TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#attention #woldiaUniversity

ከትላንት ለሊት ጀምሮ "በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ" በተለይም አዲስ ገቢ ተማሪዎች የሚኖሩባቸው ህንፃዎች አካባቢ አለመረጋጋት መፈጠሩን የቲክቫህ ቤተሰቦች በላኳቸው መልዕክቶች አስረድተዋል። እስካሁን ድረስም የትኛውም የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ስጋት ላይ የወደቁ ተማሪዎችን አላነጋገሩም። በተማሪዎች ላይ ስለደረሰ ጉዳት፣ በምን ምክንያት ይህ አለመረጋጋት ሊፈጠር እንደቻለ፣ ከተማሪዎች፣ ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ፣ ከተማሪ ተወካዮች ተጨማሪ መረጃዎችን ጠይቀን ወደናተው እናደርሳለን። በዚህ አጋጣሚ ይህን መልዕክት የምትመለከቱ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች ለጉዳዩ ትኩረት እንድትሰጡም እናሳስባለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#WoldiaUniversity

ትናንት ቅዳሜ ምሽት በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ ሁለት ተማሪዎች መሞታቸው ተነገረ። BBC ያነገውራቸው የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች እና መምህር የብሄር መልክ በያዘው ግጭት የሁለት ተማሪዎች ህይወት ማለፉን እና በርካቶች መቁሰላቸውን አረጋግጠዋል።

በዩኒቨርሲቲው መምህር የሆኑት የቢቢሲ ምንጭ ትናንት ምሽት በተፈጠረው ግጭት ሁለት ተማሪዎች መሞታቸውን ወደ ዩኒቨርሲቲው ደውለው መስማታቸውን ተናግረዋል።

የሆስፒታል ምንጮች እንደጠቆሙት ደግሞ ወደ ወልዲያ ጄኔራል ሆስፒታል 14 ተማሪዎች ተጎድተው መጥተዋል።

ስማቸወን መግለጽ ያልፈለጉ የወልዲያ ጀነራል ሆስፒታል ባልደረባ ለቢቢሲ "እኔ የገባሁት ዛሬ [እሁድ] ጠዋት 2፡30 ላይ ነው። ተማሪዎቹ ጉዳት ደርሶባቸው ሲመጡ አልተመለከትኩም። ግን አሁን ከ14-15 የሚሆኑ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በሆስፒታሉ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

እኚሁ የሆስፒታል ባልደረባ በተማሪዎች ላይ የደረሰው ጉዳት ከቀላል እስከ ከባድ መሆኑን የጠቀሱ ሲሆን፤ ጉዳቱ ያጋጠመው በድብደባ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ከዚህ በተጫማሪ ትናንት ምሽት የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በተፈጠረባቸው የደህንነት ስጋት ከዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ለመውጣት የሞከሩ ተማሪዎች ከግቢው እንዳይወጡ መከልከላቸውን BBC ያነጋገራቸው ተማሪዎች ተናግረዋል።

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-10

(BBC አማርኛው አገልግሎት)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#WoldiaUniversity

ኦቢኤን ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ከተማሪዎች በስልክ ደውዬ አጣራው ብሎ እንደዘገበው ትላንት ማታ የተነሳው ችግር ከኳስም ግጭት የዘለለ እንደነበርና በዶርም አከባቢም ተማሪዎች ባልታወቁ አካላት ጥቃት እንደደረሰባቸው ይጠቁማል፡፡ ግጭቱም ከሊቱ 6 አከባቢ የተነሳ ነው ይላል ዘገባው። BBC በሰራው ዘገባ ግጭቱ ዶርም አከባቢ የተፈጠረ ነው ብሏል፡፡ እንደ BBC ዘገባ ጥቃቱን ያደረሱት አካላት ዶርም ለዶርም በመዞር ዶርም በመስበር ጥቃት አድርሰዋል ብለዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#WoldiaUniversity

በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል ትናንት ሌሊት ተነስቶ የነበረው ብጥብጥ መረጋጋቱን የሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ። የፖሊስ መምሪያው ኃላፊ ኮማንደር ሀብታሙ ሲሳይ ለኢዜአ እንደገለጹት ብጥብጡ የተከሰተው ተማሪዎች ትናንት ምሽት ኳስ አይተው በተመለሱበት ወቅት ነው። በብጥብጡ የሁለት ተማሪዎች ህይወት ሲያልፍ በስምንት ተማሪዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።

የብጥብጡን መንስኤ ለማወቅና አጥፊዎችን ለመያዝ በአሁኑ ወቅት የማጣራት ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም ኮማንደር ሀብታሙ አስታውቀዋል። እንደ ኮማንደሩ ገለጻ ፖሊስ ችግሩ እንደተፈጠረ ወደ ዩኒቨርሲቲው ገብቶ የማረጋጋት ሥራ ከመስራት ጎን ለጎን ተቋሙ ጋር በመተባበር ተጎጂዎችን ወደ ወልድያ ሆስፒታል በማድረስ ሕክምና እንዲያገኙ አድርጓል።

በአሁኑ ወቅት የዩኒቨርሲቲው ሰላም ወደነበረበት በመመለሱ ከተማሪዎች ጋር የጋራ ውይይት እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል። ተማሪዎች የመጡበትን የትምህርት ዓላማ ለማሳካት ሌት ተቀን ተግተው ከመስራት ውጪ ለብጥብጥ መንስኤ መሆን እንደሌለባቸው ኮማንደር ሀብታሙ መክረዋል።

(ኢዜአ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ ፦

#WolaitaSodoUniversity

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እለተ ዛሬ 29 ቀን 2013 ዓ.ም በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት መርሃ-ግብር በቅድመ ምረቃ እና በድህረ ምረቃ ያሰለጠናቸውን 5,310 ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።

#WoldiaUniversity

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ላለፋት ዓመታት በተለያዩ ትምህርት መስኮች ሲያሰለጥናቸው የቆዩ ተማሪዎቹን ዛሬ በሼህ ሙሃመድ ሁሴን አሊ ኣላሙዲን ስታዲየም እያስመረቀ ይገኛል።

በመደበኛው፣ በተከታታይ እና በክረምት መርሃግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 2785 የሚሆኑ እጩ ተመራቂ ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው።

ከጠቅላላ ተመራቂዎች ውስጥም 926 ሴቶች ናቸው።

#BahirdarUniversity

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መድኮች ሲያስተምራቸው የቆያቸውን 5,117 ተማሪዎችን በፔዳ ካምፓስ በማስመረቅ ላይ ይገኛል።

4,203 የሚሆኑት የመጀመሪያ ዲግሪ (ቅድመ ምረቃ ፕሮግራም) የተማሩ ናችው። 759 በሁለተኛ ድግሪይ የተማሩ፣10 የፒኤችዲ ተመራቂዎች ይገኙበታል።

በሌላ በኩል በህክምና ስፔሻሊቲ የተመረቁ 40 የሚሆኑ ሰልጣኞች ዛሬ እየተመረቁ ነው።

ከአጠቃላይ ተመራቂዎቹ ውስጥ 1,623 የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።

#DebarkUniversity

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 773 ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በማስመረቅ ላይ ይገኛል፡፡

#MizanTepiUniversity

ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ከ2 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።

በሌላ በኩል፦

ሂልኮ የኮምፒዩተር ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ኮሌጅ ነገ ጥር 29/2013 ዓ/ም ተማሪዎቹን ያስመርቃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#WoldiaUniversity

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የመጀመሪያ አመት መደበኛ ተማሪዎች ጥሪ እንዲደረግላቸው ውሳኔ አሳለፈ።

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

ሴኔቱ በዛሬው ዕለት ከስዓት በፊት በነበረው ስብሰባ ዋነኛ አጀንዳ ከነበሩት መካከል የመምህራን የደረጃ እድገት እና የመጀመሪያ አመት መደበኛ ተማሪዎች የጥሪ ሁኔታን የሚመለከቱ ነበሩ።

ሴኔቱ ከነባር የመጀመሪያ አመት ኤክስቴሽንና የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች በመቀጠል የመጀመሪያ አመት መደበኛ ተማሪዎቹን ተቀብሎ ለማስተማር የሚያስችል ሁኔታ እየተፈጠረ በመሆኑ በየካቲት ወር 2014 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ተማሪዎቹ እንዲጠሩ ውሳኔ አሳልፏል።

በሌላ አጀንዳ የመምህራንን የደረጃ እድገት ተመልክቶ 10 መምህራን ከጤና ኮሌጅ ፣ 1 መምህር ከግብርና ኮሌጅ በጥቅሉ 11 መምህራኖቻችን የትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው አዲስ የማወዳደሪያ መስፈርት ተመዝነው ከሌክቸረርነት ወደ ረዳት ፕሮፌሰርነት ደረጃ ያደጉ በመሆኑ ሴኔቱ የደረጃ እድገቱን ገምግሞ አፅድቋል።

በደረጃ እድገቱ የተተካቱት መምህራን፦ ረ/ፕ አብዱ ሰይድ ሙሃመድ ፣ ረ/ፕ አደም ወንድሜነህ በላይ ፣ ረ/ፕ አዲሱ ጌቴ ንጋቱ ፣ ረ/ፕ አጃናው ነገሰ ፣ ረ/ፕ አስማማው ደምስ ብዙነህ ፣ ረ/ፕ አየልኝ መንገሻ ካሴ፣ ረ/ፕ ብርሃን አለምነው ታመነ፣ ረ/ፕ ብሩክ በለጠው አባተ ፣ ረ/ፕ ጌታሁን ፈንታው ሙላው ፣ ረ/ፕ ጌትነት ገደፋው አዘዘ እና ረ/ፕ ሙሃመድ አህመድ ይማም ናቸው።

መረጃውን ከወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ነው ያገኘነው።

@tikvahethiopia