የኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጅ እያወዛገበ ነው!
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለውይይት ቀርቦ ለገቢዎች በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች የተመራው የኤክሳዝ ታክስ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ እያወዛገበ ነው። አዋጁ በመሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ ሳይቀር ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚያሳድርና የአምራች ኩባንያዎችን ህልውና የሚፈታተን ነው ተብሏል፡፡
በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ የሚገኘው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ 307/1995 ያሉበትን ክፍተቶች ለማሟላትና ለመንግሥትም ከፍተኛ ገቢ ለማስገኘት ያስችላል ተብሎ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለውይይት የቀረበውና ለገቢዎች በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች የተመራው የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ፤ በአገር ውስጥ በሚመረቱና ከውጪ አገር በሚገቡ የተለያዩ ምርቶች ላይ ተጨማሪ ታክስ የሚጥል ነው፡፡
በማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ የቅንጦት ዕቃዎች ተብለው የተለዩትና ተጨማሪ የኤክሳይዝ ታክስ ከተጣለባቸው ምርቶች መካከል ዘይት፣ ስኳር፣ ጨው፣ ጣፋጭና ጨዋማ ምግቦች የአልኮል መጠጦች፣ የትምባሆ ምርቶች፣ የተሰፉ ልብሶች፣ የታሸጉና ጋዝ ያላቸው ውሃዎችን የለስላሳ መጠጦች፣ ይገኙበታል፡፡
https://telegra.ph/ETH-12-22-2
#AddisAdmas
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

December 22, 2019