TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.89K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ሚዲያ የሩዋንዳውን የዘር ጭፍጨፋ (ጄኖሳይድ) እንዴት አቀጣጠለ ? በ100 ቀናት ከ800,000 እስከ 1,000,000 ቱትሲዎችና ለዘብተኛ የሚባሉ ሁቱዎች ባለቁበት የሩዋንዳው የዘር ጭፍጨፋ/ጄኖሳይድ ሚዲያዎች ከፍተኛ ድርሻ ነበራቸው። እንዴት ? - ራዲዮ-ቴሌቭዥን ሊብሬስ ዴስ ሚልስ ኮሊንስ (RTML) እንዲሁም መንግታዊው ' ሬድዮ ሩዋንዳ ' በቱትሲዎች ላይ በመላ ሀገሪቱ ጥላቻ እንዲፈጠርና የሩዋንዳ…
#Kwibuka

" ክፍፍል እና ፅንፈኝነት ካልተገታ በማናቸውም ቦታ ወደ ዘር ማጥፋት ሊያመራ ይችላል " - ፖል ካጋሜ

ከ30 ዓመታት በፊት በሩዋንዳ በ100 ቀናት ብቻ እስከ 1,000,000 ሚደርሱ ሰዎች የተጨፈጨፉበት የሩዋንዳ ዘር ፍጅት እየታሰበ ይገኛል።

የዘር ፍጅቱ የተፈፀመበትን 100 ቀናት ታሳቢ በማድረግ ከሚያዚያ 7 (እ.ኤ.አ) አንስቶ ለ100 ቀናት የዘር ጭፍጨፋው ሰለባዎች ይታሰባሉ ፤ ይህም ኪውቡካ /Kwibuka/ ይባለል።

ከሳምንት በፊት በኪጋሊ በነበረ ስነስርዓት ላይ ፕሬዜዳንት ፖል ካጋሜ ፤ ከዘር ፍጅቱ በህይወት የተረፉ ዜጎች ለብሄራዊ አንድነት ሲሉ ስላደረጉት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።

" እጅግ የሚከብደውን የእርቀ ሰላም ሸክም እናተ እንድትሸከሙ ጠየቅናችሁ እንሆ ለሀገራችን ስትሉ ይሄንን በየቀኑ ማድረጋችሁን ቀጥላችኃል ስለዚህ እናመሰግናችኃለን " ነው ያሉት።

ፖል ካጋሜ ፥ አሁንም ድረስ በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት #የጎሳ_ፖለቲካ እየተባባሰ መሄዱን እና የብሄረሰብ ማጽዳት አደጋ መደቀኑን በማንሳት አስጠንቅቀዋል።

" ሩዋንዳ ውስጥ የደረሰው መከራ ማስጠንቀቂያ ሊሆን ይገባል። ክፍፍል እና ፅንፈኝነት ካልተገታ በማናቸውም ቦታ ወደ ዘር ማጥፋት ሊያመራ ይችላል " ብለዋል።

ሩዋንዳ መከራ ውስጥ በገባችበት ጊዜ በርካታ ሀገራት የሰላም አስከባሪ ልጆቻቸውን ሩዋንዳ መላካቸውን እና እነዛም ወታደሮች ለሩዋንዳ እንደደረሱላት ገልጸዋል።

" ነገር ግን #በጥላቻም ይሁን #በፍራቻ ያልደረሰልን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

በሩዋንዳው የዘር ጭፍጨፋ በወቅቱ በነበረው የሁቱ መንግሥት መሪነትና የሁቱ ብሄረሰብ አባላት በሆኑ ጽንፈኛ አክራሪዎች እንዲሁም በመንግሥት በሚደገፈው የ " ኢንተርሀምዌ '  ሚሊሻ አማካኝነት እስከ 1,000,000 ቱትሲዎች ፣ ለዘብተኛ ሁቱዎችና ትዋዎች ተጨፍጭፈዋል።

Rwandan genocide
Apr 7, 1994 – Jul 15, 1994
AP / VOA

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ

@tikvahethiopia