TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
* Congratulations !

በዛሬው ዕለት ብቻ ከተለያዩት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ከ30,192 በላይ ተማሪዎች ተመርቀዋል።

የትኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች ምን ያህል ተማሪ ? በምን ደረጃ እና የትምህርት ዘረፍ አስመረቁ ? ለጥያቄዎቹ መልስ ይህን አጭር ቁጥራዊ መረጃ አስቀምጠናል።

#HawassaUniversity

- አጠቃላይ 6 ሺህ 793 ተማሪዎችን አስመርቋል።
- ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 2 ሺህ 158ቱ ወይም 32 በመቶ ሴቶች ናቸው።
- ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ፣ በ2ኛ እና በ3ኛ ዲግሪ በመደበኛና ተከታታይ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

#BahirdarUniversity

- አጠቃላይ 5 ሺህ 586 ተማሪዎች አስመርቋል።
- ከተመራቂዎቹ 1 ሺህ 714ቱ ሴቶች ናቸው።
- በመጀመሪያ፣ በ2ኛ እና በ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናሰቁ ናቸው።

#JimmaUniversity

- አጠቃላይ 696 ተማሪዎች አሰመርቋል።
- 450 ወንድ እና 246 ሴት ተማሪዎች ናቸው።
- በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
- ከተመራቂዎቹ 252 ተማሪዎች በአጠቃላይ ሕክምናና በጥርስ ሕክምና የሰለጠኑ ናቸው።
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ በሶማሊላንድ ሀርጌሳ ካምፓሱ በ 'ኒውትሬሽን' የትምህርት ዘርፍ ያስተማራቸውን 19 የ2ኛ ዲግሪ ተማሪዎችንም አስመርቋል።

#AdamaScience_and_TechnologyUniversity (ASTU)

- አጠቃላይ 1 ሺህ 298 ተማሪዎች አስመርቋል።
- ሰባቱ በሦሥተኛ ዲግሪ (ፒኤችዲ) ተመራቂዎች ናቸው።
- 215ቱ በሁለተኛ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው።
- 1 ሺህ 76 ተማሪዎች በመጀመረያ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው።

#MettuUniversity

- አጠቃላይ 2 ሺህ 262 ተማሪዎች አስመርቋል።
- 116ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
- ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና በተከታታይ መርሃ ግብሮች በመቱ እና በበደሌ ካምፓሶች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።

#ArsiUniversity

- አጠቃላይ 831 ተማሪዎችን አስመርቋል።
- በበቆጂ ካምፓስ የሰለጠኑ ናቸው።
- ተመራቂዎቹ በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
- በመጀመሪያ እና በ2ኛ ዲግሪ ከተመረቁት መካከል 392ቱ ሴቶች ናቸው።

#AmboUniversity

- አጠቃላይ 4 ሺህ 524 ተማሪዎች አስመርቋል።
- በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ የሰለጠኑ ናቸው።
- ከተመራቂዎቹ 1 ሺህ 980ዎቹ ሴት ተማሪዎች ናቸው።
- ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 450 የሚሆኑት የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂ ሲሆኑ 11 የደቡብ ሱዳን ስደተኛ ተማሪዎች ይገኙበታል።

#JigjigaUniversity

- አጠቃላይ 1 ሺህ 202 ተማሪዎችን አስመርቋል።
- ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 336ቱ ሴት ተማሪዎች ናቸው።
- 233ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን ቀሪዎቹ 969ኙ በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።

* ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል #AdmasUniversity

- አጠቃላይ ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል።
- ከተመራቂዎቹ 67 በመቶ ሴቶች ናቸው።
- በቴክኒክና ሙያ፣ በመጀመሪያ ዲግሪ እና 2ኛ ድግሪ በቀንና በማታ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
- ከተመራቂዎቹ መካከል 1 ሺህ 532ቱ በ2ኛ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳዮችን በ @tikvahuniversity ተከታተሉ።

@tikvahethiopia
#JigjigaUniversity

የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ/ም " የነዳጅ ምህንድስና/ ፔትሮሊየም ኢንጅነሪንግ " የአዲስ የትምህርት ፕሮግራም ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ።

የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር በሽር አብዱላሂ ለኢፕድ በሰጡት ቃል፥ በሶማሌ ክልል ካሉት የተፈጥሮ ሀብቶች መካከል አንዱ የነጭና የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ነው ብለዋል።

ይህን የተፈጥሮ ሀብት አልምቶ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚደረገው እንቅስቃሴም በእውቀትና በምርምር የታገዘ ለማድረግም ዩኒቨርሲቲው በዚህ ዓመት የፔትሮሊየም ኢንጅነሪንግ የትምህርት ፕሮግራም መስጠት ይጀምራል ሲሉ አሳውቀዋል።

Credit : ኢፕድ

@tikvahethiopia
#JigjigaUniversity

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ከተቀጠሩ ከ5 ዓመት በላይ የሆናቸው እና የ2ኛ ዲግሪ የሌላቸው ከ300 በላይ መምህራኑን በ2017 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ምንም አይነት ኮርስ እንዳይሰጡ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቋል።

ዩኒቨርስቲው በመምህራኑ ላይ ወርሃዊ ደመወዝ እንዳይከፈላቸው እግድ አስተላልፎ የነበረ ቢሆንም ይህንን ውሳኔውን ለጊዜው መቀልበሱን ገልጿል።

" ይህ ውሳኔ ላይ የተደረሰው የመጀመሪያ ዲግሪ ኖሯቸው የተቀጠሩ መምህራን ፤ የድህረ ምረቃ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ዩኒቨርሲቲው ያስተላለፋቸውን ተደጋጋሚ ጥሪዎች ተቀብለው ወደ 2ኛ ዲግሪ ትምህርት ባለመግባታቸው ነው " ሲል ዩኒቨርሲቲው አመልክቷል።

የጅግጅጋ ዩኒቨርሰቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብዲ አህመድ ምን አሉ ?

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ከ1,400 መምህራን በላይ እንዳሉት ፤ ከእነዚህ ውስጥ 800 ገደማው የሁለተኛ ዲግሪ እንዳላቸው ጠቁመዋል።

ከአጠቃላይ መምህራን ውስጥ 350 ያህሉ የመጀመሪያ ዲግሪ ብቻ ያላቸው ናቸው ብለዋል።

የመጀመሪያ ዲግሪ ካላቸው መምህራን ውስጥ በትምህርት ላይ ያሉት " የተወሰኑት " እንደሆኑም ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው ከ4 ዓመት በፊት ባደረገው እንቅስቃሴ ከተቀጠሩ 5 እና ከ5 ዓመት በላይ የሆናቸው አብዛኞቹ መምህራን በ2 ዓመት ውስጥ 2ኛ ዲግሪ እንዲይዙ አድርጎ እንደነበር አስታውሰዋል።

ከዚያን ጊዜ ጀምረው 2ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ እና እየተከታተሉ ያሉ መምህራን እንዳሉ የገለጹት ም/ ፕሬዝዳንቱ፤ " አንዳንዶች ለመማር ፈቃደኛ ያልሆኑ ግን እዚያው በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የቀጠሉ ናቸው " ብለዋል።

መምህራኑ የድኅረ ምረቃ ትምህርት ላለመቀጠላቸው የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ አንስተው " አንዳንድ መምህራን ሌላ ተደራቢ ሥራ አግኝተው መምህርነቱን እንደ ሁለተኛ ሥራ መመልከታቸው አንዱ ምክንያት " ነው ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲው እነዚህ መምህራን የድኅረ ምረቃ ትምህርት ያልጀመሩበትን ምክንያት በተመለከተ በተደጋጋሚ ስብሰባዎችን ቢጠራም " ሳይሳተፉ ቀርተዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

" 2017 ዓ.ም. ሊጀመር ሲል አንደኛ ዲግሪ ያላቸውን መምህራን ብቻ ስብሰባ ጠርተን ነበር። መጀመሪያ ላይ የመጡልን 11 መምህራን ብቻ ናቸው። ሁለተኛ ዕድል እንስጥ ብለን የዛሬ ሳምንት ስብሰባ ጠርተን ነበር። ከ300 በላይ መምህራን ውስጥ 48 መምህራን ነው የመጡት "  ሲሉ ወቅሰዋል።

በዚህም መምህራኑ 2ኛ ዲግሪ ባለመያዛቸውና እና የዩኒቨርሰቲው አመራር በጠራቸው ስብሰባዎች ላይ አለመካፈላቸውን ተከትሎ እየተጀመረ ባለው የ2017 ትምህርት ዘመን " ምንም ዓይነት ኮርስ እንዳይሰጡ " ውሳኔ መተላለፉን አስታውቀዋል።

" እነዚህ መምህራን መማርም ስለማይፈልጉ፤ በአንደኛ ዲግሪ ያለ መምህር አንድም ኮርስ እንዳይሰጥ ወስነናል። " ሲሉ ተናግረዋል።

መምህራኑ ከተላለፈባቸው የማስተማር እገዳ በተጨማሪ ደመወዝም እንዳይከፈላቸው ውሳኔ ተላልፎ እንደነበር ዶ/ር አብዲ ተናግረዋል።

ይሁንና ውሳኔው በተላለፈበት በአሁኑ ወቅት የመስከረም የደመወዝ መክፈያ ጊዜ በመድረሱ እና " በዚህ ጊዜ ደመወዝ ማቋረጥ ስለማይቻል " ዩኒቨርሲቲው ይህንን ውሳኔውን ለጊዜው መሻሩን ዶ/ር አብዲ አስታውቀዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/BBC-AMHARIC-10-04

መረጃው የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia