TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Audio
AudioLab
የተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እንድሪስ መልዕክት ለወጣቶች፦

- የበላዩ የበታቹን ማወያየት አለበት፣ ማዳመጥ፣ መስማት ይገባል፡፡ ጥሩ ሀሳብ ከሆነ መከተል ነው፡፡ የበታቹ ደግሞ የበላዩን ሊያከብር ሊሰማ ይገባል፡፡ እስልምናው ይህንን ያዛል፡፡

- ጥቅም የሚገኘው ከአንድነት ነው፣ ጥቅም የሚገኘው ከሰላም ነው፣ ጥቅም የሚገኘው ከመከበር ነው፣ ጥቅም የሚገኘው ከመተባበር ከመረዳዳት ከመሰማማት ነው፡፡

- የሚጠቅመው መቀራረብ መመካከር መረዳዳት አላግባብ እንደሆነ መመለስ መጸጸት ወደፊት አንድነቱን ማጠንከር ሰላሙን ማጎልበት ማጠንከር ነው፡፡

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ
@tikvahetiopia @tsegabwolde
"በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዘላቂ ሰላምን መገንባት!" በሚል ርዕስ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከኢንሼቲቭ አፍሪካ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው መርኃግብር ነገ በUNECA መሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ በኮንፍረንሱ ላይ የሁሉም የዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንቶች፣ የተማሪዎች ህብረት ተወካዮችና የሰላም ፎረም አባላት ይገኙበታል፡፡ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦችም ባለፈው ዓመት በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ባካሄዱት "የጥላቻ ንግግር እናቁም!" ዘመቻ ምክንያት በዚህ ስብሰባ ላይ የሚገኙ ይሆናል፡፡

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ
@tikvahethiopia @tsegabwolde
ምንም ሁኔታዎች ባይመቹም ከበጎነት ወደኋላ የሚመልሰን ነገር አይኖርም!

#ቅዳሜን_ደሜን_ለወገኔ

ዶ/ር ሜላት ሰለሞን እባላለሁ፡፡ እኔ O+ በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሽ ነኝ። ለ9ነኛ ጊዜ ደም ለግሻለሁ። ደም በመለገስ ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ህይወትማዳን እንደሚቻል ተረድቻለሁ፡፡ ደም በመለገስ የሚያገኙትን የደስታ ጥግ የትም ፣ ምንም ላይ አያገኙትም ! ደም መለገስ ከየትኛውም ደግነት፣ ከየትኛውም ሩህ ሩህነት ይልቃል፡፡ዛሬ ጥቅምት 15 በሚደረገው የደም ልገሳ ላይ ይሳተፉ!

እርሶስ ደም ለግሰዋል?

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ
@tikvahethiopia @tsegabwolde
“ሁላችንም አንድ እንሁን፣ #ሰላም እናስፍን፣ ከእንደዚህ አይነቱና አላህ ከማይወደው ተግባር እንራቅ፣ እስላም ክርስቲያኑ ሁሉ በአንድ ሆነን አገራችንን እናልማ፣ ሰላም እንፍጠር፣ ከመተላለቅ እንዳን። እባካችሁ ሁላችንም ለአላህ ብለን ከዚህ ተግባር እንቆጠብ...ሰላም ማጣታችን ያሳዝናል። ፍቅር ማጣታችን ያሳዝናል። ኡለማዎችንን ማስለቀሳችን ያሳዝናል። አንድነት ማጣታችን ያሳዝናል። አሁን #አንድ_ሆነን_ቆራጥ ሆነን ልንነሳ ይገባል። አንድ እንሁን፤ የከተማውም የገጠሩም እስላም እና ክርስቲያኑም አንድ እንሁን። አንድ ሆነን ቆራጥ ሆነን እንነሳ። እውነቱም ይታወቃል፤ ውሸቱም ይታወቃል። ለእውነት እንድትሰሩ አሳስባለሁ። አደራም እላለሁ። አሚን።” ሀጂ ኡመር ሙፍቲ (ኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) ፕሬዚዳንት )

#share #ሼር

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Vote!

ፍሬወይኒ መብራቶም የ2019 CNN Hero ምርጥ አስር ውስጥ ገብታለች፡፡ ለዚህም የበቃችው የሚታጠብና መልሶ ጥቅም ላይ መዋል የሚችል የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ (ሞዲየስ) በመስራቷና ሴቶች ተማሪዎች ተፈጥሯዊ በሆነው የወር አበባ ምክንያት ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ በምትሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዋ ነው፡፡ እንደ ዩኒሴፍ ጥናት በኢትዮጵያ ከ10 ሴቶች አንዷ በዚህ ምክንያት ትምህርቷን ታቋርጣለች፡፡ ፍሬወይኒ ይህንን ውድድር ካሸነፈች 100,000 የአሜሪካን ዶላር አሸናፊ ትሆናለች፡፡

ምረጧት 👉 https://edition.cnn.com/SPECIALS/cnn.heroes/vote/10/

የድምጽ አሰጣጥ ሂደት:
1. ሊንኩን (ማስፈንጠሪያውን) መጫን። ከተጫን ነው ቡሃላ ውደድ የCNN የአመቱ 10 ጀግኖች ዝርዝር እንግርባለን ከዛ የፍሬወይን መብራቶም ስምችና ፎቶዋ ዜግነት Ethiopian የሚል ፈልገን እንጫናለኝ።
2. የሷን ፎቶ ከተጫንን ቡሃላ ዝቅ ብለን ከሷ ፎቶ በታች 1 or 0 ቁጥር ይኖራል vote ከሚለው በላይ slide for more ከሚለው በታች የለቸውን መሳቢያ ወደቀኝ በመሳብ 10 ድምጽ መስጠት ይችላሉ።
3. Vote የሚለውን ከተጫንን ቡሃላ email or fb account ያለን ብቻ ነው የምን መርጠው ከላይ አንብባቿል ዲስኮርሱን የሚል ሲመጣ ማንበብ ወይም አንቢብያለሁ ማለት ከዛ account ይጠይቀናል እናስገባና ማረጋገጫውን እንጫን ከዛ አበቃ።

ማሳሰቢያ:- ሁሉም ሰው በየቀኑ 10 ድምጽ መስጠት ይችላል። ማብቂያው ህዳር 21 ነው፡፡

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ(@tikvahethmagazine)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#CONGRATULATIONS

በአሁን ሰዓት "ጎንደር ዩኒቨርስቲ" የህክምና ተማሪዎቹን በደማቅ ሁኔታ እያስመረቀ ይገኛል፡፡ በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የተማሪ ወላጆች፣ የዩኒቨርሲቲው አመራሮችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine
በዜሮ ዓመት የወጣ ክፍት የስራ ማስታወቂያ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሐብት ልማት ቢሮ ለ2010 እና 2011 ተመራቂዎች 5095 ክፍት ቦታዎችን አውጥቷል፡፡

• በ2010 እና 2011 ዓ.ም የተመረቃችሁና ከታች መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች

• አንድ ሰው መመዝገብ የሚችለው ለአንድ የስራ መደብ ብቻ ይሆናል፡፡

• የአዲስ አበባ የነዋሪነት መታወቂያ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡

#ቲክቫህ_ጥቆማ
@tikvahethmagazine @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኡቡንቱ #አርባምንጭ #ሃይሌሪዞርት የ"ኡቡንቱ አርባ ምንጭ" የማጠቃለያ መርሃ ግብር በአሁን ሰዓት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የጋሞ አባቶች፣ የአርባ ምንጭ ከተማ ወጣቶች፣ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተገኙበት በሃይሌ ሪዞርት እየተካሄደ ይገኛል። "በምክንያት የሚያምን ሚዛናዊ በሆነ ትውልድ መካከል የሚፈጠር የሃሳብ ልዩነት የጥንካሬ ምንጭ እንጂ የጠብ መነሻ አይሆንም!" "እኛ ወንድምና…
#አርባምንጭ #ሃይሌሪዞርት #ቲክቫህ #ፒስሞዴል

የኡቡንቱ የማጠቃለያ ፕሮግራም በሀገራችን ብሔራዊ መዝሙር የተጀመረ ሲሆን የጋሞ ዞን አስተዳደር ተወካይ አቶ እሸቱ አልቶ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።

በዚሁ ንግግራቸው ወቅት የዝግጅቱ አስተባባሪዎች በሙሉ ወጣቶች መሆናቸው መርኃግብሩን ለየት እንደሚያደርገው ገልፀዋል፡፡ አቶ እሸቱ አክለውም 500,000 ቤተሰቦችን ስለ ፍቅር እና አንድነት ብቻ እየሰበከ ላሰባሰበን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የቴሌግራም ቻናል ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ቀጥሎም የኃይማኖት አባቶች፣የጋሞ አባቶች መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡ በተለይ ለወጣቱ ባስተላለፉት መልዕክት፦ እርስ በእርስ መከባበር እና ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርን ማስቀደም እንደሚገባ አበክረው ገልፀዋል፡፡

አሁን "ስለ እርቅ ለመወያየትና ለማስታረቅ እድሜ ምክንያት ሊሆን ይችላልን?" በሚል ርዕስ ወጣቱም ስለ ዕርቅ፣ ስለ ሰላም የበኩሉን እንዲወጣ በፈጣሪ አሰፋ አማካኝነት ምክክር እየተደረገ ይገኛል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ኡቡንቱ #አርባምንጭ #ቲክቫህ #ፒስሞዴል

በዛሬው የውይይት ዝግጅት ላይ በስፋት ከተነሱት ሀሳቦች መካከል ሰው በሰውነቱ፡ብቻ ሊከበር እንደሚገባውና ሰላምን የሚያስቀድም ትውልድ ለመገንባት ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡ በውይይቱ የተሳተፉ ወጣቶች ደግሞ የጋሞ አባቶች ሰላም ወዳድነት ከአንድም ሁለት ጊዜ በተግባር የተገለጠ መሆኑን ጠቅሰው እንዲህ በአንድ መድረክ ስለ ሰላም አብረው መምከራቸው ትልቅ ትምህርት እንደሚሰጣቸው አንስተዋል፡፡ በአጠቃላይ ከውይይቱ በኀላ ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዘው ስለ ሁሉም ሰው ልጆች ክብር የድርሻቸውን ለመወጣትና ይህን ለማድረግ እድሜ እንደማይገድበው በማመን የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት ሁሉ ለመወጣት ቃል ገብተዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዛሬው መርኃ ግብራችን ላይ ታዳጊ ህጻናት እንዲህ በማለት መልዕክታቸውን አቅርበዋል፡-

"እኛ ህጻናት የእናንተው ልጆች ነን ለሀገራችንም ተምረን ተስፋ የምንሆናት ትውልዶች እኛ ነን፡፡ በፍቅር አድገን ወላጆቻችንንና ሀገራችንን ማገዝ እንመኛለን፡፡"

"እኛ ህጻናት ፍቅር ያስፈልገናል፡፡ የወደፊት የሀገራችን ተስፋዎች እኛ ነንና ታላላቆቻችን ፍቅር ልታስተምሩን ይገባል"

"መልካምነትን የምንማረው ከታላላቆቻችን ነውና እባካችሁ መልካምነትን በተግባር አስተምሩን"

"አባቶቻችን ትላንት እርጥብ ሳር ይዘው ለሰው ልጅ እንዴት ክብር መስጠት እንዳለብን አስተምረውናልና እኛ ህጻናት ከልባችን እናመሰግናቸዋለን"

ይህንን መልዕክት በኮልታፋ አንደበታቸው ካቀረቡ በኀላ በትህትና ዝቅ ብለው የአባቶችን ጉልበት ስመዋል አባቶችም ህጻናቱን መርቀው የሰላም ምልክት የሆነውን ነጭ ባንዲራ አበርክተውላቸው ልጆቻቸው በሰላም እንዲኖሩ በሙሉ አቅማቸው ለሰው ልጅ ክብርና ለሰላም እንደሚተጉ ቃል ገብተውላቸዋል፡፡

#ጋሞዞን #አርባምንጭ #ቲክቫህ #ፒስሞዴል #ሃይሌሪዞርት

@tikvahethiopia @tsegabwolde
የተማሪዎች እገታ ጉዳይ...

- የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ከአምስት ቀናት በፊት ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፤ "አራት ተማሪዎች ታግተው እንደሚገኙ መረጃው አለኝ" ማለታቸው ይታወሳል።

- EBCን ጨምሮ የተለያዩ የግል ሚዲያዎች የታገቱ ተማሪዎች 17 እንደሆኑ ዘግበው ነበር። የተለያዩ የማህበረሰብ አንቂዎችም የተማሪዎችን ስም እና ፎቶ ጭምር በመዘርዘር የታገቱ 17 እንደሆኑ ሲገልፁ ነበር።

- የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ በምዕራብ ኦሮሚያ ስላለው ጠቅላላ ሁኔታ "ምንም አይነት መረጃ የለኝም። እኔ የሰማሁት ነገር የለም" ብለዋል። እንዴት መረጃ ሳይኖራቸው እንደቀረ ከቢቢሲ የተጠየቁት ኮሎኔል ገረሱ፤ "እኔ ምንም አልሰማሁም ነው የምልህ። ለምድነው የምትጠይቀኝ?" በማለት መልሰዋል።

- የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዴሬሳ ተረፈ በበኩላቸው ታፍነው የተወሰዱ ተማሪዎች የሉም ብለዋል። ኃላፊው ታፍኖ የተወሰደ ተማሪ የለም ከማለት ውጪ ማብራሪያ አልሰጡም።

- ትላንት የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የፕሬስ ሴክሬተርያት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ታግተው የነበሩ 21 የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መንግስት ባደረገው ጥረት ተለቀዋል። 13 ሴትና 8 ወንድ በድምሩ 21 ተማሪዎች በሰላማዊ ሁኔታ ተለቀዋል። ይሁን እንጂ አሁንም ቀሪ 6 ተማሪዎች በእገታ ላይ መሆናቸውን በአካባቢው የተሰማራው የፀጥታ ኃይል መረጃ ሰጥቷል ሲሉ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው ተናግረዋል።

- ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ትላንት ምሽት 4 ሰዓት ወደ ታገቱ ተማሪዎች ወላጆች እንደደወሉና ወላጆችም ስለልጆቻቸው መለቀቅ መረጃ እንደሌላቸው እንደገለፁላቸው በትዊተር ገፃቸው ገልፀዋል።

- VOA : “ልጆቻችን ስለመለቀቃቸው ያወቅነው ነገር የለም” - ቤተሰቦች

#ቲክቫህ
TIKVAH-ETHIOPIA
የቲክቫህ ነቀምት ቤተሰብ... ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በአንድ መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት ውስጥ የሚሰራ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባልን ከነቀምት ከተማ አነጋግረን ነበር። ይኸው የቤተሰባችን አባል ለስራ ጉዳይ ወደ ወለጋ አካባቢ ከሄደ ቀናት ተቆጥረዋል፤ በደህንነት ስጋት ሳቢያ ወደኃላ ለመመለስ ቢፈልግም አልቻለም። ነቀምት አካባቢ ሆኖ የታዘበውን አጋርቶናል፤ እኛም አጠር አድርገን ለናተ እናጋራለን። …
የቲክቫህ ቤተሰብ ከነቀምት...

በአሁን ሰዓት በነቀምት ከተማ የሚገኝ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ከቀናት በፊት በስልክ ደውሎ ያለውን ሁኔታ አስረድቶን ነበር። ይህ የቤተሰባችን አባል በአንድ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም ውስጥ እንደሚሰራ ገልፆልናል። ኢንተርኔት በመቋረጡም ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ከቲክቫህ እንደራቀ አሳውቆናል።

- ከሳምንታት በፊት አንድ ባለስልጣን በታጣቂዎች ከተገደለ በኃላ በፀጥታ ችግር ምክንያት ፍቃድ ጠይቄ ነው የወጣሁት፤ ከበዓል መልስ ደግሞ ወደ ስራ መግባት አልቻልኩም። የምስራው ከነቀምት 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ነው።

- ኢንተርኔትን በተመለከተ ምንም ፍንጭ የለም። WiFiም የሞባይል ዳታ የለም አይሰራም። ከነቀምት ሆስፒታል ማዶ ኢንተርኔት ብቻ ሳይሆን የሞባይል ኔትዎርክ ሙሉ በሙሉ ይጠፋል።

- አሁን ያለሁት ነቀምት ከተማ ነው። እኛ እንደሰማነው የመንግስት ፀጥታ ኃይሎችና ታጣቂዎች ግጭት ውስጥ እንደሚገኙ ነው። ብዙ ሂሊኮፍተሮች ሲመላለሱ እንደነበርም አስተውለናል።

- ምሽት ላይ በነቀምት ከተማ በኮማንድ ፖስት የሠዓት እላፊ ስለታወጀ ከምሽት 1:00 በኃላ መንቀሳሳቀስ አይቻልም። ምሽት ላይ የድርጅት መኪኖቻችን አይንቀሳቀሱም። የፀጥታው ሁኔታ አስተማማኝ አይመስልም።

- አሁን ላይ ነቀምት ከተማ ውስጥ ይህ ነው የምንለው የተኩስ ልውውጥ የለም። ከበዓል በፊት ግን አልፎ አልፎ የተኩስ ልውውጦችን እንሰማ ነበር። በግልፅ ማን ከማን ጋር እንደሚታኮስ አናውቅም።

- በነቀምት ከተማ የንግድ እንቅስቃሴው እንደድሮው አይደለም፤ ተቀዛቅዟል። የትራንስፖርት ፍሰቱም እንደድሮው አይደለም። ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት እና ፕሮጀክት ጨርሰው የወጡ ጓደኞቻችን አሉ።

#ቲክቫህ
#Election2012

ዛሬ ምርጫ ቦርድ በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ መሰረት በተዘጋጁ መመሪያዎች ላይ ከሚዲያ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል፡፡

ውይይት የሚደረግባቸው መመሪያዎች፡-

- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመገናኛ ብዙሃን እና የጋዜጠኞች የምርጫ አዘጋገብ የስነምግባር እና አሰራር መመሪያና፣

- የስነ ዜጋ እና የመራጮች ትምህርት ፈቃድ አሰጣጥ እና ስነ-ምግባር ለመደንገግ የወጣ መመሪያ ላይ ይሆናል፡፡

የመገናኛ ብዙሃንን የሚመለከተው መመሪያ በመሰረታዊነት የሚዲያዎች የምርጫ አዘጋገብ፣ ፍቃድ አሰጣጥ፣ ፍትሀዊ የአየር ሰዓት ክፍፍል እንዲሁም ሊከተሏቸው የሚገቡ የስነ ምግባር ደንቦችን ያካተተ ሲሆን የስነ ዜጋና የምርጫ ትምህርቱን የሚመለከተው መመሪያ በበኩሉ የስነ-ዜጋ ትምህርቱን የሚሰጡ የሲቪክ ማህበራትን ፈቃድ ስለመስጠትና ሊኖሯቸው የሚያስፈልጉ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል፡፡ በፕሮግራሙ መሰረት በሁለቱ መመሪያዎች ዙሪያ በዶ/ር ጌታቸው አሰፋ እና በትርሓስ ገ/እግዚአብሔር ማብራሪያ ከተሰጠ በኀላ በተሳታፊዎች በሚደረግ ውይይት ከሚገኘው ግብዓት ማጠቃለያ ተሰጥቶና አቅጣጫ ተቀምጦ ይጠናቀቃል፡፡

#ቲክቫህ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ለፍቅር እንሩጥ ጥላቻን እናምልጥ"

40 ሺ ሰው የሚሳተፍበት የአምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫና ፌስቲቫል የካቲት 15 ይካሄዳል፡፡ በዚህ ዝግጅት ላይም በዓለም ክብረ-ወሰን የሚመዘገብ ሰፊ እንጀራ ተጋግሮ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የፓለቲካ መሪዎች፣ አርቲስቶችና ታዋቂ ግለሰቦች አብረው ይቆርሳሉ፡፡

የቲሸርት ኩፖኖቹን በአሞሌ ኦላይን ላይና በሁሉም የዳሽን ባንክ ቅርንጫፎች በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡ አዘጋጆቹ ለቲክቫህ ቤተሰቦች የቲሸርት ዋጋውን ቀንሰው በ150 ብር አቅርበውልናል፡፡ በዚህ እድል መጠቀም የምትፈልጉ ቤተሰቦቻችን የምዝገባ ሊንኩን ተጠቅማችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡

https://forms.gle/H3R8nxTamrMPyieN7

#ቲክቫህ_ኢቨንት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SolveITAccelerator

5 ሚሊዮን ብር ለሥራ ጀማሪዎች ማጠናከሪያ!

iCog labs,JICA ከኩዱ ቬንቸር በተገኘው የ5,000,000 ብር [አምስት ሚሊዮን ብር] የገንዘብ ድጋፍ ሥራ ላይ ያሉ እና ምርትና አገልግሎታቸውን ማሳደግ ለሚፈልጉ እንዲሁም በቴክኖሎጂ ላይ ለተሰማሩ ሰባት ድርጅቶች የአቅም ማበልጸግ ፣ የገበያ ትስስር መፍጠር እና በትንሹ 250,000 ብር ከፍ ካለ እንደ ፕሮጀክቱ ታይቶ የሚጨመር ድጋፍ ለመስጠት ጀምሯል።

የፕሮጀክቱ ማናጀር የሆኑት አቶ ህሩይ ፀጋዬ እንደገለጹት ሥራ ጀማሪዎቹ ከፕሮግራሙ ጋር በሚኖራቸው ቆይታ ማርኬቲንግ እና ቢዝነስ ፕላናቸውን ይበልጥ እንዲያሻሽሉ የሚደረግ ይሆናል።

ከ7ቱ ፕሮጀክቶች መካከል 5ቱን በመውሰድ 10 ቀን የሚቆይ የውጭ ሀገር ልምድ ልውውጥ እና የሚያስፈልጋቸው የገንዘብ ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ገበያው እንዲገቡ ይደረጋል ብለዋል፡፡

"ይህንን መሰሉን ሥራ ስንሰራ በዋናነት ማወቅ የምንፈልገው የቴክኖሎጂው ዘርፍ በኢትዮጵያ ምን አይነት ደረጃ ላይ ደርሷል የሚለውን ነው" ያሉት አቶ ህሩይ "የወጣቱን አቅም ማጎልበትና ትርፋማ ማድረግም ሌላው ትኩረት የምንሰጠው ጉዳይ ነው" ብለዋል፡፡

በዚህ ስራ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ፣ የከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲና ጥቃቅ እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ በአጋርነት ይሰራሉ ተብሏል፡፡

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Mekelle

ከቀናት በፊት በመንግስት ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር የተፈቱት የቀድሞው የኢንሳ ም/ዳይሬክተር ሌተናል ኮሎኔል ቢንያም ተወልደ እንዲሁም ዩኩኖኣምላክ ተስፋይ ዛሬ መቐለ ሲገቡ በመቐለ ነዋሪዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

#ቲክቫህ_ቤተሰቦች_መቐለ

PHOTO : BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrMengistuBekele

በኦሮሚያ ክልል ትላንት ግንቦት 22/2012 እና ዛሬ ግንቦት 23/2012 በቫይረሱ መያዛቸው ስለተረጋገጠው ሰዎች የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መንግስቱ በቀለ ተጨማሪ መረጃዎችን አካፍለውናል።

ትላንት በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ 22 ሰዎች ፦

- በኮቪድ-19 መያዛቸው ከተረጋገጠ 22 ሰዎች መካከል ሃያዎቹ (20) የኢትዮ-ጅቢቲ መስመር ላይ የሚሰሩ አሽከርካሪዎች ናቸው።

- ከሃያ ሁለቱ (22) ሰዎች አስራ ስምንቱ (18) የተገኙት አንድ ቦታ ነው። የተቀሩት መተሃራ ላይ በተደረገ ምርመራ የተገኙ ናቸው።

- የውጭ ሀገር ጉዞ ያላቸው 20 ናቸው። ሁለት ሰዎች ደግሞ ከማህበረሰቡ የተገኙ ናቸው፤ ከሁለቱ አንደኛዋ ሴት ከምዕራብ ሸዋ ጊንደ በረት ወረዳ ነው በቫይረሱ መያዟ የተረጋገጠው።

አንድ ቦታ እንደተገኙ ከላይ የገለፅናቸው 18 ሰዎች ለዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ (ምዕራብ ሸዋ ዞን) የሚሰሩ አሽከርካሪዎች ናቸው።

የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ቦታው ድረስ ሄዶ ከወሰዳቸው ናሙናዎች መካከል ነው የተገኙት። ግለሰቦቹ ምንም እንኳን ለዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ስራዎችን ቢሰሩም የድርጅቱ #ተቀጣሪ ሰራተኞች አይደሉም።

ዛሬ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ 5 ሰዎች፦

ሶስቱ (3) ከሱሉልታ ናቸው፤ እነዚህ ግለሰቦች ለህክምና አገልግሎት በመጡበት ናሙናቸው ተወስዶ ሲመረመሩ ነው በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

አንደኛው ከሰንዳፋ ሲሆኑ እኚህ ግለሰብ ሆስፒታል ውስጥ ተኝተው እየታከሙ የሚገኙ ናቸው፤ ናሙናቸው ተወስዶ ሲመረመር ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

አንደኛው የገላን ነዋሪ ሲሆን የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያለው ነው። መተሃራ ላይ ነው ናሙናው የተወሰደው በምርመራ ውጤት መሰረት በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል።

#ቲክቫህ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የ12ኛ ክፍል ፈተና መሰጠት ተጀመረ።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከዛሬ ጥቅምት 29 ጀምሮ መሰጠት ተጀምሯል።

ፈተናው ኅዳር 02/2014 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

በዛሬ ጥዋት የፈተና መርሃ ግብር መሰረት የእንግሊዘኛ ፈተና እየተሰጠ ይገኛል።

በጸጥታ ችግር ምክንያት በመጀመሪያው ዙር ፈተናው በማይሰጥባቸው አካባቢዎች ፈተናው በሁለተኛ ዙር ለመስጠት እቅድ ተይዟል።

በ131 የፈተና ጣቢያዎች በጠቅላላው 36 ሺህ 340 ተማሪዎች ለብሔራዊ ፈተናው በመጀመሪያ ዙር አይቀመጡም።

ዛሬ ለሀገር አቀፍ ፈተና የተቀመጡ ተማሪዎች በሙሉ መልካም ፈተና እንዲሆን እየተመኘን ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ከፈተናው ጋር ተያይዞ በማህበራዊ ሚዲያ ከሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች እንድትጠነቀቁ አደራ እንላለን።

ለሚመለከተው አካል ፦ ፈተናው ገና ከመጀመሩ ከፈተና ክፍል ውስጥ የተነሱ የፈተናውን ጥያቄ የያዙ ፎቶዎች በማህበራዊ ሚዲያ በተለይ ደግሞ ቴሌግራም ላይ እየተዘዋወረ መሆኑን መመልከት ችለናል።

ይህ ትውልድ ገዳይ አገደኛ ድርጊት ፌስቡክ ላይም እየተፈፀመ ነው፤ ድርጊቱ ለዓመታት የለፉ ተማሪዎች ድካም ከንቱ የሚያስቀር በመሆኑ እጅግ አስቸኳይ መፍትሄ ይሰጠው (ሶሻል ሚዲያውን መዝጋት)

ለአክቲቪስቶች እና ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ፦ ተማሪዎች የዓመታት ድካማቸው ከንቱ እንዲሆን ለማድረግ ፎቶዎችን እየለጠፋችሁ የምትገኙ አካላት በተለይ አክቲቪስት ነን ምትሉ ምንም የማያውቁ ተማሪዎችን ህይወት ከፖለቲካ ጋር በማገናኘት የግል አላማን ለማሳካት ሚደረግ ተግባር ፍፁም ስነምግባር የጎደለ ተግባር መሆኑን በመረዳት ከድርጊታችሁ ልትቆጠቡ ይገባል።

የፖለቲካ ጉዳይን ከተማሪዎች ህይወት ጋር በማገናኘት ትውልድ አትግደሉ።

አጠቃላይ የማህበራዊ ሚዲያ ጉዳይ እጅግ አስቸኳይ መፍትሄ ይፈልጋል።

#ቲክቫህ

@tikvahethiopia
#ኮኮሜሎን

ካለፈው የታሕሳስ ወር አንስቶ በተለያዩ የውጭ ሀገራት ያሉ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እና የግብረሰዶማውያን እንቅስቃሴን የሚቃወሙ አካላት "ኔትፍሊክስ" እንዳይታይ የአድማ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።

"ኔትፍሊክስ" ላይ የአድማ ጥሪ እያደረጉ ያሉት ባለፈው ዓመት (እኤአ) መጨረሻ ለእይታ በበቃ በአንድ የልጆች ፊልም ላይ #ግብረሰዶምን ለማስፋፋት ዓላማ ያለው ትዕይንት አለበት በሚል ነው።

ኮኮሜሎን ሌን (CoComelon Lane) በተሰኘው የልጆች ፊልም ኢፒሶድ ላይ አንድ ህፃን ልጅ የዳንሰኛ አጭር ቀሚስ ለብሶ ሲጨፍር መታየቱ ከፍተኛ ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን ተቺዎች ይህ የተደረገበትን መንገድ "መጥፎና ሰይጣናዊ" ሲሉ ነው የገለጹት።

CoComelon lane ለልጆች የተሰራ የNetflix ተከታታይ ፊልም ነው። በኃላም ከ1 ወር በፊት በዩትዩብ ላይ ተጭሮ በሚሊዮኖች ታይቷል።

በዚሁ ፊልም በሲዝን 1፤ ኢፒሶድ 8 ላይ አንድ ኒኮ የተባለ ህፃን ልጅ (2 አባቶች እንዳሉት ተደርጎ የተገለፀ-ይህ ግብረሰዶማውያን አባቶች እንዳሉት የሚያሳይ ተደርጎ ተወስዷል) ከቤተሰቦቹ ጋር ለሚነሳው ፎቶ ምን መልበስ እንዳለበት ለመወሰን ተቸግሮ ይታያል።

በዚህም ወቅት የኒኮ አባቶች ተደርገው የተሳሉት ሁለቱ ገፀባህርያት " ስለ አንተ የምናውቀው ነገር ቢኖር ተነስተህ መደነስ እንደምትወድ ነው " እያሉ ይዘፍናሉ።

ከዚያም ኒኮ የዳንሰኛ አጭር ቀሚስ ለብሶ እና ዘውድ ከአናቱ ላይ አድርጎ መደነስ ይጀምራል።

የኒኮ አባት ተብሎ ከተገለፁት አንዱ፤ " ምን መምረጥ እንዳለብህ እርግጠኛ ካልሆንክ ማድረግ የምትፈልጋቸውን ነገሮች ሁሉ አስብ። አንተ እራስህን ብቻ ሁን " እያለ ይዘፍንለታል።

ከዚያም ኒኮ "እኔ ራሴን ብቻ ልሁን?" ብሎ ይጠይቃል ካዛም አባት ተብየው ገፀባህሪ " አዎ! " ሲል ይመልስለታል።

ይህ ንግግር ህፃኑ ልጅ "የማንም ተፅእኖ ሳይኖርብህ #በፈለከው_መንገድ እራስህን ሁን" የሚል ይዘት ያለው መልዕክት ለማስተላለፍ እንደሆነ ጉዳዩ ያሳሰባቸው ተቆርቋሪች ይገልጻሉ።

ትዕይቱን "ጥፎና ሰይጣናዊ" ሲሉም ገልጸው ዋነኛው አላማው ህፃናትን ማበላሸት፣ ምንም በማያውቁ ህፃናት ላይ ግብረሰዶምን ማስፋፋት ነው ብለዋል።

የግብረሰዶማውያን እንቅስቃሴና ሰዎቹን አጥብቀው የሚያወግዙት እነዚህ ተቆርቃሪዎች፤ "ትዕይንቱ ህፃናት በለጋ እድሜያቸው ስለግብረሰዶም እና ስለፆታ ማስቀየር "እንዲዘጋጁ" እያደረገ የሚሄድ ነው ብለውታል።

በዚህ ምክንያት ይህንን ለህፃናት እንዲታይ እያሰራጨው "ኔትፍሊክስ"ን ሰዎች እንዳያዩ የአድማ ጥሪ እያቀረቡ ናቸው።

ምንም እንኳን ፊልሙ በህዳር ወር ውስጥ የወጣ ቢሆን ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ተቆርቋሪዎች ወላጆች ልጆቻቸውን ከመሰል አደገኛ ይዘት ካላቸው መልዕክቶች እንዲጠብቁ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።

ይህ "CoComelon" የተባለውና ለህፃናት በተለያዩ ርዕሶች እየተዘጋጀ የሚቀርበው ካርቱን ፊልም በዓለም አቅፍ ደረጃ ብዙ እይታ ያለው ነው። ብዙ ወላጆችም ለልጆቻቸው ይከፍቱላቸዋል።

ወላጆች ዘመኑ ያለበትን ሁኔታ በመረዳት ልጆች እንዲያዩ የሚያደርጉትን ማንኛውንም ነገር በቅድሚያ መገምገም፣ ጥሩነው መጥፎ፣ ከጀርባ ምን ይዟል የሚለው መመርመር አለባቸው። ዝም ብሎ ልጅ ስላስቸገረ ስልክ መስጠትንም ተገቢ አይደለም።

ከዚህ ባለፈ ልጆች በሃይማኖት ተኮትኩተው ፣ የማህበረሰቡን ባህል፣ ስርዓት አክብረው በትምህርታቸው፣ በሃይማኖታቸው ጠንካራ ሆነው እንዲያድጉና እንዲኖሩ በተገቢው አቃጣጫ መምራት ይጠበቅባቸዋል።

ኢትዮጵጵያውያን የቴክ ሰዎችም የሀገራችን ህፃናት ወደሌላ እንዳይሳቡ በሀገር ባህል፣ ስርዓት የተቀረፁ የማስተማሪያ ካርቱን ፊልሞችን በብዛት ማዘጋጀት አለባቸው። #ቲክቫህ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሚዲያ የሩዋንዳውን የዘር ጭፍጨፋ (ጄኖሳይድ) እንዴት አቀጣጠለ ? በ100 ቀናት ከ800,000 እስከ 1,000,000 ቱትሲዎችና ለዘብተኛ የሚባሉ ሁቱዎች ባለቁበት የሩዋንዳው የዘር ጭፍጨፋ/ጄኖሳይድ ሚዲያዎች ከፍተኛ ድርሻ ነበራቸው። እንዴት ? - ራዲዮ-ቴሌቭዥን ሊብሬስ ዴስ ሚልስ ኮሊንስ (RTML) እንዲሁም መንግታዊው ' ሬድዮ ሩዋንዳ ' በቱትሲዎች ላይ በመላ ሀገሪቱ ጥላቻ እንዲፈጠርና የሩዋንዳ…
#Kwibuka

" ክፍፍል እና ፅንፈኝነት ካልተገታ በማናቸውም ቦታ ወደ ዘር ማጥፋት ሊያመራ ይችላል " - ፖል ካጋሜ

ከ30 ዓመታት በፊት በሩዋንዳ በ100 ቀናት ብቻ እስከ 1,000,000 ሚደርሱ ሰዎች የተጨፈጨፉበት የሩዋንዳ ዘር ፍጅት እየታሰበ ይገኛል።

የዘር ፍጅቱ የተፈፀመበትን 100 ቀናት ታሳቢ በማድረግ ከሚያዚያ 7 (እ.ኤ.አ) አንስቶ ለ100 ቀናት የዘር ጭፍጨፋው ሰለባዎች ይታሰባሉ ፤ ይህም ኪውቡካ /Kwibuka/ ይባለል።

ከሳምንት በፊት በኪጋሊ በነበረ ስነስርዓት ላይ ፕሬዜዳንት ፖል ካጋሜ ፤ ከዘር ፍጅቱ በህይወት የተረፉ ዜጎች ለብሄራዊ አንድነት ሲሉ ስላደረጉት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።

" እጅግ የሚከብደውን የእርቀ ሰላም ሸክም እናተ እንድትሸከሙ ጠየቅናችሁ እንሆ ለሀገራችን ስትሉ ይሄንን በየቀኑ ማድረጋችሁን ቀጥላችኃል ስለዚህ እናመሰግናችኃለን " ነው ያሉት።

ፖል ካጋሜ ፥ አሁንም ድረስ በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት #የጎሳ_ፖለቲካ እየተባባሰ መሄዱን እና የብሄረሰብ ማጽዳት አደጋ መደቀኑን በማንሳት አስጠንቅቀዋል።

" ሩዋንዳ ውስጥ የደረሰው መከራ ማስጠንቀቂያ ሊሆን ይገባል። ክፍፍል እና ፅንፈኝነት ካልተገታ በማናቸውም ቦታ ወደ ዘር ማጥፋት ሊያመራ ይችላል " ብለዋል።

ሩዋንዳ መከራ ውስጥ በገባችበት ጊዜ በርካታ ሀገራት የሰላም አስከባሪ ልጆቻቸውን ሩዋንዳ መላካቸውን እና እነዛም ወታደሮች ለሩዋንዳ እንደደረሱላት ገልጸዋል።

" ነገር ግን #በጥላቻም ይሁን #በፍራቻ ያልደረሰልን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

በሩዋንዳው የዘር ጭፍጨፋ በወቅቱ በነበረው የሁቱ መንግሥት መሪነትና የሁቱ ብሄረሰብ አባላት በሆኑ ጽንፈኛ አክራሪዎች እንዲሁም በመንግሥት በሚደገፈው የ " ኢንተርሀምዌ '  ሚሊሻ አማካኝነት እስከ 1,000,000 ቱትሲዎች ፣ ለዘብተኛ ሁቱዎችና ትዋዎች ተጨፍጭፈዋል።

Rwandan genocide
Apr 7, 1994 – Jul 15, 1994
AP / VOA

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ

@tikvahethiopia