TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#InternationalCrisisGroup

ዐለም ዐቀፉ የግጭት አጥኝ ቡድን (አይሲጄ) ባወጣው ዘለግ ያለ ሪፖርት፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የትግራይ እና አማራ ብሎም የኦሮሞ እና አማራ መሪዎች እንዲነጋገሩ ማስቻል አለባቸው፤ ከኦዴፓ አፈንጋጭ ጓዶቻቸውም ጋር መነጋገር አለባቸው ሲል አሳስቧል፡፡ ዐቢይ ለሕወሃት አቀራረባቸውን ይቀይሩ፣ ከምርጫው በፊትም ከሁሉም ፖለቲከኞች እና ሲቪል ማኅበራት ጋር ሰፊ ውይይት ይጀምሩ ሲል መክሯል፡፡ አጋር ሀገራት የኢሕአዴግ አወቃቀር ለውጥ በጥንቃቄ እንዲያዝ እና ፖለቲከኞች ግጭት ቀስቃሽ ንግግር እንዲቆጠቡ ከጀርባ ማግባባት አለባቸው፡፡

https://www.crisisgroup.org/africa/horn-africa/ethiopia/283-keeping-ethiopias-transition-rails

(CrisisGroup - wazemaradio)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#InternationalCrisisGroup

የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ International Crisis Group የተሰዉ ዓለም አቀፍ አጥኚ ተቋም የባላአደራዎች ቦርድ አባል ሆነዉ ተሾሙ።

የግጭት ምክንያቶችን እና መከላከያዎችን የሚያጠናና መፍትሔዎችን የሚጠቁመዉ አጥኚ ተቋም እንዳስታወቀዉ ከቀድሞዉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር በተጨማሪ፣ የአዉሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ፕሬዝደንትና የሕብረቱ የዉጪ ግንኙነት ኃላፊን ፍደሪካ ሞግሔረኒ የቦርዱ አባል ሆነዉ ተሾመዋል።

አጥኚዉ ተቋም እንዳለዉ ሁለቱ ፖለቲከኞች የዓለም አቀፉን ተቋም መርሕ፣ ሥራና አሰራርን የሚወስነዉ ከተፍኛ አካል አባላት ሆነዉ የተሾሙት ከዚሕ ቀደም በነበራችዉ የዳበረ ፖለቲካዊ ልምድ ነዉ።

https://telegra.ph/DW-12-18

(የጀርመን ድምፅ ሬድዮ)

@tikvahethiopiaBot