TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወላጆች ልጆቻቸውን በግል ትምህርት ቤቶች ለማስተማር እስከ 50,000 ብር እየተጠየቁ ነው!

የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የሚታየው የፀጥታ ስጋት ለግል ተቋማት ገበያ እና የሙስና በር ሆኗል። በሀገሪቱ ባሉ አንዳንድ የመንግስት ዩንቨርስቲዎች አልፎ አልፎ የሚነሳው ብሄር ተኮር ጥቃት እና አለመረጋጋት ወላጆች ላይ ስጋት በመደቀኑ በርካታ ወላጆች ልጆቻቸውን አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለማስገባት እንዳስገደዳቸው ካፒታል ጋዜጣ መታዘቡን በድረ ገፁ አስፍሯል።በዚህም የግል ተቋማት ገበያቸው በመድራቱ ለሙስና በር እየከፈተ መሆኑን፤ እና ልጆቻቸውን ለማስመዝገብ ወላጆች በአንዳንድ ተቋማት እስከ 50 ሺ ብር ጉቦ በደላሎች አማካኝነት እየተጠየቁ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

(ካፒታል ጋዜጣ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#NobelPeacePrize

ዶ/ር አብይ ኦስሎ....

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኖቤል ሽልማታቸውን ለመቀበል የኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሽልማታቸውን የሚቀበሉት ነገ ማክሰኞ ህዳር 30/2012 ዓ.ም ነው። ጠ/ሚሩ በዚሁ ጎዟቸው ወቅት ወደ ስዊድን ጎር ብለዋ ከሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ስቴፈን ሎቨን ጋር በሁለቱ ሀገሮች ግንኙነቶች ላይ ተነጋግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በኖርዌይ ኦስሎ ከኖቤል ኮሚቴ አባላት ጋር ተገናኝተዋል። #Norway #Oslo

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#NobelPeacePrize #AbiyAhemed

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የሰላም የኖቤል ሽልማታቸውን የሚቀበሉበት ሥነ ሥርዓት ነገ ማክሰኞ፤ ኅዳር 30 / 2012 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለጥያቄያችሁ መልስ!

ማስታወቂያዎችን ማስነገር የምትፈልጉ፦

1. የድርጅታችሁን ስም
2. የድርጅታችሁን ህጋዊነት የሚያረጋግጥ ማስረጃ
3. አድራሻ በ @tsegabtikvah ላይ ብቻ ላኩልን! አልያም በኢሜል [email protected] /0919743630/ መልሰን የማስታወቂያ ፓኬጁን እንልካለን!

ለቤተሰባችን የምናሰራጨው እጅግ ውስን ማስታወቂያዎች በመሆናቸው ለማስታውቂያ ደንቦች ተገዢ እንደምትሆኑ እናምናለን!

@tikvahethiopia
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል የዓይን ህክምና ማእከል አስገነባ!

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ከኦርቢስ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ያስገነባው የዓይን ህክምና ማእከል ተመርቆ ለአገልግሎት መብቃቱን ሆስፒታሉ ገለፀ። የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ሰላም አየለ በምረቃ ስንስርዓቱ ላይ እንዳሉት ማዕከሉ የተቋቋመው ከኦርቢስ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ነጻ የዐይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና አገልግሎትና ሌሎች ህክምናዎች ለመስጠት ነው። ሆሲፒታሉ ለተለያዩ የዐይን ህመሞች ህክምና ሲሰጥ የቆየ ቢሆንም የዐይን ቀዶ ህክምና አገልግሎት የሚፈልጉ ህሙማን ግን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ሲልክ መቆየቱን ጠቁመዋል።

(ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የወላይታ ዞን ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ ተቀመጧል። ጉባኤው፦

1.የወላይታ ብሄር የክልልነት ጥያቄ የደረሰበት ደረጃ ይገመግማል።

2.ቀጣይ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።

(ኦ ኤም ኤን)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaBot
#NobelPeacePrize #AbiyAhemed

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ትናንት ምሽት በኖርዌይ የኖቤል ተቋም የክብር እንግዳ መዝገብ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በክብር እንግዳ መዝገቡ ላይ በአማርኛ አስተያየታቸውን ያሰፈሩ የመጀመሪያው ሎሬት መሆናቸውን ከኖርዌይ የኖቤል ተቋም የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

(ኢቢሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም...

• አመራሩ ብሔሩን እየለየ የሚያገለግል ከሆነ አስቸጋሪ ነው። በእያንዳንዱ ክልል የተለያየ ብሔር ብሔረሰብ አለ። መንግሥት እኩል ካላገለገለ አድሎ ከተፈፀመ በአግባቡ አልተገለገልኩም የሚል ጥያቄ ያቀርባል።

• አንዱ ከአንዱ ጋር የሚገፋፋ ከሆነ አንድነት አይመጣም። ሰው ሲሞት ለምን ሞተ ከማለት ይልቅ የየትኛው ብሔር ተወላጅ ብዙ ሞተ እየተባለ ነው። ይህ ቀድሞ መሠራት የነበረበት ሥራ ባለመሥራቱ የመጣ ነው።

• ማንኛውም ሰው የራሱን ማንነት እንዲከበርለት የሚፈልግ ከሆነ የሌላውንም እኩል ማክበር አለበት። እዚህ ላይ ትልቅ ክፍተት ነበር።

• ስለብሔር ማሰብ ላይ ብቻ መተኮር የለበትም። አንዲት ትልቅ አገር መኖሯንም መዘንጋት የለበትም።

• አገርን ከመገንባት ለሌሎች ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች እኩል ክብር እና እውቅና መስጠት ያስፈልጋል።

• ብሔራዊ ማንነት ቢኖረንም ከአገራዊ ማንነት ውጭ መሆን አንችልም። እርስ በእርሳችን እንከባበር የምንለው አገራችንን ለመገንባት ነው።

• ትልቁ ችግር አገራዊ እና ብሔራዊ ማንነት ሚዛናቸውን ጠብቆ አለመሄዳቸው ነው። ለራስ ብሔር ብቻ ማሰብ ትርጉም የለውም።

More👇
https://telegra.ph/ETH-12-10

ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም (የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ)

(አዲስ ዘመን ጋዜጣ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
- ዓለም አቀፍ የወጣቶች ህብረት "IYF" የተሰኘ የኮሪያ በጎ ፈቃደኛ ቡድን የአስተሳሰብ ማቅኛ "ማይንድ ሴት" ስልጠና ከጋሞ ዞን ሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ለተወጣጡ ከ850 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች በትላንትናው እለት በአርባምንጭ ከተማ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MekelleUniversity

2 ኛው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ምሩቃን መድረክ "የአልሙናይ ተሳትፎ ለመቐለ ዩኒቨርሲቲ የላቀ ውጤት" በሚል መሪ ቃል ቅዳሜ ታህሳስ 4፣ 2012ዓ.ም በአዲስ አበባ ሃርመኒ ሆቴል ይካሄዳል። በመድረኩ ላይ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች እና የክብር እንግዶችን ጨምሮ ከ200 በላይ ታዳሚያን እንደሚገኙ ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሩዋንዳ የኢቦላ መከላከያ ክትባት መስጠት ጀመረች!

- ሩዋንዳ የኢቦላ በሽታን የሚገታ  የክትባት ዘመቻን ለመጀመሪያ ግዜ መስጠት ጀመረች። የአገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በዘመቻው ክትባቱ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሚዋሰኑ ቦታዎች ለ200 ሺ ሰዎች  ይሰጣል ብለዋል፡፡

የጤና ሰራተኞች፣ የኢሚግሬሽን ሰራተኞች፣ ፖሊሶች እና ድንበር ተሻጋሪ ንግድ ላይ ለተሰማሩት የህብረተሰብ  ክፍሎች ክትባቱ በቅድሚያ ይሰጣችዋል ተብሏል፡፡

በሩዋንዳ እስከ አሁን ምንም ዓይነት የኢቦላ በሽታ አለመታየቱ ቢገለጽም፤ በጎረቤት  ሀገር በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኢቦላ በሽታ ምክንያት ከባለፈው ነሃሴ ጀምሮ ከ2 ሺ 200 ሰዎች በላይ መሞታቸው ተገልጿል፡፡

በዚህ ምክንያትም ክትባቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠው በምስራቅ ዲሞክራቲክ ኮንጎ  በምትገኘው ጎማ  ሲሆን፤ እስከ አሁን ሩብ ሚሊዮን የሚሆኑ ኮንጎውያን ክትባቱ እንደተሠጣቸው የቢቢሲ ዘገባ ያሳያል።

(BBC)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#FerweyniMebrhatu #CNN

"ፍሬወይኒ መብራሃቱ በአውሮፓውያን አቆጣጠር የ2019 የሲ.ኤን.ኤን የዓመቱ ጀግና ተብላ በመጠራቷ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል። ሴት ልጆች በትምህርት ቤት እንዲቆዩ ያላት ቆራጥነት፣ እንዲሁም ማኅበረሰቧን የተሻለ ለማድረግ ያላት አቋም የሚደነቅ ነው። ኢትዮጵያ በፍሬወይኒ ኮርታለች።" ዶ/ር ዐብይ አህመድ (የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠ/ሚኒስትር)
.
.
"የእኛው ፍሬወይኒ CNN የ2019 ጀግና ሆነች!! እንኳን ደስ አለሽ! በተፈጥሯው ጉዳይ ለሚሸማቀቁ: ከትምህርታቸው ለሚስተጏጎሉ: ለሚያቋርጡ:ከሌላው በታች የሆኑ ለሚመስላቸው..የአገራችን ሴቶች ትልቅ ቀን ነው!ተባብረን ዘላቂ መፍትሄ እናምጣ!" ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ (የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳንት)

@tikvahethiopiaBot @tikavhethiopia
የስልክ ስክሪን ማጠንከሪያ ተብሎ አገልግሎት ላይ እየዋለ ያለው ፈሳሽ ዕውቅና የለውም ተባለ!

በየመንገዱ የስልክ ስክሪን ማጠንከሪያ ተብሎ አገልግሎት ላይ እየዋለ ስላለው ፈሳሽ የሚያውቀው ነገር አለመኖሩን የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለሥልጣን አስታወቀ።

ናኖ ቴክኖሎጂ ማለት ዘረፈ ብዙ ቴክኖሎጂዎችን በውስጡ የሚይዝ መሆኑም ተገልጿል። የሞባይል ስልክ ስክሪን ማጠንከሪያ ተብሎ ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው ፈሳሽ መፈተሽ እንዳለበት የባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አወቀ ሺፈራው ተናግረዋል።

በፍተሻውም ወቅት በስልክ ገጽ ላይ የሚቀባው ፈሳሽ ጨረራ አለው ወይስ የለውም፤ የጨረራ ይዘቱ ምን ያህል ነው የሚለው ፍተሻ እንደሚደረግበት ገልጸዋል።

በፍተሻው ውጤት መሠረት ጨረራ አመንጪ ከሆነ ደግሞ መጠኑ ከዚህ በላይ ከሆነ ጉዳት አለው፣ ከዚህ በታች ከሆነ ደግሞ ጉዳት የለውም የሚለውን በሳይንሳዊ ትንታኔ መሠረት መናገር ይቻላል፤ ይህ ባልታወቀበት ሁኔታ ግን ይህ ነው ብለን መናገር አንችልም በማለት አብራርተዋል። አያይዘውም፣ በተቋማችን አሠራር አንድ ጨረር አመንጪ ቁስ አካል ወደ አገር ውስጥ ሲገባ አስመጨዎቹ ያመጡትን ነገር ወደ ተቋማችን አምጥተው የማሳወቅ ግዴታ እንዳለባቸው ሕጉ ያስገድዳል።

https://telegra.ph/ETH-12-10-2

(ኢቲቪ)

@tikvahethiopiaBot @tikavhethiopia
የወላይታ ዞን ምክር ቤት አራተኛ ዙር ሰባተኛ ዓመት አንደኛ አስቸኳይ ጉባኤ በጠራው ስብሰባ ያወጣው የአቋም መግለጫ!

ህዳር 30/2012 ዓ.ም የወላይታ ዞን ምክር ቤት የወላይታ ብሔር በክልል የመደራጀት ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ በብሔሩ ምክር ቤት በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ ለክልሉ ምክር ቤት ለጉባኤ ቀርቦ ለምርጫ ቦርድ ተመርቶ ሕዝበ ውሳኔ ባለመደራጀቱ ምክንያት የብሔሩ ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ በዛሬው ዕለት አካሂዷል፡፡

የወላይታ ብሔር እራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ለ125 አመታት የዘለቀ ነዉ፡፡ የወላይታ ህዝብ በ1983 የሽግግር ወቅት ራሱን ችሎ በክልል ዘጠኝ ተደራጅቶ ነበረ፤ ኋላም በድንገተኛ ውሣኔ ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር ተጨፍልቆ ‹‹ የደቡብ ክልል›› በሚል እንዲዋቀር መደረጉ የቅርብ ሩቅ ጊዜ ትዉስታ ነዉ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ህዝቡ በክልል የመመስረት ፍላጐቱን በተለያዩ አግባቦች ሲያንፀባርቅና ሲጠይቅ ቆይቷል፡፡ በ1992 ዓ.ም በሚሊዮን የሚቆጠሩ የብሔሩ ተወላጆችም በቋንቋ አጠቃቀምና ክልል በመመስረት ጉዳይ ላይ ሠላማዊ ሠልፍ አድርገው እንደነበርም ይታወቃል፡፡

More👇
https://telegra.ph/WRS-12-10

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ወላይታ ዞን ምክር ቤት...

- "በኢፌዴሪ ህገ - መንግስት አንቀጽ 47 ንዑስ አንቀጽ 3 (ለ) በተጠቀሰው መሠረት እስካሁን የደቡብ ክልል ምክር ቤት የወላይታ ብሔር ክልል የመመስረት ጥያቄ ጉዳዩ ለሚመለከተው የኢትዮጰያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሳያስተላልፍ መቆየቱ ኢ-ህገመንግስታዊ በመሆኑ የተከበረው የዞኑ ምክር ቤት ሁኔታውን ያወግዛል፤ ስለሆነም የክልሉ ምክር ቤት ጉዳዩን ተቀብሎ በቀሪ አስር ቀናት ውስጥ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንዲያስተላልፍ በአፅኖት ይጠይቃል፡፡"

(የወላይታ ዞን ምክር ቤት)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የወላይታ ዞን ምክር ቤት...

"የደቡብ ክልል ምክር ቤት በቀሩት አስር ተከታታይ ቀናቶች ውስጥ አስቸኳይ የምክር ቤት ጉባኤ በመጥራት የህዝባችንን ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ ለጉባኤ በማቅረብ ለኢትዮጰያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝብ ውሳኔ እንዲያደራጅ የማይልክ ከሆነ የኢፊዴሪ ፈዴሬሸን ምክር ቤት ጠልቃ በመግባት ለደቡብ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባዔ እንዲጠራ ትዕዛዝ እንዲሰጥ እንጠይቃለን፤"

(የወላይታ ዞን ምክር ቤት)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
“በአንድ ሀገር ውስጥ የመናገር ነፃነት ያለ ገደብ ሲሰጥ የጥላቻ ንግግሮች እና ሐሰተኛ መረጃዎች ሊኖሩ ይችላሉ፤ ለዚህ ደግሞ መንግስት ገለልተኛ ተቋማትን ማቋቋምና ከዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች በመነሳት ጠንካራ ሕግ ማውጣት አስፈላጊ ነው፡፡" - በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ሕግ መምህርና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሀሳብን በነፃነት መግለፅ ልዩ ፀሐፊ ፕሮፊሰር ዴቪድ ኬይ

#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማት ተቀበሉ!

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማታቸውን ተቀበሉ። የኖቤል የሰላም ሽልማት ስነ ስርዓት በዛሬው እለት በኖርዌይ ኦስሎ በመካሄድ ላይ ይግኛል። በስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ሽልማታቸውን ተቀብለዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#NobelPeacePrize #AbiyAhemed

የኖቤል ኮሚቴ ሊቀ መንበር ቤሪት ራይስ አንደርሰን ለጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አህመድ ሽልማት ከመስጠታቸው በፊት ባደረጉት ንግግር ጠቅላይ ሚንሥትሩ ለሰላም ላበረከቱት አስተዋጽዖ ምሥጋናቸውን አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ ሰላምና ዲሞክራሲን ለማስፈን በርካታ ርምጃዎችን መውሰዳቸው እንዲሁም በካቢኔያቸው አምሳ በመቶ ሴቶችን መሾማቸዉ ተመስግኗል። በሽልማት ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የሰላም ሚንስትር ሙፈሪያት ካሚል፣ የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ሣኅለ-ወርቅ ዘውዴ እንዲሁም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ማአዛ አሸናፊ ሴቶች መኾናቸውን ሊቀመንበሯ አመስግነዋል።

ሽልማቱም የተሰጠው፦ ሰላም እና ብልጽግና በኢትዮጵያ ለማስፈን ዓልመው መነሳታቸው ሊቀመንበሯ ገልጠዉ የኖቤል ኮሚቴዉ ዕውቅና ሰጥቶታል። በምሥራቅ አፍሪቃ ሃገራት ሰላም እንዲሰፍን ጠቅላይ ሚንስትሩ ላበረከቱት አስተዋጽዖም በኮሚቴው ተመስግነዋል።

ኤርትራ እና ጅቡቲ ሰላም እንዲፈጥሩ ጥረት መደረጉ፤ በደቡብ ሱዳን እና ሱዳን ሰላማዊ መፍትኄዎችን እንደ አማራጭ መወሰዳቸው ተወድሷል። «ኢትዮጵያ የሰው ልጆች መገኛ ናት» ያሉት የኖቤል ኮሚቴ ሊቀ መንበር ቤሪት ራይስ አንደርሰን፤ «የመጀመሪያው ሆሞ ሴፒያን የፈለሰው ከእርስዎ [ጠ/ሚ ዐቢይ]ሀገር ነው፣ በዚህም እኛ ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ነን» ብለዋል። ኢትዮጵያ በአዉሮጳዉያን ቅኝ አለመገዛትዋ፤ የአፍሪቃ ኅብረት መቀመጫ መኾኗ ከመድረኩ ሲገለጥም ሞቅ ያለ ጭብጨባ ከታዳሚያን ተሰምቷል።

(DW)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
«ኢትዮጵያ የሰው ልጆች መገኛ ናት። የመጀመሪያው ሆሞ ሴፒያን የፈለሰው ከእርስዎ [ጠ/ሚ ዐቢይ] ግዛት ነው። በዚህም እኛ ሁላችንም ኢትዮጵያውያኖች ነን።» - የኖቤል ኮሚቴ ሊቀ መንበር ቤሪት ራይስ አንደርሰን

#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia