TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አሳዛኝ_ዜና

ዛሬ ማለዳ በሊቢያ የስደተኞች እስር ቤት ላይ በተፈጸመ የአየር ድብደባ በትንሹ 44 ሰዎች #መገደላቸውን የአገሪቱ መንግሥት አስታወቀ። በትሪፖሊ ከተማ ታጁራ በተባለ አካባቢ በሚገኘው የስደተኞች እስር ቤት ላይ ባነጣጠረው የአየር ድብደባ 130 በላይ ስደተኞች መቁሰላቸውን በተባበሩት መንግሥታት የሚደገፈው የሊቢያ መንግሥት የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በትንሹ 6,000 #ኢትዮጵያውያን፣ ኤርትራውያን፣ ሶማሌያውያን፣ ሱዳናውያን እና የሌሎች የአፍሪካ አገራት ዜጎች በሊቢያ ታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር በሚገኙት እስር ቤቶች ታጉረው ይገኛሉ። አብዛኞቹ ስደተኞች ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሲሞክሩ የተያዙት የአውሮፓ ኅብረት በገንዘብ በሚደግፋቸው እና ባሰለጠናቸው የባሕር በር ጠባቂዎች ነው።

Via #DW
🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና

በሶማሊያ በአንድ ሆቴል ላይ በተሰነዘረ ጥቃት ታዋቂ ጋዜጠኛን ጨምሮ 26 ሰዎች ሞቱ። በደቡባዊ ሶማሊያ በተሰነዘረ ጥቃት ከሞቱት 26 ሰዎች መካከል ታዋቂ ጋዜጠኛ ፣በርካታ የውጪ ዜጎች እንደሚገኙበት ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ከጥቃት አድራሾቹ መካከል አንድ አጥፍቶ ጠፊ ፈንጂዎችን የጫነ ተሸከርካሪ በኪስማዩ ወደብ ወደ ሚገኘው አሳሴይ ሆቴል በሃይል ጭኖ የገባ ሲሆን ሌላ ታጣቂም ወደ ህንፃው በመግባት ጉዳት አድርሰዋል፡፡

የ43 አመቷ ጋዜጠኛ ሁዳን ናላሂ እና ባለቤቷ ፋሪድ ከሟቾቹ መካከል ይገኙበታል፡፡ አልሻባብ ለጥቃቱ ኃላፊነቱን የወሰደ ሲሆን እኤአ በ2012 ከኪስማዩ ተገዶ ከወጣ በኋላ የፈፀመው አስከፊ ጥቃት ተብሏል፡፡

የሃገሪቱ ባለስልጣናት እንዳሉት የአካባቢው ፖለቲከኞች ፣ሶስት ኬንያውያን፣ሶስት ታንዛኒያውያን ፣ሁለት አሜሪካኖችና አንድ ብሪታኒያዊ በጥቃቱ ህይወታቸው አልፏል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና

በሶሪያ የአማፂያን ይዞታ በሆነ በገበያ ቦታ በተፈፀመ የአየር ጥቃት በትንሹ የ16 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ የአየር ድብደባው በሰሜን ሶሪያ ኢድልብ ግዛት ሰዎች በሚበዙበት የገበያ ቦታ በተፈፀመው በዚህ ጥቃት በትንሹ 16 ሰዎች ሲገደሉ 30 ያህል መቁሰላቸው ተነግሯል፡፡

የአየር ጥቃቱ በሶሪያ ወይንም በሩሲያ የጦር አውሮፕኖች እንደተካሄደ የሶሪያ ተቃዋሚ አክቲቪስቶች ገልጸዋል ነው የተባለው፡፡ በአየር ጥቃቱ ከተማዋ በጭስ ታፍና የነበር እና የጥቃቱ ሰለባዎች የእርዳታ ጥሪ ሲያሰሙ እንደነበረ የአይን እማኖች ተናግረዋል፡፡

የኢድልብ ግዛት በተቃዋሚዎች ቁጥጥር ስር ሲሆን፣ በሩሲያ የሚደገፈው የበሻር አል አላሳድ መንግስት ተደጋጋሚ የአየር ጥቃት የሚፈጽምበት እንደሆነ ዘገባው ያስረዳል፡፡

የአላሳድ መንግስት ይህን ጥቃት ባሳለፍነው ሚያዝያ ወር ከጀመረ ጊዜ አንስቶ ከ2ሺህ በላይ ሰዎች መገደላቸውን እና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸውም ይነገራል፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና

ሶማልያ ዋና ከተማ #ሞቃዲሾ ውስጥ ዛሬ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ፣ በትንሹ 17 ሰዎች #መሞታቸውን የሆስፒታል ምንጮችን ጠቅሶ ቪኦኤ ዘገበ። የሞቃዲሾ ትልቁ ሆስፒታል ዳይሬክተር ዶ/ር ሞሓመድ ዩሱፍ እንደገለፁት፣ ሌሎች 28 ቁስለኞች ሆስፒታል ገብተዋል። አደጋው የደረሰው አንድ ተጠርጣሪ አጥፍቶ ጠፊ፣ ይጓዝባት የነበረችውን ተሽከርካሪ፣ ሕዝብ በሚበዛበት የሞቃዲሾ አውራ-ጎዳና መጋጠሚያ ላይ በማፈንዳቱ እንደሆነም ተገልጿል። ለፍንዳታው አል-ሻባብ ኃላፊነት መውሰዱንም አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና

በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳሜ ቱሉ ጅዶ ኮምቦልቻ ወረዳ ዳሎ ቀበሌ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ አስታውቋል።

አደጋው የደረሰውም ከሻሸመኔ ወደ ቡታጂራ በማቅናት የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከሰበታ ወደ ሻሸመኔ ለቀስተኞችን ይዞ ይጓዝ ከነበረ ሚኒባስ ጋር በመጋጨቱ ነው ተብሏል።

በተከሰተው አደጋም የስድስት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ማለፉን የወረዳው ትራፊክ ተቆጣጣሪ ሳጅን አህመድ ቃለቶ ተናግረዋል። በአደጋው ቀላልና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በባቱ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ተገልጿል። የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም ሳጅን አህመድ ጠቁመዋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና

በጅማ ዞን ኦሞናዳ ወረዳ በጊቤ ሰው ሰራሽ ሀይቅ ላይ ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ባህላዊ ጀልባ መስጠሟ ተሰማ። ከጣውላ የተሰራችው ጀልባ ከቀኑ 5 ስአት ከ30 አካባቢ ወደ አሰንዳቦ ገበያ የሚመጡ 18 ሰዎችን አሳፍራ በመጓዝ ላይ እያለች ተሰብራ መስጠሟን ነው የወረዳው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፉአድ ከሊፋ የተናገሩት። አደጋው እንደተከሰተም የወረዳው አስተዳደር አካላት፣ የአካባቢው ነዋሪዎች እና ጠላቂ ዋናተኞች ደርሰው የ13 ሰዎችን ህይወት ማትረፍ ተችሏል ብለዋል።

ቀሪዎቹ 5 ሰዎች ግን እስካሁን አልተገኙም፤ ፍለጋውም መቀጠሉ ነው የተነገረው።የጀልባዋ ቀዛፊም በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል። አደጋው የደረሰባቸው የጀልባዋ ተሳፋሪዎች ከሰኮሩ እና ኦሞናዳ ወረዳ ወደ አሰንዳቦ ገበያ ሲያመሩ የነበሩ ናቸው የተባለ ሲሆን÷ ህብረተሰቡ ደህንነታቸው አስጊ በሆኑ ጀልባዎች ከመጓዝ በመቆጠብ ራሱን እንዲጠብቅ ጥሪ ቀርቧል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና

በካይሮ ብሄራዊ የካንሰር ማእከል አቅራቢያ የደረሰው የመኪና ግጭት ባስከተለው ፍንዳታ 19 ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች 30 መቁሰላቸውን ነው የሃገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ያስታወቀው፡፡

የሃገር ውስጥ ሚኒስቴር በበኩሉ አንድ በፍጥነት የሚሄድ መኪና ከሌላው ጋር በመጋጨቱ ፍንዳታውን አስከትሏል ብሏል፡፡ ነገር ግን ግጭቱ ብቻውን ትልቅ ፍንዳታ ለምን እንዳስከተለ እስካሁን ግልፅ አለመሆኑንም ተናግረው አደጋው በመኪኖቹ ግጭት ብቻ መድረሱም አለመታወቁን ገልፀዋል፡፡

አደጋውን ተከትሎ የተለቀቁ ቪዲዮዎች እንደሚያሳዩት በርካታ መኪኖችን ሲያቀጣጥል የነበረውን መጠነ ሰፊ እሳት የአደጋ ግዜ ሰራተኞች ሊቆጣጠሩት ሲሞክሩ ተስተውለዋል፡፡ የካንሰር ህክምና ማእከል ውስጥ ያሉ ለቀው የወጡ ሲሆን በታዋቂው አደባባይ ታኺር አቅራቢያም መሆኑ ታውቋል፡፡

ከሆስፒታሉ በተቃራኒ ጎን የሚገኙት የባንክ ጥበቃ አብድል ራህማን ሞሃመድ እንዳሉት” በአካባቢው ፍንዳታውን ሰምተናል በአፋጣኝም መግቢያ በሮቹን ዘግተናል” ብለዋል፡፡

የሃገሪቱ የጤና ሚኒስቴር የቆሰሉ ሰዎች ወደ ህክምና መወሰዳቸውንም ገልጿል፡፡ የግብፅ አቃቤ ህግ የአደጋውን መንስኤ በመመርመር ላይ ሲሆን ለሮይተርስ የዜና ወኪል የተናገሩ ምንጮች ከመንግስት አካል ፍንዳታው ጥቃት መሆኑን አለመገለፁን ተናግረዋል፡፡ መርማሪዎች፣የወንጀል መርማሪ ላብራቶሪ እና የቦምብ ኤክስፐርቶች ፍንዳታው የደረሰበት ቦታ መገኘታቸውን ምንጮች ለአልጀዚራ ተናግረዋል፡፡

በግብፅ የመኪና አደጋ የተለመደ እንደሆነ የገለፀው የአልጀዚራ ዘገባ 8 ሺህ ግጭቶች ባለፈው አመት መመዝገባቸውንና ይህም ለ3 ሺህ ሰዎች ሞትና ለ12 ሺህ ሰዎች መቁሰል ምክንያት መሆኑን አስነብቧል፡፡

Via አልጀዚራ/ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና

16 ኢትዮጵያውያን ህይወታቸው አለፈ!

ከሊቢያ ወደ ጣሊያን በባህር ሲጓዝ በነበረ #ጀልባ ላይ በደረሰ የመስጠም አደጋ የ16 ኢትዮጵያውን ዜጎች ህይወት አለፈ። ሐምሌ 18 ቀን 2011 ዓ.ም ባጋጠመው በዚህ አደጋ 16 የትግራይ ተወላጆች ህይወት ማለፉን የክልሉ የህዝብና መንግስት ግንኙነት ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው በዛሬው ዕለት በሰጠው የሀዘን መግለጫ ከሊቢያ ወደ ጣሊያን ሲጓዝ በነበረ ጀልባ ላይ በደረሰ የመስጠም አደጋ ህይወታቸው ካለፉት ዜጎች ውስጥ 10ሩ ሴቶች መሆናቸውን ገልጿል። በአደጋው ህይወታቸውን ያጡት ዜጎችም በክልሉ ኢሮብ ተብሎ የሚጠራው ወረዳ ተወላጆች መሆናቸው ታውቋል።

የክልሉ መንግስት በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ፥ ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን ተመኝቷል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና

በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ በደረሰ የአፈር መደርመስ አደጋ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የመረጃ ኢንተለጀንስ ቡድን መሪ ሳጅን ጌታሁን ተስፋዬ እንደተናገሩት፥ አደጋው የተከሰተው በወረዳው ጋንታ ካንቻሜ ቀበሌ ልዩ ስሙ “መርከብ ጣቢያ” በሚባል ስፍራ ነው። አደጋው በአንድ ብሎኬት ማምረቻ ድርጅት ውስጥ መድረሱንም ተናግረዋል።

የአደጋው መንስኤ የብሎኬት ማምረቻ ሰራተኞች አፈር በመቆፈር ላይ እያሉ በዙሪያው ከፍተኛ መጠን ያለው አፈር መደርመሱ መሆኑንም አስታውቀዋል ፡፡ሳጅን ጌታሁን እንዳሉት በአደጋው በአፈር ቁፋሮ ላይ የነበሩ አራት ሰዎች ወድያውኑ ሕይወታቸው አልፏል። ከሟቾች መካከል ሁለቱ ወንድማማቾች መሆናቸውም ነው የተገለጸው። በቁፋሮ የወጣው የሟቾች አስክሬን በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ምርመራ ተደርጎለት ለቤተሰቦቻቸው መሰጠቱ ተዘግቧል።

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና | አርቲስት ጫንያለሁ ወልደጊዮርጊስ ከዚህ አለም በሞት መለየቱን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ዘግቧል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia