TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቡ ወረዳ #በህጻናት የአካል ክፍሎች ዝርፊያ ላይ ተሰማርተዋል በሚል መሰረተ-ቢስ መረጃ ተነሳስተው ሰላማዊ ሰዎች ላይ ግድያ የፈጸሙ #ስምንት/8/ ግለሰቦችን መያዙን የወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ኮማንደር መሀመድ አህመድ ለኢዜአ እንደገለጹት በህብረተሰቡ ዘንድ በየጊዜው የሚሰራጨው ምንጩ ያልታወቀ የተሳሳተ መረጃ የአካባቢውን ሰላም እያወከው ይገኛል።

በዚህ የተነሳም ከትላንት በስቲያ ምሽት በወረዳው ቀበሌ 029 ላይ ቤተሰባቸውን ጠይቀው በመመለስ ላይ የነበሩ አምስት ግለሰቦች የህጻናት አካል ስርቆት ላይ የተሰማሩ ናቸው በሚል መሰረተ-ቢስ ጥርጣሬ መነሻነት በተፈጸመባቸው #የደቦ ድብደባ ህይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።

በድብደባው ህይወታቸው ካለፈው ግለሰቦች መካከል የሶስቱ አስከሬን ወደ ቤተሰቦቻቸው የተላከ ሲሆን ቤተሰቦቻቸው ያልተገኙ ሁለት አስከሬኖች አስፈላጊው መረጃ ተመዝግቦ በዛሬው እለት የቀብር ስነ-ስርዓታቸው እንደሚፈጸም ገልፀዋል።

በድርጊቱ የተጠረጠሩ ስምንት ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳዩ እየተጣራ ሲሆን ቀሪ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ለማዋል ከህብረተሰቡ ጋር እየተሰራ መሆኑንም ኮማንደር መሀመድ ተናግረዋል፡፡

በትላንትናው እለትም ከህብረተሰቡ፤ ከሐይማኖት አባቶች፤ ከሃገር ሽማግሌዎች ጋር በተደረገዉ ዉይይት ቀሪ ተጠርጣሪዎችን በማጋለጥ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር ተባብረው ለመስራት ስምምነት ላይ ተድርሷል”ብለዋል።

ህብረተሰቡም በእንዲህ አይነት መሰረተ-ቢስ ወሬ ሳይታለል ሁኔታውን በማጣራት ከደቦ ፍርድ እንዲቆጠብ መክረዋል፡፡

ለውጡን ለማደናቀፍ የሐሰት ወሬ እየነዙ የወረዳውን ሰላም ለማወክ የሚሰሩ ኃይሎች ስላሉ ህብረተሰቡ አካባቢውን ነቅቶ በመጠበቅ በእያንዳንዱ ጉዳይ ምክንያታዊ እንዲሆንም ጠይቀዋል፡፡

Via #ENA