TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አምቦ_ዩኒቨርሲቲ

#Congratulations የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ከ5 ሺ 600 በላይ በተለያየ የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በታላቅ ድምቀት አስመርቋል። #AmboUniversity

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አምቦ_ዩኒቨርሲቲ🎓

#Congratulations የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ከ5 ሺ 600 በላይ በተለያየ የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በታላቅ ድምቀት አስመርቋል። #AmboUniversity

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
#አምቦ

በአምቦ ከ5መቶ በላይ ሰዎች መታሰራቸውን ቤተሰቦቻቸው ገለፁ። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የፖለቲካ ኃላፊም አባላትና፣ ደጋፊዎቼ እንዲሁም አመራሮቼ ታስረዋል ብሏል፡፡ የከተማው ፖሊስ መምሪያ የታሰረ ሰው የለም ሲል አስተባብሏል፡፡

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አምቦ #ለኩ #ጅማ #ከሚሴ #ይርጋለም #ሃዋሳ #ሶዶ

ኑ ትውልድ እንገንባ!

#አዲስ_አበባ
0970514616/ዮናስ ገ/መስቀል/
0924140293/መባ/

#ሰበታ
0932540523/ያሬድ ለማ/
0921421493/ያብስራ ካሳ/

#መቐለ
0912178520/ኤርሚያስ ደጀኔ/
0923602445/ፊራኦል መስፍን/

#ራያ_ቆቦ
+251949256094/ሉላይ/

#ጅማ
0911670454/አሰፋ/

#ድሬዳዋ
0915034762/መሃሪ/

#አዳማ
0949377735/ሰላም/

#ሀዋሳ
+251926429534/ተስፋ/
+251935932153/ብስራት/

#ለኩ
0919687777/ዳዊት እንዳለ/

#ይርጋለም
0953804369-/አሸናፊ/
0964039768-ብርሀኑ/

#ከሚሴ
0915543171/ሁሴን/

#ወላይታሶዶ
+251913776084/Aso/
0926172318/Beza/

•ከ1ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ መደበኛ የመማሪያ እና አጋዥ መፅሃፍትን በመለገስ ለመጭው ትውልድ የተሻለች ኢትዮጵያን እናውርስ!!

📚የዘንድሮው አመት ተፈታኝ ተማሪዎች እና ወላጆች በዚህ ስራ ላይ በስፋት በመሳተፍ ለመጭው ትውልድ አርዓያ ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን!

5ኛው አመት የTIKVAH-ETHIOPIA የመፅሃፍት ማሰባሰብ ዘመቻ!

በዚህ ሀገራዊ ስራ መሳተፍ የምትፈልጉ የበጎ አድራጎት ማህበራትና ግለሰቦች @tsegabwolde

በሁሉም ከተሞች ያሉ አስተባባሪዎችን በየዕለቱ እናሳውቃለን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአምቦ ወጣቶችን አመስግኑልን!

#የአምቦ_ወጣቶች_ማህበር ለወላጅ አልባ ለሆኑና እና ለአቅመ ደካማ ቤተሰብ ልጆች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል። ማህበሩ ከሰሞኑን በአምቦ ከተማ የትምህርት ቁሳቁስ ሲያሰባስብ እንደነበር በTIKVAH-ETH አሳውቀናችሁ ነበር።

"Paakko Tokko Barataa Tokkof"
/አንድ እሽግ ለአንድ ህፃን/
#አምቦ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተቃውሞ ሰልፎቹን ተከትሎ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት አጋጠመ!

ትናንት ሌሊት በአክቲቪስት ጀዋር መሃመድ መኖሪያ ቤት አጋጠመ የተባለውን ክስተት ተከትሎ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች በርካታ ሰዎች ለተቃውሞ ሰልፎች አደባባይ ወጥተዋል። የተቃውሞ ሰልፍ ከተደረገባቸው ከተሞች መካከል አምቦ፣ አዳማ እና ሻሸመኔ ከተሞች ይጠቀሳሉ። በዚህም በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

#አምቦ

በአምቦ በተቀሰቀሰው ግጭት ቢያንስ ሦስት ሰዎች በጥይት ተመተዋል ተብሏል። በአምቦ በተቀሰቀሰው ግጭት ነዋሪዎች አምስት ሰዎች በጥይት መመታታቸውን ለቢቢሲ የተናገሩ ሲሆን፤ የሆስፒታል ምንጮች በበኩላቸው ሦስት ሰዎች ለሕክምና ወደ አምቦ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

የአምቦ ከተማ ነዋሪዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ሌሊቱን በአክቲቪስት ጀዋር መሃመድ መኖሪያ ቤት ተፈጸመ የተባለውን ክስተት ተከትሎ ተቃውሟቸውን ለመግለጽ አደባባይ ወጥተዋል። ለተቃውሞ የወጡትን ሰዎች ለመበተን የጸጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ ከተኮሱ በኋላ ተቃዋሚዎች ፖሊሶች ላይ ድንጋይ መወርወር እንደጀመሩ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ያስረዳሉ።

ይህ ተከትሎም ነዋሪዎች አምስት ሰዎች በጥይት መመታታቸውን የተናገሩ ሲሆን፤ የአምቦ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ደበበ ፈጠነ በበኩላቸው ሦስት ሰዎች በጥይት ተመተው ለህክምና ወደ ሆስፒታላቸው መምጣታቸውን አረጋግጠዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-23-2

Via BBC
@tsegabwolde
#አምቦ

ትናንት በአምቦ ከተማ ከተገደሉት ሶስት ሰዎች በተጨማሪ ዛሬ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል። ዛሬ በጥይት ከተገደሉት መካከል የ80 ዓመቱ አዛውንት አቶ ሞሮዳ ሞሳ የሚባሉ ይገኙበታል በማለት ነዋሪዎች ተናግረዋል። አቶ ሞረዳ ልጃቸውን ፍለጋ በወጡበት ከጸጥታ አስከባሪ ኃይል በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸውን የከተማው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በአምቦ ዛሬ ከተገደሉት ሁለት ሰዎች በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ሰዎቸ በጥይት ተመትተዋል።

የአምቦ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር አቶ ደበበ ፈጠነ፤ "ዛሬ 14 ሰዎች በጥይት ተመተው እኛ ጋር መጥተዋል። ሁለቱ ህይታቸው አልፏል። 9 ሰዎች ደግሞ ተኝተው እየታከሙ ሲሆን የተቀሩት ቀላል ህክምና ተደርጎላቸው ወደየቤታቸው ተመልሰዋል" በማለት ያስረዳሉ። አቶ ደበበ ወደ ሆስፒታላቸው የመጡት ሰዎች በሙሉ ወንዶች መሆናቸውን እና ዕድሜያቸውም ከ17-80 እንደሚገመት ተናግረዋል። በዚህም በአምቦ ትናንት 3፤ ዛሬ 2 በድምሩ የሟቾች ቁጥር 5 ደርሷል።

#BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አምቦ | ረቡዕ እና ሐሙስ ዝግ ሆነው የነበሩት መንገዶች ከዛሬ ጠዋት (ዓርብ) ጀምሮ ክፍት ተደርገዋል። ባለፉት ሁለት ቀናት በነበሩት ግጭቶ 5 ሰዎች ተገደሉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል አንድ የፖሊስ አባል ይገኝበታል። ይህ የፖሊስ አባል የተገደለው ሐሙስ ዕለት ሲሆን ረቡዕ ዕለት በነበረው ግጭት 'ሰው ገድለሃል' ተብሎ በበቀል እርምጃ እንደተገለ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

(ቢቢሲ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia