TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DireDawa

የድሬዳዋ ፖሊስ ማንኛውም ድሬዳዋ ከተማና ገጠር ውስጥ የሚገኝ ግለሰብ በእጁ የሚገኘውን የጦር መሳሪያ ፍቃድ ቢኖረውም ባይኖረውም በአቅራቢያው በሚገኝ የቀጠናው ፖሊስ ጣቢያ ድረስ በግንባር በመሄድ ማስመዝገብ እንዳለበት በጥብቅ አሳስቧል።

ድሬዳዋ ፖሊስ ፥ ከህዳር 2 ቀንእስከ ህዳር 3 ቀን 2014 ዓ.ም ባሉት 2 ቀናት ውስጥ ማንኛውም ግለሰብ በእጁ የሚገኘውን የጦር መሳሪያ ሳያስመዘግብ የቀረ ከሆነ በህግ አግባብ ተገቢውን እርምጃ እንደሚወሰድ ገልጿል፡፡

@tikvahethiopia
#DireDawa

በድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ እና ገጠር የሚኖር ማንኛውም ግለሰብ በእጁ የሚገኝ የጦር መሳሪያ በድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ እና ገጠር በሚገኙ በሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች በግንባር ቀርቦ ማስመዝገብ እንዳለበት የድሬዳዋ ፖሊስ ማሳሰቢያ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

ዜጎች እጃቸው ላይ የሚገኝ ጦር መሳሪያ እንዲያስመዘግቡ የተቀመጠው ቀነ ገደብ ዛሬ ህዳር 6 ቀን 2014 ዓ/ም ይጠናቀቃል።

@tikvahethiopi
#DireDawa

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ወደ ትግል ሜዳ ለመዝመት ተዘጋጅቻለሁ ብለዋል።

ከንቲባው ዛሬ አመሻሹን በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፥ " ሀገርን በመሥዋዕትነት መምራት ከእኛ ይጠበቃልና፤ እኔም ከሌሎች ወንድሞቼ ጋር ወደ ትግሉ ሜዳ ለመዝመት ተዘጋጅቻለሁ። በግንባር ተገኝተን ያዘጋጀነውን ስንቅ እናቀብላለን፤ ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ ጀግናው ሠራዊታችንን በወኔ እናበረታታለን " ብለዋል።

የአስተዳደሩ የፀጥታ ኃይሎችና በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፤ ከመቼውም ጊዜ በላይ የድሬዳዋን ሠላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ፤ የልማትና አስተዳደራዊ ሥራዎችን በሙሉ አቅማቸው ለማከናወን ተዘጋጅተዋል ሲሉም አሳውቀዋል።

አቶ ከድር ጁሀር ፥ " መላው ነዋሪዎች አካባቢያችሁን በመጠበቅ፤ ሠራዊቱን በመደገፍና፤ ወደ ግንባር በመዝመት፤ እንዲሁም በፀሎት ከጎናችን እንድትሆኑ ጥሪ አቀርባለሁ። ያለጥርጥር ኢትዮጵያ ታሸንፋለች " ሲሉ ነው በተረጋገጠ ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ያሰፈሩት።

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደግንባር ዘምተው ሰራዊቱን እንደሚመሩ ካሳወቁ በኃላ የተለያዩ ባለስልጣናት ፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ታዋቂ የስፖርት ሰዎች ጨምሮ ሌሎችም ወደ ግንባር እንደሚዘምቱ እገለፁ መሆናቸው ይታወቃል።

#Teddy

@tikvahethiopia
#DireDawa

በድሬዳዋ በእርሻ ማሳ ውስጥ አደገኛ እፅ ተከለው የተገኙት ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ።

የድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ አደገኛው የካናቢስ እጽ በእርሻ ማሳቻው ላይ ተክለው የተገኙ 2 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አሳውቋል።

እጹ ሊያዝ የቻለው በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 08 ገንደ- ገበሬ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ ተጠርጣሪ ግለሰብ በእርሻ ማሳ ውስጥ የተተከሉትን አደገኛ እፅ በመኮትኮት ላይ እንዳለ መሆኑ ተገልጿል።

ፖሊስ ወደ ቦታው የደረሰው በአካባቢው ላይ ሌላ የወንጀል ድርጊት ተፈጽሞ ሲሆን የአካባቢው ሚሊሻዎች ግለሰቡ እያደረገ ያለውን ህገ-ወጥ ተግባር ተመልክተው ለፖሊስ ባደረሱት ጥቆማ መሰረት ሁለት ተጠርጣሪ ግለሰቦች ከተከሉት በርካታ እጽ ጋር በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ግለሰቦች ከዚህ ቀደም በከተማው ውስጥ ይሄንኑ አደገኛ እጽ የመሸጥ ስራ ከምትሰራ ሌላ ተጠርጣሪ ግለሰብ ጋር ግንኙነት በማድረግ ግለሰቧ አደገኛ የካናቢስ እጽ ስትሸጥ ተገኝታ ምርመራ ተጣርቶ ውሳኔ ማግኘቷን ፖሊስ ገልጿል።

በድሬዳዋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ የመጣውን አደገኛ የካናቢስ እጽ ዝውውርን ለመግታት ሰፊ ስራ እየሰራ መሆኑ ያሳወቀው ፖሊስ ወጣቱን የህብረተሰብ ክፍል እየጎዳ የሚገኘውን አደገኛ እጽ ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ መረጃ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪ አቅርቧል።

ምንጭ፦ ድሬ ፖሊስ

@tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

#Amhara, #Gashena

ጋሸና ከተማ ተቋርጦባት የቆየውን የኤሌክትሪክ ኃይል ዛሬ ማግኛቷን ተገልጿል። በአካባቢው ያሉ ሌሎች ከተሞችን የመካከለኛና ዝቅተኛ መስመር ጥገና እየተካሄደ ሲሆን በነገው እለት ፋላቂት፣ ገረገራ፣ ኮን እና በአካባቢው ያሉ ከተሞች የተቋረጠባቸውን ኃይል መልሰው ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

#Afar

በአፋር በክልል በህወሓት ወረራ ተቋርጦ የነበረው መደበኛ የመንግስት ስራ ከነገ ጀምሮ እንደሚጀመር የክልሉ የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታውቋል።

#Amhara

በአማራ ክልል በህልውና ዘመቻው ምክንያት ለአንድ ወር በላይ በከፊል ተዘግተው የቆዩት የአማራ ክልል ፍ/ቤቶች (ከጥቂቶቹ በስተቀር) ዛሬ መደበኛ ስራቸውን ጀምረዋል።

#AddisAbaba

በአ/አ ህገ ወጥ መሬት ወረራ በተሳተፉ 88 አመራሮች እና ሰራተኞች ላይ ፓለቲካዊና አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን የአ/አ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል። ከ26 ሺ ካሬ ሜትር በላይ ስፋት ያላቸውና በህገ ወጥ የመሬት ወረራ የተያዙ 671 ይዞታዎች ካርታቸው እንዲመክን ተደርጎ ወደ መሬት ባንክ መመለሳቸው ሪፖርት ተደርጓል።

#DireDawa

በድሬዳዋ ኤርፖርት የጦር መሳሪያ ፍንዳታ ተከሰተ ተብሎ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተላለፈው መረጃ ሐሰት መሆኑ የድሬዳዋ ሲቪል አቪየሺን ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አሳውቋል። ትላንት ከቀኑ 10:50 ላይ የአውሮፕላኑን አቅጣጫና የርቀት መለኪያ፣ የኃይል መቆጣጠሪያና የመገናኛ መሳሪያ፣ በኤሌክትሪክ ኃይል መጨመር (high voltage) ምክንያት በተከሰተ ቃጠሎና ፍንዳታ የኃይል መቆጣጠሪያ ስርዓቱ ላይ አደጋ ደርሷል። በኃላ ችግሩን በማስተካከል ዛሬ ጥዋት 1፡00 ሰዓት ጀምሮ የአውሮፕላን በረራ እንዲካሄድ ተደርጓል።

@tikvahethiopia
#DireDawa

የቀድሞ የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ 3.9 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የመኪና ስጦታ ተበረከተላቸው።

ለቀድሞ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ አስተዳደሩ በአመራርነት ዘመናቸው ላበረከቱት መልካም ስራዎች የምስጋና ኘሮግራም ተካሄዶል።

በዚሁ ፕሮግራም ላይ 3.9 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ዘመናዊ የመኪና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

የአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጆሀር በምስጋና ፕሮግራሙ ላይ " ጥቂት ብንዘገይም፤ እጅግ ለምንወዳቸው የቀድሞ ከንቲባችን እና ወንድማችን አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ ዛሬ ያደረግነው ሽኝትና የሰጠነው ስጦታ፤ በአመራርነት ዘመኑ ካደረጉት አሰተወፅኦ አንፃር ለሳቸው ያንስባቸዋል እንጂ አይበዛም " ሲሉ ተናግረዋል።

ስጦታው በባለሀብቶች ተሳትፎ የተበረከተ መሆኑ ተገልጿል።

የቀድሞው ከንቲባ ለሶስት ዓመት ሙሉ ከተማዋ የነበረባትን የፀጥታ ችግር የፀጥታ አካላትን በማሰባሰብ ፣ አመራሮችን በማቀናጀት የከተማዋ ሰላም በአስተማማኝነት እንዲረጋገጥ እና ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ አመራር የሰጡ ጠንካራ መሪ እንደነበሩ ተገልጿል።

በትላንትናው ዕለት ከቀድሞ ከንቲባው በተጨማሪ የድሬዳዋ ፀጥታ አካላት ፣ የፀጥታ ምክር ቤት አባላት ከ25 ሺህ ብር እስከ 100 ሺህ ብር በየደረጃው ተሸልመዋል። አጠቃላይ ሽልማቱ ከ700 ሺህ ብር በላይ እንደሆነ ተመላክቷል።

ብሩ የተገኘው ከባለሀብቶች ሲሆን የመንግስት በጀት እንዳልተነካ ተገልጿል። የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተጠይቀው ቀና ምላሽ ለሰጡ የከተማው ባለሀብቶች ምስጋና አቅርቧል።

@tikvahethiopia
#DireDawa

1443 ኛው የረመዳን ፆም ወር የአፍጢር መርሀ-ግብር በአሁን ሰአት በለገሀር አደባባይ እየተካሄደ ይገኛል።

በዚሁ የአፍጢር መርሀ-ግብር ላይ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች ፣ የሀይማኖት አባቶች እና ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

ፎቶ ፦ የድሬዳዋ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#DireDawa

" በሲሚንቶ ላይ በሚታየው ከከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ጋር በተያያዘ ማህበረሰቡ ቤት መገንባት እስከማቆም ደርሷል ፥ አንዳንድ ፕሮጀክቶችም እየዘገዩ ነው " - አቶ ከድር ጁሃር

በሀገራችን የተለያዩ ከተሞች በየጊዜው በተለያዩ የሸቀጣ ሸቀጥ ምርቶች ፣ የምግብ ፍጆታዎች እንዲሁም በኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች ላይ ሲሚንቶን ጨምሮ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ እየተስተዋለ እንደሚገኝ ይታወቃል።

ድሬድዋ ከተማም አንዷ በዋጋ ንረት ጫና እየደረሰባት ያለች ከተማ ናት፤ በተለይ ሲሚንቶን ጨምሮ የኮንስትራክሽን እቃዎች የዋጋ ንረት ነዋሪዎችን ክፉኛ እየፈተነ ነው።

ከተማ አስተዳደሩ፤ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን የገለፀ ሲሆን የስሚንቶ ፋብሪካ (ናሽናል ሲሚንቶ) እዛው ድሬዳዋ እያለ የዋጋ ንረቱ አልቀመስ ማለቱ ፥ ነዋሪው ቤት መስራት እስከማቆም መድረሱን ፣ አንዳንድ ፕሮጀክቶችም እየዘገዩ መሆኑ አስረድቷል።

እዛው ድሬዳዋ ላይ የስሚንቶ ፋብሪካ ያለው ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግስ አ.ማ (ናሽናል ሲሚንቶ) በድሬዳዋ የሚስተዋለውን ከፍተኛ የሆነ የሲሚንቶ ዋጋ ንረት ለመቆጠር ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አስታውቋል።

የድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የሚያመርተውን የሲሚንቶ ምርት በ440 ብር ለአከፋዮች ቢያቀርብም በአስተዳደሩ ታች ላለው ቸርቻሪዎችና ማህበረሰቡ ጋር ሲደርስ ግን አላግባብ በሆነ ጭማሪ ከ700 ብር በላይ እየተሸጠ እንደሚገኝ አሳውቋል።

ችግሩን ለመፍታትና ለተጠቃሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ የድሬዳዋ አስተዳደር ለይቶ ባደራጃቸውና ህጋዊ የሲሚንቶ ችርችሮ ሻጮችና ሲሚንቶ በቀጥታ ለተጠቃሚው ማህበረሰብ የማድረስ ስራል ብሏል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Dire-Dawa-04-09

@tikvahethiopia
#DireDawa

#ማሻሻያ

በድሬዳዋ አስተዳደር እሁድ ጠዋት ለትራንስፖርት እንቅስቃሴ ዝግ እንዲሆን የተወሰነው ውሳኔ ላይ ማሻሻዮች ተደርጎበታል።

በድሬዳዋ አስተዳደር በሳምንቱ መጨረሻ እሁድ ላይ ከጠዋት 12 ሰአት እስከ 4 ሰአት ድረስ በከተማዋ ላይ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ዝግ ከመደረጉ ጋር ተያይዞ ከዚህ ቀደም በጉዳዩ ዙሪያ የተለያዩ ጥያቄዎች ሲነሱ ቆይተዋል ።

በዚሁም ጉዳይ ዙሪያ ዛሬ ከሀይማኖት አባቶች ጋር ውይይት ተካሂዷል ።

በተለይም እድሜያቸው የገፍ እናት አባቶች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እሁድ ወደ ቤተ-እምነቶች ለመሄድ የትራንስፖርት አገልግሎት ካለመኖሩ ጋር ተያይዞ በእጅጉ እየተቸገሩ ከመሆናቸው ባለፈ የጤና እክል ያለባቸው አካላትም ረጅም እርቀት በእግር ለመሄድ መቸገራቸውንም የሀይማኖት አባቶቹ በውይይቱ ላይ አንስተዋል።

ስለሆነም ማሻሻያ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር እሁድ ጠዋት በከተማዋ ላይ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ዝግ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከነዋሪው ህብረተሰብ እንዲሁም ከሀይማኖት አባቶች የተነሱትን ጥያቄዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት እሁድ ጠዋት ሙሉ ከተማው ለትራንስፖርት ክፍት እንዲሆን መወሰኑን አሳውቀዋል።

ነገር ግን ከኮኔል ድልድይ አንስቶ ከዚራ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ለትራንስፖርት ዝግ እንደሚሆንም ከንቲባው ተናግረዋል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

ምንጭ፦ የድሬዳዋ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#DireDawa

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለቀጣይ አምስት ወር በመኖሪያ ቤት ተከራዮች ላይ ጭማሪ ማድረግም ሆነ ተከራዮችን ቤት ማስለቀቅ እንደማይቻል ውሳኔ አሳልፏል።

ከተማ አስተዳደሩ ፤ በመኖርያ ቤት ተከራዮች ላይ ምክንያታዊ ያልሆነ እና አለአግባብ ከፍተኛ ጭማሪ እየተደረገ መሆኑን በተለያየ መንገድ አረጋግጫለሁ ብሏል።

ይህን ተከትሎ ነው ለ 5 ወራት ተከራዮች ላይ ጭማሪ ማድረግ ሆነ ከተከራዩት ቤት ማስወጣት እንደማይቻል ውሳኔ ያሳለፈው።

#ዶቼቨለ

@tikvahethiopia