TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
211 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AxumUniversity

አክሱም ዩኒቨርስቲ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሳቢያ የደረሰበት ጉዳት 15 ቢሊዮን ብር እንደሚገመት ማስታወቁን " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ዘግቧል።

ላለፉት 19 ወራት ትምህርት መስጠት አቁሞ የቆየው ዩኒቨርስቲው፤  ሊያከናውነው ላቀደው ዳግም ግንባታ የድጋፍ ጥሪ አቅርቧል።

የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ገብረእየሱስ ብርሃነ የሰጡት ቃል ፦

- ዩኒቨርስቲው በጦርነቱ ሳቢያ በደረሰበት #ውድመት እና #ዘረፋ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስጀመር የሚያስችሉት ቁሳቁሶች እና መሳሪያዎች አጥቷል።

- ሙሉ ለሙሉ የተዘረፉ እና ከወደሙ የዩኒቨርስቲው ንብረቶች ውስጥ ኮምፒውተሮች፣ የላብራቶሪ መሳሪያዎች፣ ሰርቨሮች እና የቢሮ በሮች ይገኙበታል።

- ዩኒቨርስቲው ከጦርነቱ በፊት የነበሩት 60 ገደማ ተሽከርካሪዎች ተዘርፈው እና ተቃጥለው አሁን በስራ ላይ የሚገኘው #አንድ_መኪና ብቻ ነው።

- በጥር ወር ላይ በተደረገ ዳሰሳ የደረሰው ውድመት 15 ቢሊዮን ብር ይደርሳል።

- ጉዳት የደረሰባቸውን ንብረቶች በተወሰነ መልኩ በመተካት ወደ ስራ ለመግባት ታቅዷል።

- ለሚያከናውነው ዳግም ግንባታ እና ጥገና ስራ የገንዘብ እና የማቴሪያል ድጋፍ እንዲደረግልን  ጠይቀናል። የድጋፍ ጥሪው ለዓለም አቀፍ እና ለሀገር በቀል አጋር ድርጅቶች፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ነው።

- ዩኒቨርስቲው የሚያገኘውን ድጋፍ በፌደራል መንግስት ከሚመደበለት በጀት ጋር በማጣመር በአጭር ጊዜ ውስጥ የመማር ማስተማር አገልግሎቱን ለመስጠት ታቅዷል። 

- ቁሳቁሶችን በተወሰነ መልክ ቅድሚያ እየሰጠን ካስገባን፤ የግዢ ሂደቱ ፈጣን ከሆነ፤ ተማሪዎችን #በሶስት_ወር ውስጥ ማስገባት እንችላለን። በትግራይ ክልል የሚኖሩ እና ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርት ያቋረጡ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎችን ትምህርት ማስጨረስ ላይ ትኩረት ይደረጋል።

አክሱም ዩኒቨርሲቲ እስካሁን ከፌደራል መንግስት በጀት ባይለቀቅለትም፤ በስሩ ለሚገኘው የጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 43 መምህራንን ለመቅጠር ከ2 ሳምንት በፊት ማስታወቂያ አውጥቷል።

የቅጥር ሂደቱ የሚፈጸመው በትምህርት ሚኒስቴር ተፈቅዶ፣ በጀት ሲለቀቅ መሆኑ ተገልጿል።

ከፌደራል መንግስት የሚለቀቀው በጀት፤ ለዩኒቨርስቲው ሰራተኞች ደመወዝ ለመክፈል እና ትምህርት ለማስጀመር ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

#አራት_ሺህ ገደማ የሚሆኑት የዩኒቨርስቲው መምህራን እና ሰራተኞች ከሐምሌ 2013  ዓ.ም. ወር ጀምሮ #ደመወዝ_አለማግኘታቸውን ዩኒቨርስቲው አስታውቋል።

Credit : www.ethiopianInsider.com

@tikvahethiopia