TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
እስቴ ወረዳ~ደቡብ ጎንደር‼️

‹‹ኢትዮጵያ #ሰላም እንዳትሆን የሚፈልጉ የፖለቲካ አራማጆች የዘሩት ጥል አልሆን ሲላቸው ወደ #ሀይማኖት ተዘዋውረዋል። ... ኢትዮጵውያን #የሀይማኖት_ልዩነት ሳይለያየን ለብዙ ዓመታት በሰላም እና በፍቅር ኖረናል፤ አሁንም እንኖራለን፤ የሴረኞችን ድርጊት አውግዘን በፍቅራችን እቀጥላለን ... ሀይማኖት ሀገር መገንቢያ እንጂ ሀገር ማፍረሻ አይደለም።... ድርጊቱ የክርስትና ሀይማኖት ተከታዮችን አይወክልም፡፡›› የአማራ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ሸኽ #ሙሐመድ_ሀሰን

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአርባ ምንጭ...

"ወንድሞቼ ከላይ ያነሱት ሀሳብ እዳለ ሁኖ የኔ እይታ #ሀይማኖት ተቋማት ላይ በደንብ መሠራት አለበት፡፡ ወጣቶች ሀይማኖቱን በሁለቱም አለም ስኬታማ የሚሆንበትን ጉዳይ ትቶ ዛሬ ገደል የሚከተውን መጤ መንገድ ተከትለናል። በተለይ ወጣቱን ወደ ሀይማኖቱ የማምጣት ስራ ቢሠራ በየቸርቹ፣ በየመስጅዱ ትምህርቱ ከአንድ ሰሞን የዘለለ ቢሆን ባይ ነኝ! ሙሀመድ ከአርባምንጭ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰልፉ በሰላም ተጠናቋል~ሀዋሳ🔝

"ህገመንግሰታዊ #መብታችን_ይከበር!" በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ከተማ የተካሄከው ሰለማዊ ሰልፍ #በሰላም ተጠናቋል። በሰልፉ ላይ ከሲዳማ 36 ወረዳዎች እና ከተማ መስተዳድሮች የተውጣጡ እንዲሁም የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ተሳትፈውበታል።

ሰለማዊ ሰልፈኞቹ፦ “ህገ መንግስቱ እንዲከበር፤ የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ መልስ እንዲሰጠው፤ የሪፈረንደም ቀን በአስቸኳይ ተወስኖ ለህዝብ እንዲነገር ጠይቀዋል።

በሰልፉ ላይ ሰልፈኞች ከያዟቸው መፈክሮች መካከል፦

•ሲዳማነት ከሌለ #ኢትዮጵያዊነት የለም!

•ለውጡን እንደግፋለን!

•በኮሚሽን የሚመለስ ጥያቄ የለንም!

•ለማንም ዘረኛ የማንበረከክ በባህላችን የምንኮራ ህዝን ነን!

•ህገ መንግስታዊ #መብታችን ይከበር!

•የሪፈረንደም ቀን #ተቆርጦ ይነገረን!

•የሲዳማ ህዝብ መንግስትን እንዳከበረ መንግስትም የሲዳማን ህዝብ ያክብር!

•ሁሉንም #ብሄር እንወዳለን፤ እናከብራለን!

•ሁሉንም #ሀይማኖት እንወዳለን፤ እናከብራለን!

•የሁሉንም #ባህል እንወዳለን፤ እናከብራለን! የሚሉት ይገኙበታል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ #TIKVAHETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia