TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#StopHateSpeech

ተማሪዎች ከጥላቻ_ንግግር ተቆጥበው ለሀገራቸው #ሰላም እና #እድገት የበኩላቸውን እንዲወጡ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች ጠየቁ። TIKVAH-ETHIOPIA መጋቢት 28 እና 29 በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ባካሄደው የ#StopHateSpeech መድረክ ላይ የተገኙ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ለወጣቶች ሀገራዊ ጥሪ አስተላልፈዋል። #ዶክተር_ይቻለ_ከበደ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዘዳንት - ወጣት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ አላማ እንዲጠቀሙ፤ አሁን ያላቸውን የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን እንዲፈትሹ መልዕክት አስተላልፈዋል። ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያ እንደቀላል የምንለዋወጣቸው የጥላቻ ንግግሮች ነገ ሀገር ሊያሳጣን ስለሚችል ሁሉም ለሰላም ቅድሚያ የሚሰጥ እና ሀገሩን የሚወድ ወጣት ከጥላቻ ንግግር እንዲቆጠብ፤ ይልቅም በህዝብ መካከል አንድነት እንዲፈጠር ስለፍቅር እንዲሰብክ ጥሪ አቅርበዋል።

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ኮሌጅ ዲን #ዶክተር_አብደላ_ከማል በበኩላቸው ወጣት ተማሪዎች በዕለት ተዕለት ህይወታቸው ብሎም በማህበራዊ ሚዲያ ከጥላቻ ንግግሮች እንዲርቁ ጠይቀዋል። ሰዎችን መጥላት ራስን ከመጥላት እና ካለማክበር የሚፈጠር በመሆኑ ሁሉም ራሱን የሚወድ ወጣት ሌላውን እንደራሱ አደርጎ እንዲወድ እና እንዲያከብር መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በተለይ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰራጩ ዜናዎችን በደንብ ማጣራት እንደሚገባ ጠቁመው የሚሰራጩ የጥላቻ መልዕክቶችን ሼር ባለ ማድረግ ለሀገሪቷ ሰላም ዘብ እንዲቆሙ ጠይቀዋል።

~መጋቢት 28 እና 29 አርባምንጭ~
@tsegabwolde @tikvahethiopia