TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ‼️

አሶሳ ዩኒቨርሲቲን ወደ ቀድሞ ሰላሙ #ለመመለስ እየተሠራ መሆኑን ተወካይ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡

ካለፈው እሑድ ጀምሮ ዩኒቨርሲቲው ውስጥ ሰላማዊ መማር ማስተማሩ ተስተጓጉሏል፡፡ ተማሪዎች እና ተወካይ ፕሬዝዳንቱ እንደነገሩን የግጭቱ መነሻ የሁለት ተማሪዎች አለመግባባት ነው፡፡ ይህም እየተስፋፋ ሄዶ ወደ ቡድን ፀብ ተቀይሮ ነበር፡፡

ተወካይ ፕሬዝዳንቱ ዶክተር #ሃይማኖት_ዲሳሳ ችግሩን ለመፍታት ከሃይማኖት አባቶች እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመሆን ከተማሪዎች ጋር ምክክር ተደርጎ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ በውይይቱም መግባባት ላይ መደረሱ ተማሪዎች አረጋግጠዋል፡፡

ይሁን እንጂ የዓይን እማኞች እንደተናገሩት ትናንት ጠዋት ላይ ተማሪዎች ወደ መመገቢያ አዳራሽ ሲገቡ እንደገና #ረብሻ ተጀምሮ ነበር፡፡

እንደ ተማሪዎቹ መረጃ የግጭቱ ዋነኛ ምክንያት የተማሪዎች መማክርት በወቅቱ አለመመረጥ ኢ-ፍትሐዊ አሠራር ፈጥሯል የሚል ነው፡፡

ተማሪዎቹ ምርጫው ‹‹ባለፈው ዓመት ሰኔ ላይ መካሄድ ነበረበት፤ በወቅታዊ ጉዳዮች ምክንያት አልተካሄደም፤ እስካሁን ግን መቆየት አልነበረበትም›› የሚል አቋም አላቸው፡፡

አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ችግሮችን ተወካዮቻቸው በወቅቱ አለመፍታታቸውም ለችግሩ መከሰት ምክንያት መሆኑን ነው ተማሪዎቹ የተናገሩት፡፡

ተወካይ ፕሬዝዳንቱ ግን ‹‹በውይይቱ ለከፋ ግጭት የሚዳርግ ችግር አላገኘንም›› ነው ያሉት፡፡

በረብሻው ምክንያት ‹‹34 ተማሪዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች ህክምና እየተደረገላቸውም ይገኛል ብለዋል
ዶክተር ሃይማኖት፡፡

በተከሰተው ግጭት የሶስት ተማሪዎች ህይወት አልፏል፡፡ የጸጥታ ኃይሎች ግቢውን ወደ ቀድሞ ሰላሙ ለመመለስ እየሠሩ መሆናቸውን ተወካይ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎችም ይህን መመልከታቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ይሁን እንጂ ተረጋግተው ለመኖር እና ለመንቀሳቀስም ስጋት ውስጥ መሆናቸውንና ለሰላማቸው #ዋስትና እንደሚፈልጉ ነው የተናገሩት፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia