TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray

ህወሓት ፤ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ባወጣው መግለጫ " አምባገነን " ሲል የጠራቸው የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በትግራይ ዘግናኝ ግፍ እየፈፀሙ ነው ብሏል።

በአጠቃላይ የኤርትራ ጦር በደቡብ አፍሪካ የጦርነት ማቆም ስምምነት ከተፈረመ በኋላም በትግራይ እና በህዝቡ ላይ የሚያደርሰውን #ሁሉን_አቀፍ ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል ሲል ከሷል።

የኢትዮጵያ መንግሥት #ኃላፊነቱን_እንዲወጣ ፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ኢሳያስ አፈወርቂ በትግራይና በህዝቡ ላይ እየፈጸመው ያለውን ግፍ እና በደል በአስቸኳይ እንዲያስቆም እንዲያደርግ ፤ ከትግራይ እንዲወጣ እንዲያስገድዱ ፤ ሲፈጽመው ለነበረው ወንጀል #ተጠያቂ እንዲሆን እንዲያደርጉ ሲል ጥሪ አቅርቧል።

" ህወሓት " በዛሬው መግለጫው ያነሳቸው ነጥቦች ምንድናቸው ?

- በተፈረመው #የሰላም_ስምምነት መሰረት ጦርነት እንዲቆም ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት እንዲከበር፣ የኤርትራና ሌሎችም ሃይሎች ከትግራይ እንዲወጡ ስምምነት ላይ ተደርሷል ብሏል።

- ህወሓት ፤ " አምባገነን " ሲል የጠራቸው የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ፤ በሰላም ስምምነቱ #እንዳልተደሰቱ ገልጾ ፤ " ወታደሮቹን ያስወጣል ተብሎ ቢጠበቅም ተጨማሪ ክፍሎችን (ኃይሎቹ) ወደ ትግራይ እያመጣ ነው " ብሏል። ይኸው ጦር በህዝባችን ላይ አሰቃቂ ወንጀል እየፈጸመ ይገኛል ሲል ገልጿል።

- የኤርትራ ጦር በሴቶቻችን ላይ ጾታን መሰረት ያደረገ እጅግ አረመኔያዊ ጥቃት እየፈፀመ ፤ ንፁሀን ዜጎችን እየጨፈጨፈ ፣ የህዝብና የግል ንብረት እየዘረፈ ወደ ኤርትራ እያጓጓዘ ፤ የተረፈውን ደግሞ #እያጠፋ እና እያቃጠለ ነው ፤ የትግራይ ቅርሶችም በከፍተኛ ደረጃ እየወደሙና እየተዘረፉ ነው ፤ በአጠቃላይ የኤርትራ ጦር በደቡብ አፍሪካ (ፕሪቶሪያ) የጦርነት ማቆም ስምምነት ከተፈረመ በኋላም በትግራይ እና በህዝቡ ላይ የሚያደርሰውን ሁሉን አቀፍ ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል ብሏል።

- ህወሓት የኢትዮጵያ መንግሥት ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ኢሳያስ አፈወርቂ በትግራይ እና በሕዝቡ ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍ እና በደል #በአስቸኳይ_እንዲያስቆም ፤ ከትግራይ እንዲወጣም እንዲያስገድደው እንዲሁም በትግራይ ሲፈጽመው ለነበረው ወንጀል ሁሉ ተጠያቂ እንዲሆን ማደረግ አለበት ብሏል።

- ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተለይም አፍሪካ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ፣ የአሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት በኢሳያስ አፈወርቂ " አምባገነን " ስርዓት ላይ ትክክለኛ ማዕቀብ እንዲጥልና ተጨባጭ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አቅርቧል።

ይህንን የህወሓት ክስ በተመለከተ ከ "ኤርትራ" በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ጦርነት እንዲያበቃ ፤ ያሉት ችግሮችም #በሰላም እንዲፈቱ ፤ የሰብዓዊ ድጋፍ ያለገደብ ለተቸገሩት ዜጎች ሁሉ እንዲደርስ ፤ መሰረታዊ አገልግሎቶች ስራ እንዲጀምሩ ለማድረግ በደቡብ አፍሪካ እና ኬንያ (የስምምነቱ ማስፈፀሚያ ላይ) ስምምነት መፈረማቸው አይዘነጋም።

በናይሮቢ ስምምነት በትግራይ ክልል ያሉ ታጣቂዎችን ትጥቅ ማስፈታት የውጭ ኃይሎችን እና ከኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጭ የሆኑ ኃይሎችን ሁሉ ከክልሉ (ከትግራይ ክልል) ከማስወጣት ጋር #አብሮ እንደሚከናወን መገለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia