TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የእርቀ ሰላም ውይይት ተጀመረ!

በምዕራብ ጎንደር ዞን ነጋዴ ባሕርና አካባቢው የሚኖሩ #የአማራና #የቅማንት ህዝቦች ተወካዮች የእርቀ ሰላም ውይይት ጀምረዋል፡፡ ውይይቱ ነጋዴ ባሕር ከተማ ላይ ነው እየተካሄደ ያለው፡፡ የእርቀ ሰላም ውይይቱ እንዲጀመር ያደረጉት ከሁለቱም ወገኖች የኃማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ናቸው፡፡ የውይይቱም ዓላማ አሁን ላይ ያለው #አለመግባባት እንዲያበቃና ወደቀደመው መከባበርና አንድነት ለመመለስ ነው፡፡ የሰዎች ሞትና የንብረት ውድመት እንደማይጠቅምና ተጎጅዎችም ራሳቸው መሆናቸውን ተወያዮቹ ተናግረዋል፡፡

#ከግጭት ይልቅ የቀደመውን #አንድነት ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ነው የተናገሩት፡፡ ‹‹የጥፋቱ መንስኤ የቅማንት የማንነት ጥያቄ ከሆነ ህግን ተከትሎ መንግስት ሊፈታው ይገባል፤ እኛ ሰላማዊ ነዋሪዎች ነን፤ ሰላማችንን ልንጠብቅ ይገባናል›› ነው ያሉት፡፡ በጥፋቱ የሚጠየቁ ግለሰቦች ካሉም በጋራ ሆነን ተጠርጣሪዎችን ለህግ እንዲቀርቡ እናደርጋለን ብለዋል ተወያዮቹ፡፡

‹‹መንግስት የሚደርሰው ጥፋት ከተከሰተ በኋላ ነው፤ ስለዚህ ለጥፋቱ የድርሻውን ይውሰድ፤ እኛም ችግሩን ወደ ሌላ ሳንገፋ የድርሻችንን ልንወስድ ይገባል›› ብለዋል፡፡ ለዘራፊዎች በራቸውን መክፈት ሳይሆን ሰላማቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባቸውም ተናግረዋል፡፡

የሰሜን ዕዝ ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል #አማረ_ገብሩ በውይይቱ ላይ ተገኝተው የሀገር መከላከያ ሰራዊት #ህይዎትን_ለማትረፍ ቅድሚያ እንደሚሰጥ አረጋግጠውላቸዋል፡፡ ‹‹ሕዝብ ከሌለ ሀገር የለም፤የህግ የበላይነትን ለማስከበር የሚችል መከላከያ ሰራዊት በአካባቢው አለ፤ ከሕዝብ የምንጠብቀው ወንጀለኞችን አሳልፎ መስጠትና ለችግሮች መፍትሔ መስጠት ነው›› ብለዋል፡፡ ሰራዊቱን ሕዝቡ እንዲደግፈውም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

#በእርቀ_ሰላም ውይይቱ እንዲሳተፉ ከአካባቢው 16 ቀበሌዎች ጥሪ ቀርቦላቸው እንደነበር ተገልጧል፡፡ አብዛኛዎቹ ተሳትፈዋል፤በተለያዩ ምክንያቶች ከሁለቱም ወገኖች ለውይይት ያልተገኙ የቀበሌ ተወካዮችም አሉ፡፡ ሁሉን አቀፍ የጋራ መግባባት እንዲኖር ለማድረግም ለየካቲት 15/2011 ዓ.ም ሕዝባዊ ውይይት ለማካሄድ ቀጠሮ ተይዞ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia