TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የዕለቱ መልዕክት፦

ከጭፍን ጥላቻ መላቀቅ ይቻላል!

አብዛኞቹ ሰዎች ጭፍን ጥላቻን በመሠረተ ሐሳብ ደረጃ የሚያወግዙ ቢሆኑም ከጭፍን ጥላቻ መዳፍ የሚላቀቁ ግን ጥቂቶች ናቸው። እንዲያውም ሥር የሰደደ ጭፍን ጥላቻ ያላቸው ብዙ ሰዎች ጥላቻ እንደሌላቸው ሊናገሩ ይችላሉ። ሌሎች ደግሞ ሰዎች ጭፍን ጥላቻቸውን ይፋ እስካላወጡ ድረስ ምንም ጉዳት የለውም ይላሉ።

ይሁን እንጂ ጭፍን ጥላቻ ሰዎችን የሚጎዳና የሚከፋፍል መጥፎ ነገር ነው። ጭፍን ጥላቻ የድንቁርና ልጅ ነው ቢባል የልጅ ልጁ ደግሞ ጠላትነት ነው። ቻርልስ ካለብ ኮልተን የተባሉት ደራሲ (1780-1832) “አንዳንድ ሰዎችን ስለማናውቃቸው #እንጠላቸዋለን። ስለምንጠላቸውም #ልናውቃቸው አንችልም” ብለዋል። ጭፍን ጥላቻን ሰዎች መማር እንደሚችሉ ሁሉ ማስወገድም ይችላሉ።

Via #JW

#ፍቅር #ሰላም #አንድነት #ተስፋ #ኢትዮጵያ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በቆሻሻ ሽታ ምክንያት ለበሽታ እየተዳረግን ነው!

"በዚሁ በመዲናችን አዲስ አበባ የሚገኘው በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው የአዲስ አበባ ቆሻሻ መጣያ ቦታ ከጊዜ ወደጊዜ ሽታው እየጨመረ መጥቶ የአካባቢውን ሰው ለበሽታ እየዳረገ ይገኛል። ልጆች እየታመሙ ነው በተለያየ ጊዜ ሰው ታሞ ወደሆስፒታል በሚሄድበት ጊዜ ዶክተሮች የሚሰጡት ምላሽ በዚህ ቆሻሻ አማካኝነት የተነሳ ነው የሚሉት። ይሄ ሽታ በአካባቢው ብቻ አይደለም ሚሸተው ረጅም ርቀት ድረስ ያሉ ቦታዎች ይደርሳል፤ በተጨማሪ ከቆሻሻ ፋብሪካው የሚወጣው ጭስ በጣም አሳሳቢ ነው የሚመለከተው አካል ይህን ችግር ቢመለከተው ተገቢ ነው።" #JW

@tsegabwolde @tikvahethiopia