#FakePage
ይህ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ስም የተከፈተ እና ከ4,000 በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገፅ ሃሰተኛ ነው። ገፁ ላይም እየተላለፉ የሚገኙት መልዕክቶች የጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳልሆኑ አረጋግጠናል። ትክክለኛው የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አሊ የግል የፌስቡክ ገፅ በፌስቡክ Verify የተደረገና ከ300,000 በላይ ተከታይ ያለው ብቻ ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ስራ አመራር ቦርድ አባላት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክትን እየጎበኙ ነው!
በአምባሳደር ግርማ ብሩ የተመራው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የስራ አመራር ቦርድ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት የመስክ ጉብኝት እያደረገ ነው፡፡ በጉብኝቱ ወቅት አምባሰደር ግርማ እንደተናገሩት ጉብኝቱ ፕሮጀክቱን ከሰነድ ሪፖርት ባለፈ በአካል የማየት እና የመገምገም ዓላማ አለው።
ጉብኝቱ ከፕሮጀክቱ የስራ ተቋራጮች ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ጋር በመወያየት ያጋጠሙ ችግሮችና ደካማ አፈፃፀሞች ካሉ በግልፅ በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫ ለመስቀመጥ እንዲሁም ፕሮጀክቱ በቀጣይ በተሻለ አፈፃፀም ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በመስክ ምልከታውም የስራ አመራር ቦርድ አባላቱ የፕሮጀክቱን የተለያዩ የሲቪልና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ በዶ/ር አብርሃም በላይ እና በፕሮጀክቱ ዋና ስራ አስኪያጅ በኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ሰፋ ያለ ገለጻና ማብራሪያ ተሠጥቷቸዋል፡፡
ከጉብኝቱ በኋላም ከፕሮጀክቱ የስራ ተቋራቱጮች ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ጋር በተለይ በቅድሚያ ኃይል ያመነጫሉ ተብሎ በሚጠበቁት ሁለቱ ዩኒቶች ማለትም ዩኒት 9 እና 10 የስራ አፈጻጸም ዙሪያ ጥልቅ ውይይት ማካሄዳቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡
(ኢቢሲ)

#ETHIOPIA
10 የፓለቲካ ፓርቲዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ በጋራ ለመስራት በትላንትናው ዕለት ስምምነቱ ላይ ደርሰዋል። ፓርቲዎቹ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት በትላንትናው እለት በአዲስ አበባ ኢሌሌ ሆቴል ተፈራርመዋል።
ፓርቲዎቹም፦
•የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)
•የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ)
•የአፋር ህዝቦች ነፃነት ፓርቲ ፣
•የሲዳማ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ ፣
•የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ
•የጋምቤላ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ
•የቅማንት ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
•የአገው ሀገር አቀፍ ሸንጎ
•የሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እና
•የካፋ አረንጓዴ ፓርቲ ናቸው።

#GAMBELA
በጋምቤላ ያለ ሰሌዳ ቁጥር ሲንቀሳቀሱና መንጃ ፈቃድ በሌላቸው ግለሰቦች ሲነዱ የነበሩ 101 ሞተር ሳይክሎች መያዙን የከተማዋ ፖሊስ ገለፀ።
በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ ቁጥጥር ስታቲስቲክስ ኦፊሰር ምክትል ኢንስፔክተር ታደለ አየለ ንደገለፁት ሞተር ሳይክሎቹ የተያዙት አንዳንዶቹ ያለ መንጃ ፈቃድ ሲያሽከረክሩ ቀሪዎቹ ደግሞ የሰሌዳ ቁጥር ስለሌላቸው ነው ብለዋል።
በተደረገው ድንገተኛ ቁጥጥር 101 ሞተር ሳይክሎች የተያዙ ሲሆን ቁጥጥሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል። ከተያዙት ሞተር ሳይክሎች መካከል 27ቱ የሰሌዳ ቁጥር የሌላቸው ሲሆኑ ቀሪዎቹ ደግሞ የመንጃ ፈቃድ በሌላቸው ግለሰቦች ሲሽከረከሩ የነበሩ ናቸው።
በተለይም በከተማዋ የሰሌዳ ቁጥር የሌላቸው ሞተር ሳይክሎች አደጋ አድርሰው የሚጠፉበት ሁኔታ መኖሩን ምክትል ኢንስፔክተሩ ጠቁመው ችግሩን ለመፍታት የትራፊክ ፖሊስ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
(ENA)

#ODP #ADAMA
የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) የክልል አመራሮች በብልጽግና ፓርቲ ፕሮግራም እና መተዳደሪያ ህገ ደንብ ዙሪያ እየመከሩ ነው። በአዳማ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ ውይይት በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የኦዲፒ የዞን አመራሮች ተሳትፈዋል።
በምክክር መድረኩ በውህድ ፓርቲው ፕሮግራም፣ በመተዳደሪያ ህገ ደንብና የድርጅቱ አወቃቀር ዙሪያ ውይይት እየተደረገ ይገኛል። ከዚህ ባለፈም በፓርቲው ዙሪያ በሚነሱ የተለያዩ የግልጸኝነት ጥያቄዎች ዙሪያ ውይይት የሚደረግ መሆኑን ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
(ኤፍ ቢ ሲ)

#TIGRAY
በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን መኾኒ ከተማ ትናንት ሌሊት በደረሰው የእሳት አደጋ 2 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን የራያ አዘቦ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ገለፀ።
የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ሓየሎም ረዳኢ እንደገለፁት የእሳት አደጋው ያጋጠመው ትናንት ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ላይ ነው የደረሰው። የአደጋው መንስኤ የኤሌክትሪክ ገመድ እርስ በራሱ ተጠላልፎ በፈጠረው እሳት ሲሆን በከተማው የገበያ ቦታ ሁለት ሚሊዮን ብር የሚገመት ጉዳት አድርሷል።
በአደጋው የ56 ነጋዴዎች ዘይትና ጫማ ሙሉ በሙሉ ወድሟል ። ህብረተሰቡ ባደረገው ርብርብ በሌሎች መኖሪያ ቤቶችና የንግድ ሱቆች ላይ ተጨማሪ አደጋ ሳያደርስ በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል።
(ኢዜአ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

#ህዳር29
ለ14ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ የሚከበረው የኢትዮጰያ ብሔር ፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በሰላም እንዲከበር የፀጥታ አካለት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
“ህገ-መንግስታዊ ቃል ኪዳናችን ለዘላቂ ሰላም” በሚል መሪ ቃል ህዳር 29 ቀን 2012 ዓ/ም በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አዘጋጅነት 14ኛው የኢትዮጰያ ብሔር ፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በአዲስ አበባ ስታዲየም በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ይከበራል፡፡
በበዓሉ ላይ ለመታደም እንግዶች ወደ አዲስ አበባ እየገቡ መሆኑን ኮሚሽኑ ጠቁሞ በብሔራዊ ደረጃ በሚከበረውና በርካታ ህዝብ የሚታደምበት በዓል በሰላም እንዲከበር ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ፣ የኦሮሚያና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽኖች እንዲሁም ሌሎች ተቋማትን ያካተተ የፀጥታ ኮማንድ ፖስት ተዋቅሮ ስራ መጀመሩን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡
More👇
https://telegra.ph/ETH-12-07

የሚዘጉ መንገዶች!
ህዳር 29 "የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን" አስመልከቶ በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚከናወኑ ልዩ ልዩ ስነ-ስርዓት ተጀምረው እስከሚጠናቁ ድረስ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር፡-
• ከሰንጋ ተራ ወደ ለገሃር
• ከሜክሲኮ አደባባይ በለገሃር ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም
• ከብሔራዊ ቲያትር ወደ ለገሃር
• ከሀራምቤ ሆቴል ወደ ለገሃር
• ከሀራምቤ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ሲሆኑ፡-
ከፕሮግራሙ ዋዜማ ማታ ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲዮም የሚካሄደው ስነ-ስርዓት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በስታዲየም ዙሪያ እና አካባቢው በግራና ቀኝ ለረጅም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የገለፀ ሲሆን፤ ህብረተሰቡ ለጸጥታ አጠራጣሪ የሆኑ ነገሮች ሲያጋጥሙት ይሁን የፖሊስ አገልግሎት ለማግኘት በስልክ ቁጥሮች-
11-5-52-63-03 ፣
011-5-52-40-77 ፣
0115-52-63-02 ፣
011-1-11-01-11 ወይም በነፃ ስልክ መስመር 991 እና 987 መጠቀም እንደሚችል ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

ባህርዳር ከነማ ከ መቐለ 70 እንደርታ!
የባሕር ዳር ከነማ እና የመቀሌ 70 እንደርታ ቡድኖች ደጋፊዎች ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ በጋራ የጽዳት ዘመቻ አካሂደዋል፡፡
በከተማዋ የሚገኙ የመንገድ ዳርቻዎችንና መናፈሻዎችን ነው በጋራ ሲያጸዱ ያረፈዱት፡፡ የጽዳት ዘመቻው በባሕር ዳር ከተማ የጽዳት ዘመቻ ሥራ በቋሚነት በሚያከናውኑ
በጎፈቃደኞች የተዘጋጀ ነው።
(TIKVAH FAMILY)
Join👇
@tikvahethsport

እግር ኳስ ለሰላም፣ ለፍቅር፣ ለአንድነት፣ ለአብሮነት፣ ለሀገር ግንባታ!
#ባህርዳር_ከነማ
#መቐለ70_እንደርታ
PHOTO : ጋንታ መቐለ 70 እንደርታ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ባህርዳር_ከነማ
#መቐለ70_እንደርታ
PHOTO : ጋንታ መቐለ 70 እንደርታ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ህዳር29
ዘንድሮ ለ14ኛ ጊዜ በኦሮሚያ ክልል አዘጋጅነት ለሚከበረው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በድምቀትና በሰላም መጠናቀቅ የቡራዩ ከተማ ድርሻ ወስዶ እየሠራ መሆኑ ተገለጸ። እንግዶችን ተቀብሎ ከማስተናገድ ጀምሮ እስከበዓሉ ፍጻሜ የሚያግዙ ከ100 በላይ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በከተማ አስተዳደሩ መዘጋጀታቸውም ተጠቁሟል።
(EPA)

TIKVAH-ETHIOPIA
ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ የተሰማሩ ሁለት ፖሊሶች ተገደሉ! በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ አዱላላ ቦኩ በሚባል ቀበሌ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተጠርጣሪን ለመያዝ የተሰማሩ ሁለት የዞኑ የፖሊስ አባላት መገደላቸውን ፖሊስ አስታወቀ። የምስራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮማንደር ሽፈራው ጉቱ "ፖሊሶች ወደ ቀበሌው ሄደው ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ሲሉ 'ለምን ይያዛሉ?' በሚል ረብሻ ተነስቶ የአከባቢው…
የፖሊስ አባላት ላይ የግድያና የአካል ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ 46 ተጠርጣሪዎች ተያዙ!
በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ ህግን ለማስከበር በተሰማሩ የፖሊስ አባላት ላይ የግድያና የአካል ጉዳት አድርሰዋል ተብለው የተጠረጠሩ 46 ግለሰቦች መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።
የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር አስቻለው አለሙ እንደገለጹት ትናንት የተያዙ እነዚህ ተጠርጣሪዎች የፍርድ ቤት ትእዛዝ ለማስፈጸም በተሰማሩ የፖሊስ አባላት ላይ ጥቃት ፈጽመዋል ተብለው ነው።
እንደ ኮማንደሩ ማብራሪያ አራት የፖሊስ አባላት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለማስከበር በአዳማ ወረዳ አዱላላ ቦኩ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ህዳር 24/2012 ዓ.ም ከንጋቱ አስራ ሁለት ሰዓት ከሩብ አካባቢ ያመራሉ።
ፖሊሶቹ በአካባቢው እንደደረሱ ተጠርጣሪዎቹን ለመያዝ ሲሞክሩ ለምን ይያዛሉ በሚል በአካባቢው ሁከት ይነሳል። በዚህ ወቅት የፖሊስ አባላቱ ሁከቱን ለማረጋጋት ቢሞክሩም ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ሁለት አባላት በስላት በአሰቃቂ ሁኔታ እንደተገደሉ ኮማንደር አስቻለው አመልክተዋል።
“ፖሊሶቹ የታጠቁት መሳሪያ በርቆም አንድ ሲቪል ህይወቱ ሲያልፍ በሁለት የፖሊስ አባላት ላይ ደግሞ በድብደባ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል “ብለዋል።
የማቾቹ አስክሬን ለቤተሰቦቻቸው በማስረከብ የቀብር ስነ ስርዓታቸው መፈጸሙን የገለጹት ኮማንደር አስቻለው ጉዳት የደረሰባቸው ሁለቱ የፖሊስ አባላት ደግሞ ፌዴራል ፖሊስ ሆስፒታል ተልከው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑንም አስታውቀዋል። በአካባቢው በተደረገው አሰሳ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 46 ግለሰቦች ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑንም ገልጸዋል።

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የ170 ሚሊየን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ!
የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የ170 ሚሊየን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኦርሱላ ቮን ደር ሌይን ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ ወቅትም ህብረቱ ለኢትዮጵያ ጤና፣ ምርጫ ቦርድ ማጠናከሪያ፣ የስራ እድል ፈጠራ እና ኢንቨስትመንት የሚውል የ170 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አድርጓል።
ከዚህ ውስጥ 50 ሚሊየን ዩሮ ለጤና የሚውል ሲሆን፥ 10 ሚሊየን ዩሮው ደግሞ ለስራ እድል ፈጠራና ኢንቨስትመንት እንዲሁም 10 ሚሊየን ዩሮ ለምርጫ ቦርድ ማጠናከሪያ ይውላል ተብሏል።
ከዚህ ባለፈም 100 ሚሊየን ዩሮው በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ህብረት ማዕቀፍ ስምምነት መሰረት ሃገር በቀል ማሻሻያውን በቀጥታ ለማገዝ ይውላል ነው የተባለው። በተጨማሪም ድጋፉ የቀጠናውን መሰረተ ልማት ትስስር ለማሳደግ የሚውልም ይሆናል።
(ኤፍ ቢ ሲ)
@tikvahethiopiabot @tikvahethiopia

#ኡቡንቱ #አርባምንጭ #ሃይሌሪዞርት
የ"ኡቡንቱ አርባ ምንጭ" የማጠቃለያ መርሃ ግብር በአሁን ሰዓት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የጋሞ አባቶች፣ የአርባ ምንጭ ከተማ ወጣቶች፣ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተገኙበት በሃይሌ ሪዞርት እየተካሄደ ይገኛል።
"በምክንያት የሚያምን ሚዛናዊ በሆነ ትውልድ መካከል የሚፈጠር የሃሳብ ልዩነት የጥንካሬ ምንጭ እንጂ የጠብ መነሻ አይሆንም!"
"እኛ ወንድምና እህት ነን፤ እዚህ ምድር ላይ አብረን እንጓዛለን!"
ዝርዝር መረጀዎች ይኖሩናል!
#ቲክቫህኢትዮጵያ #ፒስሞዴል #ጋሞዞን

ታላቅ አለም አቀፍ የዳዕዋ ዝግጅት በቡታጀራ ከተማ!
ከ 1 መቶ ሺህ በላይ ኢትዮጵያዋንም ጨምሮ የአለም ሀገራት የእስልምና እምነት ተከታዮችን እንግዶች ተቀብላ እያስተናገደች ነዉ። "አበሻ እጅቲማዕ" በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
ይህ በሀገራችን ለመጀመርያ ጊዜ የሚካሄደዉን ታላቅ አለም አቀፍ የዳዕዋ ዝግጅት ነዉ። ከህንድ ፣ከሱዳን ፣ከኬንያና ከሌሎች የአለም ሀገራት የተዉጣጡ የእስልምና እምነት ተከታዮች የዳዕዋዉ ተሳታፊ ናቸዉ።
ከ1 መቶ ሺህ በላይ አትዮጵያዉያን ጨምሮ የአለም ሀገራት እያስተናገደች ትገኛለች። "አበሻ እሽቲማ" ዳዕዋ ከሕዳር 26 ቀን 2012 ዓ.ም ለተከታታይ ሶስት ቀናት ማለት እስከ እሁዱ የሚቀጥል ነዉ፡፡
የከማዉ ነዋሪዎች መኖሪያ ቤታቸዉን ለእንግዶች ክፍት አድርገዉ እንግዳ የመቀበል ባህላቸዉን በከፍተኛ ሁኔታ እያንጸባረቁ ነዉ። ከተለያዩ የአለም ሃገራት ማለትም ከአፍሪካና ከአውሮፓ ሃገሮች ከ አንድ መቶ ሺህ በላይ የእስልምና የእምነቱ ተከታዮች የዳዕዋዉ ተሳታፊዎች ናቸዉ።
(Gurage Zone Administration Public Relation Office)
#SRTA

#ኡቡንቱ #አርባምንጭ #ሃይሌሪዞርት የ"ኡቡንቱ አርባ ምንጭ" የማጠቃለያ መርሃ ግብር በአሁን ሰዓት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የጋሞ አባቶች፣ የአርባ ምንጭ ከተማ ወጣቶች፣ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተገኙበት በሃይሌ ሪዞርት እየተካሄደ ይገኛል። "በምክንያት የሚያምን ሚዛናዊ በሆነ ትውልድ መካከል የሚፈጠር የሃሳብ ልዩነት የጥንካሬ ምንጭ እንጂ የጠብ መነሻ አይሆንም!" "እኛ ወንድምና…
#አርባምንጭ #ሃይሌሪዞርት #ቲክቫህ #ፒስሞዴል
የኡቡንቱ የማጠቃለያ ፕሮግራም በሀገራችን ብሔራዊ መዝሙር የተጀመረ ሲሆን የጋሞ ዞን አስተዳደር ተወካይ አቶ እሸቱ አልቶ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።
በዚሁ ንግግራቸው ወቅት የዝግጅቱ አስተባባሪዎች በሙሉ ወጣቶች መሆናቸው መርኃግብሩን ለየት እንደሚያደርገው ገልፀዋል፡፡ አቶ እሸቱ አክለውም 500,000 ቤተሰቦችን ስለ ፍቅር እና አንድነት ብቻ እየሰበከ ላሰባሰበን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የቴሌግራም ቻናል ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ቀጥሎም የኃይማኖት አባቶች፣የጋሞ አባቶች መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡ በተለይ ለወጣቱ ባስተላለፉት መልዕክት፦ እርስ በእርስ መከባበር እና ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርን ማስቀደም እንደሚገባ አበክረው ገልፀዋል፡፡
አሁን "ስለ እርቅ ለመወያየትና ለማስታረቅ እድሜ ምክንያት ሊሆን ይችላልን?" በሚል ርዕስ ወጣቱም ስለ ዕርቅ፣ ስለ ሰላም የበኩሉን እንዲወጣ በፈጣሪ አሰፋ አማካኝነት ምክክር እየተደረገ ይገኛል፡፡

#ኡቡንቱ #አርባምንጭ #ቲክቫህ #ፒስሞዴል
በዛሬው የውይይት ዝግጅት ላይ በስፋት ከተነሱት ሀሳቦች መካከል ሰው በሰውነቱ፡ብቻ ሊከበር እንደሚገባውና ሰላምን የሚያስቀድም ትውልድ ለመገንባት ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡ በውይይቱ የተሳተፉ ወጣቶች ደግሞ የጋሞ አባቶች ሰላም ወዳድነት ከአንድም ሁለት ጊዜ በተግባር የተገለጠ መሆኑን ጠቅሰው እንዲህ በአንድ መድረክ ስለ ሰላም አብረው መምከራቸው ትልቅ ትምህርት እንደሚሰጣቸው አንስተዋል፡፡ በአጠቃላይ ከውይይቱ በኀላ ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዘው ስለ ሁሉም ሰው ልጆች ክብር የድርሻቸውን ለመወጣትና ይህን ለማድረግ እድሜ እንደማይገድበው በማመን የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት ሁሉ ለመወጣት ቃል ገብተዋል፡፡