TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዲላ ሆስፒታል‼️

ዲላ ሆስፒታል በጌድዮ ዞን ለሚገኙ ተፈናቃዮች #ድጋፍ ለማድረግ የጤና ባለሙያዎች ቡድን ወደ ስፍራው እንደሚልክ አስታወቀ።

የዲላ ሆስፒታል ከዞኑ ጤና መምሪያ ጋር በመሆን በጌድዮ ተፈናቅለው ለሚገኙ ዜጎች ህክምና በሚሰጥባቸው ሆስፒታሎች የጤና ድጋፍ እና እገዛ ለማድረግ የጤና ባለሙያዎችን ወደ ስፍራው እንደሚልክ የሆስታሉ የህክምናና ተግባር ስልጠና ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር #ሰላማዊት_አየነ ለኢቢሲ ገልጸዋል፡፡

ከሀኪሞችና ነርሶች የተውጣጣው የባለሞያዎች ቡድን መድሀኒት፣ የህክምና ቁሳቁሶችንና ሌሎች ግብዓቶችን በመያዝ የህክምና እርዳታ ስራ እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡

ገደብ እና ይርጋ ጨፌ ሆስፒታሎች ለተፈናቃዮች ህክምና እየተሰጡ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ፎቶዋ ሲዘዋወር የነበረችው እናት በዲላ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላት መሆኑም ታውቋል፡፡

ታካሚዋ ላጋጠማት የምግብ እጥረት የህክምና እርዳታ እየተደረገላት ሲሆን መንቀሳቀስ እንድትችልም የፊዝዮ ቴራፒ ህክምና እያገኘች መሆኗ ተጠቅሷል፡፡

ለእናቲቱ ሌሎች የጤና ምርመራዎችም እየተደረጉላት እንደሆነም ነው የተገለፀው፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia