TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ብዙ ጊዜ #ቀላል ነው ብለን የተናግርነው አንድ ቃል የሌላውን ሰው #ቅስም ይሰብራል። ያንኮታኩታል። ድባቅ ይመታል። ከአፋችን የሚወጡት ቃላቶቻችን እጅግ ትልቅ ሀይልን የተሞሉ ናቸው። ይህ የቃላት ሀይልም #በመልካምነት ካልተዋጀ ቃላቱን በሚቀበለው ሰው ላይ ትልቅ ችግር ሊፈጥር ይችላል።  ስለዚህ በእያንዳንዱ ካፋችን በሚወጡ ቃላት ላይ !ቁጥብ እንሁን። ከዚህ በፊት ያስቀየምናቸውም ሰዎች ካሉ ዛሬ !ይቅር እንዲሉን ለመጠየቅ ትክክለኛው ጊዜ ነው። ዛሬ ነገ ይቅርታ እጠይቃለሁ ስትል ልዩነታችሁ ይበልጥ እየሰፋ ይሄዳል። ማስተካከልም የሚከብድበትና የማይቻልበት ሁኔታ ላይም ይደርሳል። አንተ ግን ዛሬ ትልቅ እድል አለህ። በአንድ የአፍ ወለምታ ያስቀየምከውን ሰው ዛሬ ይቅርታ ለመጠየቅና በድጋሚ ጓደኝነታችሁን ለመቀጠል ዛሬን በህይወት ኖረህ ሌላ እድል ተሰቶሀል። ይህንን እድልህን ይቅርታ በመጠየቅ አሳልፈው። ውስጥህንም ሲረብሽህ የነበረውን የሁልጊዜ ሀሳብ ከላይህ ላይ ተገላገለው።  ይቅርታ መጠየቅ የበታች አያደርግም። ይቅርታ መጠየቅ መዋረድ አይደለም። ጥፋትን አውቆ ይቅርታ መጠየቅ ትንሽ መሆን አይደለም ትልቅ መሆን እንጂ!

Via ብሩክ የሺጥላ
@tsegabwolde @tikvahethipia