TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የወላይታ ዞን አስተዳደር ዛሬ ማምሻውን በወቅታዊ ዞናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል!

የወላይታ ብሔር በክልል የመደራጀት ህገ-መንግሥታዊ ጥያቄ በቀበሌ ምክር ቤቶችና በወረዳና የከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶች ደረጃ ተወስኖ በመጨረሻም በዞኑ ምክር ቤት ተወስኖ በጽሑፍ ለደቡብ ክልል ምክር ቤት መቅረቡን አስታውሰዋል።

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ከወላይታ ዞን ምክር ቤት በህገ -መንግሥቱ መሠረት ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ ሳይሰጥ አንድ ዓመት ማቆየቱ አግባብ እንዳይደለ የዞኑ ህዝብ ሲያወግዝ ቆይቷል ብለዋል።

በህዳር 30/2012 ዓ-ም የተሰበሰበው የዞኑ ምክር ቤቱ የወላይታ ብሔር በክልል የመደራጀት ህገ-መንሥታዊ ጥያቄ ዙሪያ ውክልና የተሰጠው አስፈጻሚ አካል ጥያቄው የደረሰበትን ደረጃ በመገምገም በሰላማዊ መንገድ መሄድ እንዳለበት ሀሳብ መስጠቱን አውስተዋል።

ምክር ቤቱ በቀሪዎቹ ቀናት የደቡብ ክልል ምክር ቤት ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ በህገ መንግሥቱ መሠረት አቤቱታ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት መቅረብ እንዳለበት አቅጣጫ ማስቀመጡን ጠቁመዋል።

ሰሞኑን ሴቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ነጋዴ ማህበረሰብ፣ ፐብሊክ ሰርቫንት እንዲሁም የባጃጅ አሽከርካሪዎች ጭምር በሶዶ ከተማ ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ የእግር ጉዞ በማድረግ የደቡብ ክልል ለወላይታ ህዝብ ጥያቄ አለመስጠቱን አውግዘዋል ብለዋል።

የወላይታ ህዝብ የክልል ጥያቄ ለደቡብ ክልል ምክር ቤት ቀርቦ ምላሽ ሳይሰጥ አንድ ዓመት የሞላው በመሆኑ ይህንን ለማውገዝ ህዝቡ ነገ ታህሳስ 10/2012 ዓም ሰላማዊ ሰልፍ ለመውጣት ጥያቄ ሲያቀርብ የቆየ ቢሆንም በክልሉ ኮማንድ ፖስቱ ፈቃድ ስላልተሰጠ ነገ ሰላማዊ ሰልፍ እንደማይካሄድ ገልጸዋል።

More👇
https://telegra.ph/WRS-12-19

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FAKE_PHOTO #ERSS01

ይሄ ዛሬ ማምሻውን 'ይህችናት ሳተላይቷ' ነገ ኢትዮጵያ የምታመጥቀው ሳተላይት (#ERSS01) ይህቺ ናት እየተባለ ሲሰራጭ የነበረው ፎቶ ሀሰተኛ ነው። ፎቶው 2013 ላይ የተነሳ ነው። በሚግርም ሁኔታ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ተከታይ ያላቸው የፌስቡክ ገፆች ሳይቀሩ ፎቶውን ሳያጣሩ ሳያረጋግጡ ሲቀባበሉት ነበር።

ማስታወሻ #ETRSS01 -- ሀገራችን ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያ ሳታላይቷን ነገ አርብ ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ ህዋ የምታመጥቅ ይሆናል። የቲክቫህ ቤተሰቦች ከወዲሁ እንኳን ደስ አለን ለማለት እንወዳለን!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETRSS01

ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ ኢትየጵያ ለመጀመርያ ግዜ የምታመጥቃት #ETRSS01 ሳተላይት ከቻይና ዋና ከተማ ቤይጂንግ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው የቻይና ሳተላይት ማስወንጨፊያ ጣቢያ ወደ ህዋ ትላካለች፡፡

ከደቂቃዎች በኃላ ወደህዋ የምትመጥቀው የኢትዮጵያ ሳተላይት ETRSS-01፦

• የሳተላይቷ ጠቅላላ ከሸብደት 72 ኪሎ ግራም ሲሆን ነገ ታሕሳስ 10 ከማለዳው 12 ሰዓት ከ21 ደቂቃ ከቻይና ዋና ከተማ ቤይጂንግ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው የቻይና ሳተላይት ማስወንጨፊያ ጣቢያ ወደ ህዋ ትላካለች፡፡

• ሳተላይቷ በተወነጨፈች በግማሽ ሰዓት ውስጥ ከመሬት 700 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ የህዋ ጥግ ላይ የምሕዋር ቦታዋን ትይዛለች፡፡

• በኢትዮጵያና ቻይና መንግስት በጀት የተገነባችው የመረጃና ኮሙኒኬሽን ሳተላይት የምትመጥቀው ከቻይና የጠፈር ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ነው።

• ሳተላይቷ ለግብርና፣ ለማዕድን፣ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ፣ ለመሳሰሉት አገልግሎት መረጃ ለመስጠት ነው፡፡

• የሳተላይቷ የመረጃ መቀበያ እንጦጦ ላይ የተሰራ ሲሆን ከማምጠቅ ስራው ጀምሮ ቁጥጥሩ ሙሉ ለሙሉ እንጦጦ ላይ በኢትዮጵያውያን ይከናወናል።

• እንጦጦ የሳተላይት መቆጣጠሪያ እና መረጃ መቀበያ ጣቢያ እንጦጦ ኦብዘርቫቶሪና የምርምር ማዕከል ቅጥር ግቢ ውስጥ ተገንብቶ ለአገልግትት ተዘጋጅቷል፡፡

• ጣቢያው የሳተላይቷን ደህንነት ክትትል የሚደረግበትና ከሳተላይቷ የሚገኙ መረጃዎች የሚሰበሰቡበት ነው፡፡

(A/A City Press Secretariat Office)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
READY FOR LAUNCH? ለምጥቀት ዝግጁ?

#ETRSS1 #ESSS #ESSTI #Ethiopia #SpaceGeneration #SatelliteLaunch
#እውንሆነ

(Ethiopian Space Science Society)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BREAKING_NEWS

ኢትዮጵያ የመጀመርያ ሳተላይቷን አመጠቀች!

ኢትየጵያ ለመጀመርያ ግዜ ETRSS-1 የተሰኘ ሳተላይቷን ከቻይና ዋና ከተማ ቤይጂንግ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው የቻይና ሳተላይት ማስወንጨፊያ ጣቢያ ወደ ህዋ ልካለች፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዓለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት...

- ኢትዮጵያ መጀመርያ ሳተላይት ለመላክ አስባ የነበረው ከፊንላንድ ነበር። ይህ ፕሮጀክት 12 ሚልዮን ዩሮ የሚፈጅ መሆኑ እና ገንዘቡን ማሰባሰብ ባለመቻሉ ቀርቷል። በሁዋላ ግን ከቻይና ስፔስ አካዳሚ ጋር በመተባበር ETRSS- 1 እውን ሆኗል።

- ሳተላይቱ የሚመጥቀው ከቻይናዋ በሻንግዚ ግዛት ሲሆን ቦታው ከቤጂንግ 400ኪሜ ርቀት ላይ ይገኛል።

- ETRSS- 1 የመሬት ምልከታ እንጂ የኮሚኒኬሽን ሳተላይት አይደለችም። ኢትዮጵያ ብዙ ወጪ የሚጠይቀውን የኮሚኒኬሽን ሳተላይት ወደ ህዋ ለማምጠቅ ሀሳብ እንዳላት የተገለፀ ሲሆን ይህን ሶስት አመት ሊወስድ ይችላል ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ደስ አለን!

ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ሳታላይቷን ወደ ህዋ አምጥቃለች። ሳታላይቷ ቻይና ከሚገኘው የሳተላይት ማስወንጨፊያ ጣቢያ ወደ ህዋ የመጠቀችው። “ETRSS-1” ምድርን እየቃኘች እና በፎቶ እየመዘገበች መረጃ ትሰበስባለች። እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቆጣጠር፣ ከግብርና ጋር የተያያዙ ጥናት እና ምርምሮችን ለመሥራት እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ የመሠረተ ልማት ተግባራትን ለማከናወን ታስችላለች።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETRSS1

- ሀገራችን ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት በታሪኳ የመጀመሪያ የሆነውን ሳተላይት ወደ ህዋ አምጥቃለች። መላው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በዚህ ታሪካዊ ቀን በሰማነው የብስራት ዜና እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን ለማለት እንወዳለን።

እውን ሆኗል!

(Armonium Solomon)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE #ETRSS1

የኢትዮጵያ የመሬት ምልከታ ሳተላይት የ700 ኪሎ ሜትር ጉዞዋን አጠናቅቃ የታሰበላትን ምህዋር በመያዝ መረጃ መላክ መጀመሯን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETRSS1-EBC የኢትዮጵያን ባንዲራ አድርጎ በፎቶ ሾፕ አቀናብሮ ያሰራጨው ፎቶ የETRSS1 ሳተላይት ትክክለኛ ፎቶ አይደለም። ትክክለኛውን ፎቶ ማግኘት ባለመቻሉ እጅግ በርካታ የተቀናበሩ ፎቶዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጩ ነው። EBC ፎቶውን ካሰራጨ በኃላ በርካታ የመንግስት ተቋማት፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና ሚዲያዎችም ፎቶውን ሲጠቀሙት ተመልክተናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FactCheck

በዓለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት...

EBC ከጠዋት ጀምሮ በዘገባዎቹ ዛሬ ወደ ጠፈር የተላከውን ሳተላይት "የኮሚኒኬሽን" አገልግሎት እንዳለው እየገለፀ ነው። ይህ ቢሆን ሳተላይቱ የቴሌቭዥን፣ ሬድዮ እና ሌሎች ዌቮችን ያስተላልፋል ማለት ነው።

ነገር ግን ETRSS-1 የ "መሬት ምልከታ" ሳተላይት ነች። ለእርሻ፣ የአየር ሁኔታ እንዲሁም አካባቢ ጥበቃ የሚውሉ ምስሎችን የመላክ አቅም ግን አላት።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"...በጣም በእርግጠኝነት የምናገረው ሁሉም ሃገር ለሁለት ዓመታት በሴቶች ቢመራ፤ የተሻለ የኑሮ ዘይቤ እና ደረጃ ይኖረናል። በሁሉም ዘርፍ ለውጥ እንመለከታለን" - ባራክ ኦባማ (የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት)
.
.
.
"የሰጣችሁኝን የአመራር ቦታ የምትረከበው ሴት እንድትሆን እመኛለሁ። ንግግሬን የሚያዳምጡ አዳራሹ ውስጥ ያሉ ወንዶች እንደማይቀየሙኝ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ለነገሩ የነሱም ምኞት እንደኔ አይነት ሊሆን ይችላል"-ፖል ካጋሜ (የሩዋንዳ ፕሬዘዳንት-ትላንት ኪጋሊ በተጀመረው ብሔራዊ የውይይት መድረክ የተናገሩት)

PHOTO: ፋይል
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BODITI

የቦዲቲ ከተማ ወጣቶችና የከተማው ማህበረሰብ የወላይታ ክልል ህገ መንግስታዊ ጥያቄ ምክር ቤት ሳያፀድቅ አመት በመሙላቱ ህዝቡ ምክር ቤቱን በማውገዝ በህግ እንድጠየቅና ፌዴሬሽን ምክር ቤት በአስቸካይ የህዝባችንን ጥያቄ እንድመልስ ሰላማዊ በሆነ መልክ እያስተጋባ ይገኛል።

(ወላይታ ዞን ዋና አሰተዳደር)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሰላማዊ ሰልፍ እየተደረገ ይገኛል...

ክንዶ ድዳዬ ወረዳ የወላይታ ህዝብ በክልል የመደራጀት ህገ መንግሥታዊ ጥያቄ ለደቡብ ክልል ም/ቤት ካቀረበ አንድ ዓመት መሆኑን ተከትለው ጥያቀው ምላሽ ባለማግኘቱ የኪንዶ ዲዳዬ ህዝቡ በሠለማዊ ሰልፍና በቀጣይ ትግል አቅጣጫ ላይ ውይይት እያደረገ ይገኛል።

(ወላይታ ዞን ዋና አሰተዳደር)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የክልሉ ምክር ቤት በህግ ሊጠየቅ ይገባል!" - የሰልፉ ተሳታፊዎች

#WolaitaZone #BolosoBombe

የወላይታ ዞን ቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ህዝብ ከንጋቱ 11፡00 ጀምረው የወላይታ ህዝብ ህገ መንግሥታዊ ጥያቄ የክልሉ ምክር ቤት በማፈኑ አውግዘዋል። በአንድ ቅርጫት መታፈን አንችልም እኛ የጠየቅነው ህገ መንግስታዊ መብት ሊታፈን አይችልም። የክልሉ ምክር ቤት በህግ ልጠየቅ ይገባል። ሰላማዊ ሰልፉ በሰላም እየተካሄደ ይገኛል።

(ወላይታ ዞን ዋና አሰተዳደር)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የክልሉ ምክር ቤት በህግ ይጠየቅ!" - የሰልፉ ተሳታፊዎች

በወላይታ ዞን የሆብቻና የአበላ አባያ ወረዳ ወጣቶችና የከተማው ማህበረሰብ የወላይታ ክልል ህገ መንግስታዊ ጥያቄ ምክር ቤት ሳያፀድቅ አመት በመሙላቱ ህዝቡ ምክር ቤቱን በማውገዝ በህግ እንድጠየቅና ፌዴሬሽን ምክር ቤት በአስቸካይ የህዝባችንን ጥያቄ እንድመልስ ሰላማዊ በሆነ መልክ እያስተጋባ ይገኛል።

(ወላይታ ዞን ዋና አሰተዳደር)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#AbiyAhemedAli

የETRSS1 ሳተላይት መምጠቅን በማስመልከት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አሊ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የቤቲንግ ነገር...

"የስፖርት ውርርድ እንጂ ቁማር ስላልሆነ ፈቃድ ሰጥቻለሁ፤ እንደውም ለበርካቶች የስራ እድል ፈጥሯል!" - ብሄራዊ ሎተሪ
.
.
"ውርርድ በሚል ሽፋን ስሙን ለውጦ የመጣው ‹‹ቁማር›› ነው፤ እየተሰጠ ያለው ፈቃድም የወንጀለኛ መቅጫ ሕጉን የጣሰ ነው!" - የህግ ባለሙያዎች

More👇
https://telegra.ph/EPA-12-20

(EPA)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ወላይታ ሶዶ...

በደቡብ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ የማህበራዊ አግልግሎት መስጫዎች እና የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች መቋረጣቸው ተሰማ።

ከአካባቢው እየወጡ የሚገኙት መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ዛሬ በከተማው መደበኛ አንቅስቃሴዎች አይስተዋሉም፣ አብዛኞቹ የንግድና የመንግስት አግልግሎት ሰጪ ተቋማትም ተዘግተዋል።

የአግልግሎት መስጫዎች እና የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ሊቋረጥ ያቻለው የወላይታ ዞን ራሱን በቻለ የራስ ገዝ አስተዳደር (ክልል) ለመደራጀት ያቀረበው ጥያቄ ምላሽ ካለማግኘቱ ጋር በተያያዘ ሁከት „ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት በመኖሩ ነው“ ተብሏል።

የጀርመን ሬድዮ ያነጋገራቸው የዓይን አማኞች "በከተማዋ ዋና ዋና ጎዳናዎች የጸጥታ አባላትን ከጫኑ ወታደራዊ ካሚዮኖች በስተቀር የታክሲ፣ የባጃጅ እና የህዝብ ማመላለሻ አውቶቢሶች አንቅስቃሴ አይስተዋልም ፣ መንገዶችም ጭር ብለው ይስተዋላሉ" ብለዋል።

የወላይታ ዞን ምክር ቤት በክልል ለመደራጀት የሚያስችለውን ውሳኔ በማሳለፉ ጥያቄውን ለደቡብ ክልል ምክር ቤት ካቀረበ ዛሬ ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ/ም አንድ ዓመቱን አስቆጥሯል።

"ያቀረብኩት ህገ መንግስታዊ ጥያቄ ምላሽ ተነፍጎታል" ያለው የዞን ምክር ቤትም ከሁለት ሳምንታት በፊት አስቸኳይ ጉባኤ በመጥራት የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለጥያቄው በአስር ቀናት ውስጥ ምላሽ እንዲሰጥ የሚጠይቅ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።

ምክር ቤቱ ዳግም ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ "የላጋ" የተባለው የለውጥ አራማጅ ስብስብን ጨምሮ የከተማው ሴቶችና አባቶች ተከታታይ ሰልፎችን በማድረግ ጥያቄው አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጠው በመጠየቅ ላይ ይገኛሉ።

(የጀርመን ሬድዮ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በወላይታ ሶዶ ከተማ ስድስት ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ!

በወላይታ ዞን - ወ/ሶዶ ከተማ በደቡብ ክልል ጥያቄ በተቋቋመው የኮማንድ ፖስት ከትናንት ታኅሳስ 9 ማምሻውን ጀምሮ እስከ ዛሬ ታህሳስ 10 ድረስ ስድስት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና የዞኑን የክልልነት ጥያቄ ተሟጋቾች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካለከል አሸናፊ ከበደ፣ ወርቅነህ ገበየሁ እና ቡዛየሁ ቡቼ የተባሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች የሚሟገቱ ግለሰቦች ሲሆኑ ብርቱካን የተባሉ አንዲት ሴትም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የወላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ተከተል ላቤና ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡

የዎብን ጽህፈት ቤት ሃላፊ የሆኑት አንዱለም ታደሰ ትላንት አመሻሹ ላይ በቁጥጥር መዋላቸውንም ጨምረው ገለፀዋል፡፡ በወላይታ ዞን በሚገኙ ስምንት ዋና ዋና ወረዳዎች ውስጥ በየወረዳው ቢያንስ አምስት መቶ ወታደሮች መግባታቸውን የገለፁት ተከተል ትናንት አመሻሹ ላይ የዞኑ አስተዳዳሪ በአካባቢው ሬዲዮ በዛሬው ቀን እንቅስቃሴ እንዳይኖር መልዕክት ማስተላለፉንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

‹‹ከአስር በላይ ኦራል መኪኖች በከተማው ውስጥ በፍጥነት እየተንቀሳቀሱ ሲሆን፣ በፒክ አፕ የተጫኑ ወታደሮች እንዲሁም አምስት ስድስት የሆኑ ወታደሮች በእግራቸው እየተዘዋወሩ ይገኛሉ›› ብለዋል፡፡ ‹‹ዛሬ ጠዋት የክልልነት ጥያቄ ያለበት ቲሸርት የለበሱ ሰዎች ታስረዋል›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ እስካሁን ባለው መረጃ በቁጥጥር ስር የዋሉት ሰዎች የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ውስጥ እንደሚገኙ የታወቀ ሲሆን የመከላከለያ ሰራዊት በበኩሉ ለግዜው የተሟላ መረጃ እንደሌለው ገለፆ መረጃዎቹን እንዳሰባበሰበ እና የተሟላ መረጃ ሲያገኝ እንደሚያሳውቅ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ገለጿል፡፡

(አዲስ ማለዳ ጋዜጣ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

ምርጫ ቦርድ በተሻሻለው አዋጅ ለመመዝገብ የቀረበ ፓርቲ አለመኖሩን ገልጿል!

-በነባሩ አዋጅ 80 የፖለቲካ ፓርቲዎች ተመዝገበዋል

የተሻሻለው የምርጫ ቦርድ አዋጅ የሚጠይቀውን መስፈርት አሟልቶ ለመመዝገብ የቀረበ ፓርቲ አለመኖሩን ምርጫ ቦርድ ገልጿል። በቀድሞው አዋጅ እስካሁን 80 የፖለቲካ ፓርቲዎች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

የቦርዱ የኮሙኒኬሽን አማካሪ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ አዲስ የሚያመለክቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሊስተናገዱ የሚችሉት በተሻሻለው የምርጫ ቦርድ አዋጅ ቁጥር 1162 መሰረት ነው:: ይህ አዋጅ የሚጠይቀውን አሟልቶ ለመመዝገብ የቀረበ ፓርቲ ግን የለም ብለዋል።

በተሻሻለው የምርጫ ቦርድ አዋጅ 1162 ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለመመዝገብ ለሃገር አቀፍ ፓርቲ 10 ሺ የድጋፍ ፊርማ ፣ ለክልላዊ ፓርቲነት ደግሞ 4 ሺ የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብ እንደሚጠበቅባቸው አብራርተዋል።

(አዲስ ዘመን)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia