሌ ከተማ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድን የለውጥ አመራር የሚደግፍ ሰልፍ እየተደረገ ይገኛል። የሰልፉ ተሳታፊዎች እንደነገሩን ሀገር በጥላቻ፣ በስድብ እና የሰዎችን ስራ በማሳነስ አይገነባም፤ የተለያዩ አካላት ከስድብ እና ከማንቋሸሽ ይልቅ ለህዝብ ያላቸውን ሀሳብ ያቅርቡ ህዝቡ የሚሆነውን ይመርጣል የሚል መልዕክት በሰልፉ ተላልፏል።
በተመሳሳይ፦
በሻሸመኔ ከተማ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይን የለውጥ አመራር የሚደግፍ ሰልፍ እየተደረገ ይገኛል። በስለፉ የከተማው ነዋሪዎች የትኛውም ወገን ከስድብና ከጥላቻ እንዲቆጠብ መልዕክት ተላልፏል።
በሌላ መረጃ፦
ትላንት ምሽት ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን ቢሮ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ እንደተመለከትነው ነገ ዓርብ የካቲት 13 የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስራ የሚያበረታታ፣ የለውጥ ኃይሉንም የሚደግፍ ሰልፍ ይደረጋል ተብሏል።
[ፎቶ : በደሌ እና ሻሸመኔ ቲክቫህ ቤተሰቦች]

የሸገር ዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታ...
በሜድሮክ እህት ኩባንያ ‹‹ሆራይዘን ፕላንቴሽን›› እየተገነባ ያለው የሸገር ዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ ተጠናቆ ሥራ ሊጀምር የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደደረሰ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ።
በሆራይዘን ፕላንቴሽን የእቅድ ቢዝነስ ልማትና ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ ይበልጣል ሽመልስ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት ግንባታው ከተጀመረ ወራትን ያስቆጠረው የሸገር ዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል።
የመሰረት ድንጋይ ከተጣለ ጀምሮ ሥራው በጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እየተመራ እንደነበር የተናገሩት ሥራ አስኪያጁ በቀን 18 ሰዓት በመስራት ግንባታውን ማፋጠን እንደተቻለና ጎን ለጎንም የማሽነሪዎችንና የሌሎች ግብዓቶችን ግዢ ተፈፅሞ ሀገር ውስጥ መግባታቸውን ገልጸዋል።
ምንጭ፦ አዲስ ዘመን ጋዜጣ

የኢንጅነር ስመኘው በቀለ የመታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ!
የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ የነበሩት የኢንጅነር ስመኘው በቀለ የመታሰቢያ ሐውልት በዛሬው ዕለት ተመረቀ፡፡
በመታሰቢያ ሐውልቱ የምርቃት ሥነ ስርዓት ላይ በኦርቶዶክስ እምነት ስርዓት መሰረት የፍትሃትና የፀሎት ሥነ - ስርዓት ተካሂዷል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በሐውልቱ ምርቃት ስነ ስርዓት ላይ የተገኙ የተለያዩ ድርጅቶ፣ ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፡፡
[የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል]