TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#GamoZone #EmbassyOfItaly

የጋሞ ዞን ከጣሊያን ኢምባሲ ጋር በመተባበር Italian Trade Agency (ICE) ከተባለ ድርጅት ጋር በአትክልትና ፍራፍሬ ምርት አቅርቦትና ማቀነባበር ዙሪያ ውይይት እየተካደ ነው፡፡ በውይይቱ ላይ በአትክልትና ፍራፍሬ ማቀነባበር የሚታወቁ ሶስት የጣሊያን ኩባንያዎች (Tropical Food Machinery, CERMAC,MACFIRUT) የተባሉ ድርጅቶች የተሳተፉ ሲሆን የአከባቢውን ምርት ማቀነባበር እና በቀላሉ ለአለም ገበያ ማድረስi በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከዞኑ አመራር፣ ከኢንቨስተሮች እና ህብረት ሥራ ማህበራትና ዩኒየኖች ጋር ተወያይተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብሰባ ተበተነ! ፖለቲካ ፓርቲዎች በዛሬው ዕለት ከምርጫ ቦርድ ጋር ሊያደርጉት የነበረው ውይይት በተፈጠረ አለመግባባት ተበተነ። የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባና የስነምግባር አዋጅ መፅደቁ ይታወሳል። የፀደቀው አዋጅ ማስፈፀሚያ ደንብ ላይ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት ለማድረግ በምርጫ ቦርድ አማካኝነት ቢሰባሰቡም መግባባት ላይ ባለመድረሳቸው ውይይቱ ተበትኗል። (AhaduTV) …
የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብሰባ መበተን...

ውይይቱ ሊቋረጥ የቻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ህግ አዋጅ ሆኖ ከመውጣቱ በፊት ረቂቁ ላይ የሰጡት አስተያየት ግብዓት ሆኖ አላገለገለም የሚል ሃሳብ ስላላቸው እንደሆነ ተገልጿል።

”በመሆኑም የኢትዮጵያ የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ህግ አዋጅ ለማስፈጸም በወጣ ረቂቅ ደንብ ላይ ከመወያየታችን በፊት በአዋጁ ላይ ያነሳነው ጥያቄ ሊመለስልን ይገባል” ሲሉ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱኳን ሚደቅሳ አዋጁ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀ በመሆኑ ከዚህ በኋላ ቦርዱን የሚመለከት ጉዳይ እንዳልሆነ አስገንዝበዋል።

በመሆኑም እንደተቋም የአዋጁን ማስፈጸሚያ ደንብ ማውጣትና መተግበር ስለሚያስፈልግ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደባለድርሻ አካላት በረቂቁ ላይ ሃሳብ እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

ነገር ግን የፖለቲካ ፓርቲዎቹ አባላት ”ከዚህ በፊት  በአዋጁ ረቂቅ ላይ የሰጠነው ሃሳብ ግብዓት ሆኖ ባለማገልገሉ አሁን በዚህ ደንብ ላይ የምንሰጠው አስተያየት ግብዓት ይሆናል የሚል እምነት የለንም” ብለዋል።

በዚህ የተነሳም ለግማሽ ቀን ተጠርቶ የነበረው መድረክ ካለስምምነት ተበትኗል። የምርጫ ቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱኳን ሚደቅሳና ሌሎች የቦርዱ አባላት የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በሌላ ጊዜ ለውይይት ተዘጋጅተው እንዲመጡ አሳስበው፤ ያላቸውን ጥያቄ በጽሁፍ ለቦርዱ እንዲያቀርቡ ጠይቀዋል።

ረቂቅ ደንቡ ፓርቲዎቹ ተወያዩበትም አልተወያዩበትም መጽደቁ ስለማይቀር ለፖለቲካ ሂደቱ ስኬት ሲባል ቢወያዩበት የሚመረጥ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

(ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከላይ የምትመለከቱት በድሬ ትዩብ (DireTube) የፌስቡክ ገፅ ላይ ከቀረበው ዜና ጋር የተያያዘው ፎቶ ሀሰተኛ ነው። መረጃው እና ፎቶው ምንም አይነት ግንኙነት የላቸውም።

@tikvahethiopia @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ በትላንትናው እለት ሁለት ሰዎች ውሀ ውስጥ ገብተው መሞታቸው ተገለጸ!

የአዲስ አበባ የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 እንዳስታወቀው በትላንትናው እለት ሁለት ሰዎች ውሃ ውስጥ ገብተው ህይወታቸው አልፏል ብላል፡፡ የመጀመርያው የሞት አደጋ የደረሰው በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ እድሜው 40 አመት የሆነ ጎልማስ ወንዝ ውስጥ ገብቶ ህይወቱ አልፏል ተብሏል፡፡

ሁለተኛው የሞት አደጋ የደረሰው ደግሞ በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ዮሴፍ ቄስ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተቆፈረ ጉድጓድ ውስጥ እድሜው 50 አመት የሆነ ጎልማሳ ህይወቱ እንዳለፈ ነው ኮሚሽኑ ያስታወቀው፡፡

በአዲስ አበባ ከቀርብ ጊዜ ወዲህ ጉድጓድ እና ወንዝ ውስጥ ገብተው የሚሞቱ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን በያዝነው ዓመት ብቻ 25 ሰዎች ውሃ ውስጥ ገብተው ሞተዋል፡፡ በከተማዋ ለተለያዩ አገልግሎት ተብለው የሚቀፈሩ ጉድጓዶች በተለይም ለግንባታ እና ለቆሻሻ ማጠራቀምያ እና ለውሀ ማጠራቀሚያ ተብለው የሚቆፈሩ ጉድጓዶች ከፍተኛ አደጋ እያደረሱ እንደሆነ የአዲስ አበባ የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያው አቶ ስለሺ ተስፋዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ተናግረዋል፡፡

(ETHIO FM 107.8)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የእንጦጦ የሳተላይት መረጃ መቀበያ አንቴና ግንባታ ተጠናቀቀ!

በእንጦጦ ኦብዘረቫቶሪና ምርምር ማዕከል የሚካሄደው የሳተላይት መረጃ መቀበያ አንቴና ግንባታ ተጠናቀቀ፡፡ በማዕከሉ የተገነባው የመረጃ መቀበያ አንቴና ኢትዮጵያ በቅርቡ የምታመጥቃትን ሳተላይት ጨምሮ ለሳተላይት መቆጣጠሪያ እና መረጃ መቀበያ አገልግሎት የሚውል መሆኑን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

(የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከሰምንታት በፊት በአዳማ ከተማ ተከስቶ የነበረውን አለመረጋጋት ወደ ሰላማዊ መንገድ ለመመለስ የከተማው አስተዳደርና ህብረተሰቡ በጋራ በመሆን በአዳማ ከተማ የእርቅ ስነ ስርዓት በትላንትናው ዕለት ተካሂዷል፡፡

የከተማዋ ከንቲባ አቶ አሰግድ ጌታቸው እንደተናገሩት ከባህላችን ውጪ በሆነ መንገድ የተፈጠረው ነገር ማንም የተጠቀመ የለም ያሉ ሲሆን የከተማዋን ፀጥታ ለማደፍረስ የሚሰሩትን ከዚህ በኀላ ዝም ብለን አንመለከትም ብለዋል፡፡ አቶ አሰግድ አክለውም ከሁሉም ብሔሮች ጋር ተከባብረን ተደጋግፈን ለሀገራችን ለውጥ በአንድነት መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የሃይማኖት አባቶችም የአዳማ ህዝብና የኦሮሞ ህዝብ አቃፊና የሰላም ምሳሌ እንደሆነ ገልጸው በሰላም መኖር ወሳኝ መሆኑን አሳስበዋል፡፡

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ብልፅግና ፓርቲና የ‹ባለ አደራ መንግሥት›...

ሕወሓት፤ ብልፅግና ፓርቲ በ2012 ዓ/ም እንደሚደረግ ከሚጠበቀው አገር ዐቀፍ ምርጫ በፊት ከተመሰረተ ኢትዮጵያ በባለ አደራ መንግሥት መመራት አለባት አለ፡፡ ከቀናት በፊት ሊቀመንበሩ ደብረፂዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ብልፅግና ፓርቲን መመስረቱም ሆነ ኢሕአዴግን የማፍረሱ ሒደት ሕጋዊ መንገዱን አልተከተለም በሚል ኢትዮጵያ ከምርጫ በፊት በባለ አደራ ልትመራ ትገደዳለች ማለታቸው ይታወሳል፡፡

በተመሳሳይ ኅዳር 18 ምሽት በትግራይ ቴሌቪዥን ቆይታ የነበራቸው የሕወሓት እና ኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ጌታቸው ረዳ ይህንኑ ሀሳብ ደግመውታል፡፡
ኢሕአዴግ አራቱን ብሔራዊ ድርጅቶች የማፍረስ ስልጣን አልተሰጠውም የሚሉት ጌታቸው፤ በሐዋሳው ጉባኤ ሀላፊነቱ ተሰጥቶታል የሚባለው #ውሸት ነው ሲሉ የሰላ ትችት ሰንዝረዋል፡፡

‹‹ብልፅግና ፓርቲ ውኅድ ሳይሆን አዲስ ፓርቲ ነው በማለትም›› ብልፅግናን መስርተው አሁን ባለው የመንግሥትነት ቦታ እንቀጥላለን ካሉ፤ ያን ጊዜ ሕግ የሚፈታው ጉዳይ ይሆናልም ብለዋል፡፡ በመሆኑም ብልፅግና ፓርቲ ኢህአዴግን መውረስ አይችልም፤ የብልፅግና ፓርቲ እየሄደበት ያለው ሂደትም ጨፍላቂ ነው ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡ በአንጻሩ ብልፅግና ፓርቲ ሕጋዊ ሂደቶችን ተከትሎና ኢሕአዴግን አዋኅዶ እየተፈጠረ መሆኑን በተደጋጋሚ የሚናገሩት የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ዐቢይ አሕመድ፤ አዲሱ ውህድ ፓርቲ እውነተኛ ፌደራሊዝምን የሚተገብር እንጂ ጨፍላቂ አይደለም ሲሉ ይደመጣሉ፡፡

(አሃዱ ቴሌቪዥን)

@tikvahethiopia @tikvahethipiaBpt
"የሀዋሳ ጉባኤ ውህደቱን እንዲያስፈፅም ለኢህአዴግ ምክር ቤት ውክልና ሰጥቶታል የሚባለው፣ ንፁህ ውሸት ነው!"- አቶ ጌታቸው ረዳ

"ኢህአዴግን ለማፍረስ የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ ቢንስ ሶስቱ የግምባሩ ድርጅቶች ሌላ ነገር ነው የምንፈልገው ብለው ቢያንስ አቋማቸው ስለገለፁ ፣ ቢያንስ በአመራር ደረጃ ማለት ነው፤ ስለዚህ ኢህአዴግን ለማፍረስ የሚያስችሉ መስፈርቶች ይነስም ይብዛም የተሟሉ ነው የሚመስለው፡፡ ፖለቲካሊ ማለቴ ነው፡፡ በፖለቲካ ደረጃ የኢአዴግ አባል ድርጅቶች ፍላጎት ሲኖራቸው ነው ኢህአዴግ ሊኖር የሚችለው፡፡ ስለዚህ ኢህአዴግ እንደ ግምባር ሊቀጥል የሚችልበት እድል አባል ድርጅቶቹ እንዲቀጥል ሲፈልጉ ነው፡፡ ስለዚህ እንዲቀጥል አንፈልግም የሚል እምነት የሚያረጋግጥ የሚመስል ውሳኔዎች ቢያንስ በአመራሮቹ ደረጃ ወስነዋል። ቢሆንም ኢህአዴግን የማፍረስ ሂደት በህግ ማለቅ የሚኖሩባቸውን ጉዳዮች እስኪማሉ ድረስ ቴክኒካሊ ፈርሰዋል ለማለት ግን አይቻልም፡፡ ያው ፍቺ ሲፈርስ የጋራ ሀብት፣ ንብረት የመከፈል ጉዳይ ስለሚኖር።

More👇
https://telegra.ph/TPLF-11-29

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Ethiopian Airlines 🛫 ደምቢ ዶሎ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከታህሳስ 7 ጀምሮ በሳምንት ሁለት ቀን ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ ደምቢ ዶሎ የበረራ አገልግሎት እንደሚጀምር አስታውቋል።

(የኢትዮጵያ አየር መንገድ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ለሦስት የመንግስት የስራ ኃላፊነት ቦታዎች ሹመት ሰጡ!

ጠቅላይ ሚንስትር ፅህፈት ቤት ለኢቲቪ በላከው ደብዳቤ እንዳስታወቀው፦

1. አቶ አህመድ ቱሣ የብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣

2. ዶ/ር አለሙ ስሜ በሚንስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ማእከል ዘርፍ አስተባባሪ፣

3. አቶ አወሉ አብዲ በሚንስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ማእከል የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ላይ ተመድበዋል፡፡

ተሿሚዎቹ ከህዳር 18 ቀን 2012 ጀምሮ በተጠቀሱት የስራ ኃላፊነት ቦታዎች ላይ ተመድበዋል፡፡

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የኢራቁ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣናቸውን ሊለቁ ነው!

ጸረ-መንግሥት ተቃውሞ በናጣት ኢራቅ ጠቅላይ ሚንሥትር አደል አብደል ማኅዲ ሥልጣናቸውን እንደሚለቁ ዛሬ ዐስታወቁ። ጠቅላይ ሚንሥትሩ በጽሑፍ ባሰራጩት መግለጫ ለሀገሪቱ ምክር ቤት የሥልጣን መልቀቂያ ደብዳቤያቸውን በይፋ እንደሚያስገቡ ገልጠዋል። የሥልጣን መልቀቂያ ጥያቄው ኢራቅ ውስጥ የጸጥታ ኃይላት ተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ ተኩሰው ቢያንስ ዐርባ ሰዎችን በገደሉ ማግስት ነው። የሀገሪቱ የሺዓ እምነት ከፍተኛ ባለሥልጣን ዓሊ ኧል ሲስታኒ ለመንግሥት የሚያደርጉት ድጋፍን «እንደሚያጤኑበት» ለምክር ቤቱ ዛሬ ቀደም ብለው ዐስታውቀው ነበር። ጠቅላይ ሚንሥትር አደል አብደል ማኅዲ ሥልጣናቸውን እንደሚለቁ በመግለጣቸው በርካታ ተቃዋሚዎች መዲናዪቱ ባግዳድ ወደ ሚገኘው ታኅሪር አደባባይ በብዛት በመሰባሰብ ደስታቸውን ገልጠዋል።

(የጀርመን ድምፅ ሬድዮ)

@tikvahethiopia @tsegabwolde
አቶ ለማ መገርሳ በመደመር ፍልስፍና እንደማይስማሙ ገለፁ!

የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር እና የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳ በመደመር ፍልስፍና ወይም በፓርቲዎች መዋሃድ እንደማይስማሙ ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ ራድዮ በሰጡት ቃለ ምልልስ ገልፀዋል፡፡

አቶ ለማ መገርሳ የኢህአዴግ ምክር ቤት የፓርቲዎችን ውህደት ባፀደቀ ጊዜ የምክር ቤት ስብሰባ ላይ ተገኝተው እንደነበር ገለፀው ስለሂደቱ ግን አሁን ማብራራት አልፈልግም ብለዋል፡፡

(VOA)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ለማ መደመርን የተቃወሙበት ምክንያት...

"በአጠቃላይ ከመጀመሪያ ጀምሮ እስከ መጨረሻ የፓርቲዎች መዋሃድን በተመለከተ የተለየ ሃሳብ ነው ያለኝ። ከመጀመሪያው ጀምሮ #የማላምንበት መሆኑን ለስራ አስፈፃሚውና ለሁሉም በስፋት ገልጫለሁ። መዋሃዱ ትክክል አይደለም፤ ከሆነም በችኮላ መሆን የለበትም፤ ወቅቱም አይደለም።"

@tikvahethiopia @tsegabwolde
የኦሮሞ እና አማራ የምሁራን መድረክ እየተካሄደ ነው!

የኦሮሞ እና አማራ የምሁራን መድረክ በአዲስ አበባ ኢሊሊ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በመድረኩ የህዝቦችን ትስስርና የሃገርን አንድነት ለማጠናከር ይመከራል።

ከዚህ በተጨማሪም የሁለቱ ክልል ምሁራን፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ተመሳሳይ የህዝብ ለህዝብና የምሁራን መድረኮች ከዚህ ቀደም መካሄዳቸው ይታወሳል።

ከዚህ ባለፈም በቅርቡ የሁለቱ ክልል ባለሃብቶች እና የወጣቶች የውይይት መድረክ መካሄዱም የሚታወስ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከሀሰተኛ ገፆች ተጠንቀቁ!!

29,000 like ያለው ይህ በEritrean Press ስም መረጃዎችን የሚያሰራጭ ገፅ ሃሰተኛ ነው!!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"እንዲህ አዝኜ አላውቅም" - አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ

ሱሌይማን ደደፎ በተባብሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ባለ ሙሉ ሥልጣን አምባሳደር፤ የመከላከያ ሚኒስትር ለማ መገርሳ "በመደመር ፍልስፍና አልስማማም፤ የኢሕአዴግንም ውሕደት አላምንበትም" ማለታቸውን አሳዝኝ እንደሆነ አስታወቁ።

አቶ ለማ ለቪኦኤ ኦሮምኛ ቋንቋ ዝግጅት ክፍል በሰጡት ቃለ ምልልስ "ከመጀመሪያው ጀምሮ የፓርቲዎችን መዋሃድ በተመለከተ የማላምንበት መሆኑን ለሥራ አስፈጻሚውና ለሁሉም በስፋት ገልጫለሁ። መዋሃዱ ትክክል አይደለም፤ ከሆነም በችኮላ መሆን የለበትም። ወቅቱ አይደለም" ብለዋል።

አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎም በበኩላቸው አቶ ለማ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ጋር ያላቸውን ልዩነቶች እንደሰሙበት ወቅት አዝነው አንደማያውቁ በቲዊተርና ፌስቡክ ገጾቻቸው ላይ አኑረዋል።

#SBS

@tikvahethiopia @tsegabwolde
የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሃላፊዎች በፓርቲው ወቅታዊ ሁኔታ እና የስራ ዕቅድ ዙሪያ እየተወያዩ ነው!

የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤት እና የክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሃላፊዎች በዛሬው እለት በፓርቲው ዋና ፅህፈት ቤት በወቅታዊ የፓርቲው ሁኔታ ላይ እየመከሩ ይገኛሉ። ሃላፊዎቹ ፓርቲው በመጪው ጊዜያት በሚፈፅማቸው አበይት ተግባራት ዙሪያም ውይይት ያደርጋሉ።

በኢህአዴግ አባል እና አጋር ድርጅቶች ውህደት በተፈጠረው ብልፅግና ፓርቲ የመጀመሪያ ስብሰባ ላይ ሁሉም ህብረ ብሄራዊ ውህድ ፓርቲውን የተቀላቀሉ ፓርቲዎች ፅ/ቤት ሃላፊዎች መገኘታቸውን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

(ኢቢሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በማናቸውም የኦዲፒ እና የኢሕአዴግ ስብሰባዎች ላይ ውህደቱንና የመደመር ዕሳቤን አስመልክቶ ከአቶ ለማ የልዩነት ሃሳብ አልሰማንም፤ የተለየ አማራጭ ሃሳብም አላቀረቡም!" - አቶ ታየ ደንደኣ(የብልፅግና ፓርቲ ኦሮሚያ ቅርንጫፍ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ)

አቶ ታየ ደንደኣ ስለ ብልፅግና ፓርቲ አመሠራረት ሂደት፣ ፋይዳዎቹና የአቶ ለማ መገርሣ በውህደቱ አላምንም ማለትን አስመልክተው ከSBS አማርኛ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፦ "አቶ ለማ በኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ውህደቱ አስፈላጊ እንደሆነና የመደመር ዕሳቤ ከኢትዮጵያ ዐልፎ ለምሥራቅ አፍሪካም ጠቃሚ ሃሳብ እንደሆነ ተስማምተው ነው ያጸደቁት፤ የልዩነት ሃሳብ አልሰማንም። ከዚያም ዐልፎ በኦዲፒ ማዕከላዊ ኮሚቴና ጉባኤ፣ በኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባዎች ላይ ሁሉ የተለየ አቋም አላንጸባረቁም። በዚህ መሄድ አለብን የሚል የተለየ አማራጭ ሃሳብም አላቀረቡም" ብለዋል።

#SBS
@tikvahethiopia @tsegabwolde
ሶዴፓ ድርጅታዊ ጉባዔውን እያካሄደ ይገኛል!

ሶዴፓ ጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው ጉባዔ የሶዴፓ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እና ማእከላዊ ኮሚቴ የብልጽግና ፓርቲን ለመዋሃድ ባሳለፈው ውሳኔ ዙሪያ እንደሚመክር ተነግሯል። ሶዴፓ በድርጅታዊ ጉባኤው የብልፅግና ፓርቲን ለመቀላቀል ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። እስካሁን የኢህአዴግ አባል እና አጋር ድርጅት የሆኑ ሰባት ፓርቲዎች ብልፅግና ፓርቲን ለመቀላቀል በጉባዔያቸው መወሰናቸው ይታወቃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የወላይታ ዞን ተወካዮች ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ጋር ሊወያዩ ነው!

የወላይታ ዞን በክልል የመደራጀት ጥያቄን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከሕዝብ ተወካዮች ጋር ለመነጋገር ነገ ማለዳ በጽህፈት ቤታቸው እንደጠሯቸው BBC ያነጋገርናቸው የተወካዮች አባላት አረጋግጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የክልሉ ሕዝብ ተወካዮችን በዞኑ አስተዳደር በኩል ለስብሰባ እንደጠሯቸው ቢነገርም በምን ጉዳይ ላይ እንደሚወያዩ ግን የተገለፀ ነገር የለም።

አቶ አሸናፊ ከበደ የወላይታ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር የወጣቶች ክንፍ አመራር ሲሆኑ፤ በስብሰባው ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ካቀኑት አባላት መካከል ይገኙበታል።

እርሳቸው እንደሚሉት፤የወላይታ ዞን ክልል የመሆን ጥያቄውን ካቀረበ ታሕሳስ 10 አንድ ዓመት የሚሆነው ሲሆን፣ ከዚያ በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዚሁ ዙሪያ ሊያነጋግሯቸው እንደጠሯቸው እንደሚገምት ተናግረዋል። ጥያቄው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበው አርብ ዕለት መሆኑን በመግለጽም በዞኑ አመራሮች በኩል ጥሪው ደርሶናል ብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከዚህ በፊት ወደ ዞኑ በማምራት ከሕዝብ ተወካዮችና ከዞኑ አመራሮች ጋር በተወያዩበት ወቅት የክልል መሆን ጥያቄው መነሳቱን የሚያስታውሱት የሀገር ሽማግሌዎችን ወክለው ስብሰባው ላይ የሚገኙት አቶ ነጋ አንጎሬ በወቅቱ ከሕዝባችሁ ጋር ተወያዩ መባላቸውን በማንሳት፣ እነርሱ ግን ተወያይተው መጨረሳቸውን መናገራቸውን ያስታውሳሉ።

አቶ አሸናፊ ከበደም በበኩላቸው ይህንኑ ስብሰባ በመጥቀስ ይህ የዘመናት የወላይታ ሕዝብ ጥያቄ የሚወሰንበትን ቀን አስታውቁ በተባልነው መሰረት አሳውቀናል ሲሉ ታሕሳስ 10፣ 2011 ዓ. ም. ጥያቄያቸውን ማቅረባቸውን ይናገራሉ።

More👇
https://telegra.ph/BBC-11-30

(BBC አማርኛ አገልግሎት)

@tikvahethiopia