TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UPDATE

የአማራ ክልል ምክር ቤት በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የቀረበውን ሰባት የካቢኔ አባላት ሹመት ተቀብሎ አጸደቀ።

በዚህም መሰረት፦

1ኛ. ለክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ—ዶክተር መለሰ መኮንን

2ኛ. ለክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ—አቶ ብርሃኑ ጣዕምያለው

3ኛ. ለክልሉ ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ኃላፊ—አቶ ግዛት አብዩ

4ኛ. ክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ— ዶክተር ሙሉቀን አዳነ

5ኛ. ለክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ— አቶ ገረመው ገብረጻድቅ

6ኛ. ለክልሉ ውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ማማሩ አያሌው እንዲሁም

7ኛ. ዶክተር መልካሙ አብቴ ለጤና ቢሮ ኃላፊ ሆነው እንዲሰሩ በርዕሰ መስተዳድሩ የቀረበውን ሹመት የክልሉ ምክር ቤት ተቀብሎ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል። እንደ ኢዜአ ዘገባ ምክር ቤቱ አቶ ገረመው ገብረፃዲቅን በተጓደለ የህገመንግስት አጣሪ ጉባኤ አባል እንዲሆኑ መርጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Ashegoda - በትግራይ ክልል የሚገኘው የአሸጎዳ የነፋስ ኃይል ማመንጫ 54 ተርባይኖች አገልግሎት እየሰጡ አለመሆኑ ተገለጸ። "የአሸጎዳ ነፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ" ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ብሩክ ኤባ እንዳሉት፣ ኃይል ያመነጩ ከነበሩ 84 ተርባይኖች መካከል በአሁኑ ወቅት 54ቱ ማመንጨት አቁመዋል። ብዙዎቹ የኃይል ማመንጫ ተርባይኖች አገልግሎት መስጠት ያልቻሉት በመለዋወጫ እቃዎች እጥረት መሆኑንም ጠቁመዋል።

(ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፦

በዩኒቨርስቲዎች ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሰላማዊ መማር ማስተማር እየተካሄደ ባለበት በአሁኑ ጊዜ በወልድያ ዩኒቨርስቲ ትናንት ማታ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የሁለት ተማሪዎች ሕይወት አልፏል፡፡

ይሄንን ድርጊት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በፅኑ የሚያወግዘው ሲሆን አጥፊዎቹንም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት እና በመለየት የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ ያስታውቃል፡፡

ዩኒቨርስቲው በአሁኑ ጊዜ በመረጋጋት ላይ ያለ ሲሆን ከፌደራልና የክልሉ የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበርም አጥፊዎቹን በአፋጣኝ ለይቶ ወደ ህግ የማቅረብና ወደፊት እንዲህ አይነት አፀያፊ ድርጊቶች በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች እንዳይፈጠሩ የማድረግ ስራዎችን እየሰራን የምንገኝ በመሆኑ ህብረተሰቡ ይሄንን አውቆ የበኩሉን አስተዋፅኦና ትብብር እንዲያደርግም እንጠይቃለን፡፡

የወልደያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በተፈጠረው ችግር ሳይደናገጡ ጥፋተኞቹን በማጋለጥ፣ በተመሳሳይ ህገወጥ እና ከሥነ ምግባር ውጪ የሆኑ ድርጊቶች ላይ ባለመሳተፍና ግጭት ፈጣሪ አዝማሚያዎችን ሲመለከቱም ለሚመለከታቸው አካላት ቀድሞ ጥቆማ በማድረስ የዩኒቨርስቲያቸውን ሰላም እንዲያስከብሩ ጥሪ እናደርጋለን።

የዩኒቨርስቲው የቦርድ አመራሮች፣ የዩኒቨርስቲው አመራሮች፣ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች በዚህ ጉዳይ ላይ ክፍተት ያሳዩትን አጣርተው በአስቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱም እናሳስባለን።

ሰላም ወዳድ የሆነው የወልድያ ከተማ ማህበረሰብ፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት አባቶችና ወጣቶች የዩኒቨርስቲውን ሰላም ለማስጠበቅ እያደረጉት ላለው አስተዋፅኦ እያመሰገንን እና ወደፊትም ጥረታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ እያስተላለፍን ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛለን፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
"የመከላከያ ሠራዊት የመተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ ለዘመናዊ ሰራዊት ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው!!" - መከላከያ ሚኒስቴር

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-10-4

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እንጠንቀቅ!

"እጅግ ዘግናኝ የሆኑና የሰዎችን ስሜት የሚነኩ" ፎቶዎች በማህበራዊ ድረ ገፆች በስፋት እየተለቀቁ እንደሆነ እየተመለከትን ነው። አንዳንዶቹ ፎቶዎች በሌሎች ሀገራት የተፈፀሙ ድርጊቶችን የሚያሳዩ ናቸው።

እንጠንቀቅ…

ስሜታዊ ሆኖ ሼር ከማድረግ በፊት እነዚህ ፎቶዎችን በደንብ መመልከት፣ አላማቸው ምን እንደሆነ ማወቅ፣ ከምስሎቹ ጀርባ ለሀገራችን ምን እየታሰበ እንደሆነ መረዳት ሁላችንም ግድ ይለናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#attention

የማህበራዊ ሚዲያውን በመጠቀም ወንድም በወንድሙ ላይ እንዲነሳ ለማድረግ እየሰሩ ያሉ ሰዎች እንዳሉ እየተመለከትን እንገኛለን። የትላንቱ የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ክስተት በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም እንዳይከሰት አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።

በየዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ለሚሰጧቸው ጥቆማዎች አስቸኳይ ምላሽ ከመስጠት ጀምሮ፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ የፀጥታና የደህንነት አካላት፣ የዩኒቨርሲቲ አመራሮች እና የተማሪ ተወካዮች የተማሪዎችን ደህንነት ከማስጠበቅ አንፃር አስፈላጊውን ሁሉ እንድታደርጉ እናሳስባለን።

ከምንም በላይ ወላጆች ልጆቻችሁ በትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ እየደወላችሁ ልትመክሯቸው ይገባል። ዩኒቨርሲቲዎች በሚገኙባቸው አካባቢዎች ያላችሁ ነዋሪዎችም ለተማሪዎችን ደህንነት መጠበቅ ትልቅ ድርሻ አላችሁና እናንተም መልካም ስራችሁን ትቀጥሉ ዘንድ መልእክት እናስተላልፋለን።

በማህበራዊ ሚዲያ ነገሩን ለማባባስና ተማሪዎችን ለመቀስቀስ ሀሰተኛ መረጃዎችን እያሰራጫችሁ የምትገኙ ግለሰቦች ይኸው ተንበርክክን እንለምናችኃለን፤ ለንፁሃን ምስኪን ተማሪዎች ስትሉ ከድርጊታችሁ ተቆጠቡ!!

ቲክቫህ ቤተሰቦች!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#attention

በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች የተለያዩ መልዕክቶችን የያዙ ወረቀቶች ሲለጠፉ ነበር፤ ይህ ተማሪዎች ተረጋግተው ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉ እንዲሁም ተረጋግተው ግቢ ውስጥ እንዳይቀመጡ እያደረጋቸው ይገኛልና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ የዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ የተማሪ ተወካዮች አስፈላጊውን መፍትሄ ብትፈልጉ መልካም ነው። ተማሪዎችም እርስ በእርስ ያላቸውን አብሮነት የሚያጠናክሩበት የውይይት መድረኮችን የማመቻቸት ስራ ቢሰራ ጥሩ ነው።

ቲክቫህ ቤተሰቦች!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የውሸት ዜና ምን ማለት ነው?

የውሸት ዜና ማለት ሆን ተብለው የሚፈጠሩ፣ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ደግሞ በኅትመት ወይም በሶሻል ሚዲያ የሚሰራጩ የፕሮፓጋንዳ መሳሪያዎች ናቸው፡፡ የውሸት ዜናዎች ሲፈጠሩ ሰዎችን ለማሳሳት፣ ለአመጽ ለማነሳሳትም ሆነ ለማወናበድ ታስበው ሲሆን፣ የተለያዩ መንግሥታትም የህዝብን ሃሳብና የተቃውሞ አቅጣጫ ለመቆጣጠር በተለያዩ ጊዜያት ተጠቅመውታል፡፡ ከዚህ ቀደም የውሸት ዜናዎችን ማሰራጨት ከባድ የነበር ቢሆንም፣ በተለይም የሶሻል ሚዲያው አብዮት ከተከሰተ በኋላ በከፍተኛ ሁኔታ ስርጭቱ ጨምሯል፡፡

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-11

https://qumneger.wordpress.com/2019/03/26/fake-news/

(Fresenbet G.Y Adhanom - ቲክቫህ ቤተሰብ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Arsi_university

በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ የደርስውን አደጋ አርሲ ዩኒቨርሲቲ በጽኑ ያወግዛል። በዩኒቨርስቲዎች ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሰላማዊ መማር ማስተማር እየተካሄደ ባለበት በአሁኑ ጊዜ በወልድያ ዩኒቨርስቲ ትናንት ማታ የሁለት ተማሪዎች ሕይወት አልፏል፡፡ ይሄ ድረጊት በትኛውም መመዘኛ ተቀባይንት የሌለው መሆኑን ሁሉም ሰው መረዳት ይገባዋል፡፡ይሄንን ድርጊት አርሲ ዩኒቨርሲቲ በፅኑ ያወግሀዋል፡፡

የአርሲ ዩኒቨርሱቲ ሰራተኞች እና በአከባቢው የሚኖሩት ማህበረሰብ በዓርሲ ዩኒቨርሲቲ ተመድበው ከየተለያየዩ የአገሪቱ ክፍል የመጡትን ተማሪዎች #እነደራሱ ልጆች በማሰብ አስፈልጊውን እንክብካቤ እና ጥበቃ እያደረገላቸው መሆኑ ይታወቃል፣ ለወደፊቱም ይሄንኑ መለካም ተግባር እየሰራ የሚቀጥል መሆኑን በአፅኖት እንገልፃለን፡፡

(አርሲ ዩኒቨርሲቲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የደቡብ ክልል የፓርላማ ተመራጮች የመስክ ምልከታ ሪፖርት ለክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት አስፈፃሚ አካል አቀረቡ። የፓርላማ ተመራጮቹ በአመት ሁለት ጊዜ ወደ መረጣቸው ህዝብ በመምጣት የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ህዝብ የሚያነሳውን ጥያቄ ለክልሉ መንግሥት በማቅረብ ምላሽ እንዲያገኝ የመስራት ሃላፊነት ተጥሎባቸዋል። የዛሬው የመስክ ምልከታ ግብረ መልስም የዚህ ተግባር አካል ነው።

(FBC)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአሁኑ ሰዓት የወልድያ ከተማ የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ከተማሪዎች ጋር እየተወያዩ ነው!

ከግጭቱ ጋር በተያያዘ ተሳታፊና ተባባሪዎች ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ 13 ተማሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው!

(ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ)

የዩኒቨርሲቲያችንን ወቅታዊ መረጃ በተመለከተ!!

በቅድሚያ ከትናንት ወዲያ ጥቅምት 29/2012 ዓ.ም ምሽት 5:00 ስዓት ላይ በወልድያ ዪኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

ግጭቱ የሁለት ተማሪዎቻችንን ህይወት የቀጠፈና በሌሎች 13 ተማሪዎችቻን ላይም ቀላል የሚባል ጉዳት መድረሱን የህክምና ምርመራ ውጤታቸው ላይ መረዳት ተችሏል፡፡ በመሆኑም ድርጊቱ መላውን የዩኒቨርሲቲያችንን ማህበረሰብ መምህራንን፣ ሰራተኞቻችንና ተማሪዎቻችንን ከዛም አልፎ የአካባቢውን ማህበረሰብ ያሳዘነ ድርጊት በመሆኑ ክስተቱን እያወገዝን በደረሰው ጉዳት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን አንገልፃለን።

የሟቾቹን ነፍስ ፈጣሪ እንዲምር፤ ጉዳት የደረሰባቸው የተማሪ ወላጆችና በተሰቦችም መፅናናቱን እንዲሠጣቸውና ህክምና በመከታተል ላይ ያሉ ተማሪዎችም በቶሎ እንዲያገግሙ እንመኛለን፡፡ በመቀጠል ከትናንት ወዲያም ሆነ ትናንት የነበረውንና አሁን ተቋሙ ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ መረጀዎችን ለመስጠት እንወዳለን ፡፡

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-11-2

ህዳር 1 /2012 ዓ.ም
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Dr. Amir Aman

የጤና ሚኒስቴር ከ14 አመት በፊት መተግበር የጀመረውን የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ላይ የሰራውን የጥናት ውጤት ይፋ አደረገ።

የጥናት ውጤቱ በጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ላይ ተጠናክረው መቀጠል በሚገባቸውን የፕሮግራሙ ጠንካራ ጎኖች እና መቀጠል በሌለባቸው የፕሮግራሙ ክፍሎች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው።

በዚህም መሻሻል በሚገባቸው እና መጨመር ያለባቸው የፕሮግራም ክፍሎች ላይ ቀጣይ አቅጣጫዎች ማስቀመጡን የጤና ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን አስታውቀዋል።

ዝርዝር ጥናቱን ሚኒስቴሩ በመርክ አማካሪዎች አማካኝነት ያሰራው ሲሆን፥ ቢል ኤንድ ሚሌንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን እና ኢንተርናሽናል ኢንስቲቲዩት ፎር ፕራይመሪ ሄልዝ ኬር ድጋፍ ማድረጋቸውን ከሚኒስትሩ የፌስ ቡክ ገጽ የተገኘነው መረጃ ያመላክታል።

(ዶ/ር አሚር አማን)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#update በጊቤ ሸለቆ ብሄራዊ ፓርክ ከሚያዚያ 6 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ትላንት አመሻሽ ድረስ 28 ጉማሬዎች ሞተው መገኘታቸወን ፓርኩ አስታውቋል። Via #fbc @tsegabwolde @tikvagethiopia
በጊቤ ሸለቆ የሞቱት ከ30 በላይ ጉማሬዎች በአካባቢዉ ነዋሪዎች ተመርዘው መገደላቸው በጥናት ተረጋገጠ!

ሚያዝያ ወር 2011 ዓ.ም በጊቤ ሸለቆ ከ30 በላይ የሚሆኑ ጉማሬዎች መሞታቸዉ ይታወቃል፤ ጉማሬዎቹ በአካባቢዉ ነዋሪዎች ተመርዘዉ እንደተገደሉ የወልቂጤ ዩንቨርሲቲ በጥናት አረጋግጫለሁ ብሏል። ዩንቨርሲቲው የጉማሬዎቹን አሟሟት ምክንያት ለማወቅ ጥናት ማካሄዱን ያስታወቀ ሲሆን ጉማሬዎቹ የተገደሉት በአካባቢዉ ሰዎች ነዉ ብሏል፡፡ የወልቂጤ ዩንቨርሲቲ የምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሲሳይ ከኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ጋር በነበራቸዉ ቆይታ እንደተናገሩት፤ጉማሬዎቹ የተገደሉት በአካባቢዉ ነዋሪዎች ተመርዘዉ እንደሆነ በጥናት አረጋግጠናል ብለዋል፡፡

(ኢትዮ ኤፍ ኤም)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ሰብሌን ያዳነችልንን "ሰብልዬን" እናመሠግናለን!" - በቃሉ ወረዳ የ019 የአብቾ ቀበሌ አርሶ አደሮች

የቃሉ ወረዳ የ019 የአብቾ ቀበሌ አርሶ አደሮቹ በአምበጣ መንጋው ክፋት እና በሚያደርሰው ጉዳት የተማረሩ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ ለ4ኛ ጊዜ በአብቾ በቀበሌ የሠፈረው የበረሀ አንበጣ መንጋ በሰብልና በእንስሳት መኖ ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡

ይህን መንጋ ለመከለካል የምስራቅ አፍሪካ አንበጣ መከላከል ድርጅት በተደጋጋሚ በአውሮፕላን የታገዘ የኬሚካል ርጭት ቢያከናውንም እንደዛሬው የተሳካ ርጭት አለማከናወኑን አርሶአደሮቹ ተናግረዋል፡፡ አርሶአደሮቹ እንደሚሉት አውሮፕላኗ ለመሬት ያላት ቅርበት አንበጣው ላይ ኬሚካሉን በቀላሉ ለመርጨት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የኬሚካሉ የመግደል አቅም ከፍተኛ ሲሆን መንጋውን ከመግደል አልፎ ወደተለያዩ አቅጣጫወች እንዲበተን አድርጎታል ብለዋል፡፡ አርሶ አደር ሠይድ መሀመድ የተባሉት ግለሰብ በዛሬው ርጭት ከመደሰታቸውም በላይ ትንሿን ሰብልየን አመስግኑልኝ ብለዋል፡፡

የቃሉ ወረዳ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዯች ፅ/ቤት በበኩሉ በአርሶ አደሮቹ ስም የተሠማውን ደስታ ገልጾ፤ ትንሿ ሰብልየን ከልብ እናመሠግናለን ብሏል፡፡ በሁሉም አካባቢዎች እየተደረገ ያለው ድጋም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

(የቃሉ ወረዳ ኮሚኒኬሽን)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሌሎችም የትምህርት ተቋማት ስጋት ማንዣበቡን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ!

የኢፌዴሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከሰሞኑን ከተፈጠረው ክስተት ጋር ተያይዞ በሌሎችም ዩኒቨርሲቲዎች ስጋት አንዣቧል ጉዳዩን እየተከታተልኩ ነው ብሏል። ነገር ግን ሚኒስቴሩ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥቧል።

በኢትዮጵያ አንድ ዩኒቨርሲቲ የሚከሰት የግለሰቦች ግጭት ፈጥኖ የብሔር መልክ ሲይዝና ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ሲዛመት ይስተዋላል፡፡

የሰሞኑን ክስተት ተከትሎም በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ላይ የደኅነት ስጋት መፈጠሩን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የተጠየቀው የሳይንስና እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ነገሮችን በትኩረት እየተከታልኩ ነው ያለ ሲሆን፣ አሁን ላይ ግን ለመገናኛ ብዙኃን የሚመጥን ምንም ዓይነት መረጃ የለኝም፤ ታገሱኝ ብሏል፡፡

(AhaduTelevision)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiBot
#attention

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቤተሰቦቹ እንደሰማው ከትላንት ምሽት ጀምሮ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ስጋት አንዣቧል፤ አንዳንድ ግቢዎች ላይም ከዚሁ ጋር ተያይዞ በተማሪዎች ላይ አለመረጋጋት እንደተፈጠረ ለመረዳት ችለናል።

በተለይም ማንነታቸው በማይታወቁ አካላት በየግርግዳው ላይ የሚለጠፉ መልዕክቶች ተማሪዎችን ከፍተኛ ስጋት ላይ እየጣሉ፤ አንዳንዶችም ከመፍራቻ የተነሳ ግቢ ለቀው ለመውጣት መገደዳቸውን ለመረዳት ችለናል።

ትላንት ምሽት እንዳሳሰብው ይህን መሰሉ ክስተት ቶሎ ወደ ሌሎች ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የመዛመት እንድሉ ሰፊ በመሆኑ ምልክቶችን የሚታዩበት፣ ተማሪዎችም ጥቆማ የሚሰጡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ላይ መንግስት ቅድመ ጥንቃቄ በማድረግ የተማሪዎችን ደህንነት ቀድሞ ሊጠብቅ ይገባል።

ከምንም በላይ ደግሞ ተማሪዎች በተረጋጋ መንፈስ በወንድማማችነት የሚመክሩበትን መድረኮችም ማመቻቸት ይገባል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተቻለ አቅም ለሚመለከታቸው ሁሉ መልዕክቶቻቹን ያደርሳል።

ተማሪዎች ከስሜታዊነት ርቃችሁ፤ ለራሳችሁ፣ ለቤተስቦቻችሁ፣ ለሀገራችሁ ብላችላሁ በማስተዋል ሁኔታዎችን፣ ያሉ ስጋቶችን እና ውጥረቶችን እንድታረግቡ በፈጣሪ ስም እንማፀናለን!!

ቲክቫህ ቤተሰቦች!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#attention

ከሰሞኑን ክስተት ጋር በተያያዘ "በአንዳድ ዩኒቨርስቲዎች" አሁንም ስጋቶች እየተስተዋሉ ይገኛሉ፡፡ ኃላፊነቱ የሁሉም ነው፡፡ የሀገር መሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የፓለቲካ መሪዎች፣ የሀገሪቱ የመንግስት እና የግል ሚዲያዎች፣ አክቲቪስቶች፣ ወጣቶች፣ ያገባኛል የምትሉ በሙሉ ለችግር መፍትሔው ችግር አይሆንምና መልዕክታችሁን አሰሙ! በኃላ ክቡር የሆነው የሰው ነፍስ ከጠፋ በኃላ ሁላችንም ተናጋሪዎች መሆን፣ መግለጫ መስጠት...አይጠቅምም!!

ቲክቫህ ቤተሰቦች!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በህገወጥ መንገድ ወደጅቡቲ ሲጓዙ የነበሩ 72 ሰዎች ተያዙ!

በህገወጥ መንገድ በአይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ወደጅቡቲ ድንበር ሲጓዙ የነበሩ 72 ሰዎች መያዙን የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በክልሉ ፖሊስ ኮሚሸን የወንጀል መከላከል ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር ተወካይ ምክትል ኮማንደር መሃመድኑር አደም እንዳሉት በክልሉ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም አሁንም እየተፈጸመ ይገኛል።

በተለይም ከአማራ ክልል ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞን እንዲሁም ከትግራይ ክልል በህገ-ወጥ መንገድ ለሚካሄድ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር በአፋር ክልል የሚገኘው ጋላፊ ዋነኛ የመውጫ በር መሆኑን ተናግረዋል።

ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመቆጣጠር የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ከክልሉ ጸጥታ አስከባሪዎች እንዲሁም ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንና ከአገር መከላከያ ሠራዊት ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑን አመልክተዋል።

(ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#DIREDAWA

ትናንት እሁድ በድሬደዋ ከተማ በተቀሰቀሰ ግጭት 4 ሰዎች የመሳርያ ጥቃት እንደደረሰባቸዉ የድሬደዋ የድል ጮራ ሪፈራል ሆስፒታል ማስታወቁን የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Addis Abeba 🤝 Washington DC.

አዲስ አበባ እና ዋሽንግተን ዲሲ "የእትማማች ከተማነት" ስምምነታቸውን በአዲስ መልክ ለማደስ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ። ስምምነቱን ኢ/ር ታከለ ኡማና የዋሽንግተን ዲሲ ከንቲባ ሙሪየል ቦውሰር ተፈራርመዋል፡፡ ሁለቱ ከተሞች በኢኮኖሚ፣ ጤና፣ የባህል ልውውጥና አረንጓዴ ልማት ላይ በጋራ ለመስራት ተሰማምተዋል፡፡ በኢኮኖሚው ዘርፍ ላይ መረጃ ለመለዋወጥና በጋራ የሚሰሩ የልማት ስራዎች ላይ ለመሳተፍ ተስማምተዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia