TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከሚያደርጋቸው ከፍተኛ ቅድመ ጥንቃቄዎች አንዱ ከቻይና እና ቫይረሱ ከታየባቸው ሀገራት የሚመጡ አውሮፕላኖችን በኬሚካል የማፅዳት ስራ (Disinfecting) ይገኝበታል።" - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ፖሊስ የአ/አ ከተማ ነዋሪዎችን አመስግኗል...

33 ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በሠላም እንዲጠናቀቅ የአ/አ ከተማ ነዋሪዎች ላደረጉት ቀና ትብብር የከተማው ፖሊስ ኮሚሽን ምስጋናውን አቅርቧል፡፡ ኢትዮጵያ 33ኛውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና ሌሎች ተያያዥ ስብሰባዎችን ከጥር 26 እስከ የካቲት 2/2012 ዓ/ም ማስተናገዷ ይታወቃል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአፍሪካ ሕብረት የወጣቶች ልዩ መልዕክተኛ አያ ቺቢ...

የጥይት ድምጽ የማይሰማባት አፍሪካን የመፍጠር ዘመቻው እውን እንዲሆን ወጣቶች በመንግስታት ላይ ጫና እንዲያደርጉ በአፍሪካ ሕብረት የወጣቶች ልዩ መልዕክተኛ አያ ቺቢ ጠይቃለች።

ልዩ መልዕክተኛዋ 33ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ትናንት ሲጠናቀቅ እንደገለጸችው የበርካታ ወጣቶችን ሕይወት እየቀጠፈ ያለው ጦርነት ሊያበቃ ይገባል ብላለች።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የጥይት ድምጽ የማይሰማባት አፍሪካን ለመፍጠር ወጣቶች በመንግስታት ላይ ጫና ሊያደርጉ ይገባል" - አያ ቺቢ

በአፍሪካ ህብረት የወጣቶች ልዩ መልዕክተኛ 33ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ሲጠናቀቅ ለኢዜአ ከተናገረችው የወሰድነው፦

- የበርካታ ወጣቶችን ሕይወት እየቀጠፈ ያለው ጦርነት ሊያበቃ ይገባል።

- የጥይት ድምጽ የማይሰማባት አፍሪካን ለመፍጠር እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ እውን ለማድረግ የተቀናጀ ጥረት ያስፈልጋል።

- እ.አ.አ በ2063 አፍሪካ የበለጸገችና ሠላም የሰፈነባት፤ ወጣቶችና ሴቶች በምጣኔ ሃብት፣ በአመራር ሰጪነት እንዲሁም በፖሊሲ አውጪነት በመሳተፍ ተጠቃሚ የሚሆኑባት አህጉር እንድትሆን ከወዲሁ መስራት ያስፈልጋል። ይህን እውን ለማድረግ ሴቶችና ወጣቶች ትልቅ ሚና አላቸው።

- ሴቶችና ወጣቶች አጀንዳዎችን በመቅረጽ፣ ወደ ጦርነት ከሚወስዱ ድርጊቶች በመቆጠብ፣ የወጡ ፖሊሲዎች እንዲተገበሩ ሠላማዊና ሌሎች መንገዶችን በመጠቀም በመንግስታት ላይ ጫና ሊደረግ ይገባል።

- በአህጉሪቱ የወጣቶች መገለጫ የሆነውን ስራ አጥነት፣ ስደት፣ አመጽና ሌሎች የተሳሳቱ ትርክቶችን መቀየር ያስፈልጋል።

- አፍሪካ የምትፈልገውን ለውጥ ለማምጣት ያላትን ወጣት ኃይል ለፈጠራና ለሠላም ማስፈን መጠቀም ጊዜው አሁን ነው።

- የጥይት ድምጽ የማይሰማባት አፍሪካን የመፍጠር እንቅስቃሴን እውን ለማድረግ ዘመቻ ተጀምሯል። ወጣቶች ይህንን እንዲቀላቀሉም ጥሪ አቅርባለሁ።

- መንግስታት ወጣቶችን በውሳኔ ሰጪነት፣ በፖሊሲ፣ በምክር ቤት፣ በሲቪል ማህበርና ሌሎች ዘርፎች በማካተት ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት ይቻላል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ለኮረና ተህዋሲ መድሐኒትና ክትባት ለመፈለግ የሚደረገውን ጥረት ያፋጥናል የተባለ የሳይቲስቶች፣ የተመራማሪዎችና የባለሙያዎች ጉባኤ ዛሬ ዤኔቭ ሲዊትዘርላድ ውስጥ ተጀምሯል።

ለ2 ቀን የተሰበሰቡት የዓለም የጤና ሳይቲስቶችና ባለሙዎች ከገዳዩ ተሕዋሲ የሚያድን መድሐኒት ወይም የሚከላከል ክትባት ለማግኘት ስለተደረገ እና መደረግ ስላለበት ምርምር ይወያያሉ።

ስብሰባውን ያዘጋጀው የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የበላይ ኃላፊ ቴዎድሮስ አድሐኖም ለተሰብሳቢዎች እንደነገሩት ተሕዋሲው እስካሁን ከቻይና ውጪ ብዙ ጉዳት ባያደርስም ሥርጭቱ ለመላዉ ዓለም አሳሳቢ ነው ብለዋል።

[DW]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በትራፊክ አደጋ ዛሬም የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል...

በምስራቅ ጎጃም ዞን የጁቤ ወረዳ ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 4 ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ በ24 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የዞኑ ፖሊስ ገለፀ።

በምስራቅ ጎጃም ፖሊስ መምሪያ የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ክፍል ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ጎበዜ ይርሳው እንደገለፁት አደጋው የደረሰው ከባሶ ሊበን ከተማ 28 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ ኮርክ ከተማ በመጓዝ ላይ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 አማ 01594 አይሱዙ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በመገልበጡ ነው።

አደጋው የደረሰው ልምጭም በተባለው ቀበሌ ሲሆን 4 ሰዎች ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ በ9 ሰዎች ከባድ በ15 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ዋና ኢንስፔክተሩ ገልፀዋል።

የሟቾቹ አስከሬን ለቤተሰቦቻቸው የተሰጠ ሲሆን የአካል ጉዳት የደረሰባቸው 24 ሰዎች ደግሞ በደብረማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታልና በየጁቤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በህክምና ላይ ናቸው ተብሏል። አሽከርካሪው ለጊዜው በመሰወሩ ክትትል እየተደረገ ነው ያሉት ዋና ኢንስፔክተሩ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም ተናግረዋል።

[ENA]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#JIMMAA #AGGAAROO

ዛሬ የጅማ እና የአጋሮ ከተማ የነዋሪዎች አደባባይ በመውጣት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አመራር ያላቸውን ድጋፍ ገልፀዋል። በጅማ ከተማ "ለብልፅግና እንሩጥ" በሚል የጎዳና ላይ ሩጫም ተካሂዷል። የጠቅላይ ሚኒስትሩን አመራር እናደንቃለን ያሉት ወጣቶች 'እኛም ዶ/ር አብይ ነን" ሲሉ ተደምጠዋል። ስድብ እና ጥላቻ፣ እንዲሁም የኦሮሞን ህዝብ መከፋፈል ላይ የተጠመዱ አካላትም ከድርጊታቸው ይቆጠቡ ብለዋል።

[ፎቶዎቹ የጅማ ዞን ኮሚኒኬሽን ናቸው]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FACEBOOK

ፌስቡክ ከዘጠኝ አጋር አካላት ጋር በመተባበር ለአፍሪካ የኢንተርኔት  መረጃ ደህንነት እሰራለሁ ብሏል፡፡ ፌስቡክ ከሰሃራ በርሃ በታች ላሉ  አፍሪካ አገራት የኢንተርኔት መረጃ  አጠቃቀምንና አገልግሎቱን ለማሳደግ ከዘጠኝ መንግስታዊ እና  መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር  እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮሮና ቫይረስ በሽታ ትክክለኛውን ስያሜ አግኝቷል...

የኮሮና ቫይረስ በሽታ እስካሁን ትክክለኛ ስም እንደሌለው ይታወቃል። ቫይረሱን ለመለየት ብቻ ሳይንቲስቶች ኖቬላ ወይም "አዲስ" እያሉ ሲጠሩት ቆይተዋል።

ቫይረሱ 'ኮሮና' የሚል ስም ያገኘው በማጉሊያ መነጽር በሚታይበት ጊዜ ባለው ከዘውድ ጋር የሚመሳሰል ቅርጽ ነው።

አሁን ግን የጤና ባለሞያዎች ከ1,000 በላይ ሰዎችን የገደለውና ከ43,000 በላይ ሰዎችን ያጠቃውን የኮሮና ቫይረስ በሽታን COVID-19 የሚሰኝ ስያሜ ሰጥተውታል።

[BBC]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለመሆኑ COVID-19 ምን ማለት ነው?

- CO stands for corona
- VI for virus and
- D for disease

የኮሮና ቫይረስ ጊዜያዊ መጠሪያ የነበረው 2019-nCoV እንደነበር ይታወቃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከጅማ ዞንና ከከተማዋ የተውጣጡ የተለያዩ የማህበረሰብ አካላት የተሳተፉበትና በህዝቦች አብሮነት እሴት ላይ ትኩረቱን አድርጎ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ተሳታፊዎች ምን አሉ?

- የህዝቡን አብሮ የመኖር እሴት የሚሸረሽሩ ተግባራት ተነቅፈዋል።

- የኦሮሞ ህዝብ በሰላም የመኖር እሴትና አኩሪ ባህል እንዳለው ተብራርቷል።

- በመሰዳደብ፣ጥላቻና ነቀፋ ላይ ያተኮሩ ተግባራትን ሊወገዙ እንደሚገባቸው ሀሳብ ተሰጥቷል።

- ህዝቡን እንወክላለን የሚሉ አካላት እየተፈፀሙ ያሉ የህዝቡን አብሮነት እሴት የሚሸረሽሩ ተግባራት ተወግዘዋል።

የተወሰኑ የውይይት ተሳታፊዎች ሀሳብ፦

"ከየትኛውም ብሄርም ይሁን ሃይማኖትም ይሁን ክልል ተንኮል የሚያስብ ሰው የትም አይደርስም። በመሳደብ የሚመጣ ለውጥ የለም።"

"አዋቂና ለኦሮሞ ተስፋ ናቸው ከምንላቸው ሰዎች ያየነው ነገር የማይጠበቅ ነው። ይህ በጣም የሚያሳዝን ነው። እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም"

"ሰውነት የሚለካው በስራ ነው እንጂ በስድብ አይደለም። የአብይን ስራ ማሳነስ በእጅ መዳፍ የፀሃይን ብርሃን መከላከል እንደማለት ነው።"

"ሽማግሌ ሆኖ ልትፈርስ የነበረችን ሀገር ያዳነና ሰላምን ያወረደው ጠ/ሚ አብይ አህመድ ነው። ይህን ደግሞ ዓለም ሁሉ መስክሮለታል። እኛ እንደ ቄሮ ማንም ሰው እንዳሻው የሚጫወትብን መሆን አይገባንም።"

"እኛን እየሰደበ እና የአንድ አባት ልጆችን ለማባላት የሚመጣብንን ሰው አንፈልግም። የሚያጋጨንን ሰው በፍፁም አንቀበልም"

"እኛ ከአባጅፋር የተማርነው አቃፊነትንና በአንድነትና በወንድማማችነት በጋራ መኖር ነው። እኛ ረገጣና ጭቆናን ነው የምንቃወመው"

"ስድብና ጥላቻ በየትኛውም ሃይማኖት ተቀባይነት የለውም። ህብረተሰቡ አብሮነቱን የሚያጠናክር እሴቶችን ሊጠብቅ ይገባዋል"

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
"ለፍቅር እንሩጥ ጥላቻን እናምልጥ"

40 ሺ ሰው የሚሳተፍበት የአምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫና ፌስቲቫል የካቲት 15 ይካሄዳል፡፡ በዚህ ዝግጅት ላይም በዓለም ክብረ-ወሰን የሚመዘገብ ሰፊ እንጀራ ተጋግሮ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የፓለቲካ መሪዎች፣ አርቲስቶችና ታዋቂ ግለሰቦች አብረው ይቆርሳሉ፡፡

የቲሸርት ኩፖኖቹን በአሞሌ ኦላይን ላይና በሁሉም የዳሽን ባንክ ቅርንጫፎች በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡ አዘጋጆቹ ለቲክቫህ ቤተሰቦች የቲሸርት ዋጋውን ቀንሰው በ150 ብር አቅርበውልናል፡፡ በዚህ እድል መጠቀም የምትፈልጉ ቤተሰቦቻችን የምዝገባ ሊንኩን ተጠቅማችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡

https://forms.gle/H3R8nxTamrMPyieN7

#ቲክቫህ_ኢቨንት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE - የሟቾች ቁጥር 1,018 ደርሷል - በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 43,102 በኮሮና ቫይረስ [2019-nCoV] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1,018 የደረሰ ሲሆን 43,102 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 4,043 መድረሳቸውን ተመልክተናል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

- የሟቾች ቁጥር 1,115 ደርሷል
- በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 45,117

በኮሮና ቫይረስ [2019-nCoV] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1,115 የደረሰ ሲሆን 45,117 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 4,881 መድረሳቸውን ተመልክተናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞንንና አፋር ክልልን በሚያጎራብቱ አካባቢዎች በሚፈጠሩ ግጭቶች የሚጠፋው ህይወትና የሚደርሰው ጉዳይ እያሳሰበው እንደሆነ የአፋር ሰብዓዊ መብቶች ድርጅት አስታውቋል።

“ደም አፋሳሽ ግጭቶች እንዳይደገሙ መንግሥት የህግ የበላይነትን ያስከብር” ብሏል ድርጅቱ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጠው መግለጫ። የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ደግሞ ችግሩን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አመልክቷል።

ይሁን እንጅ ጥቃቶቹ የሚፈፀሙት በደፈጣ ከመሆኑ ባሻገር ኅብረተሰቡም አጥፊዎችን አሳልፎ የመስጠት ልማድ አለማዳበሩና የመንግሥት አካላትም በሚጠበቅባቸው ልክ አለመንቀሳቀሳቸው መፍትኄ ለማግኘት የሚደረገውን ጥረት እንዳከበደው የዞኑ አስተዳደር ጠቁሟል።

[VOA]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia