#Semera
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በዛሬው ዕለት በአገር አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ቀን ለማክበር ሰመራ ከተማ ገብተዋል።
ፕሬዝዳንቷ ከክልሉ አመራሮች፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከአገር ሽማግሌዎችና ከፌዴራል ባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚመክሩም ይጠበቃል።
በከተማው በሚኖራቸው ቆይታ በሰመራ ዩኒቨርስቲ ከሴት ተማሪዎችና አመራሮች ተሳትፎና ከስርዓተ-ጾታ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩም ተመልክቷል። ከዚህ ጎን ለጎን የዱብቲ ሪፈራል ሆስፒታልን የሥራ እንቅስቃሴ ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በተጨማሪም በሰመራ ዩኒቨርስቲና በተመረጡ የከተማው አካባቢዎች ችግኝ ይተክላሉ ተብሎም ይጠበቃል። ፕሬዝዳንቷ ብሔራዊ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ምክር ቤት ሰብሳቢ መሆናቸው ይታወቃል።
ምንጭ፡- ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

የሸገር ዳቦ ፋብሪካ የሲቪል ስራው ተጠናቀቀ!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ከ6 ወራት በፊት ግንባታው የተጀመረውን በሰዓት 80 ሺህ ዳቦ የሚያመርተው የዳቦ ፋብሪካ ግንባታ ያለበትን ደረጃ በቦታው በመገኘት ተመልክተዋል፡፡
በከተማዋ ያለውን የዳቦ አቅርቦት ከፍ የሚያደርገውና የዋጋ ንረቱንም በተጨባጭ መልኩ እንደሚያረጋጋ የሚጠበቀው ይህ ግዙፍ የዳቦ ፋብሪካ በአሁኑ ወቅት የሲቪል ስራው ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁ በጉብኝቱ ወቅት ተጠቅሷል፡፡
በሀገራችን በዓይነቱ የመጀመርያ የሆነው ይህ የዱቄትና የዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ የማሽን ተከላው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ እና በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ወደ ምርት እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
(Mayor Office of AA)

አንድ ፓድ ለእህቴ!
የወሎ ዩኒቨርስቲ ሴቶች ክበብ አባላት ለሶስት ቀን የሚቆይ "አንድ ፓድ ለእህቴ" የሞዴስ ማሰባሰብ ስራ እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡ ሞዴሱ ተሰብስቦ የሚሠጠው ለሴት ታራሚዎች እና ግቢ ውስጥ ላሉ የተቸገሩ ሴት ተማሪዎች እንደሆነ ነው የተገለፀልን፡፡
አንድ ፓድ ለእህቴ!
- በዚህ መልካም ስራ ላይ እየተሳተፋችሁ ለምትገኙ ወጣቶች በሙሉ በቲክቫህ ኢትዮጵየ ስም ያለንን ትልቅ አክብሮት ለመግለፅ እንወዳለን!
@tikvahethiopia @tikvahethiopia

በሞጣ ከተማ 15 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ!
በሞጣ ከተማ በተፈጠረው የእምነት ተቋማት ቃጠሎና የንብረት መውደም እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ 15 ግለሰቦችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጿል። እስካሁን ከተያዙት ተጠርጣሪዎች በተጨማሪ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየሰራ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል። ሞጣ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሷ እየተነገረ ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሞጣ ከተማ በተፈጠረው የእምነት ተቋማት ቃጠሎና የንብረት መውደም እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ 15 ግለሰቦችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጿል። እስካሁን ከተያዙት ተጠርጣሪዎች በተጨማሪ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየሰራ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል። ሞጣ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሷ እየተነገረ ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መረጃ ስለ ኤክሳይዝ ታክስ!
ኤክሳይዝ ታክስ /excise tax/ የቅንጦት ዕቃዎች ሆነው ዋጋቸው ጨመረም አልጨመረ መሠረታዊ በመሆናቸው ምክንያት የገበያ ተፈላጊነታቸው በማይቀንስ ዕቃዎች ላይ እንዲሁም የኅብረተሰቡን ጤና የሚጎዱ እና ማህበራዊ ችግሮችን የሚያስከትሉ ዕቃዎችን አጠቃቀም ለመቀነስ ሲባል የሚጣል ነው፡፡
https://telegra.ph/ETH-12-22
#MinistryofRevenuesofEthiopia

የኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጅ እያወዛገበ ነው!
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለውይይት ቀርቦ ለገቢዎች በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች የተመራው የኤክሳዝ ታክስ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ እያወዛገበ ነው። አዋጁ በመሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ ሳይቀር ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚያሳድርና የአምራች ኩባንያዎችን ህልውና የሚፈታተን ነው ተብሏል፡፡
በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ የሚገኘው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ 307/1995 ያሉበትን ክፍተቶች ለማሟላትና ለመንግሥትም ከፍተኛ ገቢ ለማስገኘት ያስችላል ተብሎ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለውይይት የቀረበውና ለገቢዎች በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች የተመራው የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ፤ በአገር ውስጥ በሚመረቱና ከውጪ አገር በሚገቡ የተለያዩ ምርቶች ላይ ተጨማሪ ታክስ የሚጥል ነው፡፡
በማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ የቅንጦት ዕቃዎች ተብለው የተለዩትና ተጨማሪ የኤክሳይዝ ታክስ ከተጣለባቸው ምርቶች መካከል ዘይት፣ ስኳር፣ ጨው፣ ጣፋጭና ጨዋማ ምግቦች የአልኮል መጠጦች፣ የትምባሆ ምርቶች፣ የተሰፉ ልብሶች፣ የታሸጉና ጋዝ ያላቸው ውሃዎችን የለስላሳ መጠጦች፣ ይገኙበታል፡፡
https://telegra.ph/ETH-12-22-2
#AddisAdmas

#HappeningNow
በሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚልና በስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በአቶ አሊ ከድር መሪነት በዞኑ የባህል አዳራሽ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል። እየተደረገ በሚገኘው የውይይት መድረክ ላይ የመንገድ፣ የመብራት፣ የውሃና ሌሎች የመሰረተ ልማቶችን በማስመልከት ተሳታፊዎች ጥያቄዎችን በማንሳት ላይ ናቸው።

#UPDATE
በደሴ ከተማ አስተዳደር ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ ክፍሎች የተወጣጡ የእምነቱ ተከታዮች በሞጣ ከተማ በእምነት ተቋማት ላይ ደረሰው ጥቃት አሳፋሪ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የእምነቱ ተከታዮች በደሴ ከተማ በሚገኘው ዐረብ ገንዳ መስጂድ ባደረጉት ውይይት አጥፊዎቹ በሕግ ሊጠየቁ እንደሚገባም ጠይቀዋል፡፡ ጥቃቱ ከመድረሱ በፊትም ሆነ ከደረሰ በኋላ መንግሥት እያሳዬ ያለው ለዘብተኛ አቋም መታረም እንደሚገባውም አሳስበዋል፡፡
የክልሉ መንግሥት በመስጂዶች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እንደሚደርስ መረጃዎች እንደነበሩት በማንሳትም ቅድመ መከላከል አልሠራም በሚል ወቅሰዋል፡፡ ድርጊቱ ከተፈጸመ በኋላም በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው ተጠርጣሪዎች ቁጥር አነስተኛ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
መንግሥት የተቃጠሉ ቤተ እምነቶችን እንዲሠራና የተዘረፉ ንብረቶችን እንዲመለሱ ማድረግ እንደለበትም ተናግረዋል፡፡ችግሩ እንዲባባስም ሆነ የቤተ እምነቶች እንዲቃጠሉ የሚዲያ አካላት ድርሻ ከፍተኛ እንደሆነም ነው ተወያዮቹ ያነሱት፡፡ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ሚዲያ አውታሮች በተለይ በመስጂዶች ላይ ጥቃት ሲደርስ የሚሰጡት ሽፋን ሚዛናዊ እንዳልሆና መታረም እንደሚገባውም መክረዋል፡፡ መንግሥት የተቃጠሉ ቤተ እምነቶችን እንዲሠራና የተዘረፉ ንብረቶችን እንዲያስመልስም አሳስበዋል።
#AMMA
#TIKVAH_ETH
በሞጣ ከተማ በእምነት ተቋማት ላይ የተፈፀመው ድርጊት የሚያወግዙ ሰልፎች በተለያዩ ከተሞች እና አካባቢዎች እንደተደረጉ መረጃዎች ደርሰውናል። በባሌ ደሎ መና በተካሄደ ሰልፍ የሙስሊሙ እና ክርስትያኑ ማህበረሰብ አባላት ድርጊቱን አደባባይ በመውጣት በጋራ አውግዘዋል። በተለያዩ ከተሞች እና አካባቢዎች የተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎችን ማስፈንጠሪያውን በመጫን መመልከት ትችላላችሁ https://telegra.ph/TIKVAH-12-22
@tikvahethiopiaBot

በሀገሪቱ የተከሰቱ ግጭቶች የፍርድ ቤቶች አገልግሎት አሰጣጥ ላይ እንቅፋት ፈጥረዋል ተባለ!
የክልል ፍርድ ቤቶች አገልግሎት አሰጣጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ ቢሆንም በሀገሪቱ በተለያዩ ቦታዎች ተከስተው የነበሩ ግጭቶች ለአገልግሎት አሰጣጡ ተግዳሮት እንደሆኑ ተገልጿል፡፡
ይህ የተገለፀው እየተካሄደ ባለው 4ኛው የፌዴራል ፍ/ቤት ጉባኤ ላይ ነው፡፡ በጉባኤው በክልል ፍ/ቤቶች አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ባጋጠሙ ችግሮች ላይ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ አሁን በአገሪቱ ያለው የፖለቲካ ትኩሳት በዳኝነት ነፃነት ላይ እንቅፋት እየፈጠረ እንደመጣም ተገልጿል፡፡
(ኢቲቪ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

#PMOEthiopia
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከአዲስ አበባ የታክሲ ባለቤቶች፣ አሽከርካሪዎችና ረዳቶች ጋር የታክሲ ጣቢያውን አጸዱ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በካዛንቺስ የሚገኘውንና የ8 መሥመሮች መነሻ የሆነውን ጣቢያ ያጸዱት ለታክሲ አሽከርካሪዎችና ረዳቶች አገልግሎት ያላቸውን ክብር ለማሳየት መሆኑን ገልጠዋል።
ምንጭ፡- የጠ/ሚር ፅ/ቤት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከአዲስ አበባ የታክሲ ባለቤቶች፣ አሽከርካሪዎችና ረዳቶች ጋር የታክሲ ጣቢያውን አጸዱ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በካዛንቺስ የሚገኘውንና የ8 መሥመሮች መነሻ የሆነውን ጣቢያ ያጸዱት ለታክሲ አሽከርካሪዎችና ረዳቶች አገልግሎት ያላቸውን ክብር ለማሳየት መሆኑን ገልጠዋል።
ምንጭ፡- የጠ/ሚር ፅ/ቤት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EthiopianAirlines
- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ18 ዓመታት በፊት ተቋርጦ የነበረውን የግሪክ አቴንስ በረራ አገልግሎት መጀመሩን አስታወቀ። አየር መንገዱ እንዳስታወቀው፤ የግሪኳ አቴንስ ዳግመኛ ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ መረብ ውስጥ ተቀላቅላለች። አየር መንገዱ ታህሳስ 8 ቀን 2012 ዓ.ም የጀመረው የአቴንስ በረራ በአለም ላይ በሁሉም አህጉራት ያሉትን መዳረሻዎች ወደ 127 ከፍ እንደሚያደርገው ተገልጿል።
(ኢዜአ)

አልፈልግም ማለት አልፈልግም ነው!
• "አቁም" ማለት አልፈልግም ነው!
• "መሸሽ" ማለት አልፈልግም ነው!
• "እምቢ" ማለት አልፈልግም ነው!
• "መግፋት/መገፍተር" ማለት አልፈልግም ነው!
• "ዝግጁ አይደለሁም" ማለት አልፈልግም ነው!
• "ተወኝ" ማለት አልፈልግም ነው!
• "ዞር በል" ማለት አልፈልግም ነው!
• "መጮህ" ማለት አልፈልግም ነው!
• "እረፍ" ማለት አልፈልግም ነው!
• "ማልቀስ" ማለት አልፈልግም ነው!
የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ያንቺ ንቅናቄ ( Yanchi movement ) ለሶስት ቀን በሚቆየው የሴት ልጅ ጥቃትን በመቃወም የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅተዋል፡፡ ዝግጅቱ ትላንት የተጀመረ ሲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የ16 ቀን ንቅናቄ አንድ አካል እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልጸውልናል፡፡ በዚህ ንቅናቄ በዩኒቨርሲቲው የሚገኙ ሌሎች ክበባትም ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በሌላ በኩል በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሚገኘው "መራሂት ክበብ" አትኩሮቱን ሴት ተማሪዎችን በማብቃት ላይ አድርጎ እየሰራ ሲሆን ለሴት ተማሪዎች የፅዳት መጠበቂያ የሚሆን 88 ካርቶን ሞዴስ በመግዛት ለሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሴቶች ህፃናት ወጣቶች እና ኤችአይቪ ኤድስ ዳይሬክትቶሬት አስረክበዋል። የመጀመሪያውን ድጋፋቸውንም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቅርንጫፍ በሆነው በአዋዳ ካምፓስ አድርገዋል።
- በቲክቫህ ኢትዮጵያ ስም እየሰራችሁት ላለው መልካም ስራና ለሌሎች ወጣቶች ትምህርት የሚሰጥ ተግባር ላይ በመሳተፋችሁ ያለንን አክብሮት እና ምስጋና እናቀርባለን!
#HawassaUniversity
በርቱልን!

#AddisAbeba
የጥምቀት ክብረ በዓል በዩኔስኮ መመዝገቡን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ መድረክ በሚሌኒየም አዳራሽ ተካሂዷል። የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የጥምቀት በዓል አከባበርን ከመስቀል በዓል፣ የገዳ ስርዓት እና የፍቼ ጨምበላላ ክብረ በዓላትን ተከትሎ አራተኛው የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ የሚታወስ ነው፡፡
(Mayor Office of AA)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጥምቀት ክብረ በዓል በዩኔስኮ መመዝገቡን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ መድረክ በሚሌኒየም አዳራሽ ተካሂዷል። የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የጥምቀት በዓል አከባበርን ከመስቀል በዓል፣ የገዳ ስርዓት እና የፍቼ ጨምበላላ ክብረ በዓላትን ተከትሎ አራተኛው የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ የሚታወስ ነው፡፡
(Mayor Office of AA)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SomaliRegionalState
የሶማሌ ክልል በተወካዮች ምክር ቤት ያለው የውክል ቁጥር እንዲስተካከል የክልሉ ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፋ መሐመድ ዑመር ብሔራዊ ምርጫ ቦርድንና የፌዴሬሽን ምክር ቤትን በደብዳቤ ጠይቀዋል። ክልሉ 23 መቀመጫዎች በተወካዮች ምክር ቤት አሉት። ክልሉ በሕገ መንግሥቱ መሠረት 32 መቀመጫዎች ሊኖሩት ቢገባም ዘጠኝ ተቀንሶበት ለረጅም አመታት በ23 የውክልና መቀመጫ መቆየቱን አቶ ሙስጠፋ በደብዳቤያቸው ገልጸዋል።