TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
211 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እንድታውቁት

የተሽከርካሪ ቀረጥና ታክስ አወሳሰን !

አንድ ተሽከርካሪ ወደ ሀገር ሲገባ ቀረጥና ታክስ የሚታሰበው ፦

- በተሽከርካሪው ዓይነት (የቤት አውቶሞቢል፣ የህዝብ ማመላለሻ ወይም የዕቃ ማመላለሻ፣ ልዩ ልዩ)

- የተሸከርካሪዉን የመጫን አቅም (የሰው ብዛት፣ የጭነት ኪሎ መጠን)፣

- ጉልበት (ለቤት አውቶሞቢሎች) መሰረት በማድረግ እንዲሁም ClF (የተገዛበት ዋጋ + የትራንስፖርት ወጪ + የኢንሹራንስ ወጪ እና ሌሎች ወጪዎችን ጨምሮ) በሚገኘዉ ጠቅላላ ወጪ ነው፡፡

#ተገጣጥመው_ወደ_ሀገር_ውስጥ_የሚገቡ አዲስ የቤት አውቶሞቢል ተሽከርካሪዎች ጉልበታቸው እስከ 13ዐዐ ከሆነ 75.67% ሲሆን ጉልበታቸው ከ1301 እስከ 1800 ደግሞ 116.79% እንዲሁም ከ18ዐዐ በላይ ጉልበት ያላቸው ከሆኑ ደግሞ 231.9% አጠቃላይ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ምጣኔ ተጥሎባቸዋል፡፡

ሹፌሩን ጨምሮ እስከ 16 የመቀመጫ አቅም ያላቸው የሰው ማጓጓዣዎች እና እስከ 1.5 ቶን እቃ የመጫን አቅም ያላቸው የእቃ ማጓጓዣዎች አጠቃላይ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ 52.5% ሲሆን ከ16 ሰው በላይ የሚጭኑ የህዝብ ማመላለሻዎች እና ከ1.5 ቶን በላይ እቃ የሚጭኑ ተሸከራካሪዎች ደግሞ 29.5% አጠቃላይ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ ተጥሎባቸዋል፡፡

በሌላ በኩል ሀገር ውስጥ ለመገጣጠም በአምራች ድርጅቶች ወደ ሀገር የሚገቡ ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የተበተኑ (CKD/SKD) የሆኑ ተሽከራካሪዎች በተመለከተ በአዲስ ይዞታ ተገጣጥመው ወደ ሀገር ከሚገቡ ተሸከራካሪዎች በተለየ በዝቅተኛ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ የሚስተናገዱ ሲሆን በተቃራኒው #ያገለገሉ (USED) ተሽከራካሪዎች ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የኤክሳይዝ ታክስ ስለተጣለባቸው በአዲስ ይዞታ ከሚገቡ ተሸከራካሪዎች በአንፃራዊነት በጣም ከፍተኛ አጠቃላይ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ አላቸው፡፡

የተሽከርካሪው ቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ (duty paying value) በተሽከርካሪው ጠቅላላ ቀረጥና ታክስ ማስከፈያ ምጣኔ ተባዝቶ የብዜቱ ውጤት ተከፋዩ ቀረጥና ታክስ ይሆናል፡፡

እንደ ተሽከርካሪው አይነት ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የተሸከርካሪዎች ላይ እስከ #አራት_ዓይነት የቀረጥና ታክስ ዓይነት የሚጣልባቸው ሲሆን ከአምራች ድርጅቶች ውጪ የሚገቡ ተሽከርካሪዎች ከሆኑ ደግሞ በተጨማሪነት #የዊዝሆልዲንግ_ታክስ ይሰበሰባል፡፡

የቀረጥ እና የታክስ ማስከፈያ መሠረት (Tax base) የሚሆነው የእቃው ዋጋ (CIF) እና በቅድም ተከተል የሚሰላው የቀረጥ ወይም ታክስ መጠን ፦
* የጉምሩክ ቀረጥ፣
* ኤክሳይዝ ታክስ፣
* የተጨማሪ ዕሴት ታክስ፣
* ሱር ታክስ ድምር ይሆናል፡፡

የቀረጥና ታክስ መጠኑን እንዴት ተደርጎ እንደሚታሰብ ለምሳሌ ሁሉም ዓይነት ታክስ በሚመለከተው በቤት አውቶሞቢል ተሽከርካሪ በምሳሌነት እንመልከት፡፡

የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋው ብር 4ዐዐ,ዐዐዐ፣ የሲሊንደር አቅሙ 13ዐዐ የሆነ አዲስ አውቶሞቢል ወደ ሀገር ሲገባ ፦

🚘 በቅድሚያ የጉምሩክ ቀረጥ የሚሰላ ሲሆን ማስከፈያ ዋጋው በጉምሩክ ቀረጥ ምጣኔ በማባዛት የሚሰላ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ተከፋዩ የጉምሩክ ቀረጥ 400,000 × 3ዐ%(ከፍተኛው መጣኔ) = 12ዐ,ዐዐዐ ይሆናል፡፡

🚘 ቀጥሎ ኤክሳይዝ ታክስ የሚሰላ ሲሆን ስሌቱ የአውቶሞቢሉ የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ እና ተከፋዩ የጉምሩክ ቀረጥ በመደመር በኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ ማባዛት ነው፡፡ በዚህ ስሌት መሰረት ተከፋዩ ኤክሳይስ ታክስ መጠን (400,000 + 120,000) 5%= 26,000 ብር ይሆናል፡፡

🚘 በሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚሰላው ተከፋይ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ሲሆን በዚህ ስሌት የአውቶሞቢሉን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ ፣ ተከፋይ የጉምሩክ ቀረጥ እና ኤክሳይዝ ታክስን በመደመር በተጨማሪ ዕሴት ታክስ መጣኔ ይባዛል፡፡ በዚህ መሰረት የሚከፈለው ተጨማሪ ዕሴት thn (400,000 + 120,000 + 26,000) 15% = 81,9ዐዐ ብር ይሆናል፡፡

🚘 በአራተኛ ደረጃ የሚሰላው ሱር ታክስ ሲሆን ስሌቱ የአውቶሞቢሉን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ፣ ተከፋይ የጉምሩክ ቀረጥ፣ ኤክሳይዝ ታክስ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ በመደመር በሱር ታክስ መጣኔ በማባዛት ነው፡፡ በዚህ መሰረት የሚከፈለው ሱር ታክስ (400,000 + 120,000 + 26,000 +81,900) 10% = 86,190 ብር ይሆናል፡፡

🚘 ተሽከርካሪው በመደበኛ አስመጪ (ከአምራች ድርጅት ውጪ...) የሚመጣ ከሆነ በአምስተኛ ደረጃ ተከፋዩን ዊዝሆልዲንግ ታክስ ነው፡፡ ይህ ታክስ የሚሰላው የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋን በዊዝሆልዲንግ ታክስ መጣኔ በማባዛት ነው፡፡ በዚህ መሰረት ተከፋዩ የዊዝሆልዲንግ ታክስ 4ዐዐ, 000 × 3%= 12,ዐዐዐ ብር ይሆናል፡፡

በመጨረሻም የስሌት ደረጃ ሁሉም ተከፋይ ቀረጥና ታክስ የሚደመሩ ሲሆን በዚህ መሰረት መንግስት ከዚህ አውቶሞቢል የሚሰበስበው ቀረጥና ታክስ ስሌት 120,000 + 26,000 + 81,900 + 86,190 + 12, 000= 326,090 ብር ይሆናል፡፡

#ማሳስቢያያገለገሉ ተሸከርካሪዎች የአገልግሎት ጊዜያቸው መሠረት በማድረግ የተለያየ ኤክሳይዝ ታክስ ይጣልባቸዋል።

ይህ መረጃ የገቢዎች ሚኒስቴር ነው።

@tikvahethiopia