TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ዶዶላ #ሻሸመኔ #ቡታጅራ #ጅማ #ከሚሴ

ኑ ትውልድ እንገንባ!

ቤት ካላችሁ የመማሪያ መፅሃፍ ቢያንስ አንዱን ለሀገራችሁ በስጦታ አበርክቱ!

#ዶዶላ
0920068173/ቶሎሳ/

#ከሚሴ
0921632606/ኑር አህመድ/
0915543171/ሁሴን/

#ሻሸመኔ
+251915596576/አሸናፊ/

#ቡታጅራ
0910899212/Yab/

#ጅማ
+251942630419/ፍላጎት/
0911670454/አሰፋ/

•ከ1ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ የመደበኛ የመማሪያ እና አጋዥ መፅሃፍትን በመለገስ ለመጭው ትውልድ የተሻለች ኢትዮጵያን እናውርስ!!

📚የዘንድሮው አመት ተፈታኝ ተማሪዎች እና ወላጆች በዚህ ስራ ላይ በስፋት በመሳተፍ ለመጭው ትውልድ አርዓያ ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን!

5ኛው አመት የTIKVAH-ETHIOPIA የመፅሃፍት ማሰባሰብ ዘመቻ!

በዚህ ሀገራዊ ስራ መሳተፍ የምትፈልጉ የበጎ አድራጎት #ማህበራትና #ግለሰቦች @tsegabwolde

በሁሉም ከተሞች ያሉ አስተባባሪዎችን በየዕለቱ እናውቃለን!

📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚

ትግራይ ክልል #ኢሮብ አካባቢ የምትገኙ የቤተሰባችን አባላት መልዕክት አስቀምጡልን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዶዶላ #ቢሾፍቱ #ሀረር

በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ከተማ ትናንት እና ዛሬ በነበሩ ግጭቶች በጠቅላላው 6 ሰዎች መገደላቸውን ታውቋል። ዛሬ በነበረ ግጭት 4 ሰዎች ሞተው ወደ ዶዶላ አጠቃላይ ሆስፒታል መምጣታቸውን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ቶላ ቢዮ ተናግረዋል። ትናንት ደግሞ ሁለት ሰዎች ተገድለው ነበር። በአካባቢው ከጠዋት ጀምሮ ሠልፍ እንደነበር የተናገሩት ሜዲካል ዳይሬክተሩ ከሰዓት በኋላ ግን ይህ ሠልፍ መልኩን መቀየሩን ይናገራሉ። ሁኔታው አስፈሪ ስለነበር ለሕይወታቸው የሰጉ ሰዎች በአካባቢው በምትገኘው ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው አንደሚገኙ ተናግረዋል። በሐረር ከተማ በትናንትናው ዕለት 3 ሰዎች መገደላቸውን ቢቢሲ ከነዋሪዎች ሰምቻለሁ ብሎ ዘግቧል። በቢሾፍቱ ከተማ ዛሬም በቀጠለው አለመረጋጋት የሰዎች ህይወት ማለፉን የቢሾፍቱ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ተናገርዋል። ዛሬ ከተማይቱ በተኩስ ስትናጥ እንደዋለች፣ በየቦታው መንገዶች ሲዘጉ እንደነበርና ወታደሮች መንገድ ለማስከፈት ሲንቀሳቀሱ መዋላቸውን ገልፀዋል። አመሻሹን ግን ሁኔታዎች ረገብ ብለዋል።

#BBC

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዶዶላ

በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ከተማ ረቡዕና ሐሙስ በነበሩ ግጭቶች በጠቅላላው 6 ሰዎች መገደላቸውም ታውቋል። ሐሙስ በነበረ ግጭት 4 ሰዎች ሞተው ወደ ዶዶላ አጠቃላይ ሆስፒታል መምጣታቸውን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ቶላ ቢዮ ተናግረዋል። ረቡዕ ደግሞ ሁለት ሰዎች ተገድለው ነበር።

@tsegabwolde @tikvahethiopia