TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኢትዮ-ኤርትራ⬇️

ወደ ጦርነት ገብተው ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ግንኙነታቸውን አቋርጠው የኖሩት እና በቅርቡ ግኑኝነታቸውን ያደሱት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ #ነገ በሳዑዲ አረቢያ በሚካሄድ ስነ ስርዓት በቅርቡ የገቧቸውን #የሰላም ስምምነቶች የሚያጠናክር ስምምነት ይፈራረማሉ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይን ጠቅሰው የተለያዩ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡትም በሪያድ በሚካሄደው የፊርማ ስነ ስርዓት ላይ የተመድ ዋና ፀሃፊ #አንቶኒዮ_ጉተሬዝ እና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ እንዲሁም የሳዑዲ አረቢያው ንጉስ #ሳልማን ይገኛሉ ተብሏል።

📌የስምምነቱ ዝርዝር ይዘት ይፋ አልተደረገም።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia