TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#TPLF #እንዳስላሰሽረ

በሊቀ መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ተከለከለ።

ህወሓት ሰላማዊ ስልፍ ለማካሄድ ከጳጉሜን 3 - 5 ባሉት ቀናት የጠየቀ ሲሆን ሰልፉ የሚካሄድበት ቦታ ደግሞ በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን እንዳስላሰ ሽረ ከተማ ነው።

የህወሓት ፅህፈት ቤት እንዳስላሰ ሽረ ቅርንጫፍ ነሃሴ 29/2016 ዓ.ም በፃፈው የሰላማዊ ሰልፍ የፍቃድ ደብዳቤ በክልሉ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ በሰላማዊ መንገድ ድምፁ ለማሰማት መፈለጉ ያትታል።

ቅርንጫፍ ፅህፈቱ ፍቃድ በጠየቀበት ሰላማዊ ሰልፍ ፦

"
- ከባቢያዊ መለያየትና አገር የሚበትኑ ተግባራት ይቁሙ !
- ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ይመለሱ !!
- የፀለምቲና ራያ ተመላሽ ተፈናቃዮች ድህንነታቸው ይጠበቅ !
- የህዝበኝነት ፓለቲካ በትግራይ እንቃወማለን !
- የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ይተግበር !
- ጊዚያዊ አስተዳደር የተቋቋመለት ዓላማ ይተግብር !
- ህወሓትን ለማፍረስ የሚደረግ እንቅስቃሴ ይቁም !
- ህወሓት ሰላምን ይደግፋል !
- ጦርነት የሚናፍቅ የህወሓት መሪ የለም ! "

የሚሉና ሌሎች መፈክሮች እንደሚያሰማ በፍቃድ መጠየቂያ ደብዳቤው ላይ ገልጿል።

ቅርንጫፍ ፅህፈቱ ለጠየቀው ' ሰላማዊ ሰልፍ ' የማካሄድ ጥያቄ መልስ የሰጠው የእንዳስላሰ ሽረ ከተማ አስተዳደር በወቅቱ ባለው የፓለቲካ ትኩሳት እና የአዲስ ዓመት መለወጫ በመሆኑ ምክንያት የፀጥታ ሃይሉ የተደራረቡ ስራዎች ስላሉበት ሰላማዊ ስልፉ እንዳልተፈቀደ አሳውቋል።

በጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ልኡክ በተምቤን ዓብዩ ዓዲ ዓዲግራትን ማይጨው ካካሄዳቸው ህዝባዊ ውይይቶች በመቀጠል በአክሱምና በእንዳስላሰ ሽረ ከተማዎች ለማካሄድ አቅዶ የነበረ ቢሆንም አቶ ጌታቸው ባጋጣመቸው የጤና እክል ምክንያቱ ውይይቱ ለሌላ ጊዜ መዛወሩን የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል መዘገቡ ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia