TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኦፌኮ⬇️

መንግስት በየአካባቢው እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮችን ህብረተሰቡን በማሳተፈና  ህግን መሰረት በማድረግ  ሊፈታው እንደሚገባ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ  ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ገለፁ።

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ወቅታዊ የሀገሪቱን ሁኔታ በተመለከተ አባላቶቹና ደጋፊዎቹ  የተሳተፉበት ሲምፖዚየም በአዲስ አበባ አካሂዷል።

ሊቀመንበሩ ዶክተር መረራ ጉዲና ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ ወጣቶች ትውልድ በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች እየተስተዋሉ ባሉ ችግሮችና  የሀገር አንድነትን ሊያፈርሱ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ መሆን የለባቸውም።

ዶክተር መረራ የሀገር አንድነትን የበለጠ ለማጠናከር፥ በአፋጣኝ ብሄራዊ መግባባትን ሊፈጥር የሚችል መድረክ እንዲመቻች አሰስበዋል።

እንዲሁም አሁን በሀገሪቱ እየተስተዋለ ያለውን ለውጥም በፍጥነት ወደ ሁሉም አካባቢዎች ማዳረስ እንደሚገባ ነው ሊቀመንበሩ ዶክተር መረራ ጉዲና የተናገሩት።

#ወጣቱ ሁሌም ለለውጥ ተሰላፊ መሆኑን የገለፁት ሊቀመንበሩ፥ ነገ የተሻለ እንዲሆን የወጣቱ ሀላፊነት እንደሆነ ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈ ወጣቱ የአንድ ድርጅት አገልጋይ  ሳይሆን የህዝብ ውክልና በመያዝ ትግሉን በአንድነት መቀጠል አለበት ብለዋል።

©FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update CNN⬆️

ዓለም አቀፉ ብዙኃን መገናኛ ሲኤን ኤን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር. ዐብይ አህመድን
በተመለከተ ሰፊ ትንታኔ አስነብቧል፡፡

#ወጣቱ#ዲሞክራቱ እና #ሰላምን ሰባኪዉ መሪ ኢትዮጵያዉያን ለዘመናት ሲመኙት የነበረ አይነት መሪ መሆኑ በዘገባዉ ተገልጿል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን በመምጣታቸዉ ኢትዮጵያን ከእርስ በርስ ግጭት እና መበታተን ታድገዋል፡፡

በአስተዳደር ቆይታቸዉም እስረኞች ተለቀዋል፣ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ሰላም ፈጥረዋል፣ የሚዲያ ነፃነትን አዉጀዋል፣ አስቸኳይ አዋጁን አንስተዋል፣ ኢኮኖያዊ ለዉጦችን የተመለከቱ ዉሳኔዎችን አሳልፈዋል፡፡ ከሁሉም በላይ የኢትዮጵያዉያንን ተስፋ አለምልመዋል ብሏል ዘገባዉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተወዳጅነታቸዉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ጠቅሶ በሃገሪቱ መዲና የጠቅላይ ሚኒስትሩን ምስሎች እና እሳቸዉን የሚደግፉ መልዕክቶች መኪኖች ላይ እና በማህበራዊ ሚዲያዎች ማየት የተለመደ ነዉ ብሏል፡፡ ምስላቸዉን የያዙ ቲሸርቶችም ይሸጣሉ ሲል ገልጿል፡፡

ዶ.ር ዐብይ ከሳቸው በፊት ከነበሩት መሪዎች ልዩ ናቸው ያለዉ #ዘገባዉ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን በፍቅር ይቀበላሉ፣ ከአድናቂዎቻቸው ጋር #ፎቶግራፍ ይነሳሉ፣ ፈገግታቸውም ለካሜራ ሳይሆን #ከልብ ነው ሲል አስፍሯል፡፡

ቶም ጋርድነር የተሰኘ እንግሊዛዊ ጋዜጠኛን ዋቢ አድርጎ ዘገባዉ እንዳሰፈረዉ ዶር. ዐብይ ከፈጣሪ የተላኩ መሪ ተደርገዉ እንደሚቆጠሩ ገልጿል፡፡

የተወሰኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ነብይ እንደሆኑ ያምናሉም ብሏል፡፡ ዶር. ዐብይ የመበታተን ስጋት ተጋርጦባት የነበረችዉን ሀገር መታደግ ችለዋል ፡፡

መሪዉ #በወታደራዊ አስተዳደር በቂ ልምድ ማካበታቸዉን እና ይህም እንደጠቀማቸዉ አስነብቧል።

ሲኤን ኤን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ደህንነት እና በተለያዩ አካባቢዎች የሚነሱ የመንጋ ፍትህ እንዲሁም ሁከቶች ጥንቃቄ ያሻችዋል ብሏል፡፡

እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት ዶር. ዐብይን የመሰሉ ሰዎች ከሚሊየን አንድ ናቸዉ ያለዉ ዘገባዉ አፍሪካ ካፈራቻቸዉ ጥቂት ታላቅ መሪዎች አንዱ ሊሆኑ ይችላሉ ሲል ትንታኔዉን ደምድሟል፡፡

ምንጭ፦ ሲኤን ኤን (በአመብድ ወደ አማርኛ ተቀየረ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬆️

የጋሞ ብሔረሰብ ተወካይ የሆኑ #አባቶች፣ ሴቶችና ወጣቶች ከቡራዩ እና አካባቢዋ #ተፈናቅለው በአዲስ አበባ በተለያዩ መጠልያዎች ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ቦታው ድረስ በመገኘት ጎበኙ፡፡

የጋሞ አባቶች የተከሰተውን ችግር በሠላምና በፍቅር መፍትሔ የሚያገኝበትን መንገድ ለማመቻቸት የጋሞን #ወርቃማ ባህል በመከተል ዕርቅ መፍጠር ይገባል ብለዋል፡፡

#ወጣቱ ትውልድም ባህሉን በማይወክል መልኩ ለሌላ በቀል እንዳይነሳሳ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንጅባራ🔝

123ኛው የዓድዋ ድል #እንጅባራ ላይ ተከብሯል። በአከባበሩ ላይ የተገኙት አባት አርበኞች #ወጣቱ ትውልድ ጀግኖች አባቶችና እናቶች ለሃገር ሉዓላዊነት የከፈሉትን መስዋዕትነት በማሰብ ለሀገር አንድነት ዘብ መቆም እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጎንደር #Gondar

2.8 ሚሊዮን የፌስቡክ ተከታዮች ያሉት "Mereja.com" የተባለ ገፅ በተመሳሳይ በጎንደር ከተማ #ወጣቱ ከሀገር መከላከያ ሰራዊቱ ጋር ችግር ውስጥ እንደገባ ዘግቦ ከ1 ሰዓት በኃላ መረጃውን ከገፁ ላይ አጥፍቶታል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia