TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የደህንነት ካሜራ በዩኒቨርሲቲዎች...

መንግስት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በደህንነት ካሜራዎችና በር ላይ በሚደረግ ጥብቅ ቁጥጥርና ፍተሸ እንዲታጀብ እንደሚያደርግ በዛሬው ዕለት አሳውቋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NEBE #SBSRADIO

SBS "በአገርኛ ሪፖርት" የኢትዮጵያ አገር አቀፍ ምርጫ ግንቦት 12 ይደረጋል ሲል ዘግቧል። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እንዲህ እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው፤ የምርጫው ቀን ገና አልታወቀም ሲል መረጃውን አጣጥሎታል። ያንብቡ👇

"ግንቦት 12 በኢትዮጵያ አገር አቀፍ ምርጫ ሊካሄድ ነው። ግንቦት 12, 2012 በኢትዮጵያ አገር አቀፍ ምርጫ ሊካሄድ መወሰኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አስታውቋል። የምርጫ ቦርድ ቀኑ እንደሁኔታው ሊሸጋሸግም እንደሚችል ከወዲሁ ፍንጭ ሰጥቷል። - (SBS RADIO)
.
.
"የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ" ቀጣዩ አገር አቀፍ ምርጫ የሚካሄድበትን ቀን አሳወቀ በሚል በተለያዩ ሚዲያዎች እየታየ ያለው ዘገባ ከእውነት የራቀ ሲሆን ቦርዱ አገራዊ ምርጫ የሚካሄድበትን ቀን እና ጊዜ ሰሌዳ አዘጋጅቶ ሲጨርስ የሚያሳውቅ ሲሆን ዜጎች ከቦርዱ ኦፌሴላዊ መግለጫ ውጪ የሚወጡ ሪፓርቶችን እና “ውስጥ አዋቂ መረጃዎችን” ችላ እንዲሉ ቦርዱ ያሳስባል፡፡"

(የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ)

@tikvahethiopia @tsegabwolde
ቀጣዩ ምርጫ የሚካሄድበትን ቀን አልታወቀም!

SBS.COM.AU

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀጣዩ አገር አቀፍ ምርጫ የሚካሄድበትን ቀን አሳወቀ በሚል በተለያዩ ሚዲያዎች እየታየ ያለው ዘገባ ከእውነት የራቀ ሲሆን ቦርዱ አገራዊ ምርጫ የሚካሄድበትን ቀን እና ጊዜ ሰሌዳ አዘጋጅቶ ሲጨርስ የሚያሳውቅ ይሆናል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከሰዓታት በፊት በትዊተር ገፁ አዲስ ፎርቹን ይዞት ለወጣው ዘገባ ምላሽ ሰጥቷል። ምርጫው የሚደረግበት ቀን እስካሁን አልታወቅምም ብሏል #misinformation

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የልዩ ሎተሪ ወጣ!

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የልዩ ሎተሪ ህዳር 29/2012 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዕድል አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ በህዝብ ፊት ወጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት የወጡት የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች እንደሚከተሉት ሆነዋል፦

1ኛ. 7,000,000 ብር የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ ቁጥር ------0465232

2ኛ. 3,000,000 ብር የሚያስገኘው የ2ኛ ዕጣ ቁጥር------0246073

3ኛ. 2,000,000 ብር የሚያስገኘው የ3ኛ ዕጣ ቁጥር -------1083734

4ኛ. 1,000,000 ብር የሚያስገኘው የ4ኛ ዕጣ ቁጥር ---------1143663

5ኛ. 500,000 ብር የሚያስገኘው የ5ኛ ዕጣ ቁጥር -------0376779

(ብሄራዊ ሎተሪ)

@tikvahethiopia
በቤኒሻንጉል ወደ  7 ሺህ ተማሪዎች ትምህርት አልጀመሩም ተባለ!

በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ 10 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እስካሁን ትምህርት አለመጀመራቸውን የዳንጉር ወረዳ አስተዳደር ገለፀ፡፡ 

የወረዳው ዋና አስዳዳር አቶ ካሳሁን ፎሊስ ትምህርት ቤቶቹ አገልግሎት መስጠት ያልጀመሩት በጸጥታ ስጋት ምክንያት መሆኑን አስታዉቀዋል። በዳንጉር ወረዳ ሁለት ትምህርት ቤቶች ባለፈው ዓመት በነበረው ግጭት እንደፈረሱም ታዉቋል።

የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል የሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ በበኩሉ በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ትምህርት እንዳይጀምር የሚያደርግ የፀጥታ ችግር የለም ማለቱም ተመልክቶአል።

ባለፈው ዓመት በፀጥታ ችግር ውስጥ የነበረው ዳንጉር ወረዳ 49 የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ያሉት ሲሆን ከነዚህም መካከል አስር ትምህርት ቤቶች እስካሁን የመማር ማስተማር ስራ አልጀመሩም ተብሏል፡፡

የዳንጉር ወረዳ አስተዳዳር አቶ ካሳሁን ፎሊስ በዘንድሮ ዓመት በዳንጉር 20ሺ  ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ መገኘት የነበረባቸው እስካሁን ግን 13ሺ ተማሪዎች ብቻ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ጠቁዋል፡፡

እስካሁን ትምህርት ካልጀመሩት 10 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል አምስት ትምህርት ቤቶች በፀጥታ ስጋት ምክንያት ወደ ስራ ያልገቡ ሲሆን ድልባንጂና ካራንቻች የየተባሉ ሁለት ትምህርት ቤቶች ደግሞ ባለፈው ዓመት በወረዳው በነበረው ግጭት እና አለመረጋጋት መፍረሳቸውን ተናግረዋል፡፡

አካባቢውን ለቆ ወደ ሌላ ስፍራ የሄዱ ነዋሪዎች መኖራቸውን ያመለከቱት የወረዳው አስተዳዳሪ በአንድ አንድ ትምህርት ቤቶች ደግሞ ነዋሪዎች ባለመኖራቸው ስራ ያልጀመሩ ናቸው ብለዋል፡፡

(የጀርመን ድምፅ ሬድዮ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አሳሳቢው የዩኒቨርሲቲዎች ጉዳይ... የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችን በፌደራል ፖሊስ ሊያስጠብቅ እንደሆነ ሰምታችኃል። ከሳምንታት በፊት በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች የጀመረው አለመረጋጋት አሁንም ድረስ ሙሉ በሙሉ ያልረገበበት፣ መደበኛው የትምህርት ስርዓትም የተቋረጠበት እንዳለ እየተመለከትን ነው። ቁጥራቸው ቀላል ያልሆኑ ተማሪዎችም ትምህርታችን ከህይወታችን አይበልጥም…
ከ5,000 በላይ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች (በተለይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጆች፣ መምህራን...) ቀደም ብለን ባነሳነው ሃሳብ ላይ አስተያየት እና ሀሳብ አቅርበዋል።

ሁሉንም የተላኩትን ሃሳብ ላቀርብላችሁ ባልችልም በዋነኝነት የተነሱት ግን እንዲህ ተጨምቀው ቀርበዋል፦

• አብዛኛው የቤተሰባችን አባል የሀገሪቱን መንግስት እጅግ በጣም ወቅሰዋል። የዩኒቨርሲቲ አስተዳደሮች በሚዲያ እየወጡ ምንም እንዳልተፈጠረ በግልፅ ችግሮች ቶሎ እንዳይፈታ እያደረጉ ነው። በዩኒቨርሲቲዎች ላይ የሚታይ ቸልተኝነት፣ እንዲሁም አንዳንድ አካላት የሚያሳዩት ወገንተንኝነት ዩኒቨርሲቲን ከሚያክል ትልቅ ተቋም የማይጠበቅ ነው። ተማሪ እስኪሞት፣ እስኪጎዳ፣ ግቢ እስኪለቅ ድረስ ተግባራዊ መፍትሄ አለመስጠት።

• ዘላቂው መፍትሄ ወንድም በወንድሙ ላይ እንዲነሳ እያደረጉ ያሉ አካላትን በመለየት እርምጃ መውሰድ። የተማሪውን ጥያቄ ማዳመጥ፣ ተማሪዎችን እርስ በእርስ ማቀራረብ፣ የግጭት አደገኝነቱን፣ እሳቱ ሁሉንም እንደሚያጠፋ ማስተማር ያስፈልጋል።

• በፌደራል ፖሊስ ጊዜያዊ ሰላም እና መረጋጋት ማምጣት ይቻላል ነገር ግን ዘላቂ መፍትሄ የሚመጣው የተማሪውን ድምፅ ሰምቶ ተማሪዎችን ማቀራረብ ሲቻል ብቻ ነው። ችግሮች የሚፈጠሩት፣ ማስፈራሪያዎች የሚለጠፉት፣ ተማሪዎች የሚጠቁት የፀጥታ አካላት በሌሉበት በየዶርሙ እና በየመፀዳጃ ቤቱ ስለሆነ የፌደራል ፖሊስ ይህን ሁሉ የመቆጣጠር አቅም የለውም። እውነተኛ እርቅ መኖር አለበት። ጥፋተኞች ተያዙ ብቻ ሳይሆን ምን እርምጃ ተወሰደባቸው የሚለውም በግልፅ መታወቅ አለበት።

• ዩኒቨርሲቲዎችን ከሚያስተዳደረው ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ጀምሮ፣ የዩኒቨርሲቲ አመራሮች ከላይ እስከ ታች ይፈተሹ፣ መምህራን፣ በግቢ ውስጥ ሆነው ፖለቲካ ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ ያላቸው አካላት ላይ ፍተሻ ሊደረግ ይገባል። የግቢ ጥበቃዎች እጅጉን ሊፈተሹ ይገባል። የክልል ልዩ ኃይሎች ወገንተኝነት ይታይባቸዋል፤ በግቢ ውስጥ መሆን የለባቸው ፌደራል ይግባ የሚለው ሃሳብ ተገቢ ነው።

• ዩኒቨርሲቲዎች ለዚህ ሁሉ ነገር ተጠያቂ ናቸው። የተባረሩ ተማሪዎች በግቢው እንዲቆዩ በማድረግ፣ የተለያዩ የግጭት ምልክቶች ሲታዩ ችግር ከመድረሱ በፊት ባለመከላከል፣ የዲሲፒልን እርምጃ ለመውሰድ ማመንታት፣ የግቢ ሰራተኞች በተማሪዎች መካከል ለሚፈጠሩ ችግሮች ተባባሪ መሆን፣ የውጭ አካላት ወደ ውስጥ እንዲገቡ ማድረግ፣ የፀጥታ ኃይሎች አልታዘዝንም በማለት ችግር ከተፈጠረ በኃላ ለማብረድ መሞከር ይታያል። ይህ መስተካከል አለበት።

• ቁጥሩ ቀላል የማይባል ሰው ተማሪዎች ለጊዜው ወደቤታቸው እንዲሄዱ ዩኒቨርሲቲዎች ችግራቸው እንዲፈቱ መክረዋል።

• በዩኒቨርሲቲዎች ጠንካራ ደህንነት አካላትን መፍጠር። እያንዳንዱን እንቅስቃሴ መከታተል። የተማሪዎች አደረጃጀቶችን ከወገንተኝነት በነፃ መልኩ ለመላው ተማሪ ደህንነት መጠበቅ እንዲሰሩ ማድረግ። በፀጥታ ላይ የሚሰሩ ተፅኖ ፈጣሪ ተማሪዎችን አነጋግሮ እንዲተባበሩ ማድረግ።

• የአካባቢውን ተማሪዎች በማደራጀት ከሌላ አካባቢ የሚመጡ ተማሪዎች ችግር እንዳይደርስባቸው እርሳቸው ከለላ ማድረግ። ወንድማዊነትን ማጠናከር።

• ችግር ፈጣሪዎች ጥቂት በመሆናቸው ለይቶ እንዲወጡ መስራት። የኔ ወገን ስለሆነ ወንጀለኛም ቢሆን ችግር የለውም የሚል አደገኛ አመለካከት እንዲቀየር መስራት።

• ከምንም በላይ በዩኒቨርሲቲ አካባቢ ያለው ማህበረሰብ ወሳኝ ነው። የዩኒቨርሲቲ መኖር ማህበረሱቡን እጅግ ይጠቅማልና ችግር የሚፈጥሩትን አካላት ለይቶ ለህግ ማቅረብ አለበት። በአንድ አካባቢ የሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ለማህበረሱ የሚሰጠው ጥቅም እንዲህ በቀላሉ የሚገለፅ አይደልም። ጥፋት አጥፍተው የሚታዩ ተማሪዎችን ማህበረሰቡ ለህግ አካላት ማስረከብ ይኖርበታል።

• የሀገሪቱ የደህንነት አካላት የዩኒቨርሲቲ ጉዳይ እልባት ካላገኘ ትልቅ ችግር እንደሚፈጠር በማወቅ በንቃት መከታተል አለባቸው። በማህበራዊ ሚዲያ ተማሪ የሚያነሳሱትን መከታተል አለባቸው።

• ለሰው ልጅ ዋናው ዳኛው ህሊና ነው። ስለዚህ ለተማሪዎች ቢያንስ የ15 ቀን ከፖለቲካ የፀዳ ስልጠና መስጠት ያስፈልጋል። የሁሉም መገኛ አደም እና ከግራ ጎኑ ደግሞ ሀዋን/አዳምና ሔዋን ናቸው። ስለዚህ ከልዩነታችን አንድነታችን ይበልጣል። ዘር፣ሀይማኖት፣ ብሔር ሊለያየን እንደማይገባ ተማሪውን ማሳመን።

• ጋዜጠኞች፣ ሚዲያዎች፣ አክቲቪስቶች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መምከር። አንድ ቦታ ጥፋት ሲፈፀም ዝም ይላሉ፣ የኔ ወገን ነው ብለው ሲያስቡ ይጮሃሉ፤ ይህ ትግል አይደለም መፍትሄም አያመጣም ሁሉም ለተማሪዎች በአንድ ላይ መጮህ አለበት። ወገንተኝነት ተማሪውን ስቃይ እያባባሰው ነው።

• ከባለድርሻ አካልት ጋር ወጣቱ ከሚሰማቸው አካላት ጋር ውይይት ማድረግ፣ ውይይቱ ከፖለቲካዊ ጉዳዮች የፀዳና ከወገንተኝነት የነፃ መሆን አለበት።

• የተፈጠረው አሳዛኝ ነገር ተፈጥሯል ነገር ግን እንዲህ መቀጠል ስለሌለብን ሁሉም ይቅርታ ተጠያይቆ እውነተኛ እና ከፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ የፀዳ እርቅ ሊፈፀም ይገባል። ህዝቡ የሚቀበላቸው፣ ወጣቱ የሚከተላቸው፣ በህዝቡ ክብር ያላቸው አካላት ስራቸውን መስራት አለባቸው ችግር ሲፈጠር ሃዘን ለመግለፅ ከመውጣት ይልቅ የተራራቁትን ማቀራረብ አለባቸው።

• እጅግ በሚያሳዝን መልኩ የተማሪ መታወቂያ እየታየ ከግቢያችን ውጡ የሚሉ አካላት የሚሰሩት ስራ ሀገርን ወደለየለት አደጋ ውስጥ እንደሚከት ነገ እሳቱ እነሱንም ሊያጠፋ እንደሚችል ማስተማር።

• ሀገር አስተዳዳሪዎች፣ ፖለቲከኞች፣ ተቃዋሚዎች፣ አክቲቪስቶች፣ በሙሉ ከመጠላለፍ፣ እርስ በእርስ ከመገፋፋት፣ አንዱ አንዱን ጎትቶ ከመጣል መቆጠብ፣ ወጣቱን ከጥላቻ እንዲርቅ መስራት አለባቸው። የሀገሪቱ ምኑም የማይጨበጥ የፖለቲካ ሁኔታው ትልቅ ችግር በወጣቶች መካከል እየፈጠረ ነው።

• ብሄራዊ እርቅ በእጅጉ ያስፈልጋል። ፖለቲካው በታመመበት ሁኔታ ይህን መሰል ችግር እየባሰ ሊሄድ ስለሚችል ችግሩ ወደ ሌሎች ስፍራዎችም ሊዛመት ስለሚችል ብሄራዊ እርቅ አስፈላጊ ነው። አመቱ ምርጫ የሚደረግበት ከመሆኑ አንፃር ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልጋል።

አስተያየት መስጫ👉@TikvahethiopiaBot

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ወላጆች ልጆቻቸውን በግል ትምህርት ቤቶች ለማስተማር እስከ 50,000 ብር እየተጠየቁ ነው!

የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የሚታየው የፀጥታ ስጋት ለግል ተቋማት ገበያ እና የሙስና በር ሆኗል። በሀገሪቱ ባሉ አንዳንድ የመንግስት ዩንቨርስቲዎች አልፎ አልፎ የሚነሳው ብሄር ተኮር ጥቃት እና አለመረጋጋት ወላጆች ላይ ስጋት በመደቀኑ በርካታ ወላጆች ልጆቻቸውን አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለማስገባት እንዳስገደዳቸው ካፒታል ጋዜጣ መታዘቡን በድረ ገፁ አስፍሯል።በዚህም የግል ተቋማት ገበያቸው በመድራቱ ለሙስና በር እየከፈተ መሆኑን፤ እና ልጆቻቸውን ለማስመዝገብ ወላጆች በአንዳንድ ተቋማት እስከ 50 ሺ ብር ጉቦ በደላሎች አማካኝነት እየተጠየቁ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

(ካፒታል ጋዜጣ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#NobelPeacePrize

ዶ/ር አብይ ኦስሎ....

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኖቤል ሽልማታቸውን ለመቀበል የኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሽልማታቸውን የሚቀበሉት ነገ ማክሰኞ ህዳር 30/2012 ዓ.ም ነው። ጠ/ሚሩ በዚሁ ጎዟቸው ወቅት ወደ ስዊድን ጎር ብለዋ ከሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ስቴፈን ሎቨን ጋር በሁለቱ ሀገሮች ግንኙነቶች ላይ ተነጋግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በኖርዌይ ኦስሎ ከኖቤል ኮሚቴ አባላት ጋር ተገናኝተዋል። #Norway #Oslo

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#NobelPeacePrize #AbiyAhemed

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የሰላም የኖቤል ሽልማታቸውን የሚቀበሉበት ሥነ ሥርዓት ነገ ማክሰኞ፤ ኅዳር 30 / 2012 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለጥያቄያችሁ መልስ!

ማስታወቂያዎችን ማስነገር የምትፈልጉ፦

1. የድርጅታችሁን ስም
2. የድርጅታችሁን ህጋዊነት የሚያረጋግጥ ማስረጃ
3. አድራሻ በ @tsegabtikvah ላይ ብቻ ላኩልን! አልያም በኢሜል [email protected] /0919743630/ መልሰን የማስታወቂያ ፓኬጁን እንልካለን!

ለቤተሰባችን የምናሰራጨው እጅግ ውስን ማስታወቂያዎች በመሆናቸው ለማስታውቂያ ደንቦች ተገዢ እንደምትሆኑ እናምናለን!

@tikvahethiopia
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል የዓይን ህክምና ማእከል አስገነባ!

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ከኦርቢስ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ያስገነባው የዓይን ህክምና ማእከል ተመርቆ ለአገልግሎት መብቃቱን ሆስፒታሉ ገለፀ። የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ሰላም አየለ በምረቃ ስንስርዓቱ ላይ እንዳሉት ማዕከሉ የተቋቋመው ከኦርቢስ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ነጻ የዐይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና አገልግሎትና ሌሎች ህክምናዎች ለመስጠት ነው። ሆሲፒታሉ ለተለያዩ የዐይን ህመሞች ህክምና ሲሰጥ የቆየ ቢሆንም የዐይን ቀዶ ህክምና አገልግሎት የሚፈልጉ ህሙማን ግን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ሲልክ መቆየቱን ጠቁመዋል።

(ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የወላይታ ዞን ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ ተቀመጧል። ጉባኤው፦

1.የወላይታ ብሄር የክልልነት ጥያቄ የደረሰበት ደረጃ ይገመግማል።

2.ቀጣይ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።

(ኦ ኤም ኤን)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaBot
#NobelPeacePrize #AbiyAhemed

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ትናንት ምሽት በኖርዌይ የኖቤል ተቋም የክብር እንግዳ መዝገብ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በክብር እንግዳ መዝገቡ ላይ በአማርኛ አስተያየታቸውን ያሰፈሩ የመጀመሪያው ሎሬት መሆናቸውን ከኖርዌይ የኖቤል ተቋም የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

(ኢቢሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም...

• አመራሩ ብሔሩን እየለየ የሚያገለግል ከሆነ አስቸጋሪ ነው። በእያንዳንዱ ክልል የተለያየ ብሔር ብሔረሰብ አለ። መንግሥት እኩል ካላገለገለ አድሎ ከተፈፀመ በአግባቡ አልተገለገልኩም የሚል ጥያቄ ያቀርባል።

• አንዱ ከአንዱ ጋር የሚገፋፋ ከሆነ አንድነት አይመጣም። ሰው ሲሞት ለምን ሞተ ከማለት ይልቅ የየትኛው ብሔር ተወላጅ ብዙ ሞተ እየተባለ ነው። ይህ ቀድሞ መሠራት የነበረበት ሥራ ባለመሥራቱ የመጣ ነው።

• ማንኛውም ሰው የራሱን ማንነት እንዲከበርለት የሚፈልግ ከሆነ የሌላውንም እኩል ማክበር አለበት። እዚህ ላይ ትልቅ ክፍተት ነበር።

• ስለብሔር ማሰብ ላይ ብቻ መተኮር የለበትም። አንዲት ትልቅ አገር መኖሯንም መዘንጋት የለበትም።

• አገርን ከመገንባት ለሌሎች ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች እኩል ክብር እና እውቅና መስጠት ያስፈልጋል።

• ብሔራዊ ማንነት ቢኖረንም ከአገራዊ ማንነት ውጭ መሆን አንችልም። እርስ በእርሳችን እንከባበር የምንለው አገራችንን ለመገንባት ነው።

• ትልቁ ችግር አገራዊ እና ብሔራዊ ማንነት ሚዛናቸውን ጠብቆ አለመሄዳቸው ነው። ለራስ ብሔር ብቻ ማሰብ ትርጉም የለውም።

More👇
https://telegra.ph/ETH-12-10

ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም (የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ)

(አዲስ ዘመን ጋዜጣ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
- ዓለም አቀፍ የወጣቶች ህብረት "IYF" የተሰኘ የኮሪያ በጎ ፈቃደኛ ቡድን የአስተሳሰብ ማቅኛ "ማይንድ ሴት" ስልጠና ከጋሞ ዞን ሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ለተወጣጡ ከ850 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች በትላንትናው እለት በአርባምንጭ ከተማ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MekelleUniversity

2 ኛው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ምሩቃን መድረክ "የአልሙናይ ተሳትፎ ለመቐለ ዩኒቨርሲቲ የላቀ ውጤት" በሚል መሪ ቃል ቅዳሜ ታህሳስ 4፣ 2012ዓ.ም በአዲስ አበባ ሃርመኒ ሆቴል ይካሄዳል። በመድረኩ ላይ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች እና የክብር እንግዶችን ጨምሮ ከ200 በላይ ታዳሚያን እንደሚገኙ ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሩዋንዳ የኢቦላ መከላከያ ክትባት መስጠት ጀመረች!

- ሩዋንዳ የኢቦላ በሽታን የሚገታ  የክትባት ዘመቻን ለመጀመሪያ ግዜ መስጠት ጀመረች። የአገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በዘመቻው ክትባቱ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሚዋሰኑ ቦታዎች ለ200 ሺ ሰዎች  ይሰጣል ብለዋል፡፡

የጤና ሰራተኞች፣ የኢሚግሬሽን ሰራተኞች፣ ፖሊሶች እና ድንበር ተሻጋሪ ንግድ ላይ ለተሰማሩት የህብረተሰብ  ክፍሎች ክትባቱ በቅድሚያ ይሰጣችዋል ተብሏል፡፡

በሩዋንዳ እስከ አሁን ምንም ዓይነት የኢቦላ በሽታ አለመታየቱ ቢገለጽም፤ በጎረቤት  ሀገር በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኢቦላ በሽታ ምክንያት ከባለፈው ነሃሴ ጀምሮ ከ2 ሺ 200 ሰዎች በላይ መሞታቸው ተገልጿል፡፡

በዚህ ምክንያትም ክትባቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠው በምስራቅ ዲሞክራቲክ ኮንጎ  በምትገኘው ጎማ  ሲሆን፤ እስከ አሁን ሩብ ሚሊዮን የሚሆኑ ኮንጎውያን ክትባቱ እንደተሠጣቸው የቢቢሲ ዘገባ ያሳያል።

(BBC)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#FerweyniMebrhatu #CNN

"ፍሬወይኒ መብራሃቱ በአውሮፓውያን አቆጣጠር የ2019 የሲ.ኤን.ኤን የዓመቱ ጀግና ተብላ በመጠራቷ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል። ሴት ልጆች በትምህርት ቤት እንዲቆዩ ያላት ቆራጥነት፣ እንዲሁም ማኅበረሰቧን የተሻለ ለማድረግ ያላት አቋም የሚደነቅ ነው። ኢትዮጵያ በፍሬወይኒ ኮርታለች።" ዶ/ር ዐብይ አህመድ (የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠ/ሚኒስትር)
.
.
"የእኛው ፍሬወይኒ CNN የ2019 ጀግና ሆነች!! እንኳን ደስ አለሽ! በተፈጥሯው ጉዳይ ለሚሸማቀቁ: ከትምህርታቸው ለሚስተጏጎሉ: ለሚያቋርጡ:ከሌላው በታች የሆኑ ለሚመስላቸው..የአገራችን ሴቶች ትልቅ ቀን ነው!ተባብረን ዘላቂ መፍትሄ እናምጣ!" ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ (የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳንት)

@tikvahethiopiaBot @tikavhethiopia
የስልክ ስክሪን ማጠንከሪያ ተብሎ አገልግሎት ላይ እየዋለ ያለው ፈሳሽ ዕውቅና የለውም ተባለ!

በየመንገዱ የስልክ ስክሪን ማጠንከሪያ ተብሎ አገልግሎት ላይ እየዋለ ስላለው ፈሳሽ የሚያውቀው ነገር አለመኖሩን የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለሥልጣን አስታወቀ።

ናኖ ቴክኖሎጂ ማለት ዘረፈ ብዙ ቴክኖሎጂዎችን በውስጡ የሚይዝ መሆኑም ተገልጿል። የሞባይል ስልክ ስክሪን ማጠንከሪያ ተብሎ ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው ፈሳሽ መፈተሽ እንዳለበት የባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አወቀ ሺፈራው ተናግረዋል።

በፍተሻውም ወቅት በስልክ ገጽ ላይ የሚቀባው ፈሳሽ ጨረራ አለው ወይስ የለውም፤ የጨረራ ይዘቱ ምን ያህል ነው የሚለው ፍተሻ እንደሚደረግበት ገልጸዋል።

በፍተሻው ውጤት መሠረት ጨረራ አመንጪ ከሆነ ደግሞ መጠኑ ከዚህ በላይ ከሆነ ጉዳት አለው፣ ከዚህ በታች ከሆነ ደግሞ ጉዳት የለውም የሚለውን በሳይንሳዊ ትንታኔ መሠረት መናገር ይቻላል፤ ይህ ባልታወቀበት ሁኔታ ግን ይህ ነው ብለን መናገር አንችልም በማለት አብራርተዋል። አያይዘውም፣ በተቋማችን አሠራር አንድ ጨረር አመንጪ ቁስ አካል ወደ አገር ውስጥ ሲገባ አስመጨዎቹ ያመጡትን ነገር ወደ ተቋማችን አምጥተው የማሳወቅ ግዴታ እንዳለባቸው ሕጉ ያስገድዳል።

https://telegra.ph/ETH-12-10-2

(ኢቲቪ)

@tikvahethiopiaBot @tikavhethiopia