TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#SituationReport | #Amhara #Tigray #Afar

#UN_OCHA በአፋር ፣ ትግራይ እና አማራ ክልል ስላለው ሁኔታ እና እየተደረገ ስላለው የሰብዓዊ ድጋፍ እንቅስቃሴ ሪፖርት አውጥቷል።

ዋና ዋና ነጥቦች ፦

- በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ግጭት 9.4 ሚሊዮን የሚገመቱ ሰዎች የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።

- እኤአ ከህዳር 20 ጀምሮ ከትግራይ ምዕራብ ዞን ወደ ማይ-ፀብሪ፣ ሸራሮ እና ደደቢት ወረዳዎች በርካቶች ተፈናቅለው የገቡ ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት እንደሚያሳየው ከሽሬ በስተ ምዕራብ 70 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ደደቢት ብዙ ሺህ ሰዎች ደርሰዋል፤ አዲስ ተፈናቃዮች ፍሰት የቀጠለ በመሆኑ ቁጥሩ ሊጨምር ይችላል።

- በትግራይ ክልል 5.2 ሚሊዮን ህዝብ ሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ቢያንስ 400,000 ያህሉ በርሃብ መሰል ሁኔታ ላይ ያሉ ናቸው።

- በአፋር ክልል በዚህ ዙር በተደረገ ድጋፍ ከ86,000 በላይ ሰዎች ምግብ አግኝተዋል።

- በአማራ ክልል 3.7 ሚሊዮን ዜጎች አስቸኳይ ሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።

- በአማራ ክልል በሰ/ወሎ፣ ዋግ ኽምራና ከፊል ደቡብ ወሎ እንዲሁም በአፋር ክልል ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ያለው ሰብዓዊ ሁኔታ በተለይ በአኗኗር ፣ በገበያ መቋረጥ እና የሰብዓዊ ዕርዳታ ለማድረስ ባለመቻሉ አሳሳቢ ነው።

- በአማራ ክልል አዲስ ተፈናቃዮች አሁንም አሉ። በደብረ ብርሃን ከተማ ተፈናቃዮችን የሚያስተናግዱ የጋራ ቦታዎች ቁጥር ከስድስት ወደ 10 ከፍ ብሏል፣በተመሳሳይ በኮምቦልቻ ከ2 ወደ 17 ከፍ ብሏል።

ሙሉ ሪፖርት : https://reports.unocha.org/en/country/ethiopia/

@tikvahethiopoa
TIKVAH-ETHIOPIA
Situation_Report_Northern_Ethiopia_Humanitarian_Update_19_Feb_2022.png
#SituationReport :

#Tigray #Amhara #Afar📍

የሰሜን ኢትዮጵያ #ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ወይም #UN_OCHA የዚህን ሳምንት ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል።

ዋና ዋና ነጥቦች ፦

#Afar

• በአፋር የተለያዩ አካባቢዎች #አሁንም ግጭት ቀጥሏል። በዋናው ኮሪደር (A1) [አፋር ሰመራን ከመቐለ ትግራይ የሚያገናኘው] እና ትግራይ እና አፋር በሚዋሰኑባቸው ኤሬብቲ ፣ በርሀሌ እና መጋሌ ወረዳዎች ፣ በኡሩህ እና ዋህዲስ ቀበሌዎች፣ በሁሉም የኬልበቲ ዞን ግጭት መኖሩ ተመላክቷል።

• በአፋር ያለው ሰብዓዊ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቷል። መጠነ ሰፊ መፈናቀል በመኖሩ የሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎቱ እየጨመረ መጥቷል።

• በአፋር ክልል በተከሰተው ግጭት እስካሁን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን የተፈናቀሉ ሲሆን አብዛኞቹ በመጋሌ፣ በርሀሌ፣ ኮነባ፣ ኢረብቲ እና ዳሎል ወረዳዎች መጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው ይገኛሉ። አካባቢዎቹ በመንገድ ሁኔታ እና በፀጥታ ስጋት ምክንያት ለሰብአዊ አጋሮች ተደራሽ አይደሉም።

#Tigray

• በትግራይ ክልል እ.ኤ.አ. የካቲት 12 በምስራቅ ዞን አፅቢ ከተማ ላይ በደረሰ የአየር ድብደባ የንፁሀን ዜጎች ህይወት መጥፋቱ እና ሰዎች መቁሰላቸውን ተመድ አመልክቷል። የተመድ አጋሮች እስካሁን የተጎጂዎችን ቁጥር ማረጋገጥ እንዳልቻሉ ተገልጿል።

• በትግራይ ክልል በአብዛኛው ሰሜናዊ ክፍል [ከኤርትራ ድንበር በሚዋሰኑ ቦታዎች] የተወሰኑ ቀበሌዎች በማዕከላዊ ዞን ራማ ፣ በምስራቅ ዞን ኢሮብ፣ በምስራቅ ዞን ዛላ አምበሳ ከተማ ጨምሮ ተደራሽ አይደሉም። በእነዚያ አካባቢዎች ላለፉት ጥቂት ወራት ምንም አይነት እርዳታ ሳያገኙ የቆዩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖች አሉ።

• እኤአ ከታህሳስ 15 አንስቶ የፀጥታ ችግሮችና ግጭቶች ወደ ትግራይ ክልል በየብስ በ #ሰመራ- #አብዓላ- #መቐለ መንገድ እርዳታ እንዳይገባ እንዳገዱ ይገኛሉ። ከታህሳስ አጋማሽ በፊት ተፈቅዶ የነበረው የአቅርቦት መጠን በዋናነት በቢሮክራሲያዊ እክል ከሚያስፈልገው በታች በመሆኑ አሁን በፀጥታ ችግር እና በግጭት መንገድ መዝጋቱ ወደ ትግራይ ክልል የሚደርሰውን የሰብአዊ አቅርቦት ችግር የበለጠ እንዳባባሰው ተገልጿል።

• እ.ኤ.አ. ከሀምሌ 12 አንስቶ አጠቃላይ 1,339 የጭነት መኪናዎች ከሰመራ ወደ ትግራይ ክልል የገቡ ሲሆን ይህ በትግራይ ክልል ያለውን ሰፊ ​​የሆነ የሰብአዊ ፍላጎት ለማሟላት ከሚያስፈልጉት አቅርቦቶች ውስጥ 8 በመቶውን ብቻ የሚሸፍን ነው። ተጨማሪ 17 የጭነት መኪናዎች ባለፈው ህዳር ወር ከኮምቦልቻ ፣ አማራ ክልል ወደ ትግራይ ገብተው ነበር።

• የዓለም ጤና ድርጅት-WHO የላከው የህክምና ቁሳቁሶች መቐለ ቢደርሱም አጋር አካላት በነዳጅ እጥረት ምክንያት በክልሉ ወዳሉ ጤና ተቋማት መላክ እና ማከፋፈል እንዳልቻሉ ተመድ ገልጿል። በተለይም ከ800 ሺህ በላይ ተፈናቃዮችን ወዳስጠለለው የሰሜን ምእራብ ዞን ማድረስ አልተቻለም። በዞኑ ከአጠቃላይ የውስጥ ተፈናቃይ 1.8 ሚሊዮን 44 % ይሸፍናል።

• በሰሜን ምዕራብ ዞን ተፈናቃዮችን ባስጠለሉ ቦታዎች የእከክ በሽታ እና ወባ ኬዞች መጨመራቸው ተመላክቷል። ከ1,100 በላይ የእከክ በሽታ ኬዝ በ22 ሳይቶች ፣ከ1800 በላይ የወባ ኬዞች በዞኑ ከዓመቱ መጀመሪያ (የፈረንጆች) ጀምሮ ተመዝግቧል። የአቅርቦት ችግር፣ የመድሃኒትና የነዳጅ እጥረት ተመድ የጤና አጋሮቹ የበሽታዎችን ስርጭት እንዲቀንስ ለማድረግ የሚሰሩትን ስራ እየገደበ መሆኑን ገልጿል።

• ተ.መ.ድ. በትግራይ ክልል ላሉት የሰብአዊ ድጋፍ አጋሮቹ ያለው ነዳጅ፣ ጥሬ ገንዘብ እና አቅርቦቶች በጣም አነስተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ በመግለፅ ይህም ሁኔታ የሰብአዊ አገልግሎቶችን በተለይም የምግብ ፣ የውሃ ፣ የጤናና የስነ - ምግብ አገልግሎቶች ስርጭትን በእጅጉ እየቀነሰው መሆኑን አመልክቷል።

#Amhara

• በአብዛኛው የአማራ ክልል በአንጻራዊ የተረጋጋ ሁኔታ ያለ ሲሆን በሰሜን ወሎ በትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች ያለው ሁኔታ ግን ውጥረት እንደነገሰበት ነው።

• አማራ ክልልን ከትግራይ ክልል የሚያዋሱ አካባቢዎች አሁንም ባለው የፀጥታና የደህንነት ስጋት ተደራሽ አይደሉም። መድረስ አልተቻለም። ይህም በሰሜን ጎንደር፣ ዋግ ኽምራና ሰሜን ወሎ ያሉ አካባቢዎች ያካትታል። ባለው ሁኔታ ህዝቡ የአስፈላጊ የምግብ እደላ ጨምሮ አጠቃላይ ሰብአዊ ርዳታ እንዳያገኝ ሆኗል።

• በሰሜን ጎንደር ፣ ዋግ ኽምራ እንዲሁም ሰሜን ወሎ ዞኖች አካባቢዎች አዲስ መፈናቀል መኖሩ ተመላክቷል።

• በዋግ ኽምራ እና ሰሜን ወሎ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ ነው። በርካታ ሰዎች በተደጋጋሚ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። በአዋሳኝ አካባቢ ባለው የፀጥታ ሁኔታ ድጋፍ የሚፈልጉ ወገኖች ውስን የሰብዓዊ ዕርዳታ ብቻ እንዳገኙ ተገልጿል። በዋግ ኽምራ በዋናነት በዝቋላ ወረዳ እና ሰቆጣ ወረዳ በአሁኑ ወቅት ከ30,000 በላይ ተፈናቃዮች አሉ።

• ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ከ12,000 በላይ ሰዎች ሰብአዊ እርዳታ ለማግኘት ወደ ራያ ቆቦ አማራ ክልል ገብተዋል።

• በሰሜን ወሎ ዞን ውስጥ ከ21 ሺ የሚበልጡ ተመላሾች አስቸኳይ የመጠለያ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል። የመኖሪያ ቤታቸውን መልሶ የማቋቋም እና የመልሶ ግንባታ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። በዞኑ ሆስፒታሎችና ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ ከ4 ሺህ በላይ ቤቶችና ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ የመንግስት ተቋማት ጉዳት ደርሶባቸዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USAID " ... ኢትዮጵያውያን ሲቪሎችን ለመመገብ የሚደረገውን ጥረት ማደናቀፍ እጅግ የጭካኔ ተግባር ነው። የተዘረፈውን ነዳጅ መልሱ  " - ሳማንታ ፓወር የአሜሪካ ህዝብ ተራድኦ ድርጅት (USAID) አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር ፤ ህወሓት (TPLF) የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለስራ የሚጠቀምበትን 150,000 ጋሎን ነዳጅ መዝረፉን በመግለፅ ድርጊቱን አጥበቀው አውግዘዋል። በተጨማሪም በእርዳታ ሰራተኞች…
#UN_OCHA

" ውጤቱ እስከፊ ሊሆን ይችላል " - ማርቲን ግሪፊትስ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ረዳት ዋና ጸሃፊና የአስቸኳይ ድጋፍ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትስ በትላንት በስቲያ በትግራይ ክልል፣ መቐለ ከሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን በኃይል የነዳጅ ታንከሮች መወሰዱን መስማታቸው እጅግ እንደረበሻቸው ገልፀዋል።

የነዳጅ ታንከሮቹ 12 መሆናቸውን ያመለከቱት ግሪፊትስ 570,000 ሊትር ነዳጅ መያዛቸውን ገልፀዋል።

ነዳጁ ተመድ እና አጋሮቹ በከፋ ሁኔታ ውስጥ ላሉ ሰዎች አስፈላጊ ድጋፍ ለማድረግ የሚረዳ መሆኑን አመልክተዋል።

ያለዚህ ነዳጅ ሰዎች ያለ ምግብ፣ ያለ ድጋፍ ሰጪ ንጥረነገሮች፣ ያለ መድሃኒት እና ያለሌሎች ወሣኝ አስፈላጊ ነገሮች ይቀራሉ ብለዋል።

የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እና የምግብ ዋስትና እጦት እየተባባሰ ባለበት በዚህ ወቅት #ውጤቱ_አስከፊ_ሊሆን_ይችላል ሲሉም አስጠንቅቀዋል።

ይህን መሰሉን ድርጊት አወግዛለሁ ያሉት ግሪፊትስ " የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦቶች በመላው ኢትዮጵያ ሊጠበቁ ይገባል። የሰብዓዊ ዕርዳታ ማደናቀፍ መቆም አለበት " ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በትግራይ የባንክ ፣ የመብራት እና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲመለሱ የጠየቁ ሲሆን ይህ በክልሉ ያለውን የሰብዓዊ ሁኔታ ለማሻሻል አስተዋፆ እንዳለው አስረድተዋል።

@tikvahethiopia