TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጥንቃቄ‼️ በአዲስ አበባ ከተማ ነገ የሚደረግ እውቅና የተሰጠው ሰልፍ የለም። በከተማዋ ውስጥ ህገ ወጥ ሰልፍ በሚያደርግ ማንኛውም አካል ላይ ፖሊስ #እርምጃ እንደሚወስድ #አስጠንቅቋል። በመሆኑም ውድ የTIKVAH-ETH ተከታዮች እና የተከታዮቻችን ወዳጆች በሙሉ በየትኛውም አይነት ህገ ወጥ ሰልፍ ላይ እንዳትሳተፉ #አጥብቀን እንመክራለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአሜሪካ ኤምባሲ ማስጠንቀቂያ‼️

በኬንያ የአሜሪካ ኢምባሲ ከታማኝ ምንጮች አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት በምዕራባዊያን ላይ ጥቃት ሊፈፀም እንደሚችል #አስጠንቅቋል፡፡ ጥቃቱ በተለያዩ #የምስራቅ_አፍሪካ ሃገራትም ሊኖር እንደሚችል ኢምባሲው ገልጿል፡፡ በናይሮቢ በመናፈሻ እና በባህር ዳርቻዎች ላይ ባሉ ቦታዎች እና የውጭ ጎብኝዎች በሚበዙባቸው አካባቢዎች ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡ በተጨማሪ ብሪታንያ ዜጎቿ ወደ ሶማሊያ እና ኬንያ ድንበር እንዲሁም ወደ ባህር ዳርቻዎች አካባቢ እንዳይጓዙ የተጓዦች አማካሪ ገጿን አድሳለች፡፡

ምንጭ፦ አልጀዚራ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#AtoAknawKawza

በደቡብ ክልል እስከ 12 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በኮቪድ - 19 ቫይረስ ሊጠቁ ይችላሉ ሲል የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ #አስጠንቅቋል

የቢሮው ሃላፊ አቶ አቅናው ካውዛ እንዳሉት የከፋ የተጋላጭ ሁኔታ አመልካች እንደሚያሳየው አሁን በበሽታው ዙሪያ የሚያታየውን 'የጥንቃቄ ጉድለት' መቅረፍ ካልተቻለ በክልሉ 60 በመቶ የሚሆነው ነዋሪ በቫይረሱ ሊጠቃ ይችላል።

📹#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrMikeRyan

የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ተጠቂዎች ቁጥር እየቀነሰባቸው ባሉ ሀገራት ቫይረሱን ለመከላከል የተጣሉ እገዳዎች በቶሎ የሚነሱ ከሆነ ወረርሽኙ ለሁለተኛ ጊዜ ወረርሽኙ ከፍተኛ ደረጃ ይደርሳል ሲል #አስጠንቅቋል፡፡

የድርጅቱ የአስቸኳይ ጊዜ ጉዳዮች ኃላፊ ዶ/ር ማይክ ርያን አለም በመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሞገድ ውስጥ ነች፤ ምንም እንኳን በብዙ ሀገራት በቫይረሱ የመያዝ መጠን እየቀነሰ ቢሆንም በማእከላዊና በደቡብ አሜሪካ እየጨመረ ነው ብለዋል፡፡

እንደ ዶክተር ማይክ ርያን ከሆነ ወረርሽኞች ሁሌም ወቅታዊ ናቸው ፤ በዚህ አመት የመጀመሪያው ሞገድ ያቆመባቸው ሀገራት እንደገና ይመለሳል ብለዋል፡፡ ቫይረሱን ለመከላከል የተጣሉ ክልከላዎች ቶሎ የሚነሱ ከሆነ ቫይረሱ በፍጥነት ሊስፋፋ የሚችልበት እድል እንዳለ ገልጸዋል - #AlAin

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

በአባይና ተከዜ ወንዝ ተፋሰስ ስር ባሉ አካባቢዎች በቀጣይ ቀናት ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል የኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ አጀንሲ #አስጠንቅቋል

በተፋሰሱ ስር ያሉ ነዋሪዎች እራሳቸውን እና ንብረቶቻቸውን ከጎርፍ እንዲጠብቁ ኤጀንሲው ማሳሰቢያ መስጠቱን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia