#ዎሕዴግ
የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ዎሕዴግ) በነገው ዕለት ጥቅምት 30/2012 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ጀምሮ በወቅታዊ ጉዳይ፣ በዎላይታ ክልልነት እና በአጠቃላይ በሀገሪቱ ፖለቲካዊ በማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ከየወረዳውና ከየዞኑ የተገኙ የዎላይታ ተወላጆች በተገኙበት ዉይይት እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ የግንባሩ ከፍተኛ ኃለፊዎች፣ በዞኑ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርትዎችም እንደሚገኙ ተገልጿል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#congratulations
ጎንደር ዩንቨርሲቲ በዛሬው ዕለት 251 የህክምና ዶክተሮችን አስመርቋል። ተመራቂዎች እና የተመራቂ ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ!
(ፎቶ-ቴዎድሮስ-ቲክቫህ ቤተሰብ ጎንደር)

#JIMMA
በጅማ ከተማ በነባሩ መናኽሪያ ይሰጥ የነበረው አገልግሎት በጊዜያዊነት ወደ ሌሎች አካባቢዎች መዛወሩን የከተማው የትራንስፖርት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ የባለስልጠኑ ኃላፊ አቶ ረሻድ አባሚልኪ እንደገለጹት በመናኽርያው ይሰጥ የነበረው አገልገሎት ከትላንት ጀምሮ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዲዛወር ተደርጓል።
“የነባሩ መናኽሪያ በማስፋፊያ ግንባታ ላይ በመሆኑና በተለዋጭነት በመሰራት ላይ የሚገኘው የቴክኒክ ሜዳን ባለው ዝናባማ የአየር ጸባይ ወደ ስራ ማስገባት ባለመቻሉ አገልግሎቱ ወደሌሎች አካባቢዎች እንዲዛወር ተደርጓል ” ብለዋል።
በነባሩ መናኽሪያ ይሰጡ የነበሩ አገልገሎቶች መካከል የሀገር አቋራጭ አውቶቢሶች መሳፊሪያ ---- ወደ ከተማው የስፖርት ማዝወተሪያ ስፍራ፣ የአጋሮ መስመር ጉዞ ስታዲዬም አጠገብ፣ የሰቃ መስመር ጉዞ ረሃ ሆቴል አጠገብ መዛወራቸውን አስታውቀዋል።
የሰርቦ መስመር ጉዞ --- አበጋዝ ሆቴል አጠገብ፣ የወልቂጤ መስመር ጉዞ በሬለምኔ ምግብ ቤት አጠገብ፣ የዴዶና ጭዳ መስመር ጉዞ ሳዳት ዳቦ ቤት አጠገብ ተደርጓል።
(ኢዜአ)

የጅማ ከተማ "ስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራ" መናኽሪያ ሆነ በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ የተሳሳተ እንደሆነ የጅማ ከተማ የትራንስፖርት ባለስልጣን አስታውቋል። ህብረተሰቡ አገለግሎቱ ወደ ነባሩ መናኽርያ እስኪመለስ በጊዜያዊነት በተዘጋጁ ስፍራዎች በትዕግስት እንዲጠቀምም የትራንስፖርት ባለስልጣኑ መልዕክት አስተላልፏል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት...
የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ሥርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ በምክር ቤቱ የታየ ጉዳይ ነው፡፡ የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት ለማህበራዊ ስምረት፣ ለፖለቲካ መረጋጋት፣ ለሀገራዊ አንድነት፣ ለሰብአዊ ክብር፣ ለብዝሃነት ጠንቅ መሆኑን በመገንዘብ በተለይም በአሁኑ ወቅት በአገራችን በህብረተሰቡ መካከል ያሉ የመልካም እሴቶች በጥላቻ ንግግሮችና በሀሰተኛ መረጃ ስርጭት ምክንያት በከፍተኛ ደረጃ እየተሸረሸሩና ለሀገርም ስጋት የደቀኑ በመሆናቸው እንዲሁም እነዚህን ችግሮች አሁን ባሉት ህጎች መፍታት የማይቻል በመሆኑ የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ሥርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ም/ቤት ውሳኔ አቅርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ አንዳንድ ማስተካከያዎችን በማከል ተቀብሎ ይጸድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል።
More👇
https://telegra.ph/ETH-11-09

#AddisAbeba
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በነገው እለት ሶስት አዳዲስ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ግንባታ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በሚገኙበት በይፋ ያስጀምራል።
ፕሮጀክቶቹ ከቦሌ ሚካኤል ቀለበት መንገድ የላይና የታች መንገድ-ቡልቡላ ካባ መግቢያ የሚደርሰው 5.5 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው፣ ሁለተኛው ደግሞ ከአውቶቡስ ተራ-መሳለሚያ-18 ቁጥር ማዞሪያ አድርጎ ኮልፌ ቀለበት መንገድ ፕሮጀክት 3.4 ኪ.ሜ ርዝመትና 40 ሜትር የጎን ስፋት የሚኖረው ሲሆን ከአውቶቢስ ተራ-18 ቁጥር ማዞሪያ ያለው ነባር መንገድ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ያለበት እንደሆነ ይታወቃል።
በተያያዘም ከለገሀር በጥላሁን ገሰሰ አደባባይ እስከ ጋዜቦ አደባባይ የመንገድ ፕሮጀክት በባለስልጣኑ የራስ ሀይል የሚገነባ ሲሆን 1. 1 ኪሎ ሜትር ርዝመትና የእግረኛ መንገድን ጨምሮ የ 10 ሜትር ስፋት ይኖረዋል። የመንገድ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ከለገሀር በፍላሚንጎ ጀርባ አድርጎ ወደ ቦሌ ለመጓዝ አማራጭ መንገድ በመሆን በመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ ይደረግ የነበረውን የትራፊክ መጨናነቅ ችግር በከፍተኛ ደረጃ ይቀርፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው እነዚህን የመንገድ ፕሮጀክቶች በሁለት አመታት ለማጠናቀቅ በልዩ ትኩረት ይሰራል ተብሏል።
(EPA)

ኢ/ር ታከለ ኡማ መኪና ሲያሽከረክሩ የነበሩት ቀበቶ ሳያስሩ ነበር?
በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ የገቡት የዋሽንግቶን ዲሲ ከተማ ከንቲባ አብረዋቸው ከ50 በላይ የሚሆኑ በተለያየ የስራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች መጥተዋል። ከንቲባዋ አዲስ አበባ ሲገቡ በኢ/ር ታከለ እና በሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል ተደርጎላቸው ነበር። ሁሉቱ ከንቲባዎች በአንድ መኪናም ሲጓዙ ነበር። ኢ/ር ታከለም ከከንቲባዋ ጋር አብረው የነበሩበትን መኪናም ሲያሽከረክሩ ታይተዋል።
ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ የመኪና መሪ ይዘው የሚያሳይ አንድ ፎቶ ግን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት ሲሰራጭና መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። የዋሽንግቶን ዲሲ ከተማ ከንቲባዋ ቀበቶ አስረው ይታያሉ፤ ኢ/ር ታከለ ደግሞ የነበሩበትን መኪና መሪውን ይዘው ቀበቶ እንዳላሳሩ ፎቶው ያሳያል፣ ቀበቶ ሳያስሩ መታየታቸውም መነጋገሪያ ሆኖ ውሏል።
የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ፅ/ቤት ኢትዮፒካሊንክ ለተባለ የሬድዮ ዝግጅት ስለሁኔታው እንደገለፀው፦ ኢ/ር ታከለ የያዙት መኪና ሲሽከረከር አልነበረም፤ ምክንያት የተባለውም መኪናው ቆሞ ሌሎች ተሳፋሪዎችን ከኃላ እያስገባ ነበር። የደህንነት መኪኖችም ቦታ ቦታቸውን ሲይዙ ነበር። በዚህ ወቅት ኢ/ር ታከለ የያዙት መኪና እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ እስኪነገራቸው በመጠባበቅ ላይ በነበሩበት ሰዓት የተነሳ ፎቶ እንጂ መኪናው እየተሽከረከረ እንዳልነበር ከከንቲባ ፅ/ቤት ተገልጿል። መኪናውን ማሽከርከር ሲጃምሩ የመኪናው መስታወቶች ተዘግተው ነበር። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲናፈስ የነበረውም ወሬ ሀሰተኛ እንደነበር ፅ/ቤቱ ገልጿል።
(ኤፍ ኤም 98.1)

"አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ ያሳስበኛል፤ እኔ አሁን 86 ዓመት ሊሞላኝ ነው፤ ሌሊት እንቅልፍ የለኝም፤ ለ2 ሰዓታት ብተኛ ነው ቀሪውን አለቅስበታለሁ። ለምንድነው ብዙ ለማንቆይበት የምንጋደለው? ለምንስ ነው የምንጫረሰው? በጣም ያሳስበኛል ያስለቅሰኛል።" ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ኡመር እንድሪስ በሸገር ኤፍ ኤም በነበራቸው ቆይታ ከተናገሩት የተወሰደ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#attention #woldiaUniversity
ከትላንት ለሊት ጀምሮ "በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ" በተለይም አዲስ ገቢ ተማሪዎች የሚኖሩባቸው ህንፃዎች አካባቢ አለመረጋጋት መፈጠሩን የቲክቫህ ቤተሰቦች በላኳቸው መልዕክቶች አስረድተዋል። እስካሁን ድረስም የትኛውም የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ስጋት ላይ የወደቁ ተማሪዎችን አላነጋገሩም። በተማሪዎች ላይ ስለደረሰ ጉዳት፣ በምን ምክንያት ይህ አለመረጋጋት ሊፈጠር እንደቻለ፣ ከተማሪዎች፣ ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ፣ ከተማሪ ተወካዮች ተጨማሪ መረጃዎችን ጠይቀን ወደናተው እናደርሳለን። በዚህ አጋጣሚ ይህን መልዕክት የምትመለከቱ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች ለጉዳዩ ትኩረት እንድትሰጡም እናሳስባለን።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

"ሰው መሆን ይቀድማል!" ኪነ ኢትዮጵያ- አዲስ መንፈስ የተሰኘ የህዝብ ለህዝብ መድረክ የመክፈቻ ስነ ስርዓት በትላንትናው ዕለት በኤሊያና ግራንድ ሆቴል ተካሂዷል፡፡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሞያተኞች ጋር በጋራ በመሆን ያዘጋጀው ይህ መድረክ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ነበር የተከፈተው፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ ታዋቂና አንጋፋ አርቲስቶች፣ የክልል ርዕሰ መስትዳድሮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው ነበት፡፡ የህዝብ ለህዝብ መድረኩ ዓላማም ሀገራዊ አንድነትን፣ ሰላምን፣ ወንድማማችነትንና አብሮነትን በማጠናከር ኢትዮጵያዊ አንድነትን ማጎልበት መሆኑን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

#WoldiaUniversity
ትናንት ቅዳሜ ምሽት በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ ሁለት ተማሪዎች መሞታቸው ተነገረ። BBC ያነገውራቸው የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች እና መምህር የብሄር መልክ በያዘው ግጭት የሁለት ተማሪዎች ህይወት ማለፉን እና በርካቶች መቁሰላቸውን አረጋግጠዋል።
በዩኒቨርሲቲው መምህር የሆኑት የቢቢሲ ምንጭ ትናንት ምሽት በተፈጠረው ግጭት ሁለት ተማሪዎች መሞታቸውን ወደ ዩኒቨርሲቲው ደውለው መስማታቸውን ተናግረዋል።
የሆስፒታል ምንጮች እንደጠቆሙት ደግሞ ወደ ወልዲያ ጄኔራል ሆስፒታል 14 ተማሪዎች ተጎድተው መጥተዋል።
ስማቸወን መግለጽ ያልፈለጉ የወልዲያ ጀነራል ሆስፒታል ባልደረባ ለቢቢሲ "እኔ የገባሁት ዛሬ [እሁድ] ጠዋት 2፡30 ላይ ነው። ተማሪዎቹ ጉዳት ደርሶባቸው ሲመጡ አልተመለከትኩም። ግን አሁን ከ14-15 የሚሆኑ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በሆስፒታሉ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
እኚሁ የሆስፒታል ባልደረባ በተማሪዎች ላይ የደረሰው ጉዳት ከቀላል እስከ ከባድ መሆኑን የጠቀሱ ሲሆን፤ ጉዳቱ ያጋጠመው በድብደባ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ከዚህ በተጫማሪ ትናንት ምሽት የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በተፈጠረባቸው የደህንነት ስጋት ከዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ለመውጣት የሞከሩ ተማሪዎች ከግቢው እንዳይወጡ መከልከላቸውን BBC ያነጋገራቸው ተማሪዎች ተናግረዋል።
More👇
https://telegra.ph/ETH-11-10
(BBC አማርኛው አገልግሎት)

ኦቢኤን ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ከተማሪዎች በስልክ ደውዬ አጣራው ብሎ እንደዘገበው ትላንት ማታ የተነሳው ችግር ከኳስም ግጭት የዘለለ እንደነበርና በዶርም አከባቢም ተማሪዎች ባልታወቁ አካላት ጥቃት እንደደረሰባቸው ይጠቁማል፡፡ ግጭቱም ከሊቱ 6 አከባቢ የተነሳ ነው ይላል ዘገባው። BBC በሰራው ዘገባ ግጭቱ ዶርም አከባቢ የተፈጠረ ነው ብሏል፡፡ እንደ BBC ዘገባ ጥቃቱን ያደረሱት አካላት ዶርም ለዶርም በመዞር ዶርም በመስበር ጥቃት አድርሰዋል ብለዋል፡፡

በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የሁለት ተማሪዎች ህይወት ማለፉን አብመድ አረጋግጧል!
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ወደነበረበት ሠላማዊ ሁኔታ እየተመለሠ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ትናንት ምሽት ተፈጥሮ በነበረ ግጭት ጉዳት ደርሷል፡፡ ትናንት ከምሽቱ 4፡00 እስከ 5፡00 ገደማ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የሁለት ተማሪዎች ሕይወት ማለፉና ስምንት ተማሪዎች ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳት እንዳጋጠማቸው ተገለጸ፡፡
የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወልደትንኤ መኮንን ለአብመድ በስልክ እንደገለጹት ምሽት ተማሪዎች ኳስ በቴሌቪዝን በጋራ ሲከታተሉ አምሽተው ሲመለሱ በተፈጠረ ግጭት ነው የተማሪዎች ሕይወት ያለፈውና የአካል ጉዳት ያጋጠመው፡፡
ጉዳት ካጋጠማቸው ስምንት ተማሪዎች ሦስቱ ቀላል ጉዳት ያጋጠማቸው ስለነበር መጠነኛ ሕክምና አግኝተው ወደ ዩኒቨርሲቲው መመለሳቸውንም አቶ ወልደትንሳኤ አስታውቀዋል፡፡ የተወሰኑ ተማሪዎችንና የተማሪ ተወካዮችን በችግሩ ዙሪያ ማወያዬታቸውን ያመለከቱት አቶ ወልደትንሳኤ ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን ለመያዝና ለሕግ ለማቅረብ እየተሠራ እንደሆነ አስውቀዋል፡፡
More👇
https://telegra.ph/ETH-11-10-2

የሶስት አዳዲስ የመንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታ በይፋ ተጀምሯል!
ኢ/ር ታከለ ኡማ ከአውቶቡስ ተራ- መሳለሚያ - 18 ቁጥር ማዞሪያ አድርጎ ኮልፌ ቀለበትየሚያናኘውን መንገድ በይፋ አስጀምረዋል፡፡ የግንባታ ስራ ከሚጀመርላቸው የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል ከቦሌ ሚካኤል ቀለበት መንገድ የላይና የታች መንገድ እስከ ቡልቡላ ካባ መግቢያ ድረስ ያለው አንዱ ሲሆን 5.5 ኪ.ሜ ርዝመትና ከአስር እስከ 40 ሜትር የሚደርስ የተለያየ የጎን መንገድ ስፋት ይኖሩታል፡፡
በሌላ በኩል ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ያለበት እና ለረጅም ጊዜ አገልግሎት ከመስጠቱ የተነሳ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበትን ከአውቶቡስ ተራ- መሳለሚያ - 18 ቁጥር ማዞሪያ አድርጎ ኮልፌ ቀለበት መንገድ ጋር የሚደርሰው ሁለተኛው ግንባታ የሚጀመርለት የመንገድ ፕሮጀክት ሲሆን 3.4 ኪ.ሜ ርዝመትና 40 ሜትር የጎን ስፋት ይኖረዋል፡፡ ከለገሀር በጥላሁን ገሰሰ አደባባይ እስከ ጋዜቦ አደባባይ የሚደርሰው የመንገድ ፕሮጀክት ሶስተኛው ግንባታ ከሚጀመርላቸው የመንገድ ፕሮጀክቶች ውስጥ ይገኝበታል፡፡

በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል ትናንት ሌሊት ተነስቶ የነበረው ብጥብጥ መረጋጋቱን የሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ። የፖሊስ መምሪያው ኃላፊ ኮማንደር ሀብታሙ ሲሳይ ለኢዜአ እንደገለጹት ብጥብጡ የተከሰተው ተማሪዎች ትናንት ምሽት ኳስ አይተው በተመለሱበት ወቅት ነው። በብጥብጡ የሁለት ተማሪዎች ህይወት ሲያልፍ በስምንት ተማሪዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።
የብጥብጡን መንስኤ ለማወቅና አጥፊዎችን ለመያዝ በአሁኑ ወቅት የማጣራት ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም ኮማንደር ሀብታሙ አስታውቀዋል። እንደ ኮማንደሩ ገለጻ ፖሊስ ችግሩ እንደተፈጠረ ወደ ዩኒቨርሲቲው ገብቶ የማረጋጋት ሥራ ከመስራት ጎን ለጎን ተቋሙ ጋር በመተባበር ተጎጂዎችን ወደ ወልድያ ሆስፒታል በማድረስ ሕክምና እንዲያገኙ አድርጓል።
በአሁኑ ወቅት የዩኒቨርሲቲው ሰላም ወደነበረበት በመመለሱ ከተማሪዎች ጋር የጋራ ውይይት እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል። ተማሪዎች የመጡበትን የትምህርት ዓላማ ለማሳካት ሌት ተቀን ተግተው ከመስራት ውጪ ለብጥብጥ መንስኤ መሆን እንደሌለባቸው ኮማንደር ሀብታሙ መክረዋል።

Dr. Momina Ahmed
ለኩላሊት ህክምና አስፈላጊው የግብዓት አቅርቦት እጥረት በመኖሩ ብዙዎችን መታደግና መድረስ እንዳልተቻለ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የኩላሊት ንቅለተከላ ህክምና ማዕከል አስታወቀ።
የማዕከሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ሞሚና አህመድ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ የግብአት አቅርቦት ችግሩን በቀላሉ በአሠራር መፍታት ቢቻልም ትኩረት ተሰጥቶ ባለመሠራቱ ብዙዎችን ማዳን አልተቻለም።
በተለይ የግዢ መቆራረጥ ማሽኖችና መድሃኒቶች በወቅቱ እንዳይደርሱ እንቅፋት ሆኗል። “ችግሩ ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ መጥቶ ዘወትር ከእንቅልፍ የሚያባንን ሆኗል” ያሉት ዶክተር ሞሚና፤ ባለሙያዎችም ከታካሚዎች እኩል በሰቀቀን ውስጥ መሆናቸውን ተናግረዋል።

‹‹የመከላከያ ኃይል ወደ ግቢው እንዲገባ እየተነጋገርን ነው፤ ማምሻውንም ወደ ግቢያችን ይገባል›› የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የአካደሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት እና ተወካይ ፕሬዝዳንት ዶክተር አስረስ ንጉሥ
.
.
"በወልድያ ዩኒቨርሲቲ" በትላንትናው ዕለት ምሽት 5፡00 አካባቢ በተፈጠረ ግጭት የተማሪዎች ሕይወት አልፏል፡፡ በተወሰኑ ተማሪዎች ላይ ደግሞ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡ የተፈጠረውን ችግር አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የአካደሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት እና ተወካይ ፕሬዝዳንት ዶክተር አስረስ ንጉሥ ‹‹ምሽት አካባቢ የተፈጠረው ችግር ምንጩ እስከሚጣራ ድረስ ከመገመት የዘለለ በትክክል አይታወቅም›› ብለዋል፡፡
በግጭቱ የሁለት ተማሪዎች ሕይወት ማለፉን እና በስምንት ተማሪዎች ላይ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የተናገሩት ተወካይ ፕሬዝዳንቱ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በወልድያ አጠቃላይ ሆስፒታል ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡
‹‹በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ሃይማኖትን በመስበክ እና ወደ ግጭት የሚያመሩ እንቅስቃሴዎችን ሲያካሂዱ የነበሩ ተማሪዎች በሥነ ምግባር ግድፈት ከትምህርት ገበታ መታገዳቸው እና በሰሞኑ በሀገሪቱ የነበረው የፖለቲካ ችግር መነሻ ሊሆኑ እንደሚችሉ እንገምታለን›› ያሉት ተወካይ ፕሬዝዳንቱ ትክክለኛ ችግሩ ተጣርቶ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ነው የተናገሩት፡፡
‹‹ከጉዳቱ በኋላ ከተማሪ ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገን መግባባት ላይ ደርሰናል›› ያሉት ዶክተር አስረስ ተማሪዎች ተማሪዎች ተረጋግተው ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ በማሳሰብ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ እና ለሕግ ለማቅረብ እንደሚሠራ አስታውቀዋል፡፡
More👇
https://telegra.ph/ETH-11-10-3

በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ሁከት ላይ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ሰላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ አገኘው ተሻገር ተናገሩ!
በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ትናንት በተከሰተው ችግር ዙሪያ የአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ አገኘው ተሻገር እየተካሄደ በሚገኘው 5ኛ ዙር 5ኛ አመት 14 መደበኛ ጉባኤ ላይ ወቅታዊ የክልሉ የጸጥታ ሁኔታን አስመልክቶ ለክልሉ ምክር ቤቱ በሰጡት ማብራሪያ በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ትናንት ምሽት ላይ ተማሪዎች እግር ኳስ እየተመለከቱ እያለ በደጋፊዎች መካከል ግጭት ተከስቶ ነበር፡፡
ግጭቱን የሚፈልጉት ሀይሎች ስለነበሩ ግጭቱን ወዲያውኑ የብሔር ግጭት አደረጉት፤ በዚህም ተማሪዎች ተጎድተዋል ብለዋል፡፡
በአሁኑ ሰአት የተፈጠረውን ግጭት አረጋግተነዋል፤ በዚህ ወንጀል ላይ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩትንም በቁጥጥር ስር አውለናል በማለት አቶ አገኘሁ ተናግረዋል፡፡
በአማራ ክልል በሚገኙ አስሩም ዩኒቨርሲቲዎች ሰላም እንዲደፈርስ አቅደውና አልመው የሚሰሩ ሀይሎችን ለይተን እርምጃ ለመውሰድ እየተንቀሳቀስን ነው ሲሉም ለምክር ቤቱ ገልጸዋል፡፡
በዚህም "በግለሰቦች መካከል የሚፈጠሩ ግጭቶችን" ወደ ብሔር ግጭት ለመውሰድ የሚንቀሳቀሱ ሀይሎችን ለመታገል የምክር ቤት አባላት እና መላው የክልሉ ህዝብ ከጸጥታ ሀይሉ ጎን በመሆን እንዲተባባር ቢሮ ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
(AC)

በመቐለ ፆታዊ ጥቃቶችን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ!
በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ የሚፈፀመውን ፆታዊ ጥቃት የሚያወግዝ የተቃውሞ ሰልፍ ዛሬ በመቐለ ተካሄደ። በሰልፉ ላይ ፆታዊ ጥቃትን የሚያወግዙ መፈክሮች በፅሑፍ የቀረቡ ሲሆን አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ጥቃቶች በጥበባዊ መንገድ ተንፀባርቀዋል። ከዛሬው ሰላማዊ ሰልፍ አስቀድሞ “ይኾኖ” በሚል መሪ ቃል በክልሉ የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶችን የሚቃወም እና የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ ያለመ ዘመቻ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ሲካሄድ ቆይቷል።
(DW)
PHOTO: Elias Meseret

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ትናንት በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የተፈጸመውን ክስተት አውግዟል!
የኦሮሚያ ክልያ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲስ ዛሬ [እሁድ] ከሰዓት በጽሁፍ በሰጡት መግለጫ፤ "እስካሁን ባለን መረጃ በሰላማዊ ተማሪዎች ላይ በተፈጸመ ድብደባ የተገደሉት ተማሪዎች ቁጥር ሁለት ናቸው" ያሉ ሲሆን በበርካቶች ላይ ደግሞ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት መድረሱን እና በተለያዩ ተቋማት የሚገኙ ተማሪዎች በሁኔታው መደናገጣቸውን ጠቁመዋል።
ምክትል ፕሬዝደንቱ፤ "አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአቋራጭ ስልጣን ለመያዝ እና አስተሳሰቦቻቸውን በኃይል ህዝብ ላይ ለመጫን ጥረት እያደረጉ ነው" ያሉ ሲሆን፤ እንዲህ አይነት በፖለቲካ ንግድ የሰከሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚዘሯቸው አጀንዳዎች የኦሮሞ እና የሌሎች ብሄር ልጆች ያልተገባ መስዕዋትነት እየከፈሉባቸው ይገኛሉ" ብለዋል።
ለትናንት ምሽቱ ጥቃት ተጠያቂ ናቸው የተባሉት ለፍርድ እንዲቀርቡ ከፌደራል እና ከአማራ ክልል መንግሥት ጋር አብረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
ምክትል ፕሬዝደንቱ፤ "ወደ ክልላችን ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ ተማሪዎችን ደህንነታቸወን በማስጠበቅ እንደ ልጆቻችን እንድንከባከባቸው እና የጥፋት ኃይሎች ፍላጎትን አንድናከሽፍ መልዕክት ማስተላለፍ እፈልጋለሁ" ብለዋል።
(BBC)

TIKVAH-ETHIOPIA
በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ሁከት ላይ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ሰላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ አገኘው ተሻገር ተናገሩ! በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ትናንት በተከሰተው ችግር ዙሪያ የአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ አገኘው ተሻገር እየተካሄደ በሚገኘው 5ኛ ዙር 5ኛ አመት 14 መደበኛ ጉባኤ ላይ ወቅታዊ የክልሉ የጸጥታ ሁኔታን አስመልክቶ ለክልሉ ምክር ቤቱ…
#UPDATE
የአማራ ክልል "ሰላም እና ደህንነት ግንባታ ቢሮ" በክልሉ በሚገኙ አስር ዩኒቨርስቲዎች ተመሳሳይ ግጭት ለማስነሳት አቅደው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ በዝግጅት ላይ መሆኑንም ገልጿል።
(የጀርመን ድምፅ ሬድዮ)