የኦሮሞ እና የአማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ውይይት እያካሄዱ ነው!
የኦሮሞ እና የአማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች በክልሎቹ ባሉ ዩኒቨርስቲዎች በተፈጠሩ ችግሮች የመፍትሔ አካል ለመሆን ውይይት እያካሄዱ ነው። በውይይቱ አመራሮቹ የህዝብን ሰላም እና ደህንነት የሚያረጋጉ የጋራ አጀንዳዎች ላይ እየመከሩ እንደሆነ ተገልጿል።
ከዚህ ቀደም በሁለቱ ክልሎች የፖለቲካ ምሁራን፣ አክቲቪስቶች እና ባለሀብቶች መካከል የተለያዩ ውይይቶች ሲደረጉ ቆይተዋል ተብሏል። በሁለቱ ወገን ያሉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከፍተኛ የሆነ የህዝብ ድጋፍ ስላላቸው ችግሮችን ለመፍታት ወሳኝ ሚና አላቸው ነው የተባለው።
ተሳታፊዎቹ፣ ፖለቲካ የህዝብን ጥቅም ማእከል ማድረግ አለበት፤ ህዝብ ችግር ውስጥ በሚከት አካሄድ መሆን የለበትም ብለዋል። በውይይቱ ላይ ዶ/ር ዲማ ነገዎ፣ አቶ ሌንጮ ለታ እና አቶ ንጉሱ ጥላሁንን ጨምሮ አንጋፋ የፖለቲካ ሰዎች ተሳትፈዋል።
(EBC)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

በፖሊስ ሲፈለግ የነበረው ኮሎኔል ሙክታር ተያዘ!
የቀድሞው የሱማሌ ክልል ደኅንነት ሃላፊ ኮሎኔል ሙክታር ሙሐመድ ሱባኔ ሐርጌሳ ላይ መያዙን ሆርን ዲፕሎማት ድረ ገጽ ዘግቧል፡፡ ሙክታር በቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አብዲ ኢሌ ዘመን፣ በንጹሃን ላይ ግርፋት እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በመፈጸም እና በማስፈጸም ይጠረጠራል፡፡ በዚሁ ወንጀልም በፖሊስ ሲፈለግ የነበረ ነው፡፡
https://www.horndiplomat.com/2019/12/16/ethiopia-former-abdi-iley-spy-chief-muktar-sheik-subane-arrested-in-somaliland/
(HornDiplomat - wazemaradio)

#ETHIOPIA #ERITREA
በባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ብዙነሽ መሰረት የተመራው የኢትዮጵያ የባሕል ቡድን ዛሬ ከሠዓት በኋላ ወደ ኤርትራ አምርቷል። ቡድኑ ከውጭ ጉዳይና ከባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴሮች፣ ከብሔራዊ ቲያትር፣ ከታዋቂ ድምጻዊያንና የጃኖ ባንድ የተውጣጡ ከ60 በላይ አባላትን መያዙ ተገልጿል። የባሕል ቡድኑ ጉዞ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተደረሰውን የሠላም ስምምነት ተከትሎ የተፈጠረውን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ እንደሆነም ተነግሯል። የባሕል ቡድኑ በኤርትራ ቆይታው በአስመራ፣ ከረን እና ምጽዋ ከተሞች የተለያዩ የሙዚቃ ዝግጅቶችን እንደሚያቀርብ ከውጭ ጉዳይ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

#InternationalCrisisGroup
ዐለም ዐቀፉ የግጭት አጥኝ ቡድን (አይሲጄ) ባወጣው ዘለግ ያለ ሪፖርት፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የትግራይ እና አማራ ብሎም የኦሮሞ እና አማራ መሪዎች እንዲነጋገሩ ማስቻል አለባቸው፤ ከኦዴፓ አፈንጋጭ ጓዶቻቸውም ጋር መነጋገር አለባቸው ሲል አሳስቧል፡፡ ዐቢይ ለሕወሃት አቀራረባቸውን ይቀይሩ፣ ከምርጫው በፊትም ከሁሉም ፖለቲከኞች እና ሲቪል ማኅበራት ጋር ሰፊ ውይይት ይጀምሩ ሲል መክሯል፡፡ አጋር ሀገራት የኢሕአዴግ አወቃቀር ለውጥ በጥንቃቄ እንዲያዝ እና ፖለቲከኞች ግጭት ቀስቃሽ ንግግር እንዲቆጠቡ ከጀርባ ማግባባት አለባቸው፡፡
https://www.crisisgroup.org/africa/horn-africa/ethiopia/283-keeping-ethiopias-transition-rails
(CrisisGroup - wazemaradio)

አቶ ጌታቸው ረዳ (የህወሓት ሥራ አስፈፃሚ አባል)...
"ስለዲሞክራሲና ልማት መግባባት ካልቻልን በምንም መግባባት አንችልም፡፡ ሰላም፣ ልማት፣ ዴሞክራሲ አይደለም የሚያስፈልገኝ ሌላ ነው የሚል ካለ ሌላ ጉዳይ ነው፡፡ ሊበራል ዴሞክራሲ ምን እንደሆነ አንድም ቀን ሰምቶ የማያውቅ ሰው ሊበራል ዴሞክራቲክ አስተሳሰብ ነው የሚሻለኝ ይላል፡፡ ሊበራል ዴሞክራሲ ምንድነው ብንል ሊበራል ዴሞክራሲ የሚባለው አንድ ወቅት ብርና ንብረት ላላቸው ሰዎች ብቻ የመምረጥ መብትን ማጎናጸፍ የፈለገ ሀብታሞችን ከድሆች ለመከላከል ተብሎ ሲራመድና ሲቀነቀን የነበረ ስርዓት ነው፡፡"

ኢህአፓ ከ10 ሺ በላይ የደጋፊዎች ፊርማ አሰባስቧል!
የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ(ኢህአፓ)ለመመዝገብ በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፓርቲ የሚጠየቀውን የደጋፊ አባላት ማሰባሰቡን አስታወቀ።
ፓርቲው የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ መሰረት በማድረግ ከተለያዩ ክልሎችና ከከተማ መስተዳደሮች ከ10 ሺህ በላይ የደጋፊዎች ፊርማ ማሰባሰቡን ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስተውቋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ(ኢህአፓ)ለመመዝገብ በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፓርቲ የሚጠየቀውን የደጋፊ አባላት ማሰባሰቡን አስታወቀ።
ፓርቲው የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ መሰረት በማድረግ ከተለያዩ ክልሎችና ከከተማ መስተዳደሮች ከ10 ሺህ በላይ የደጋፊዎች ፊርማ ማሰባሰቡን ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስተውቋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጀነራል ብርሀኑ ጁላ (የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም) ...
- ለውጡን ተከትሎ መንግሥት የታመቁ ሀሳቦችና ጥያቄዎች በነጻነት ይውጡ በማለቱ በሀገሪቱ ሕግና ስርዓት የሌለ እስኪመስል ድረስ ሁሉም እንደፈለገው ሲሆን ከርሟል፤ አሁን ግን ይበቃል።
- ይህ ሁሉ የሆነው መንግሥት መምራት ስላልቻለ፤ የሀገሪቱ መከላከያና የደህንነት ወይንም የፌዴራል ፖሊስና የመደበኛው ፖሊስ ኃይል አቅም ስላነሰው አይደለም።
- ጊዜው የለውጥ ስለሆነ የታመቀው ብሶት ይተንፍስ በሚል በየቦታው የሚነሱትን ግጭቶችና ሁከቶች ጥፋቶች እንደ እሳት አደጋ በየቦታው እየበረርን መስዋእትነት እየከፈልን ስናስታግስ የኖርነው።
- በየቦታው ንጹሀን ዜጎችን በጭካኔና አረመኔነት ከማረድ አልፎ ቤተክርስቲያንና መስጊድ እስከማቃጠል የደረሱበትን የስርዓተ አልበኛነት ጫፍ ለማየት ተገደናል። ወዴት ሊያመራ እንደሚችል ይታወቃል።
- ሕዝቡም ያለው በጅምላ በመደዳ እርምጃ አይወሰድ ነው እንጂ ሰው የሚገድሉ፤ ቤትና ንብረት፤ ፋብሪካ፤ ቤተክርስቲያንና መስጊድ በሚያቃጥሉ፤ ተደራጅተው በሚዘርፉና ነፍሰ ገዳዮች ላይ እርምጃ አይወሰድ አላለም።
- ስለሆነም የማያወላዳ እርምጃ ይወሰዳል። ሕዝቡ ከመንግስት ጎን ለራሱ ሰላምና ደህንነት ሲል ቆሞ መስራት አለበት።
- መከላከያ ግለሰቦች ሲጣሉ ጣልቃ የሚገባ አይደለም። መከላከያ የሀገርን ሉአላዊነት ለመጠበቅ የተደራጀ፤ የታጠቀ ሁልግዜም በተጠንቀቅ የሚገኝ የሀገሪቱ የመጨረሻው ፈርጣማ ክንድ ነው።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-12-16
(አዲስ ዘመን ጋዜጣ)
@tikvahethiopiaBot @tikvagethiopia

- ያላግባብ ከሥራ ታግደናል የሚሉ የአየር መንገዱ ሠራተኞች ቅሬታቸውን ገልፀዋል።
- አየር መንገዱ በዲሲፕሊን ግድፈት ምክንያት አስተዳደራዊ ዕርምጃ ተወስዷል ብሏል።
ያላግባብ ከሥራ ገበታችን ታግደናልና ተባረናል ያሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች በተወካያቸው በኩል ቅሬታቸውን ገለጹ፡፡ በተለያዩ ጊዜያት ዕግድ የወጣባቸው አሥር የአየር መንገዱ ሠራተኞች፣ የታገዱበትንና የተባረሩባቸውን ደብዳቤዎች አያይዘው ለሪፖርተር ልከዋል፡፡
መደበኛ ያልሆነ የመገናኛ መድረክ ተጠቅመው የተቋሙን ማኔጅመንት ስም የሚያጎድፍ መልዕክት ለሠራተኞች በማስተላለፋቸው፣ ይህም ተቋሙ የሚተዳደርበትን የሥነ ምግባር መርህ የሚጥስ በመሆኑ ጉዳያቸው እስኪጣራ ድረስ ከሥራ መታገዳቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ መስከረም 24 ቀን 2012 ዓ.ም. የደረሳቸው ካፒቴን አዲሱ ወልደ ሚካኤል ናቸው፡፡ ድርጊቱ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 መሠረት የሥራ ውል እስከማቋረጥ የሚደርስ ቅጣት የሚያሰጥ ቢሆንም፣ ውሉ ሳይቋረጥ ምርመራ እንዲደረግበት መወሰኑን በደብዳቤው ተገልጿል፡፡
https://telegra.ph/ETH-12-16-2
(ሪፖርተር)

የቤት እመቤቷ የጅማ ከተማ ነዋሪ የ2,000,000 ብር እድለኛ ሆና ሽልማቷን ተረከበች!
የጅማ ከተማ ነዋሪ የሆነችው ወ/ሮ ትዕግስት ከተማ በእድል ሎተሪ 2ኛ ዕጣ የ2,000,000 ብር እድለኛ በመሆኗ የሽልማት ቼኳን በምትኖርበት የጅማ ከተማ በህዝብ ፊት ተረክባለች፡፡ እድለኛዋ የሶስት ልጆች እናት ስትሆን ባለቤቷ ደግሞ በቀን ሰራተኝነት በመስራት በሚገኝ ገቢ በዝቅተኛ ገቢ ይተዳደራሉ፡፡
በተደጋጋሚ ጊዚያት ሎተሪ በመቁረጥ እድላቸውን ይሞክሩ የነበሩት ቤተሰብ እድሉ የወ/ሮ ትእግስት ሆነና የእድል ሎተሪ 2ኛ ዕጣ 2,000,000 ብር እድለኛ ሆናለች፡፡
በደረሳት ገንዘብም ምን ለመስራት እንዳሰበች ስትናገር “የምንኖርበት ቤት በተዳጋጋሚ በጎርፍ የሚያጠቃውና ቆሻሻ አካባቢ የሚገኝ በመሆኑ የተሻለ መኖሪያ ቤት ለመግዛትና በቀሪው ደግሞ ከልጆቼ ጋር የንግድ ስራ እንሰራበታለን” በማለት ተናግረዋል፡፡
(ብሄራዊ ሎተሪ)

ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ስለ ዩኒቨርሲቲዎች የተናገሩት...
"በዩኒቨርሲቲዎች ላይ እያገኘን ያለነው መረጃ ረብሻ የሚፈጥሩት፤ በብሄር የሚያጋጩት፤ ሰው በጩቤ የሚወጉት የተላኩ የተገዙ ሰዎች ናቸው። ያሰማራቸው የላካቸው ከጀርባቸው ያለ የተደራጀ ኃይል ነው። ይሄን የሚያደርጉት አማራ ክልል ያለውን ኦሮሞ በጩቤ ስንወጋው ኦሮሞ በሙሉ ያምጻል፤ በተመሳሳይ ኦሮሞ ክልል ያለው አማራ በጩቤ ሲወጋ አማራው በሙሉ ያምጻል በሚል የተሳሳተ ስልትና እቅድ ነው። የዚህ የሴራ ፖለቲካ ቀመር አባትና ባለቤት አለው። በዚህ ስሌታቸው ሕዝቡ አምጾ ወደ እርስ በእርስ መተላለቅ ይገባል ብለው ነው ያቀዱት። አንዳንዶች የዴሞክራሲ ምህዳሩ ይስፋ እየተባለ እያወቅን ዝም ያልናቸው ኃይሎች አሉ። በዚህ ዓመት የተቀመጠው አቅጣጫ ሕግ የግድ መከበር እንዳለበት ወስነናል። አሁን አንጻራዊ ሰላም አለ። ሆን ተብሎ እንዲበጠበጥ በሚፈልጉ ኃይሎች የሚመሩ ተልእኮ ይዘው የሚንቀሳቀሱ አልፎ አልፎ ብልጭ ድርግም የሚሉ እንቅስቃሴዎች አሉ። በእነዚህ ላይም እርምጃ ይወሰዳል።"
#FDRE_Defense_Force

በኢፌዲሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ብዙነሽ መሰረት የተመራው የአገራችን የባህል ቡድን ዛሬ ታህሳስ 6 ቀን 2012 ዓም ከስዓት በኋላ አስመራ ገብቷል። ቡድኑ አስመራ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርስ በኤርትራ የባህል እና ስፖርት ኮምሽነር አምባሳደር ዘመዴ ተክሌ፣ በኤርትራ የኢፌዲሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ በአፍሪካ ህብረት የኤርትራ ቋሚ መልእክተኛ አምባሳደር አርዓያ ደስታ፣ ታዋቂ የኤርትራ አርቲስቶች፣ የኤርትራ የሴቶች ማህበር እንዲሁም ሌሎች የስራ ኃላፊዎች እና የህብረተሰብ ተወካዮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
(ኢቢሲ)

#WolitaSodo
በደቡብ ከልል የዎላይታ ሶዶ ከተማ ሴቶች «የዎላይታ ህዝብ በክልል ለመደራጀት ያቀረበው ጥያቄ ምላሽ ይሰጠው» ሲሉ ዛሬ በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀዋል። ወጣት ሴቶችና እናቶችጥያቄአቸውን ያቀረቡት ዛሬ ከማለዳው አንስቶ በዎላይታ ሶዶ ከተማ ዋና ዋና ጎዳናዎች በመጓዝ ነው። በወቅቱም ሴቶቹ «የሪፈረንደሙ ቀን በአስቸኳይ ይገለጽልን!!» ፣ «ለሰላማዊ የህዝብ ትግል ክብር ይሰጠው!!» የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል። የሰልፉ ዓላማ ህዝቡ ከዓመት በፊት በክልል ለመደራጀት ያቀረበው ጥያቄ የደቡብ ክልል ምክር ቤትን ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት በአፋጣኝ ገቢራዊ እንዲያደርጉ ለማሳሰብ ያለመ መሆኑን ከሰልፉ አሰተባባሪዎች አንዷ ወይዘሪት በረከት ቶማስ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ገልጸዋል።
(የጀርመን ድምፅ ሬድዮ)

#Mekelle
በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በመንገድ ትራፊክ ደህንነት ዙሪያ የሚመክር የምክክር መድረክ በመቐለ ከተማ ተካሄደ። መድረኩ የትራንስፖርት ሚኒስቴር በህዳር ወር እንደርሳለን በሚል መሪ ቃል የጀመረው ግንዛቤ የማስጨበጪያ ንቅናቄ አንዱ አካል ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ አሳሳቢነቱ እየጨመረ የመጣውን የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኮንስትራክሽ፣ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ከክልሉ ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር መክረዋል።

"በየትኛውም አካባቢ የሚኖሩ የህዝቦች ፍላጎት ተመሳሳይነት አለው፤ የፖለቲካ ልሂቃን እነዚህን ጥያቄዎች ለመፍታት በጋራ መነጋጋር አለባቸው። ይህ መሆን ካልቻለ ግን በፖለቲካ ድርጅቶች መካከል ያለው የእርስ በርስ እይታ የተዛባና ጥርጣሬ የተሞላበት ይሆናል። በልሂቃኑ መካከል የሚደረገው ምክክር የግድ አንድ አይነት አቋም ለመያዝ መሆን የለበትም። ፍርሃትና ጥርጣሬ በተሞላበት ግንኙነት አገር መገንባት አይቻልም። የኦሮ-ማራ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክክርም ይህን ችግር በመፍታት ረገድ ፋይዳው የጎላ ነው።" አቶ ስዩም መንገሻን (የአማራ ማህበራዊ ራእይ ግንባር ፕሬዚዳንት)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
"በአማራና ኦሮሚያም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች የሚከሰቱ የጸጥታ ችግሮች ዋነኛ ምክንያት የፖለቲካ ልሂቃን የሚፈጥሩት ያልተገባ ፉክክር ነው። በመሆኑም ፓለቲከኞች የዴሞክራሲ ሜዳ መጫዎቻ ህጉ ላይ በመነጋጋር መስማማት አለባቸው፤ ከዚህ አንጻር በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የሚንቀሳሱ የፖለቲካ ኃይሎች በጋራ መወያየት መጀመራቸው ከሁለቱ ህዝቦች ቁጥር አንጻር ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ትልቅ ፋይዳ አለው። ሁለቱ ህዝቦች ዘመናትን የተሻገረ አብሮነት አላቸው።" - አክቲቪስት ጃዋር መሃመድ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#DemekeMekonen #DrTedrosAdhanom
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር ጄኔቫ በሚገኘው የድርጅቱ ፅ/ቤት ተገናኝተው ተወያይተዋል። በሁሉ አቀፍ የጤና ሽፋን፤ በቅድመ ጤና አጠባበቅ፤ በተመጣጠነ ምግብ፤ በፋማሲዮቲካል አቅርቦት እና በአቅም ግንባታ ዙሪያ በስፋት መክረዋል።
(Office of Deputy Prime Minister)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር ጄኔቫ በሚገኘው የድርጅቱ ፅ/ቤት ተገናኝተው ተወያይተዋል። በሁሉ አቀፍ የጤና ሽፋን፤ በቅድመ ጤና አጠባበቅ፤ በተመጣጠነ ምግብ፤ በፋማሲዮቲካል አቅርቦት እና በአቅም ግንባታ ዙሪያ በስፋት መክረዋል።
(Office of Deputy Prime Minister)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
“መጪው ምርጫ ሁከትን ሊያቀጣጥል ይችላል” - ክራይስስ ግሩፕ #Election2020
ኢትዮጵያ ዉስጥ ዘንድሮ ይደረጋል የተባለዉ ምርጫ በሀገሪቱ ውስጥ የሚታየውን ክፍፍል ሊያሰፋው እና ሁከትንም የበለጠ ሊያቀጣጥል እንደሚችል ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ የተሰኘው ዓለም አቀፍ አጥኚ ተቋም አስጠነቀቀ። በሀገሪቱ ያለው ሁኔታ ከተባባሰ የኢትዮጵያ መንግስት መጪውን ምርጫ የሚያካሄድበትን ጊዜ እንዲያዘገይ ተቋሙ መክሯል።
ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ ይህን ያለው የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ በተመለከተ ዛሬ ሰኞ ታህሳስ 6 ባወጣው ዳሰሳ ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ ቀውስ አምጪ ሁነቶችን በመተንተን የሚታወቀው ይሄው ተቋም በኢትዮጵያ በመጪው ግንቦት ወር ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው ምርጫ በሀገሪቱ በተለያዩ ቦታዎችየሚታዩትን ሁከቶች የበለጠ ሊያባብስ እንደሚችል ተንብዩዋል።
https://telegra.ph/crisis-group-12-16
(Deutsche Welle)

#Boeing737MAX
ቦይንግ ከደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ የ737 ማክስ አውሮፕላን ምርትን በጊዜያዊነት ሊያቋርጥ መሆኑን አስታውቋል። እንደ ኩባንያው ገለፃ የ737 ማክስ አውሮፕላን ምርት ከፊታችን ጥር ወር ጀምሮ በጊዜያዊነት የሚቆም መሆኑ ታውቋል።
የኩባንያው ቦርድ ለሁለት ቀናት በአሜሪካ ቺካጎ ከተወያየ በኋላ ነው የአውሮፕላን ምርት እንዲቆም ውሳኔ ያሳለፈው ተብሏል። ይህ የሆነውም የአሜሪካ ፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር በአውሮፓውያኑ ከ2020 በፊት አውሮፕላኖቹ ወደ በረራ እንዲገቡ ፍቃድ አልሰልጥም ማለቱን ተከትሎ ነው።
የቦይንግ ምርት የሆኑት 737 ማክስ አውሮፕላኖች በኢትዮጵያ እና በኢንዶኔዢያ በደረሰ አደጋ በድምሩ የ346 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትትሎ ካሳለፍነው ዓመት መጋቢት ወር ጀምሮ ከአገልግሎት ውጭ ተደርገው መቆማቸው ይታወሳል።
አደጋዎቹ በ737 ማክስ አውሮፕላኖች መቆጣጠሪያ ስርዓት ላይ በነበረ ችግር መፈጠሩ የተገለፀ ሲሆን፥ በዚህም ምክንያት ኩባንያው እስከ 9 ቢሊየን ዶላር አጥቷል ነው የተባለው።
ቦይንግ የ737 ማክስ አውሮፕላኖችን ምርት ቢያቋርጥም፤ ለወታደራዊ ግልጋሎት የሚውለውን የP8 ስሪት ምርቶችን ግን እንደሚቀጥል አስታውቋል። የቦይንግ አክሲዮን ገበያው እየተቀዛቀዘ ነው የተባለ ሲሆን፥ የ737 ማክስ አውሮፕላኖች ምርትን ለጊዜያዊነት አቋርጣለሁ ማለቱን ተከትሎ የአክሲዮን ገበያው በ4 በመቶ መቀነሱ ነው የተነገረው።
ምንጭ፦ አልጀዚራ(ኤፍ ቢ ሲ)

#OLF
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ ምርጫ 2012 በሰላም እንዲጠናቀቅ እንደሚሰራ የግንባሩ ሊቀ-መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ተናግረዋል። ሊቀመንበሩ ከትናንት በስቲያ በአምቦ ከተማ ስታድዮም ለአምቦ ነዋሪዎች ባደረጉት ንግግር ኦነግ ህብረ-ብሄራዊ ፌደሪሊዝም ወደኋላ እንዳይመለስ የበኩሉን አስተዋፆ እንደሚያደርግ ገልጿል።
PHOTO:VOA

#BarackObama
ሁሉንም የዓለም ሃገራት የሚመሩት ሴቶች ቢሆኑ ኖሮ የተሻለ የህይወት ዘይቤ ይኖረን ነበረ ሲሉ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ተናገሩ። በሲንጋፖር በተካሄደ መድረክ ላይ ሴቶች ፍጹም ባይሆኑም "ያለምንም ጥርጥር ከወንዶች የተሻሉ ናቸው" ብለዋል።
ኦባማ ዓለማችን ከሚያጋጥሟት የአብዛኞቹ ችግሮች መነሾ ያረጁ ወንዶች በተለይ ስልጣን ላይ ያሉት ናቸው ሲሉ ተደምጠዋል። ኦባማ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ዓለም በሴት መሪዎች ብትመራ ምን ልትመስል እንደምትችል ያልሙ እንደነበረ ተናግረዋል። "ሴቶች፣ አሁን እንድትረዱት የምፈልገው ፍጹም አይደላችሁም ግን ያለምንም ክርክር ከእኛ ትሻላላችሁ"ብለዋል።
"በጣም በእርግጠኝነት የምናገረው ሁሉም ሃገር ለሁለት ዓመታት በሴቶች ቢመራ፤ የተሻለ የኑሮ ዘይቤ እና ደረጃ ይኖረናል። በሁሉም ዘርፍ ለውጥ እንመለከታለን" ብለዋል።
ወደፊት ወደ ፖለቲካ መድረኩ የመመለስ ዕቅድ ካላቸው የተጠየቁት የቀድሞ ፕሬዝደንት፤ ይልቁንም ለሌሎች የፖለቲካ መሪዎች ቦታ መልቀቅ እንደሚያሳምናቸው አስረድተዋል። "ዓለምን በትኩረት ከተመለከትናት የችግሮቿ ምንጮች ብዙ ጊዜ ያረጁ ስልጣን ያለመልቀቅ አባዜ ያላቸው እምቢተኛ ወንዶች ናቸው" ብለዋል።
(BBC)

አምባሳደር ጥሩነህ ዜና...
"አማራና ኦሮሞ እንዳይነጣጠሉ ሆነው በደምና ስጋ የተሳሳሩና በርካታ እሴቶችን የሚጋሩ ሕዝቦች ናቸው። ሁለቱ ሕዝቦች ለአገር ግንባታ በጋራ ዋጋ እንደከፈሉ ሁሉ በሂደቱ ቁርሾ የፈጠሩ ክስተቶች ነበሩ፤ የበርካታ አገራት የሀገረ-መንግስት ግንባታ ሂደት መሰል ታሪክ ማስተናገዱ ይታወሳል። ሕዝብን በማንቃት ደረጃ ቀዳሚ የሚባሉት የፖለቲካ ኃይሎች የሚጠበቅባቸውን ሚና ቀድመው ባለመወጣታቸው ችግሩ ተባብሶ ለሰው ሕይወት መጥፋት መንስኤ እየሆነ መጥቷል። የነገ አገር ተረካቢ ወጣቶች በጥላቻ አዙሪት ውስጥ እንዲገቡ አድርጓል። በመሆኑም ፖለቲከኞች የእነዚህን ሕዝቦች ልዩነት እየለቀሙ ከመነታረክ ወጥተው በጋራ መስተጋብሮች ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቀርባለሁ።"