TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.89K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢትዮጵያ ብቻዋን ነፃ አትሆንም!

(ዶክተር - TMES)

ከሰሞኑን በኢትዮጵያ ሪፖርት እየተደረጉ ያሉት ኬዞች ማነስ በርካቶችን እያዘናጋ እንደሆነ እየታየ ነው።

መልካም ዜናን የሚጠላ የለም ግን እውነታው ይህ አሁን ድረስ ፈውስ ያልተገኘለት በሽታ በመላው ዓለም በከፍተኛ ፍጥነት እየተሰራጨ መሆኑ ነው።

ዶክተር ፅዮን ፍሬው ከኒው ዮርክ እንዳሉት በየቀኑ የሚመዘገበው ቁጥር 0 እና 1 ሆነ ማለት የኮሮና ቫይረስ እየጠፋ ነው ማለት አይደለም።

የፋሲካ ሰሞን በሀገራችን የነበረው መዘናጋትና ቸልተኝነት እየባሰበት እንጂ እየቀነሰ አልመጣም። ይህ ደግሞ ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍለናል።

ሁላችንም በየእምነታችን ይህ በሽታ ከዓለም እንዲጠፋ፤ ፈጣሪም ለዚህ ወረርሽኝ መፍትሄ ለማምጣት የሚሰሩትን ሳይንቲስቶን መንገዱን ያሳያቸው ዘንድ እየተማፀንን በከፍተኛ ደረጃ ጥንቀቄያችን እናጠንክር።

ኢትዮጵያ ብቻዋን በፍፁም ነፃ አትሆንም ፤ ጎረቤት ሀገራት በወረርሽኙ እየታመሱ እኛ ጤና ሆነን እንኖራለን ማለት አይቻልም ፤ አይደለም ጎረቤት ሀገራት የቻይና፣ አሜሪካ፣ ኢራን፣ ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ጣልያን ...ሌሎችም ሀገራት ህዝቦች ጤና መሆን ካልቻሉ ህይወታችን እንደተቃወሰ ይቀጥላል፤ ምክንያቱም ተሳስረናልና!

ዘወትር ለኢትዮጵያ #ብቻ ሳይሆን ለዓለም ጤና መሆን፣ ለሰው ልጅ መዳን፣ ለሰው ልጅ ሰላም መሆን በየእምነታችን ፈጣሪን እንለምን።

እኛ የጤና ባለሞያዎች ደከመን ሰለቸን ሳንል ይኸው ህይወታችን ሰጥተን እያገለገልን ነው፤ እናንተም በመዘናጋት የሚመጣውን የከፋ ቀውስ ለመከላከል አብራችሁን ቁሙ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

በአዲስ አበባ የኮቪድ-19 ስርጭት በእጅጉ #እየጨመረ ነው። ከሚያዚያ 29 እስከ ዛሬ ግንቦት 11 ባሉት ቀናት #ብቻ አንድ መቶ ሃያ (120) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

• ሚያዚያ 29/2012 ዓ/ም - ሃያ አንድ (21) ሰዎች
• ሚያዚያ 30/2012 ዓ/ም - ሶስት (3) ሰዎች
• ግንቦት 1/2012 ዓ/ም - አስራ ሶስት (13) ሰዎች
• ግንቦት 2/2012 ዓ/ም - ሃያ አንድ (21) ሰዎች
• ግንቦት 3/2012 ዓ/ም - አምስት (5) ሰዎች
• ግንቦት 6/2012 ዓ/ም - አምስት (5) ሰዎች
• ግንቦት 7/2012 ዓ/ም - ስምንት (8) ሰዎች
• ግንቦት 8/2012 ዓ/ም - ሁለት (2) ሰዎች
• ግንቦት 9/2012 ዓ/ም - አራት (4) ሰዎች
• ግንቦት 10/2012 ዓ/ም - ሃያ ዘጠኝ (29) ሰዎች
• ግንቦት 11/2012 ዓ/ም - ዘጠኝ (9) ሰዎች

አሁንም ስርጭቱ ከዚህ በላይ እንዳይባባስ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ በድጋሚ መልዕክት ለማስተላለፍ እንወዳለን። የጤና ባለሞያዎችን ምክር የማናዳምጥ ከሆነ፣ የሚወጡትን መመሪያዎች የማናከብር ከሆነ ይህ ወረርሽኝ 'ከቁጥጥር ውጭ' ሊወጣ ይችላል።

መዘናጋትና ቸልተኝነት ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍላል!

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ስርጭት በአዲስ አበባ!

በአዲስ አበባ ከተማ በአራት (4) ተከታታይ ቀናት #ብቻ ሰባ ስምንት (78) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

• ግንቦት 12/2012 ዓ/ም - ዘጠኝ (9) ሰዎች
• ግንቦት 13/2012 ዓ/ም - ሶስት (3) ሰዎች
• ግንቦት 14/2012 ዓ/ም - አስራ ስምንት (18) ሰዎች
• ግንቦት 15/2012 ዓ/ም - አርባ ስምንት (48) ሰዎች

አብዛኞቹ በቫይረሱ መያዘቸው የተረጋገጠ ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ #የሌላቸው ናቸው።

መዘናጋት ዋጋ ያስከፍላል፤ ጥንቃቄ ይደረግ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ስርጭት በአዲስ አበባ!

በአዲስ አበባ ከተማ በአምስት (5) ተከታታይ ቀናት #ብቻ አንድ መቶ ሃምሳ አንድ (151) ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

• ግንቦት 12/2012 ዓ/ም - ዘጠኝ (9) ሰዎች
• ግንቦት 13/2012 ዓ/ም - ሶስት (3) ሰዎች
• ግንቦት 14/2012 ዓ/ም - አስራ ስምንት (18) ሰዎች
• ግንቦት 15/2012 ዓ/ም - አርባ ስምንት (48) ሰዎች
• ግንቦት 16/2012 ዓ/ም - ሰባ ሶስት (73) ሰዎች

አብዛኞቹ በቫይረሱ መያዘቸው የተረጋገጠ ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር 'ንክኪ የሌላቸው' ናቸው።

ይህ ከፍተኛ የሆነ ኮቪድ-19 ስርጭት በአዲስ አበባ ብቻ ተወስኖ የሚቀር አይደለም። የክልል ከተሞች ነዋሪዎች የቫይረሱ ስርጭት እየጨመረ በመምጣቱና የትራንስፖርት እንቅስቃሴም #ባለመቋረጡ እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጉ።

አስገዳጅ ካልሆነ ከቤት አትውጡ!

ከቤት ምትወጡበት አስገዳጅ ምክንያት ካለ ደግሞ ሰዎች ሚሰባሰበሰቡበት ቦታ በፍፁም አትገኙ ፣ ከሰዎች ጋር አትጨባበጡ ፣ በስራ ቦታችሁ ሳትዘናጉ ጥንቃቄ አድርጉ ፣ የእጃችሁን ንፅህና ጠብቁ ፣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ያድርጉ!

መዘናጋት ዋጋ ያስከፍላል፤ ጥንቃቄ ይደረግ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የተጠነቀቀ ይህን የከፋ ጊዜ ይሻገራል!

ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የሩቅ ሀገር በሽታ ነው ሲባል እንዳልነበር ዓለምን አዳርሶ ዛሬ ሀገራችንን እያመሰ ነው።

በአዲስ አበባ አሁንም መደበኛ ህይወት የሚመራባቸው አካባቢዎች እንዳሉ ተመልክተናል። ይህ እጅግ ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከፍል ነው።

በአ/አ የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ፍጥነት እየተሰራጨ ቢገኝም አሁንም ከክልሎች ጋር 'የህዝብ ትራንስፖርት' አልቆመም ይህ ሁኔታ መላው የሀገሪቱን ህዝብ አደጋ ላይ እየጣለ ነው።

የክልል ከተሞች ላይ የሚታየው መዘንጋት ደግሞ ችግሩን የከፋ ሊያደርገው ይችላል። ጊዜው ሳይረፍድ መፍትሄ ቢፈልግ መልካም ነው።

የክልል ነዋሪዎች ጋር ቫይረሱ በስፋት ያለው አዲስ አበባ #ብቻ ነው እኛ ጋር አይደርስም በሚል የተሳሳተ አመለካከት ካለ አሁን መታረም አለበት።

የውጭ ሀገር ነው ሲባል የነበረው በሽታ ዛሬ ሀገራችን ፣ ሰፈራችን ደርሷል፤ #ካልተጠነቀቅን የእያንዳንዳችንን ቤት ማንኳኳቱ አይቀርም።

የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መከላከያ መንገዶች እጅግ በጣም ቀላል ሆነው ሳለ ለምን የማይገባ ዋጋ እንከፍላለን ?

• የእጆቻችንን ንፅህና እንጠብቅ! /መታጠብ/

• ቤት ውስጥ እንቀመጥ! /መቀመጥ/

• የስራችን ሁኔታ ከቤት የሚያስወጣና አስገዳጅ ጉዳዮች ኖረውን ከቤት ከወጣን የአፍንጫና አፍ መሸፈኛ እናድርግ! /መሸፈን/

• በሁሉም ቦታ አካላዊ ርቀት እንጠብቅ! /መራራቅ/

የኢትዮጵያ መንግስት የቫይረሱን ከፍተኛ ስርጭት ከግምት ውስጥ ሊያስገባና በህዝብ ትራስፖርቶች ላይ ያለውን ሁኔት ሳይውል ሳያድር መፍትሄ ሊፈልግለት ይገባል። ካልሆነ በሀገር ደረጃ የሚከፈለው ዋጋ ከፍተኛ ነው!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከፍተኛ ጥንቃቄ!

#SHARE #ሼር

በኢትዮጵያ የምትኖሩ የቲክቫህ አባላት ፣ ይህን መልዕክት የኢንተርኔት አገልግሎት አግኝታችሁ ማንበብ የቻላችሁ በሙሉ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በከፍተኛ ደረጃ በሀገሪቱ እየተሰራጨ በመሆኑ ጥንቃቄ አድርጉ።

ኢትዮጵያ የመመርመር አቅሟን እያሣደገች መጥቱን ተከትሎ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ ጨምሯል።

በሀገሪቱ በሁለት ቀናት #ብቻ (ሀምሌ 9/2012 እና ሀምሌ 10/2012) 672 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በምርመራ ተረጋግጧል።

በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥርም እየጨመረ መጥቷል በትላንት እንዲሁም በዛሬ ሪፖርት መሰረት 15 ሰዎች ከቫይረሱ ጋር በተገናኘ ህይወታቸውን አጥተዋል።

ይህንን መልዕክት በስልካችሁ ያገኛቹ ወገኖቻችን እራሳችሁ እና ቤተሰባችሁን በሙሉ ከዚህ አስፈሪ ወረርሽኝ ሳትዘናጉ እንድትጠብቁ ጥሪ እናቀርባለን ፤ ኢንተርኔት ማግኘት ላልቻሉ ወዳጆቻችሁ በSMSና በመደወል አሳሳቢውን ሁኔታ አሳውቋቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የ12ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተፈታኞችን በሚመለከት ፦

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሐረጓ ማሞ ከ12ኛ እና ከ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ጋር በተያያዘ ተከታዩን ብለውናል ፦

- የ12ኛ እና የ8ኛ ክፍል ፈተና በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲሰጥ በቅድሚያ ትምህርት ቤቶች ኮቪድ-19 መከላከልን መርህ ባደረገ መልኩ ዝግጅት ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል።

- ከፈተናው አስቀድሞ የትምህርት ቤቶችን ዝግጁነት የማረጋገጥ ስራ በትምህርት ሚኒስቴር ይሰራል።

- ይህ ተግባራዊ እንዲሆን ሁሉም ትምህርት ቤቶች ፣ የጤና ተቋማት፣ ወላጆች፣ አጠቃላይ ማህበረሰቡ ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

- የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የ11ኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቀቁ እና የ12ኛ ክፍልን የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት የተከታተሉ መሆን አለባቸው።

- የ8ኛ ክፍል ተፈታኛ ተማሪዎች የ7ኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቁ እና የ8ኛ ክፍልን የአንደኛ ሴሚስተር ትምህርት የተከታተሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

- ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው በሙሉ አቅም እንዲመለሱ የስነ ልቦና ድጋፍ ይደረግላቸዋል።

- የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እና ምዝገባ በኦንላይን ይካሄዳል። ተማሪዎች የ45 ቀን የክለሳ እና የቴክኖሎጂ መለማመጃ ጊዜም ይኖራቸዋል።

- በነገራችን ላይ ትምህርት ቤቶች የሚከፈቱት ፣ ፈተናዎችም የሚሰጡት ትምህርት ቤቶች አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ ማሟላት ሲችሉ #ብቻ ነው።

- ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ቤቶች እንዲከፈቱ ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሸራረፉ እንዲተገበሩ ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠው ትምህርት ለማስቀጠል እንዲሁም ተመራቂ ተማሪዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ የቀራቸውን ትምህርት ተከታትለው እንዲመረቁ ለማድረግ ዩኒቨርሲቲዎች ጥሪ ማድረግ ጀምረዋል።

ዛሬ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ.ም ተመራቂ መደበኛ ተማሪዎች #ብቻ የምዝገባ (Registration) ጊዜ አሳውቋል።

በዚህም ተመራቂ ተማሪዎች ብቻ ጥቅምት 23 እና 24/2013 ዓ/ም እንዲመዘገቡ ጥሪ የቀረበ ሲሆን የመጀመሪያ ቀን ትምህርት (Day - One - Class - One) ጥቅምት 25 / 2013 ዓ/ም እንደሚጀምር ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TikvahFamily

ከ1 ወር በላይ ተቋርጦ የቆየው የቲክቫህ ማስታወቂያ ከነገ ጀምሮ ይቀጥላል።

ህጋዊ የንግድ ፍቃድ አውጥታችሁ የምትንቀሳቀሱ የቲክቫህ አባላት የድርጅት ባለቤቶች ፓኬጁን : @Tikvahpromo / +251942293508 #ብቻ ማግኘት ትችላላችሁ።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
* ATTENTION

ከዛሬ ነሃሴ 15/2013 ጀምሮ በሰ/ሸዋ ዞን ሚዳ ወረሞ ወረዳ የሰዓት እላፊ ገደብ ተጥሎ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል።

የሰአት እላፊ ገደቡን የወሰነው የወረዳዉ ፀጥታ ምክር ቤት ነው።

የሚዳ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት አሁን ያለዉ የሃገሪቱ የሰላም ሁኔታ ከወረዳዉ መልክአ ምድር አቀማመጥ ጋር ሲነፃፀር አሳሳቢ ሆኖ በመገኘቱ የወረዳዉ ፀጥታ መዋቅር ዉይይት አካሄዶ ለፀጥታ ስጋት ነዉ በማለት የዉሳኔ አቅጣጫ አስቀምጧል ብሏል።

በዚህ መሰረትም ከዛሬ ነሃሴ 15/2013 ዓ.ም ጀምሮ ፦

1ኛ. መጠጥ ቤቶች ከንጋቱ 12 ሰአት እስከ ምሽቱ 2 ሰአት ድረስ #ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ ተወስኗል።

2ኛ. የግል አሽከርካሪዎች ሞተር ሳይክልን ጨምሮ ከምሽቱ 1 ሰአት በኋላ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ውሳኔ ተላልፏል።

3ኛ. ማንኛዉም የመንግስት ተሸከርካሪ ለስራ የወጡ ካልሆነ በስተቀር ከሁለት ሰአት በኋላ የትም ቦታ ከመንግስት ተቋም ዉጪ መቆም የለባቸውም ፤
- የጤና ባለሙያዎች፣
- የሃይማኖት አባቶች
- ለፀጥታ ስራ ከሚንቀሳቀሱ ሰዎች በስተቀር ከምሽቱ 3 ሰአት በኋላ እንቅስቃሴ የተገደበ ነው።

ህብረተሰቡ ማንኛውም አይነት #የተለየ_ነገር ከተመለከተ ጥቆማ ለመስጠት እነዚህን ስልክ ቁጥሮች ፦
• 096602287 ፣
• 0913146121
• 0901064105 መጠቀም ይችላል።

@tikvahethiopia