TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በደቡብ ክልል፤ ወላይታ ዞን ዉስጥ በጤና ስርዓት ላይ ያለው ችግር እንዲፈታ የፌደራል መንግስት አስቸኳይ የእርምት እርምጃ ይውሰድ ሲሉ የጤና ባለሞያዎች ጠየቁ።

ባለሞያዎቹ ይህን የጠየቁት ዛሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት የፅሁፍ መልዕክት ነው።

መልዕክታቸውን የላኩ የጤና ባለሞያዎች፤ በዞኑ የጤና ዘርፍ ላይ ያሉ አመራሮች ቸልተኝነት የተነሳ የህክምናዉን አገልግሎት እንደ ሌሎች አካባቢዎች ግዜዉን የሚመጥን አልሆነም ብለዋል።

ባለሞያዎቹ እንደሚሉት የደንገተኛ ቀዶ ህክምና ከአንድ ሆስፒታል (ኦቶና) ዉጭ ማግኘት የማይታሰብ ሆኗል።

መድኃኒት፣ የምርመራ መሳሪያ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች በበቂ ሁኔታ የለም የሚሉት ባለሞያዎቹ፤ ባልተሰራ ነገር "የዉሸት ሪፖርት" እንድናቀርብም እንገደዳለን ሲሉ ገልጸዋል።

ሌላው ባለሙያዎች የሰሩበት #ደመወዝ እና #ጥቅማጥቅም ባለማግኘታቸዉ ችግር እያጋጠማቸው እንደሆነ ጠቁመዋል።

በዞኑ የተለያዩ ሆስፒታሎች የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች ከደመወዝና ጥቅማጥቅም ጋር በተያያዘ ስራ ለመስራት ስለመቸገራቸውም አስረድተዋል።

ያለውን ችግር ለበላይ አካላትና ለሚዲያ እንዳይገለፅ ጫና እንደሚደርስ እንዳንድ ባለሞያዎችንም እስከ ማሰር የሚደርስ እርምጃ እንደሚወሰድ ገልፀዋል።

በዞኑ የፋይናንስ ችግር ሳይሆን የመልካም አስተዳደር ችግር ጎልቶ እንደሚታይ አሳውቀዋል።

የጤና ሚኒስቴር፤በዞኑ የሚታየው ችግር እንዲፈታ፣በተለይም በወላድ እናቶች ላይ እያደረሰ ያለው ችግር እንዲቀረፍ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል።

በዞኑ አብዛኞቹ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ላይ ችግሩ አለ ያሉት የጤና ባለሞያዎቹ በዚህም ስራ መስተጓጎሉን አመልክተዋል።

ስለጉዳዩ ከዞን ጤና መምሪያ ምላሽ እና ማብራሪያ ለማግኘት ለአንድ አመራር ስልክ ብንደውልም ስልኩ አልተነሳም።

@tikvahethiopiaBOT