TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ቃጠሎው የተነሳው ከቅኔ ማህሌቱ ሳይሆን ከመቅደሱ ውስጥ ነው፡፡ ማን አስነሳው እንዴት ተነሳ ሻማ አብርቶ የወጣው ዲያቆኑ ነው ወይስ ቄሰ ገበዙ ለምን ሳያጠፉ ወጡ የሚለው ከፖሊስ ምርመራ በኋላ አብረን የምናየው ይሆናል!" - የደብሩ ዋና አስተዳዳሪ መላከ ሰላም አባ ሳሙኤል
.
.
በቀን 28/02/2012ዓ.ም ጥዋት 11 ሰአት ላይ በኮምቦልቻ መንበረ ሕይወት መድሐኒዓለም ቤተ ክርስትያን በደረሰው የእሳት ቃጠሎ ከደብሩ ዋና አስተዳዳሪ መላከ ሰላም አባ ሳሙኤል ለሚዲያ አካላት የተሰጠ መግለጫ፦

ትናንት በ27/02/2012ዓ.ም በመላው ቤተ ክርስያን የሚከበረው የታላቁ በአላችን መድሀኒዓለም የሰው ልጆችን ያዳነበት ነው፡፡ ይህን አስመለክቶ በሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናን በተገኙበት በደማቅ ስነስርአት ተከበሯል፡፡

በተጨማሪም በሀገሪቱ ላይ ባለው አለመረጋጋትና መከራ ስደትና የቤተክርስትያን ቃጠሎ አስመልከቶ ቅዱስ ሲኖዶስ በሰጠው መመርያ መሰረት አጠቃላይ በኢትዮጵያ የሚገኙ ገዳማትና አድባራት አምላካችን የመጣውን መከራ እንዲያስታግስልንና ቀጣይ ደግሞ ምእመናኑ ህወታቸውን እንዲጠብቁ ጸሎተ ምህላ ከጀመርን እነሆ ዛሬ አምስተኛ ቀናችን ነው፡፡

የማታው መርሀ ግብር ከንግሱ በአል በላይ የምእመኑ ቁጥር ብዙ ነበር፡፡ በአሉ ፖሊሶችና የፀጥታ አካላት ባሉበት ከቀኑ 11 ሰአት የጀመረው ከምሽቱ 2 ሰአት በሰላም ተጠናቋል፡፡ተረኛ የቤተክርስትያን አገልጋዮች ቁልፉን ለተረኛ ጥበቃ አስረክበው ወጥተዋል፡፡

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-08-3

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኮምቦልቻ

"በአካባቢው የነበሩ የሙስሊም ማህበረሰቦች ከኛ ጋር አብረው እየጮሁ፣ እየተጨነቁ፣ አፈርና ውሀ እየተሸከሙ እሳቱን ለማጥፋት ላደረጉት ርብርብ መድሀኒዓለም ጤና እና እድሜ ይስጥልን!" የደብሩ ዋና አስተዳዳሪ መላከ ሰላም አባ ሳሙኤል

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በወንጀለኞች የታገቱ ኢትዮያውያን ህጻናት ተለቀቁ!

(Ethiopian Embassy Pretoria SA)

በፕሪቶሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና በደቡብ አፍሪካ ፖሊስና የጸጥታ አካላት በተደረገው ከፍተኛ ጥረት በጆሐንስበርግ ከተማ በወንጀለኞች ታግተው የነበሩ ሶስት ኢትዮጵያውያን ህጻናት ዛሬ ጥቅምት 28 ቀን 2012 ዓ.ም. ተለቀው በፕሪቶሪያ ከተማ በሠላም ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል፡፡

የህጻናቱ ቤተሰብ አባላት ልጆቻቸው ከወንጀለኞች እጅ በሠላም መለቀቃቸው እጅግ እንዳስደሰታቸው የገለጹ ሲሆን፣ ኤምባሲው እና የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ላደረጉት ከፍተኛ ጥረት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ወንጀሉን የፈጸሙ አካላት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑና ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ኤምባሲው ከህጻናቱ ቤተሰቦችና ህብረተሰቡ ጋር በጥምረት ይሰራል፡፡

በዚህ አጋጣሚ በፕሪቶሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የዜጎችን መብትና ጥቅም ለማስከበር እንዲሁም በዜጎቻችን ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ወንጀለኞችን በህግ ለመፋረድ ለሚያደርገው ጥረት ህብረተሰቡ ከጎናችን እንዲቆም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

(Ethiopian Embassy Pretoria SA)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዋሽንግቶን ከንተባ ሙሪየል ቦውሰር አዲስ አበባ ገብተዋል!

ከንቲባው አ/አ ሲደርሱ ኢ/ር ታከለ ኡማና የተለያዩ የከተማዋና የፌደራል ክፍተኛ የስራ ሀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። ከከንቲባዋ ጋር ከ50 በላይ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ግለስቦች አብረው አዲስ አበባ ገብተዋል።

ከንቲባዋ በቆይታቸው የተለያዩ ጉብኝቶችን የሚያደርጉ ሲሆን አዲስ አበባና ዋሽንግተን ዲሲም የእህትማማች ከተማነት ስምምነታቸውን የሚያጠናክር ስምምነት የሚፈራረሙ ይሆናል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የነቢዩ ሙሐመድ (ሠዓወ) የልደት በዓልን አስመልክቶ ለመላው ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት።

#PMOEthiopia

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የስልጤ ዞን ምክር ቤት አቶ አሊ ከድርን የዞኑ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመ። ምክር ቤቱ 4ኛ ዙር 5ኛ አስቸኳይ ጉባኤዉን ትላንት በወራቤ ከተማ አካሂዷል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SUDAN

•የሱዳን ዩኒቨርሲቲ በአማርኛና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ሊያስተምር ነው!

•ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ዓረብኛ ቋንቋን ይሰጣል
!

በሱዳን ካርቱም የሚገኝው ኢንተርናሽናል ዩኒቨርሲቲ ኦፍ አፍሪካ በአማርኛና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ በዲግሪ ደረጃ ለማስተማር ስምምነት ላይ መድረሱ ተገለፀ። ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲም ዓረብኛ ቋንቋን በዲግሪ ደረጃ ሊሰጥ ነው።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሂዩማኒቲስ ቋንቋዎች ጥናት ጋዜጠኝነትና ኮሙዩኒኬሽን ኮሌጅ ዲን ዶክተር አማኑኤል አለማየሁ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በተገባደደው በጀት ዓመት ነሐሴ ወር ላይ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ፣ ከኮተቤ ሜትሮፖሊታን እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጣ አንድ ልዑክ ቡድን ወደ ሱዳን አቅንቷል።

ልዑኩ ከሱዳኑ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ጋር ባደረገው ውይይት የአማርኛና የአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎችን በሱዳን ዩኒቨርሲቲ እንዲሰጥና የዓረብኛ ቋንቋን ደግሞ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተጨማሪ በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ እንዲሰጥ የሁለትዮሽ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

(የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#CONGRATULATIONS

በአሁን ሰዓት "ጎንደር ዩኒቨርስቲ" የህክምና ተማሪዎቹን በደማቅ ሁኔታ እያስመረቀ ይገኛል፡፡ በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የተማሪ ወላጆች፣ የዩኒቨርሲቲው አመራሮችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine
#ደሴ

በህገ ወጥ መንገድ 19 ወጣቶችን ወደ አረብ ሀገር ለማስወጣት የሞከሩ ግለሰቦች ደሴ ከተማ ላይ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ። ህጻናትና ወጣቶችን ወደ የቤተሰቦቻቸው ለመመለስ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑንም ፖሊስ ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
🕌 እጅግ የምናከብራችሁና የምንወዳችሁ ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የእስልምና እምነት ተከታዮች የሆናችሁ ቤተሰቦቻችን እንኳን 1 ሺህ 494ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ በዓሉ የሰላም፣ የመረዳዳት የመደጋገፍ በዓል እንዲሆንልን እንመኛለን መልካም በዓል🕌

#TIKVAH_ETH

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HappeningNow

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሰላማዊ መማር ማስተማርን በተመለከተ ከጅማ ከተማ ማህበረሰብ ጋር ውይይት እያካሔደ ይገኛል!

ጅማ ዩኒቨርሲቲ “የ2012 ዓ.ም ሰላማዊ መማር ማስተማር ሒደትን ማረጋገጥ” በተመለከተ ከጅማ ከተማ ማህበረሰብ ጋር በግብርና እና እንሰሳት ህክምና ኮሌጅ አዳራሽ ውይይት እያካሔደ ይገኛል፡፡

በውይይቱም የዩኒቨረርሲቲው የማኔጅመንት እና የካውንስል አባላት፣ የጅማ ከተማ መስተዳድር የስራ ሐላፊዎች፣ ከአባገዳዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የሐገር ሽማግሌዎች፣ ቄሮዎች እና ቃሬዎች በ2012 ዓ.ም ሠላማዊ መማር ማስተማር ሒደት ውይይት ላይ ተሳታፊዎች ናቸው፡፡

ውይይቱን እየመሩ የሚገኙት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ዩኒቨርሲቲው መደበኛ ስራውን እንዲፈጽም ሰላም ቀዳሚ መሆኑን አንስተው ሁሉም ተሳታፊዎች የበኩላቸውን እንዲወጡ አጽንኦት በመስጠት ውይይቱን እንዲያስጀምሩ ለከተማ መስተደድሩ ከንቲባ እድሉን ሰጥተዋል፡፡

የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ መክዩ መሐመድ በቡኩላቸው በመላው ሐገሪቱ የሚገኙ አባቶችና እናቶች ልጆቻቸውን አስረክበውናል፤ በመሆኑም የልጆቻችን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ሐላፊነት አለብን በማለት ከቀበሌ አመረር ጀምሮ፣ የከተማው መስተዳድር፣ የሐይማኖት ተቋማት የየድርሻቸውቸን ወስደው መስራት እንዳለባቸወው በመግለጽ ውይይቱን ለተሳታፊዎቸ ክፍት አድርገዋል፡፡

(ጅማ ዩኒቨርሲቲ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቤንች ሸኮ ዞን ምክር ቤት አቶ ፍቅሬ አማንን ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመ። ምክር ቤቱ ሹመቱን የሰጠው ትላንት በጀመረው አራተኛ ዙር ሰባተኛ ዓመት አስቸኳይ ጉባኤ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የ2019 የሰላም ኖቤል ሽልማትን ተከትሎ በደቡብ አፍሪካ የሚታተመው The Diplomatic Society መጽሔት በኖቬምበር 2019 እትሙ ጠቅላይ ሚኒስትሩን የፊት ገጽ ሽፋን ሰጥቷቸዋል፡፡ ሽልማቱን አስመልክቶ በኢፌዴሪ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተደረገው አከባበር በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማሪያም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩን አካታች፣ ውጤታማ፣ ለህዝባቸው ቅርብ የሆኑና ለምስራቅ አፍሪካ ሰላም የሚተጉ በማለት የገለጹትን በማስቀደም ዘገባውን ጀምሯል፡፡ የእለቱን እንግዶች መልዕክትም አጠቃሎ አቅርቧል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNews

በወላይታ እና ሲዳማ ዞኖች መካከል እልባት ባላገኙ 8 ወረዳዎች የምርጫ ጣቢያ እንዳይቋቋም ከስምምነት ተደረሰ የሚለው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

በወላይታ እና ሲዳማ ዞኖች መካከል እልባት ባላገኙ 8 ወረዳዎች ላይ የህዝበ ውሳኔ ድምጽ መስጫ ምርጫ ጣቢያ እንዳይቋቋም ከስምምነት ተደረሰ ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን የምርጫ ቦርድ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 አረጋግጧል።

የቦርዱ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ቦርዱ የሚያውቀው እንዲህ አይነት ስምምነት የለም፤ ጭምጭምታዎችንም ቦርዱ አይሰማም ብለዋል።

(ETHIO FM- ትዕግስት ዘላለም)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዕርቀ ሠላም ሥነ ስርዓት እየተከናወነ ነው!

በሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ፣ ማጀቴ፣ ሸዋ ሮቢትና አካባቢው እንዲሁም በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ጅሌ ጥሙጋ እና አካባቢው ተከስተው የነበሩ ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፍታት የዕርቀ ሠላም ሥነ ስርዓት እየተከናወነ ነው። የእርቅ መድረኩ ከሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ ሰዎች በተገኙበት በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ አላላ ቀበሌ ላይ እየተከናወነ የሚገኝ መሆኑን አብመድ ዘግቧል።

(AMMA)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በቃሉ ወረዳ #ደጋንና #ገርባ አካባቢዎች ባሉ ቀበሌዎች የሰብል ማሰባሰብ ተግባግ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ተሳታፊወችም፦

• የደሴ ከተማ ኡለሞች ምክር ቤት እና የደሴ ከተማ እስልምና ቦርድ

• የደሴ ከተማ ሙስሊም ወጣቶች ማህበር

• የወሎ ኡለሞች ምክር ቤትና የወሎ እስልምና ቦርድ

• ሰላም የኮምቦልቻ ሙስሊም ወጣቶች ማህበር

• ወሎ ዩንቨርሲቲ

• የሀርቡ ሙስሊም ወጣቶች የዳእዋ ማእከል

• አማራ ብረታ ብረት

• የወሎ ኮምቦልቻ እግር ኳስ ክለብና ደጋፊ ማህበር

• የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር

• የኮምቦልቻ መሠናዶ ተማሪወችና መምህራን ተሳትፎ በማድረግ መጠነ ሰፊ የሰብል ማሰባሰብ ስራ እየሠሩ ይገኛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በትግራይ ደቡባዊ ዞን አንበጣ መንጋን ከመከላከሉ በተጓዳኝ የደረሰ "ሰብልን የመሰብሰቡ" ስራ #ተጠናክሮ ቀጥሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"ቃጠሎው የተነሳው ከቅኔ ማህሌቱ ሳይሆን ከመቅደሱ ውስጥ ነው፡፡ ማን አስነሳው እንዴት ተነሳ ሻማ አብርቶ የወጣው ዲያቆኑ ነው ወይስ ቄሰ ገበዙ ለምን ሳያጠፉ ወጡ የሚለው ከፖሊስ ምርመራ በኋላ አብረን የምናየው ይሆናል!" - የደብሩ ዋና አስተዳዳሪ መላከ ሰላም አባ ሳሙኤል . . በቀን 28/02/2012ዓ.ም ጥዋት 11 ሰአት ላይ በኮምቦልቻ መንበረ ሕይወት መድሐኒዓለም ቤተ ክርስትያን በደረሰው የእሳት…
ከደ/ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ወንጀል ምርመራ ዋና የስራ ሂደት ኮማንደር ለማ ተስፋየ በኮምቦልቻ ከተማ ቀበሌ 01 የመንበረ ህይወት መድሀኒያለም ቤተ-ክርስቲያን ቃጠሎ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ፦

ኮማንደር ለማ ተስፋየ የቤተ-ክርስቲያኑን ቃጠሎን በተመለከተ እንደተናገሩት በቀን 27/2/2012 ከሌሊቱ 11፡30 በውጭ ቤቱ ተዘግቶ ቤተ-መቅደስ ውስጥ የእሳት ቃጠሎ ደርሷል ብለዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ በወቅቱ ጥሪ የተደረገላቸው የፀጥታ ሀይልና ሌሎች የአደጋ ተከላካይ ሀይሎች ተረባርበው ለማጥፋት ችለዋል ብለዋል፡፡

እንደ ኮማንደር ገለፃ በቤት ውስጥ ያሉ አንዳንድ እቃዎች በቃጠሎው ምክንያት የወደሙ በመሆኑ የኮምቦልቻና የደቡብ ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ መርማሪዎች በጋራ በመሆን የቃጠሎውን መነሻ ሁኔታ በማጣራት ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡ የቃጠሎው መነሻ ከጥንቃቄ ጉድለት የተነሳ በመሆኑ መጠቀሚያ የሆኑ ጧፍና ሻማ በጥንቃቄ ካለማጥፋት የተነሳ የተከሰተ ክስተት የሚመስል መሆኑን በአብዛሀኛው ምርመራው ያመላክታል ብለዋል፡፡

ቃጠሎው የሚያሳየው በወቅቱ በተገቢው መንገድ እሳቱን አጥፍቶ አለመሄድ ላይ ጉድለት እንደነበረና ሀላፊነትን በአግባቡ ካለመወጣት የተነሳ በአጠቃላይ ከቤተክርስቲያኗ ውጭ ከሌሎች ጥቃት እንዳልተሰነዘረባት ለመረዳት ተችሏል ብለዋል፡፡ ለዚህም ትናንትና ማታ እስከ 2፡30 ድረስ ሲጠቀሙበት ቆይቶ ምዕመናኑ ከዚያ ወጥቶ እና አድሮ ሌሊት ላይ ምንም የተሰበረ በርና መስኮት አለመኖሩ ተረጋግጧል፡፡

በመሆኑም ምንጩን ለማግኝት የተለያየ ፎቶና መረጃዎችን እየሰበሰቡ መሆንኑ በመግለጽ በተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገጽ እንደሚባለው የገዘፈና ከሌሎች ወገኖች ጥቃት ያልደረሰ መሆኑን ለመረዳት ችለናል ብለዋል፡፡ በቃጠሎው የደረሰውን ጉዳት በማጣራት በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚያሳውቁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

@tikvahethiopia
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኙ ተቋማት ከግዥ አዋጅ መመሪያ ውጭ የተፈፀመ ከ529 ሚሊየን ብር በላይ በኦዲት ተገኝቷል!

- ለአንድ ኃላፊ የግል ችግር ዕርዳታ በሚል 125 ሺህ ብር ተሰጥቷል

- ከደንብና መመሪያ ውጭ ከ532 ሺህ ብር በላይ አበልና ደመወዝ ተከፍሏል

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኙ ተቋማት ከግዥ አዋጅ መመሪያ ውጭ የተፈፀመ ከ529 ሚሊየን ብር በላይ ክፍያ መኖሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ባቀረበው የኦዲት ሪፖርት መሰረት፤ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2010 ዓ.ም ድረስ በ27 ተቋማት ላይ በተደረገ የኦዲት ምርመራ 529 ሚሊየን 105 ሺህ ብር ከግዥ አዋጅ መመሪያ ውጭ ክፍያ መፈፀሙ ተረጋግጧል።

በተለይ የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ትልቁን ድርሻ በመያዝ የ467 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ከመመሪያ ውጭ ክፍያ የፈፀመ ተቋም ሆኗል። የትራንስፖርት ባለሥልጣን እና መንገዶች ባለሥልጣን በ2010 ዓ.ም በድምሩ ከ40 ሚሊየን ብር በላይ ከአዋጅ ውጭ ክፍያ መፈፀማቸው በሪፖርቱ ቀርቧል።

(EPA)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
(ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር)

በምስራቅ ክፍለ ከተማ አንድ የምርጫ ጣቢያ አከባቢ ሲጠጉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በፀጥታ ሀይል ቁጥጥር ስር ዋሉ!

የሲዳማ ብሔር በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱ ተረጋግጦ ህዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የሚካሄድ መሆኑን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት የቅስቀሳ ስራ የተጀመረ ከመሆኑ በተጨማሪ በሀዋሳ ከተማ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች በሰለጠነ፣ በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የድምፅ ሰጪዎች የምዝገባ ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

እነዚህ ስራዎች በሰላማዊ መንገድ ከመሄዳቸው ባሻገር የከተማው ህብረተሰብ ባደረጋቸው ውይይቶች ለሰላም ቅድሚያ የሚሰጥ መሆኑን እና ይህ የሲዳማ ብሔር በክልል የመደራጀት ህዝበ ውሳኔ ህግን ተከትሎ ሰላማዊ እና በህዝብ ዘንድ ተዓማኒነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ከመግለፅ አልፈው በአሁኑ ወቅት በተግባር እያሳዩ ይገኛል፡፡

በሀዋሳ ከተማ በ165 የምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ምዝገባ ስራ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እየተከናወነ ባለበት በአሁኑ ወቅት ካሉት የምርጫ ጣቢያዎች አንዱ በሆነው በምስራቅ ክፍለከተማ ቴሶ ቀበሌ መንደር አራት የምርጫ ጣቢያ በምሽት ወደ ምርጫ ጣቢያ ለመጠጋት የሞከሩ ግለሰቦች በተደራጀ የፀጥታ ሀይል በቀላሉ በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው፡፡

ወደ ምርጫ ጣቢያ መቅረባቸው ለምን ዓላማ እንደሆነ ተጣርቶ የሚገለፅ ቢሆንም የህዝበ ውሳኔው ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ህብረተሰቡ እና የፀጥታ ሀይሉ በቅንጅት እየሰሩ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ምንም አይነት ሂደቱን ሊያደናቅፍ የሚችል እንከን እንደማይኖርና እንደሌለ በመጠቆም ነዋሪው ያለምንም ስጋት የምዝገባ ሂደቱን መቀጠሉን እንገልፃለን።

(ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት)