TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ICRC

በግጭቶች፣ በሌሎች የብጥብጥ ሁኔታዎች / በአደጋዎች ወቅት ሰዎች በቁጥጥር ስር ሊውሉ ወይም ሊጠፉ ይችላሉ።

ይህ ሁኔታ በቤተሰቦቻቸው እና ወዳጆቻቸው ላይ ጭንቀትና አለመረጋጋት ይፈጥራል።

ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ወይም የጠፉ ዘመዶቻቸው ምን እንደገጠማቸው የማወቅ #መብት አላቸው።

የዓለም ቀይ መስቀል ኮሚቴ የዘመዶቻቸውን ዕጣ ፈንታ እና የት እንደሚገኙ ለማወቅ የሚጥሩ ቤተሰቦችን ይደግፋል፣ ያግዛል።

የICRC አገልግሎትን ለማግኘት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው የICRC ኢትዮጵያ ልዑክ 0943122207 / 011 552 71 10 ላይ በመደወል ማነጋገር ይቻላል።

* የስልክ መስመሮቹ ሊጨናነቁ ስለሚችሉ ደጋግማችሁ ሞክሩ።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ICRC

ኣብ ግጭታት እዋን ኣብ ካልኦት ናይ መጥቃዕቲ ኩነታት ወይ ከኣ ሓደጋታት ሰባት ኣብ ትህቲ ቁጽጽር ምስዋኣሉ ክጠፍኡ ወይ ክእሰሩ ይኽእሉ ፤ እዚ ድማ ኣብ ስድራቤቶም ጭንቀትን ዘይምርግጋዕን ይፍጠር።

ሰባት ኣብ ትህቲ ቁጽጽር ምስዋኣሉ ስድራቤቶም ናይ ምፍላጥ መሰል ኣለዎም።

ዓለም ለከ ቀይሕ መስቀል ኮሚቴ ድማ ስድራቤቶም ዝጠፍእዎም ቤተሰብ አበይ ከምዘለዉ ንምፍላጥ ንምድጋፍ ይደሊ።

ኣገልግሎትና ዝደቢ ዝኾነ ሰብ ድማ ናብ ኢትዮጵያ ዓለም ለከ ቀይሕ መስቀል ኮሚቴ ልኡኽ 0943122207 / 011 552 71 10 ብምድዋል ምዝራብን ምርካብን ይኽእሉ ኢዮም።

(ካብ ሶኒ እስካብ አርቢ ካብ 2፡00 ሰዓት እስካብ 11፡00 ሰዓት)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አጫጭር መረጃዎች #2 ፦ - በትግራይ መንግስት ስር የነበሩ 858 የሰሜን ዕዝ አባላት ትላንት በዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማህበር ርክክብ መደረጉን የትግራይ ቲቪ ገልጿል። ርክክቡ የICRC አባላት በተገኙበት ነበር ብሏል ቴሌቪዥን ጣቢያው። - ዶ/ር ደብረፅዮን በፌዴራል መንግስት የቀረበውን የ72 ሰዓት የእጃችሁን በሰላም ስጡ የሚለውን ጥያቄ እንዳልተቀበሉ AFP አስነብቧል፤ ዶ/ር ደብረፅዮን "እኛ ማን…
#ICRC

ICRC 858 የሰሜን ዕዝ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን እንዳልተቀበለ ገልጿል።

ትግራይ ቴሌቪዥን ባሰራጨው መረጃ በትግራይ መንግስት ስር ያሉ 858 የሰሜን ዕዝ አባላትን ICRC ተረክቧል ብሎ ነበር።

በርክክቡ ወቅትም የICRC አባላት በአካል ተገኝተው ነበርም ሲል ነው ቴሌቪዥን ጣቢያው የገለፀው።

ICRC ግን 858 የመከላከያ አባላት እንዳልተቀበለ በድረገፁ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ICRC

በመቐለ የሚገኙ ሆስፒታሎች ቁስለኞችን ለማከም የህክምና ግብአት እጥረት እንደገጠማቸው ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) አስታውቋል።

ICRC በመቐለ የሚገኘው ሆስፒታል የአስክሬን ማስቀመጫ ከረጢት እንደሌለውና የእጅ ጓንትን ጨምሮ ሌሎች መሰረታዊ አቅርቦቶች እያለቁ ነው ብሏል።

በዛሬው ዕለት መቐለ ከተማ ፀጥታ ብላ እንደዋለች #ICRC አሳውቋል።

https://www.icrc.org/en/document/ethiopia-hospitals-mekelle-struggling-care-wounded-medical-supplies-run-out-red-cross?utm_source=facebook&utm_medium=social&linkId=100000022072623

VIDEO : ICRC Africa (Tigray , Mekelle)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Tigray

የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (#ICRC) ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመተባበር በትግራይ ክልል በጦርነቱ ለተጎዱ በላይላይ ማይጨው ወረዳ 5 ቀበሌዎች ለሚገኙ ለ5,251 ቤተሰብ ፣ እንዲሁም በዓድዋ ወረዳ 4 ቀበሌዎች ለሚገኙ 6,907 ቤተሰብ የዘር እና ማዳበሪያ ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉ ወዳቋረጡት እርሻቸው እንዲመለሱ ያግዛቸዋል ተብሎ ታምኗል።

@tikvahethiopia
"...በትግራይ የምግብና የሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል" - ICRC

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር /ICRC/ በትግራይ የመሠረታዊ ሸቀጦች እና የምግብ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን አስታውቋል።

ICRC ዛሬ ባወጣው መግለጫ በተለይ ባለፉት 2 ሳምንታት የምግብ ዋጋ በከፍተኛ መጠን መጨመሩን አስታውቋል።

በመላው ትግራይ ክልል ባንኮች ዝግ በመሆናቸው ምክንያት ሰዎች መሠረታዊ ግብይቶችን ለመፈጸም የጥሬ ገንዘብ እጥረት አጋጥሟቸዋል ብሏል።

ICRC ፥ "ፋብሪካዎች ተጎድተው ቀርተዋል / እንዲወድሙ ተደርገዋል። በርካታ የንግድ ተቋማት ተዘግተዋል። በዚህም ምክንያት በርካቶች ከሥራ ውጪ ሆነዋል። ይህም የጤና አገልግሎት ጨምሮ መሠረታዊ ቁሶች እና አገልግሎቶች እንዳይገኙ አድርጓል" ሲል ገልጿል።

አብዛኛው የጤናና የመጠጥ ውሃ ማጣሪያ ተቋማት ኃይል የሚያገኙት ከጄነሬተር በሚመነጭ የኤሌክትሪክ ኃይል መሆኑን በመጥቀስ፤ በአሁኑ ወቅት በክልሉ ቋሚ የኤሌክትሪክ ኃይል እና የነዳጅ አቅርቦት አለመኖሩን ቀይ መስቀል ገልጿል።

መረጃው የተገኘው ከ #ICRC መግለጫ ሲሆን የፅሁፍ ዝግጅት ቢቢሲ ድረገፅ ነው።

@tikvahethiopia
#ICRC

ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ አገራት ውስጥ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደብዛቸው መጥፋቱ ተገለጸ።

ከ44 ሺህ በላይ ሰዎች በአሁኑ ወቅት በመላው አፍሪካ እንደጠፉ መረጋገጡን የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (አይሲአርሲ) ዓለም አቀፉን የመጥፋት ቀንን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ከነዚህም ውስጥ 45 በመቶ የሚሆኑት ህፃናት ናቸው ብሏል።

ከነዚህ ከጠፉት 82 በመቶ ያህሉ በግጭት ከሚናጡ ከተባሉ ሰባት አገሮች ብቻ መሆናቸውን ድርጅቱ አስታውቋል።

በአፍሪካ ውስጥ ከጠፉት ሰዎች ጠቅላላ ቁጥር ከግማሽ በላይ ናይጄሪያውያን ናቸው። በአገሪቱ ውስጥ ወደ 24 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች መጥፋታቸው ተመዝግቧል።

በርካቶች የጠፉ ሰዎች ቁጥር የተመዘገበባቸው ሌሎች አገሮች ኢትዮጵያ ፣ ደቡብ ሱዳን ፣ ሶማሊያ ፣ ሊቢያ ፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ እና ካሜሩን ይገኙበታል።

ድርጅቱ እንዳመለከተው ባለፈው ዓመት በተከሰቱ ግጭቶችና በሌሎች የጥቃት ዓይነቶች አህጉሪቱ የጠፉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ገልጿል።

በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ወረርሽኝ ምክንያት በተጣሉ ገደቦች የጠፉ ተጎጂዎችን ለማግኘት እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለማቀላቀል የሚደረገውን ጥረት እያደናቀፉ እንደሆነ ቢገልፅም የጠፉ ሰዎች የተረሱ ሰዎች አይደሉም ብሏል።

#ቢቢሲ

@tikvahethiopia
#Amhara #Afar #Tigray #ICRC #ERCS

በአማራ እና በአፋር ክልሎች ውስጥ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የተፈናቀሉ ዜጎች ህይወታቸውን ለማዳን ቤታቸውን ጥለው በመሠደዳቸው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ።

ተፈናቃዮቹ ምቹ ማረፊያ ባለማግኘታቸው በተጨናነቁ መጠለያዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ እንዲሁም በማንኛውም ክፍት ቦታ ላይ ለመተኛት ተገደዋል፡፡

ተፈናቃዮቹ በተሰደዱበት አካባቢ በሚኑሩ ማህበረሰቦች ቢደገፉም፣ በቂ የውሀና የምግብ አቅርቦት ይሻሉ።

የጤና ተደራሽነት በአሁኑ ወቅት ዋነኛው የሰብአዊ ጉዳይ ሆኗል።

በቅርቡ በአማራ እና በአፋር ክልሎች የተካሄደውን ግጭት ተከትሎ ፣ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ወደ ጤና ተቋማት የሚመጡ የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው።

የአለምአቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመተባበር በአማራና አፋር ክልሎች የመጠለያ፣ የንጽህና መጠበቂያ፣ የጤና አገልግሎትና ሌሎች የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፎችን እያደረገ ነው፡፡

ከነሐሴ ወር መጀመሪያ እስካሁን ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በትግራይ፣ አማራና አፋር ክልሎች ለ100,600 ሰዎች ፦
- ብርድልብሶች፣
- የማብሰያ ዕቃዎች
- የፋኖስ መብራቶች የመሳሰሉትን ቁሳቁሶች ስርጭት አድርጓል፡፡

በትግራይ ክልል በሚገኙ 18 ሆስፒታሎች ለ145,000 ህሙማንና የህክምና ባለሙያዎች የምግብ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን በአማራ ክልል ለሚገኙ 13 ሆስፒታሎች ደግሞ 2000 ቁስለኞችን ለማከም የሚበቃ መድሐኒት ተሠራጭቷል፡፡

በተጨማሪም በአፋር ለሚገኘው የዱፕቲ ጠቅላላ ሆስፒታልና በትራይ የሱሁልና ሽራሮ ሆስፒታሎችን ጨምሮ በትግራይ ክልል የሚገኙ 14 የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ጣቢያዎችን መሠረተ ልማት መልሶ የመገንባት ስራም ተሠርቷል፡፡

ያንብቡ : telegra.ph/ERC-09-12

@tikvahethiopia
#Waghimra

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በዚህ ሳምንት በአማራ ክልል ዋግህምራ ዞን ሳሃላ ሰየምት ወረዳ በግጭት ለተጎዱ ከ6,000 በላይ ሰዎች ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉ ሩዝ፣ ሽንብራ፣ የምግብ ዘይት እና የማዕድ ጨውን ያካተተ የምግብ ድጋፍ ነው።

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ባሳለፍነው ወር በዚሁ አካባቢ ለሚገኘው ማህበረሰብ የመጠለያ እና የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

#ICRC

@tikvahethiopoa
📞30 ሺህ ነፃ የስልክ ጥሪ !

በትግራይ ክልል ሽሬ የሚገኘው የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ቡድን በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ለተነጣጠሉ ሰዎች ከ30,000 በላይ ነጻ የስልክ ጥሪ አገልግሎት ሰጥቷል፡፡

ፍሬወይኒ እና አራት ልጆቿ ከብዙ ወራት ቆይታ በኋላ በቀይ መስቀል የስልክ አገልግሎት በኩል ከባለቤቷ ጋር መገናኘት በመቻላቸው በጣም ተደስተዋል፡፡

#ICRC

@tikvahethiopia