TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Election2012

በባህር ዳር ከተማ ህዝባዊ ውይይት ያደረጉት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ አመራሮች ትላንት አመሻሹን ጎንደር ከተማ ገብተዋል፤ ጎንደር ሲደርሱም ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፤ ከደቂቃዎች በኃላ ከጎንደር ነዋሪዎች ጋር ህዝባዊ ውይይት እንደሚደረግም ሰምተናል።

PHOTO : SINTAYEHU CHEKOL
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Election2012

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባ ህትመት እና ቁሳቁሶችን ግዥ አጠናቆ ከፍተኛ ጥበቃ ባለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎ መጋዘን አስገብቶ ያጠናቀቀ ሲሆን የቁሳቁስ ድልድል ስራን በቅርቡ ይጀምራል፡፡

#NEBE
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ የክልሉ ምክር ቤት ስብሰባን ሲከፍቱ እንደተናገሩት፤ ቀጣዩ ምርጫ "ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊ እና ነጻ" እንዲሆን፤ በቀጣይ ወራት የመንግስት ቀዳሚ እና ዋነኛ ስራው መሆን የሚገባው "ሰላምን ማረጋገጥ ነው" ብለዋል።

#EthiopiaElection
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ባዘጋጀው እና የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ተወካይ ወ/ሮ ሄተር ፈላይን በተገኙበት በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ባለው የለውጥ እንቅስቃሴ እና ምርጫ 2012 አስመልክቶ ውይይት ተካሂዷል፡፡

አዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል በተካሄደው እና ዓላማው በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ የፖለቲካ እና የምርጫ ዝግጅት ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መረጃ ለመሰብሰብ እንደሆነ በተገለጸው በዚሁ የውይይት መድረክ፣ የምርጫውን የግዜ ሰሌዳ፣ በተፎካካሪ ፓርቲዎች እና በገዥው ፓርቲ መካከል ያለው ግንኙነት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያጋጥሟቸው ችግሮች፣ የምርጫ ቦርድ ዝግጅት እና አቅም፣ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የሀሳብ ልውውጥ ተደርጓል፡፡

በውይይቱ የተገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች አጠቃላይ የለውጥ ሂደቱን እና ምርጫ 2012 አስመልክቶ ያጋጠሟቸውን ችግሮች እንዲሁም ገዥው ፓርቲ በተፎካካሪ ፓርቲዎች ላይ በማድረስ ላይ ነው ያሏቸውን ልዩ ልዩ ጫናዎች ለኤምባሲው ተወካዮች ገልጸዋል፡፡ የመንግስት ሀብትን እና ሚዲያን በብቸኝነት መጠቀም ፓርቲዎቹ በገዠው ፓርቲ ላይ ካነሷቸው ችግሮች መካከል ይገኙበታል፡፡

የፓርቲዎቹ ተወካዮች የአሜሪካ መንግስት ከሁሉም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በእኩል ርቀት ላይ ሊቆም እና በተለይ ለገዢው ፓርቲ የተለየ ድጋፍ ማድረግ የፖለቲካ ሜዳውን እና በዚህ አመት በሚካሄደው ምርጫ ውጤት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚኖረው ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

More https://telegra.ph/ETH-02-21-2

#FreedomandEqualityParty

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Election2012

በዛሬው የሂልተን ሆቴል የውይይት መድረክ ላይ የተሳተፉ ፓርቲዎች፦

1. ኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ)
2. አማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን)
3. ኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)
4. አረና ትግራይ ለዴሞክራሲ እና ሉአላዊነት (አረና)
5. ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)
6. የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)
7. ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ)

ምንጭ፦ ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Election2012

የትግራይ ዴሞክራቲክ ፓርቲ /ትዴፓ/ በመጪው አገራዊ ምርጫ በትግራይ ክልል በዴሞከራሲያዊ መንገድ መወዳደር የሚያስችል እንቅስቃሴ ለማድረግ ተቸግሬያለሁ አለ፡፡

የፓርቲው ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሄ እንደገለፁት ፓርቲያቸው በመጪው አገራዊ ምርጫ በክልል ደረጃ ተወዳድሮ ለማሸነፍ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል። ነገር ግን በአካባቢው ከሚንቀሳቀሰው ህወሃት የተለያዩ ችግሮች እየገጠማቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ፓርቲው በክልሉ በመቀሌ ብቻ ቅርንጫፍ መክፈቱን የገለጹት ዶክተር አረጋዊ ፤ በአብይአዲ፣ በሽሬና በአድዋ ቅርንጫፎች ለመክፈት ሙከራ ማድረጉንም ጠቅሰዋል።

ይሁንና በትግራይ ክልል ነጻና ፍትሃዊ የምርጫ እንቅስቃሴ ለማድረግ መቸገሩንና አባላቱም ለእስራት፣ ለድብደባና ለእንግልት እየተዳረጉ መሆኑን ጠቁመዋል። “ይህ ባለበትና ምርጫ ቦርድ ባለሙያዎች ባልመደበበት ሁኔታ የጊዜ ሰሌዳ አውጥቶ ምርጫ ለማከናወን ማቀዱ ተገቢ አይደለም” ነው ያሉት።

ችግሩን በተመለከተ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣ ለምርጫ ቦርድና ለጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በደብዳቤ በማሳወቅ ምላሽ እየተጠባበቁ መሆኑንም ዶክተር አረጋዊ አስረድተዋል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

የኦሮሞ ፌደራሊት ኮንግረስ ከህዝብ ጋር የሚያደርገውን ውይይት ቀጥሏል። በትለንትናው እለት የፓርቲው አመራሮች በሰበታ ከተማ ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር ህዝባዊ ውይይት አድርገዋል።

PHOTO : JAWAR MOHAMMED
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

የመድረክ አባል የሆነው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ /ሲአን/ በሀዋሳ ከተማ ሚሊኒየም አዳራሽ ከደጋፊዎቹና አባላቱ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ እየተወያየ ይገኛል። በህዝባዊ የውይይት መድረኩ ላይ የመድረክ ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ተገኝተዋል።

PHOTO : SMN
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአብን ህዝባዊ ውይይት... የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የአዲስ አበባ ማስተበባበሪያ ፅ/ቤት በመጪው እሁድ የካቲት 15 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ አባላቱና ደጋፊዎቹ ጋር አልማዝዬ ሜዳ አጠገብ በሚገኘው በቄራ ወረዳ 5 ሸማቾች ማኅበር አዳራሽ በንቅናቄው የማታግያ አጀንዳዎች እና በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ዙሪያ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ሕዝባዊ ውይይት…
#Election2012

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ፅሕፈት ቤት ዛሬ የካቲት 15 ቀን 2012 ዓ.ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ አባላቱና ደጋፊዎቹ ጋር አልማዝዬ ሜዳ አጠገብ በሚገኘው በቄራ ወረዳ 5 ሸማቾች ማኅበር አዳራሽ ውይይት አድርጓል።

ውይይቱን የመሩት የአብን የኢኮኖሚ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ካሱ ኃይሉ የአማራ ሕዝብን ውስጣዊ አንድነቱን በማጠናከር ለመብቶቹ መከበር ሊታገል እንደሚገባ ገልፀዋል።

ኃላፊው አክለውም አብን በቀጣይ አገራዊ ምርጫ በማሸነፍ በአማራ ሕዝብ ላይ የተጋረጠውን የሕልውና አደጋ በዘላቂነት ለመቅረፍ የሚረዳ አደረጃጀትና መዋቅር በመላ አገሪቱ እየዘረጋ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የንቅናቄውን የማታግያ አጀንዳዎች እና በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ዙሪያ በንቅናቄው ከፍተኛ አመራሮች ቀርቦ በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

ምንጭ፦ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሟሟላት የሚገባቸውን ዝርዝር ጉዳዮች እስከ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ/ም እንዲያሟሉ አሳስቧል።

በፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና ምርጫ አዋጅ ቁጥር 1162 / 2011 መሰረት በቦርዱ ሀገር አቀፍ እና የክልል ፓርቲዎች ማሟላት ያለባቸውን ግዴታዎች ለማስፈጸም የወጣው መመሪያ ቁጥር 3/2012 መሰረት የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ማሟላት የሚገባቸውን ዝርዝር ሁኔታ የሚያስረዱ ሰነዶች ማዘጋጀቱ እና ለፓርቲዎች እንዲደርሳቸው ማድረጉ አስታውሷል፡፡

ለእያንዳንዱ ፓርቲም በደብዳቤ ማሟላት የሚገባቸውን ሁኔታዎች ሁሉ እስከ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ/ም ድረስ አሟልተው እንዲያቀርቡ ቦርዱ አስታውቋል። ቦርዱ እስካሁን ሰነዶቻቸውን ያስገቡ ፓርቲዎች ቁጥር ዝቅተኛ መሆኑን በዛሬው ዕለት ገልጿል።

በመሆኑም ማሟላት የሚጠበቅባቸው ዝርዝር ሁኔታዎችን የሚያስረዱ ሰነዶች የደረሳቸው የፓለቲካ ፓርቲዎች በሙሉ መጋቢት 3 ቀን 2012 ከመድረሱ በፊት ማሟላት የሚገባቸውን በሙሉ አሟልተው የምዝገባ ስርአቱን እንዲጀምሩ አሳስቧል።

ምንጭ፡-የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia