TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
211 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ትግራይ - ያልመከኑ የጦር መሣሪያዎች !

" መቐለ ወደ #ስድስት_ቦታዎች አሁን ራሱ ያልመከኑ ቦንቦች አሉብን። … እስካሁን ድረስ ሞትና አደጋ 1,038 ነው በቢሯችን የያዝነው " - የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ

ባለፉት 2 አመታት የነበረው ከፍተኛ ጦርነት በግንባር ብቻ ሳይሆን በትግራይ ክልል ውስጥ ባሉ የተለያዩ ቦታዎች ላይም ስለተካሄደ አርሶ አደሮችን ጨምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ህፃናትና የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ባልመከኑ የጦር መሣሪያዎች ሞትና የአካል ጉዳት አደጋዎች እየደረሱባቸው መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትግራይ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ሰምቷል።

የትግራይ ጤና ቢሮ ፤ የድንገተኛ ሕክምና አስተባባሪ አቤንዘር እፀድንግል (ዶ/ር) ስለ ጉዳዩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲያስረዱ፣ " በትምህርት ቤቶች፣ በሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች፣ መቀሌ ወደ ስድስት ቦታዎች አሁን ራሱ ያልፈነዱ ቦንቦች አሉብን፣ ያልተነሱ ማለት ነው " ያሉ ሲሆን፣ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረቡላቸው የተለያዩ ጥያቄዎችም ማብራሪያዎች ሰጥተዋል።

ያልመከኑት የጦር መሣሪያዎች #መቐለ የት የት ቦታዎች ይገኛሉ ?

- አንደኛው #ከፕላኔት_ጀርባ አካባቢ ነው።

- ሁለተኛው ቦታ የህፃናት መጫወቻ ስፍራ የተመታበት #የአፄ_ዮሐንስ_ቤተመንግሥት_ጀርባ በኩል ነው።

- ሦስተኛው #05 አካባቢ ነው።

- ሌሎቹ ደግሞ መቐለ ውስጥ ሆነው ግን #እርሻ ቦታ ላይ ነው ያሉት።

በርግጥ በኅብረተሰቡ ላይ #አደጋን_እንደሚያደርሱ የሚገልፅ ምልክት (አጥር) ተደርጓል ግን በከፍተኛ ጥንቃቄ እና በባለሙያ መነሳት አለባቸው " ብለዋል።

ባልመከኑ የጦር መሣሪያዎች ምን ያህል ሰዎች ላይ ሞትና የአካል ጉዳት ደረሰ ?

" ሁሉንም ወደ ጤና ተቋማት አምጥተን ለማከም ሁኔታው አልተመቸም ነበር። ስለዚህ ሙሉ ዳታ የለንም።

ሙሉ ዳታ አባባሌ አንዳንዶቹ አደጋ ደርሶባቸው የሞቱ አሉ፣ ሌሎች መምጣት ያልቻሉ ብዙ ሰዎችም እንዳሉ ግምት ውስጥ ማስገባት አለብን። ባልፈነዱ የጦር መሣሪያዎች ፣ በተጣሉ ተተኳሽ እና የተቀበሩ ቦንቦች አደጋ የደረሰባቸው ባለን ዳታ መሠረት ፦

- እስካሁን ሞትና አደጋ በአጠቃላይ 1,038 ነው ያለን በእኛ በቢሯችን የያዝነው። #163 ሞት፣ 875 ደግሞ ከባድ ጉዳት ማለት ነው።

- ከ163ቱ መካከል 84ቱ ዕድሜአቸው ከ17 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት፣ 79ኙ ደግሞ ዕድሜአቸው ከ18 በላይ የሆኑ አዋቂዎች ናቸው።

- ከ84 #ህፃናት ውስጥ 75ቱ ወንዶች፣ 9ኙ ደግሞ #ሴቶች ናቸው ብለዋል።

ችግሩ አሁንም እንደቀጠለ ነው ? አሁንም የሚመጡ አሉ ?

- አዎ አሁንም ድረስ ይመጣሉ። በተለይ ክረምት ላይ በእርሻ ሥራ መቀሳቀስ ስለሚኖር፣ በመነካካትም ሳያውቁ እያረሱ እያለ መፈዳት ያጋጥማቸው ስለነበሩ ቁጥሩ እየቀነሰ ቢሄድም አልፎ አልፎ እየመጡ ነው። ምክንያቱም በተጠናከረ ደረጃ አልተጠረገም። 

- ፈንጅ ነገሮችን የማጥራት ሥራ ካልሰራን ትልቅ ችግር ነው ያለው። የመንግሥት ተዋጊ አካሎች ትምህርት ቤቶችን እንደ አውደ ማቆያ ሲጠቀሙባቸው ስለነበር እዛ ላይ የተጣሉ ጦር መሳሪያዎች አሁን ትምህርት ሲጀምሩ #ህፃናት በተለያየ ጊዜ አደጋ ይደርስባቸዋል።

- በተለያዩ መንገዶች ሰው ተሸክሟቸው ፣ በጋሪ ፣ በፈረስ ፣ በበቅሎ ሕክምና ቦታ መድረስ የቻሉ ሰዎች እንኳ (በተለይ ደግሞ ሽረ አካባቢ የመጡ ብዙ ታካሚዎች) መድኃኒት በበቂ ሁኔታ ስላልነበረ የጤና ተቋማት በቂ ሕክምና ሊሰጧቸው ባለመቻላቸው ብዙ ያጣናቸው አሉ።

- አካል ጉዳተኞችም ሆነዋል ሕክምና ቢደረግላቸው መትረፍ እየቻሉ ግን የሰርጀሪ እቃዎች እጥረት ስለነበረ አካል ጉዳተኛ የሆኑት በርከት ያሉ ሰዎች ናቸው። በአጠቃላይ በነበረው ሁኔታ ከባድ ነበር ግን አሁን ባለዉ ሁኔታ በተቻለ መጠን ባለን አቅም አገልግሎት እየሰጠን ነው።

ከመድኃኒት እጥረቱ ጋር በተያያዘ የአካል ጉዳተኛ የሆኑ ሰዎችን በቁጥር ደረጃ መግለፅ እችላለን ?

- በቁጥር እንኳ ያስቸግራል፣ ግን እኔ የማስታውሳቸው ወደ ሦስት #ህፃናት በአንድ ወቅት ገብተው የሕክምና እቃዎችን ማግኘት ስላልተቻለ ለአካል ጉዳት ተጋልጠዋል። ይህ በአንድ ወቅት ብቻ ነው። በተጠና መልኩ ግን ብዙ ሊሆኑ ይችላሉ በቁጥር ደረጃ አጋጣሚ አልያዝነውም።

ምን ተሻለ ?

- አንደኛ ከሁሉ በላይ በመጀመሪያ እንዲህ አይነት መሣሪያዎችን መነካካት እንደሌለባቸው ህፃናት፣ ማኅበረሰቡ ማወቅ እንዳለባቸው ትምህርት መሰጠት አለበት።

- የፈንጅ #አምካኝ ባለሙያዎች በስፋት በማሰማራት በእያንዳንዱ ቦታዎች ተሰብስበው ያልመከኑ የጦር መሣሪያዎች መወገድ አለባቸው ፤ በየአካባቢው በጣም በርከት ያሉ #ያልተነሱ ፈንጂዎች አሉብን።

- ከተነሱ ነው በዘላቂነት መፍትሄ የሚገኘው። ሕዝብ ባለበት ቦታ ምንም አይነት ጦርነት አለማካሄድ ላለማካሄድ የሚደነግጉ መርሆዎችም መከበር አለባቸው። የህዝብ መገልገያ ቦታዎች ለወታደራዊ አላማ አለማዋል እንሰ እሪኮመዴሽንም መወሰድ አለበት።

ዘገባው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።

@tikvahethiopia