TIKVAH-ETHIOPIA
የገቢዎች ሚኒስቴር ከዚህ ወር ጀምሮ የስራ ሰዓት መግቢያና መውጫ ለውጥ አደረገ! የገቢዎች ሚኒስቴር ከየካቲት 01/2012 ዓ.ም ጀምሮ የስራ ሰዓት መግበያና መውጫ ያሻሻለ ሲሆን ከሰኞ እስካ አርብ፦ 1. ከጠዋቱ 2፡00 - 6፡00 መደበኛ የሥራ ሰዓት፣ 2. ከ6፡00 – 7፡00 የምሳ እረፍት፣ 3. ዘወትር አርብ ግን የሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00 – 5፡30 ሲሆን ከ5፡30 -7፡30 የምሳ ሰዓት ሆኖ…
እርማት!
የገቢዎች ሚኒስቴር የስራ ሰዓት መግቢያና መውጫ፦
ዘወትር አርብ የሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00 – 5፡30 ሲሆን ከ5፡30 -7፡30 የምሳ ሰዓት ሆኖ ከሰዓት በኃላ ደግሞ ከ7፡30–11፡00 መደበኛ የሥራ ሰዓት ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

ጋና አዲስ ኢምባሲ ልትገነባ ነው...
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣሕለወርቅ ዘውዴ እና የጋና አቻቸው ናና አኩፎ ለጋና ኤምባሲ ግንባታ የመሰረት ደንጋይ አስቀምጠዋል። ኤምባሲው የሚገነባው ከአፍሪካ ህብረት ጽህፈት ቤት አቅራቢያ ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣሕለወርቅ ዘውዴ እና የጋና አቻቸው ናና አኩፎ ለጋና ኤምባሲ ግንባታ የመሰረት ደንጋይ አስቀምጠዋል። ኤምባሲው የሚገነባው ከአፍሪካ ህብረት ጽህፈት ቤት አቅራቢያ ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የካቲት 11ን አስመልክተው ከመቓልሕ ትግራይ መፅሄት ጋር ባደረጉት ቆይታ የተናገሩት፦
ብሄራዊ ጭቆና ነበር ሲያጣላን የነበረው፤ እሱን የሚፈታ በህገ መንግስት ደረጃ መጣ፤ ስለዚህ የትግል ውጤት ነው። እሱም አንድነትን አምጥቷል። ሁሉም የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እኩል ናቸው። ስለዚህ ትልቅ ትንሽ የሚባል ነገር ፈረሰ ማለት ነው። ትልቅ ድል ደግሞ ህገ መንግስት ነው።
ክልሎችም እራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩበት ዕድልም ተፈጥሯል። አንዱ ቋንቋ፣ ባህል ከሌላው ቋንቋና ባህል ይጣጣል ነበር እሱም ተወግዷል። በአጠቃላይ በመረጥነው እንድንተዳደር ተደርጓል።
ማንም ተነስቶ ነበር የሚያስተዳድረው አሁን ግን ማስተዳደር የሚችል ብቃት ያለው ሰው ይመረጣል። በአጠቃላይ ስርዓቱ ተቀይሯል። በመታገላችንና መስዋዕት በመክፈላችን የደርግን ስርዓት አፈረስን ቀበርን ብቻ ሳይሆን ቀልጣፋ የሆነ እድገት ማሳየት የጀመርንበት ጭምር ነው።
ከድህነት መውጣት ጀመርን ስለዚህ የትጥቅ ትግሉ ውጤት አንደኛ ደርግን ማፍረስ ነው፤ ሌላውና ዋናው ግን ወደ ልማት ገብተን የነበረውን አስከፊውን ድህነት ለማጥፋት ስራ መጀመራችን ነው። በመታገላችንም ትልቅ ድል አስመዝግበናል። በጤናም ይሃን በትምህርት ያስመዘገብነው አውታር ጥሩ የሚባል ነው። ከድህነትም ጨርሰን ባንወጣም የመኖር እድላችን እየተራዘመ ነው።
[ትግራይ ቴሌቪዥን፣ TIKVAH-ETH]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

Bright Real Estate Marketing
0988 969696
Bank -- Facilitate
Office -- Bole Edna Mall 3rd Floor
Location -- Bole Dembel ( M² = 28,984 )
-- Bole Atlas EU
-- Kasanchis ECA
-- Greek Club
-- Haile Garment
-- Hayat Mekadoniya
-- Bole Bulbula -- Town House
www.brightrealestatem.com
Have Your Dream Home and Let Your Life be BRIGHT !

- ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ
- በድረ ገፁ ላይ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ዕቃዎቹን ወይም አገልግሎቱን መሸጥ ይችላል።
- ከ2700 በላይ ዕቃዎች
@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com
0953707070

#UPDATE
በውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የተመራው የኢትዮጵያ ልኡክ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከግብፅ እና ሱዳን ልዑካን ጋር የተደረገውን የህግ ማዕቀፍ ድርድር ውጤት በዋሽንግተን ዲሲ መገምገም ጀመረ። ሚኒስትሩ የህግ ማዕቀፍ ድርድር ውጤቱን ለመመልከት በትናንትናው እለት አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ መግባታቸውን በትዊተር ገፃቸው አስታውቀዋል።
[ኤፍቢሲ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የተመራው የኢትዮጵያ ልኡክ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከግብፅ እና ሱዳን ልዑካን ጋር የተደረገውን የህግ ማዕቀፍ ድርድር ውጤት በዋሽንግተን ዲሲ መገምገም ጀመረ። ሚኒስትሩ የህግ ማዕቀፍ ድርድር ውጤቱን ለመመልከት በትናንትናው እለት አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ መግባታቸውን በትዊተር ገፃቸው አስታውቀዋል።
[ኤፍቢሲ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE - የሟቾች ቁጥር 910 ደርሷል - በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 40,628 በኮሮና ቫይረስ [2019-nCoV] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 910 የደረሰ ሲሆን 40,628 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 3,466 መድረሳቸውን ተመልክተናል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE
- የሟቾች ቁጥር 1,018 ደርሷል
- በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 43,102
በኮሮና ቫይረስ [2019-nCoV] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1,018 የደረሰ ሲሆን 43,102 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 4,043 መድረሳቸውን ተመልክተናል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
- የሟቾች ቁጥር 1,018 ደርሷል
- በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 43,102
በኮሮና ቫይረስ [2019-nCoV] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1,018 የደረሰ ሲሆን 43,102 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 4,043 መድረሳቸውን ተመልክተናል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE
በክብርት የኢፌዲሪ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተመራ ልዑካን በቀድሞ የኬንያ ፕሬዚደንት ዳንኤል ቶሮይቲች አራፕ ሞይ ብሔራዊ የቀብር ስነ-ስርዓት ላይ ለመገኘት ናይሮቢ ገብቷል።
ምንጭ፦ የኢፌዴሪ ኢምባሲ ኬንያ

”ለአፍሪካ ልማት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር የጦር መሳሪያ ድምጽን ማጥፋት” በሚል ርዕስ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 33ኛው የአፍሪካ ኅብረት አባል አገሮች ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ትላንት ሌሊት ተጠናቋል።
በአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ጉባኤ የጸደቀውን የተለያዩ የኅብረቱ ተቋማት ምርጫን በተመለከተም የመሪዎቹ ጉባኤ አጽድቆታል። በዚህም መሰረት ኢትዮጵያን ጨምሮ 10 አገሮች የተመረጡበትን አዲሱን የኅብረቱ የሰላምና የደህንነት ምክር ቤት አባላትና ሌሎች የአባላት ሹመትን አጽድቀዋል፡፡

ቢቢሲ ባወጣው መረጃ ቻይና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በአግባቡ አልተቆጣጠሩም ያለቻቸውን ከፍተኛ ባለስልጣናት ከሃላፊነት አሰናብታለች፡፡
በአሁን ሰዓት አሳሳቢ ደረጃ ላይ በደረሰው ኮሮና ቫይረስ በቻይና ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎ በተለያየ ደረጃ ላይ የሚገኙ ባለስልጣናት ከሃላፊነታቸው ተሰናብተዋል፡፡
ከተሰናበቱ የስራ ኃላፊዎች መካከል፦
- የሁቤይ ቀይ መስቀል ምክትል ዳይሬክተር የመጣውን እርዳታ በአግባቡ ካለማድረስ ጋር በተያያዘ ከሃላፊነታቸው ተነስተዋል።
- የሁቤይ ጤና ኮሚሽን የፓርቲው ጸሐፊ እና የጤና ኮሚሽኑ ሃላፊ ከሃላፊነታት ተነስተዋል።
[ኤፍ ቢ ሲ፣ ቢቢሲ]

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ስለ ምዕራብ ወለጋ የተናገረቱ፦ በወለጋ ተነሳ ለተባለው ችግር ሁላችሁም እንደምታውቁት በተማሪዎች ብቻ ሳይሆን በስራ አመራሮች፣ በመንግስት የታጠቁ ኃይሎች፣ በባለሃብቶች ከፍተኛ ጥቃት ደርሷል። የታጠቁ ኃይሎችን በሙሉ ካሉበት ኑ በሰላም እንታገል ብለን የጋበዝንበትን የሄድንበትን ርቀት መናገር አያስፈልግም ስለምታውቁት። በወለጋ አካባቢ በጉጂ እንኳን የሚባለው በተለምዶ ነው ይሄ በጣም…
Audio
AMH-Western-Oromia-10-2-2020
#UPDATE
ምዕራብ ኦሮምያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱትን ሸማቂዎች ለማነጋገር የአገር ሽማግሌዎች እና ምሁራን ጋር ወደ አካባቢው መሄዳቸውን የክልሉ መንግሥት ኮምኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ገልፀዋል።
የቢሮው ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል "ጥያቄ ያለው አካል ካለ እሁንም ለመነጋገርና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በራችን ክፍት ነው" ብለዋል።
[VOICE OF AMERICA]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ምዕራብ ኦሮምያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱትን ሸማቂዎች ለማነጋገር የአገር ሽማግሌዎች እና ምሁራን ጋር ወደ አካባቢው መሄዳቸውን የክልሉ መንግሥት ኮምኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ገልፀዋል።
የቢሮው ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል "ጥያቄ ያለው አካል ካለ እሁንም ለመነጋገርና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በራችን ክፍት ነው" ብለዋል።
[VOICE OF AMERICA]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የምዕራብ ኦሮሚያ የፀጥታ ሁኔታ...
መንግስት የፀጥታ ኃይሎችን ከአካባቢው [ከምዕራብ ኦሮሚያ] እንዲያነሳ ከሸማቂዎች በኩል ለሚነሳው ጥያቄ የኦሮሚያ ክልል የኮሚኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ጌታቸው ባልቻ የሰጡት ምላሽ፦
እኔ አካባቢውን ተቆጣጥሬ እቀመጣለሁ፤ የአካባቢውን ፀጥታ አካል ለቆ ይውጣ የሚባለው ነገር ትክክል አይደለም። ወደዛም የገባነው ተኩስ ስለፈለግን የግንባር ውጊያ ስላለብን አይደለም የሸመቀው ኃይል ህዝቡን ሰላም ስላሳጣ ነው። በአንድ ሀገር ውስጥ ሁለት መንግስት፤ ሁለት የታጠቀ ኃይል ሊኖር አይችልም።
የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ያደረገው የመከላከያ ኃይል አለ፣ የኦሮሚያ ክልል የራሱ የሆነ ፖሊስ ኃይል አለው፤ በቀበሌ ደረጃ የሚሊሻ ኃይል አለው ህዝቡ በራሱ አውጥቶ ያደራጃቸው የፀጥታ አካላት አሉ፤ ከዛ ውጭ የሀገሪቱን ፀጥታ ማስከበር ያለበት ሌላ አካል የለም ታጥቆ መንቀሳቀስ ያለበት።
ግን ደግሞ ጥያቄ አለኝ፣ ጥያቄዬ አልተመለሰም ስለዚህ መታጠቅ አለብኝ ብሎ፤ ታጥቆ እዛ የገባው ኃይል ትጥቃችሁን አስቀምጡና ቁጭ ብለን እንነጋገር ያልተመለሰ ጥያቄ ካለ እንነጋገር ብለናል፣ ያንን እድል ተጠቅሞ ወደሰላማዊ መንገድ መጥቶ መመጋገር ከፈለገ ዛሬም በራችን ክፍት ነው።
አለበለዚያ ግን እኛ በዚህ አካባቢ ሽብር እየፈጠርን፣ ሰው እየታፈነ እየተወሰደ፣ እየተገደለ፣ እየሞተ፣ እየተዘረፈ መንግስት ከዚህ አካባቢ መውጣት አለበት የሚባለው ነገር አይሰራም። ትክክልም ሊሆን አይችልም።

ኮሮና ቫይረስ ሀገር ዓቀፍ መረጃ፦
- የቫይረሱን ስርጭት አስመልክቶ እስከ አሁን ድረስ 39 ጥቆማዎች ለኢንስቲትዩቱ የድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል (Emergency Operation Center) ደርሰው በሁሉም ጥቆማዎች ላይ ማጣራት ረደርጓል፣
- 14ቱ የበሽታውን ምልክት ያሳዩ ስለነበረ፣ ተለይተው ወደ ማቆያ ስፍራ (Isolation center) እንዲገቡ ተደርጎ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸውን ከተረጋገጠ በኋላ ወደ ሕብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል፣
- በትላትናው እለት 1ሰው በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረ ሲሆን በኢንስቲትዩቱ የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ውጤቱም ከቫይረሱ ነፃ በመሆኑ ከለይቶ ማቆያ ማእከሉ ወጥቷል፡፡ በአሁኑ ሰዓት በለይቶ ማቆያ ማእከል ውስጥ የበሽታው ምልክት ታይቶበት የገባ ሰው የለም፡፡
- ለመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች፣ ለሆቴል ባለሙያዎችና ከክልልና ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለተውጣጡ ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡
- ከቻይና የሚመጡ መንገደኞችን የሙቀት ልየታና የበሽታው ምልክት የታየባቸው መንገደኞችን የጤና ሁኔታ የመከታተል ስራዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
- በሁሉም የኢንዱስትሪ ፓርክ ባለባቸው ክልሎች ውስጥ የለይቶ ማቆያ ማዕከልና የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ማስተባበሪያ ማእከላትን ለምላሽ ዝግጁ ለማድረግ በተያዘው እቅድ መሰረት ደቡብ ክልል በሃዋሳ ከተማ ድጋፍ ሰጪ የባለሙያዎች ቡድን በመላክ ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመሆን የዝግጅት ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
[የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት]

-ስለ ወፈሩ ብቻ ስፖርት አይጀምሩ !
-ስለጤናማ የሆነ ያመጋገብ ስርአት በቂ እውቀት ይያዙ !
- ያለ እንቅስቃሴ የሰውነትዎን ክብደት ለመቀነስ አያልሙ!!
እነዚህን አማራጭ የሌላቸውን ግንዛቤ በመያዝ በትንሽ የእንቅስቃሴ ሰአት ከፍተኛ ካሎሪ (አላስፈላጊ ስብ) የምናቃጥልባቸውን በሙሉ የሚለበሱ sauna suit ልብሶችን በመልበስ ጤናማ ያኗኗር ዘይቤን ይከተሉ።
ያዩትን ራሱኑ በብር 900 እንሸጥሎታለን። ክ/ሀ ላላችሁ በፖስታ ቤት እንልካለን ። ዋና አድራሻ ቃሊቲ ካፍደም ሲኒማ 2ኛ ፎቅ ቢ ቁ. 207. ለመረጃ ። 0906 25 25 25.
ካሱ የስፖርት መገልገያ መሸጫ!

#UPDATE INSTITUTE FOR STRATEGIC AFFAIRS : Netherlands Institute for Multiparty Democracy : #DialogueForum - Andulaem Stage - Desalegne Chanie, Dr. - Getachew Reda - Jawar Mohammed - Lidetu Ayalew - Abrha Desta - Hassan Moalin - Konte Mussa, Dr. - Merera…
#UPDATE
"የዴሞክራሲ ሽግግር በኢትዮጵያ: ተስፋዎቹ እና ተግዳሮቶቹ" በሚል ርእስ በመጪው ሀሙስ በፖለቲካ ሰዎች መሀል ሊደረግ ታስቦ የነበረው ውይይት ተራዝሟል።
አዘጋጁ Institute for Strategic Affairs "ፕሮግራሙ የተራዘመው አንዳንዶቹ ንግግር ያረጋሉ ተብለው የነበሩት ሰዎች ሌላ ስራ ስላጋጠማቸው ነው" ያለ ሲሆን ይህ ፕሮግራም ለግዜው ላልተወሰነ ግዜ ተራዝሟል ብሏል።
[Elias Meseret]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የዴሞክራሲ ሽግግር በኢትዮጵያ: ተስፋዎቹ እና ተግዳሮቶቹ" በሚል ርእስ በመጪው ሀሙስ በፖለቲካ ሰዎች መሀል ሊደረግ ታስቦ የነበረው ውይይት ተራዝሟል።
አዘጋጁ Institute for Strategic Affairs "ፕሮግራሙ የተራዘመው አንዳንዶቹ ንግግር ያረጋሉ ተብለው የነበሩት ሰዎች ሌላ ስራ ስላጋጠማቸው ነው" ያለ ሲሆን ይህ ፕሮግራም ለግዜው ላልተወሰነ ግዜ ተራዝሟል ብሏል።
[Elias Meseret]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE
የኢፌዲሪ ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ ከየካቲት 5 እስከ 7 ቀን 2012 ዓ.ም በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ለሚያደርጉት ጉብኝት የተቋቋመው አብይ ኮሚቴ ዝግጁትን ማጠናቀቁ ተገልጿል። ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አርብ የካቲት 6 ቀን 2012 ዓም በዱባይ ከተማ ሸባብ አልአህሊ ክለብ በአልመክቱም ስታዲያም የሙሉ ቀን ዝግጅት ላይ በመገኘት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና በመካከለኛው ምስራቅ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መልእክት ያስተላልፋሉ።
#EPA

"የመከላከያ ሠራዊት ቀን" የካቲት 7 ቀን 2012 ዓ.ም ይከበራል። የዘንድሮው የመከላከያ ሠራዊት ቀን “የሀገራችንን ሉዓላዊነትና የሕዝባችንን ሠላም በፅናት እንጠብቃለን” በሚል መሪ ሃሳብ እንደሚከበር ታውቋል።

ዳዊት ፍቃዱ ይባላል በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች በ ' Solve IT ' የፈጠራ ሥራና የማህበራዊ ችግር ፈቺ ፕሮጀክቶች ውድድር ዙሪያ ለተማሪዎች ግንዛቤ እየሰጠና ስለ ውድድሩ እያስተዋወቀ ይገኛል፡፡
ሌሎች አከባቢዎችስ ያሉ ተማሪዎች እንዴት መወዳደር ይችላሉ?
በ15 ከተሞች ጨምሮ በማህበራዊ ሚዲያው እየተሰራ የሚገኘው ውድድሩን የማስተዋወቅና ኃሳብ ያላቸውን ወጣቶች ዕድሉን እንዲጠቀሙ የማስቻል ሥራ፡ነው፡፡ ምዝገባው ለሁሉም በድረገፅ የሚከናወን ይሆናል፡፡ ባለፈው አመት በ ' Solve IT ' አሸናፊ ለነበሩ ወጣቶች ከ100,000 - 25,000 ሥራ መጀመሪያ ገንዘብ መሸለማቸው ይታወሳል፡፡ ቲክቫህ ኢትዮጵያም ወጣቶች ከዚህ ዕድል እንዲጠቀሙ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡
ለመመዝገብ https://www.icog-solveit.com/register/participant

የሱዳን የሽግግር መንግሥት የቀድሞ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽርን ለዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት (ICC) አሳልፎ ለመስጠት መስማማቱን ቢቢሲ ዘግቧል።
የሽግግር መንግሥቱ ውሳኔው ላይ መድረሱን ያስታወቀው የሀገሪቱ ወታደራዊ ምክር ቤት መሆኑን ነው የተሰማው።
አልበሽር በዳርፉር ግጭት ውስጥ የዘር ማፅዳት ፈፅመዋል፤ የጦር ወንጀል እና በሰብአዊነት ላይ ወንጅል ሠርተዋል የሚል ክስ በዓለም አቀፍ የወንጀል ችሎቱ የቀረበባቸው መሆኑ ይታወሳል።
የአፍሪካ ኅብረት እና መሪዎቹ ከዚህ በፊት "ዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት የአፍሪካ መሪዎችን ብቻ ነጥሎ ያጠቃል" በሚል የተቋሙን ሂደት ሲቃወሙ የነበረ ቢሆንም አዲሱ የሱዳን የሽግግር መንግሥት ግን አልበሽርን አሳልፎ ለመስጠት ወስኗል።
[BBC]

የኢትዮጵያ አየር መንገድ...
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮሮና ቫይረስን [2019-nCoV] ለመከላከል አውሮፕላኖችን በኬሚካል የማፅዳት ስራ በማከናወን ላይ ይገኛል።
አየር መንገዱ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከሚያደርጋቸው ቅድመ ጥንቃቄዎች አንዱ ከቻይና እና ቫይረሱ ከታየባቸው ሀገራት የሚመጡ አውሮፕላኖችን በኬሚካል የማፅዳት ስራ መሆኑን አስታውቋል።
[የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኤፍ ቢ ሲ]