TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#US_EMBASSY

አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በጋምቤላ ክልል ሁለት የግብረ-ሰናይ ድርጅት ሰራተኞች የገደሉ ታጣቂዎችን መንግሥት በአፋጣኝ በቁጥጥር ሥር አውሎ ለሕግ እንዲያቀርብ ጠየቀ። አክሽን አጌይንስት ኸንገር የተባለው ዓለም አቀፍ የግብረ-ሰናይ ድርጅት ሰራተኞች ጥቃት የተፈጸመባቸው በጋምቤላ ክልል ደቡብ ሱዳናውያን ስደተኞች ከሚኖሩበት ኙንዬል ከተባለ የመጠለያ ጣቢያ (Nguenyyiel Refugee Camp) ሥራቸውን አጠናቀው በመጓዝ ላይ ሳሉ እንደነበር ድርጅቱ አስታውቋል። በጥቃቱ የመስክ ሰራተኛ እና አሽከርካሪ ሕይወታቸውን አጥተዋል። የአሜሪካ ኤምባሲ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ የግብረ-ሰናይ ሰራተኞች መሆኑን የሚጠቁም ምልክት በነበረው ተሽከርካሪ ላይ ባለፈው ሳምንት የተፈጸመውን ጥቃት አውግዟል።

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#US_Embassy_AA

የሙሉ ጊዜ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር የሆናችሁ እና አሜሪካ ውስጥ የልውውጥ ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ ይህ እድል ለእናተ ነው።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የ2022-23 የፉልብራይት የማስተማር ልቀት እና ስኬት (TEA) ፕሮግራም ማመልከቻ መቀበል እንደተጀመረ ዛሬ ገልጿል።

ስኬታማ የሆኑ አመልካቾች #ለ6_ሳምንታት የአካዳሚክ ሴሚናሮች እና የክፍል ውስጥ ምልከታ ለማድረግ ወደ አሜሪካ ይጓዛሉ።

በአሜሪካ ቆይታቸው ከአስተናጋጅ ዩኒቨርሲቲ እና ከአካባቢው 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ከሚገኙ መምህራን እና ተማሪዎች ጋር ወደ የልምድ ልውውጥ ያደርጋሉ።

ፉልብራይት (TEA) በስቴት ዲፓርትመንት የትምህርት እና የባህል ጉዳዮች ቢሮ (ECA) የሚደገፍ ፕሮግራም ሲሆን በአሜሪካ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ በ #IREX የሚተዳደር ነው።

ለበለጠ መረጃ ፦ https://ow.ly/t4FO50HQPPe
ለማመልከት ፦ https://ow.ly/aIaK50HQPPc

የመጨረሻው ማመልከቻ ቀን እ.ኤ.አ የካቲት 27/ 2022 ወይም የካቲት 15 ቀን 2014 ዓ/ም ነው።

@tikvahethiopia