TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update BBC-ቤንሻንጉል⬇️

በቤንሻንጉል ጉምዝ በተፈጠረ ግጭት ከ50 ሺህ ሰዎች በላይ #ሲፈናቀሉ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱ ተሰማ።

መስከረም 16/2011 ዓ.ም የካማሼ ዞን አመራሮች ከምዕራብ ኦሮሚያ አስተዳደር ጥምር ኮሚቴ ጋር የነበራቸውን ስብሰባ አጠናቅቀው እየተመለሱ በነበሩ የዞን፣ የወረዳ አመራሮችና የፀጥታ ኃይሎች ላይ በተከፈተው ተኩስ የ4 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ በተወሰኑ ከኦሮሚያ ጋር በሚዋሰኑ ስፍራዎች በተከሰተ ግጭት ሰዎች #መሞታቸውን፣ መፈናቀላቸውን ቤቶች መቃጠላቸውን የቤንሻንጉል ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አበራ ባይታ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በተለይ በበሎይ ጅጋንፎይ ወረዳ ስር ሳይ ዳለቻ ቀበሌ ግጭት የነበረ ሲሆን በግጭቱም 75 ቤቶች ተቃጥለዋል ብለዋል። በዚሁ ወረዳ ጅጋንፎይ ቀበሌ በጭበጭ በምትባል አካባቢ ላይ ቤቶች መቃጠላቸውን ጠቅሰው ሌሎች ቀበሌዎችም ላይ ተመሳሳይ ግጭቶች መከሰሰታቸውን ተናግረዋል።

በበሎይ ጅጋንፎ ሶቤይ ከተማ ላይ በርካታ ሰዎች ተፈናቅለዋል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ በሶጌ ዙሪያ ባሉ ቀበሌዎች ልቢጋ፣ ሳይ ዳላቻ፣ ታንካራ ቀበሌዎች በርካታ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን አስረድተዋል።

"በተንካራ 105 ቤቶች ተቃጥለዋል 3 ሰዎችም ህይወታቸው አልፏል" ያሉት መስተዳድሩ በበጭበጭ 1 ሰው መሞቱንና አንገርባጃ ቀበሌ 2 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው አስረድተዋል። እንደ ክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ገለፃ ወደ ኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ እና በስጋት ምክንያት ወደ ጫካ የገቡ ሰዎች ያሉ ሲሆን ቁጥራቸው ምን ያህል ነው የሚለውን ግን የተጠናቀረ መረጃ የለኝም በማለት ሳይናገሩ ቀርተዋል።

የተፈናቀሉት ሰዎች ከቤንሻንጉል ብቻ ሳይሆን ክልሉን ከሚያዋስኑት የኦሮሚያ ቀበሌዎችም እንደሆነ የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ሳስጋ ወረዳ ዱራበሎ፣ ካምፕ፣ በሎበሬዳ፣ ስምንተኛ ከሚባሉት ቀበሌዎች በስጋት ምክንያት ወደ ነቀምትና በሎበሬዳ ወደሚገኙ ማዕከሎች #ተፈናቅለው እንደሚገኙ ተናግረዋል።

የምሥራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደርና ፀጥታ ኃላፊ የሆኑት አቶ ታከለ ቶሎሳ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በቤንሻንጉል ክልል የኦሮሚያ አዋሳኝ ቀበሌዎች በተከሰተው ግጭት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 12 ደርሷል። ከዚህ በተጨማሪም 14 ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን እነዚህም በሳስጋ ወረዳ ጤና ጣቢያና በነቀምት ሆስፒታል ህክምና እያገኙ መሆናቸውን ገልፀዋል።

እንደ ኃላፊው ገለፃ ከሆነ ቀያቸውን ጥለው ወደ ኦሮሚያ የተሰደዱ ሰዎች ቁጥር 50 ሺህ ደርሷል። እነዚህ ሰዎች የተፈናቀሉት ከበሎይ ጅጋንፎና ያሶ ሲሆን ከኦሮሚያ አዋሳኝ ወረዳዎች ደግሞ ሀሮ ሊሙ፣ ሶጌና ሳስጋ አካባቢዎች ነው።

አቶ ታከለ ጨምረውም ከእነዚህ አካባቢዎች የሚፈናቀሉ የኦሮሞ እና የአማራ ተወላጆችች ቁጥር በየእለቱ እየጨመረ መሆኑን ገልፀዋል። የተፈናቀሉት ሰዎች ሳስጋ ወረዳ፣ ነቀምት ከተማ፣ ሀሮ ሊሙ ወረዳና ጉቶ ጊዳ ወረዳ ውስጥ ኡኬ ከተማ ተጠልለው እንደሚገኙ ጨምረው አስረድተዋል።

በምሥራቅ ወለጋ የሀሮ ሊሙ ወረዳ ኮሙኑኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ በበኩላቸው አቶ #ዱጋሳ_ጃለታ ከቤንሻንጉል ክልል 7 ቀበሌዎች 20 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን ለቢቢሲ የተናገሩ ሲሆን እስካሁን ባላቸው መረጃ በወረዳው ብቻ 5 ሰዎች ሞተዋል።

2 #ነፍሰጡር እናቶች መንገድ ላይ መውለዳቸውን የተናገሩት አቶ ዱጋሳ ህፃናት፣ እናቶችና አቅመ ደካሞች የመኪና መንገድ ባለመኖሩ የተነሳ ለመሸሽ አዳጋች እንደሆነባቸውም ጨምረው አስረድተዋል።

በቤንሻንጉል ክልል #ግጭት በተከሰተባቸው በበሎይ ጅጋንፎይ ወረዳ #ሦስት አካባቢዎች እንዲሁም በካማሼ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሰፍረው እንደሚገኙ የተናገሩት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በተለያየ ጊዜ ምርት በሚደርስበት አካባቢ በክፍፍል ወቅት በተደጋጋሚ ግጭቶች እንደሚነሱ ነገር ግን እነዚህን ወስዶ #ብሄር ተኮር ግጭት ነው ማለት እንደማይቻል አስረድተዋል።

የምሥራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደርና ፀጥታ ኃላፊ የሆኑት አቶ ታከለ ቶሎሳ በበኩላቸው እስካሁን ድረስ 40 ሰዎች ከቤንሽንጉል 5 ሰዎች ደግሞ ከኦሮሚያ #በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ለተፈናቀሉ ሰዎች የአካባቢው ማህበረሰብ #እርዳታ እያደረገላቸው መሆኑን ከመንግሥት ደግሞ አስፈላጊው ድጋፍ እየተጠበቀ እንደሆነ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ BBC የአማርኛው አገልግሎት

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰሜን ዕዝ~መከላከያ‼️

የሰሜን ዕዝ የዘንድሮውን 7ኛ የሰራዊ ቀን #ባድመ ላይ ሊያከብር ነው። የኢትዮ-ኤርትራ #ሰላም መፈጠር ለአገር መከላከያ ሰራዊት ፋይዳ የጎላ ሆኖ ማገኘቱን የሰሜን ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች ተናገሩ፡፡

“ህገ መግስታዊ #ታማኘነታችንና ህዝባዊ ባህሪያችንን ጠብቀን የተጀመረው ለውጥ እናስቀጥል” በሚል እየተከበረ ያለው 7ኛው የሰራዊት ቀን በዕዝ ደረጃ ባድመ አካባቢ ለሚደረገው የማጠቃለያ ስነ ስርዓት በተመለከተ አመራሮቹ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የሰሜን ዕዝ የሎጂስቲክስ ዘርፍ ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል #ከድር_አራርሳ የኢትዮ-ኤርትራ ሰላም መፈጠር ህዝቡ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲፈጠር ከማድረጉ በተጨማሪ ሰራዊቱን ለማሰልጠንና ያለስጋት ስራዎቹን እንዲያከናውን ያግዛል ብለዋል፡፡

#በመከላከያ_ሰራዊት ውስጥ የተጀመረው የማሻሸያ ስራ በተቋም ደረጃ ከላይ እስከ ታች እየሰፋና እየተጠናከረ መሆኑን ተናግርዋል፡፡ሰራዊቱ ኃይሉን እያጠናከረና የብሄር ተዋፅኦውን ይበልጥ እያስተካከለ እንደሚገኝም ምክትል አዛዡ አስረድተዋል፡፡ የሰሜን ዕዝ የሰው ሀብት አመራር ዘርፍ ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ገ/እግዚያብሄር በየነ 7ኛው የሰራዊቱ ቀን ከስጋት ነፃ በሆነና የሁለቱም አገራት ወታደሮች ከምሽግ ወጥተው በጋራ መዋል በጀመሩበት የሚከበር በመሆ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

በዓሉ ሰራዊቱ ከለውጥ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተከበረ ያለ በመሆኑ ሰራዊቱ ቃል ኪዳኑን የሚያድስበት አጋጣሚ አድርጎ እንደሚጠቀምበትም ተናግረዋል፡፡ እስካሁን በተለያዩ ዝግጅቶች የተከበረ ያለው የሰራዊቱ ቀን የማጠቃያ ስነ ስርዕቱን ባድመ ላይ ይካሄዳል፡፡

በበዓሉ ሰራዊቱ ዝግጅቱን የሚያሳዩ የተለያዩ ወታደራዊ ትዕይንቶችና የፓናል ውይይት የሚደረግ ሲሆን ሰራዊቱን ያገለገሉ አባላት የክብር አሸኛኘት ይደረግላቸዋል ተብሏል፡፡ እንደ ኢቢሲ ዘገባ የትግራይ ክልልና አጎራባች ክልሎች ተወካዮች በበዓሉ አከባበር ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

©ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia