TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AA የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በቀጨኔ ወላጅ አልባ ማዕከል በመገኘት የስራ እንቅስቃሴውን ተመልክተዋል፡፡ የቀጨኔ ወላጅ አልባ ማዕከል ላለፉት በርካታ ዓመታት በመቶዎች ለሚቆጠሩ ልጃገረዶች ማረፊያ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ነፃ የህክምና አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል...

ጂዊሽ ቮይስ ኢንተርናሽናል የተባለ ግብረ- ሰናይ ድርጅት በአዲስ አበባ በአንድ ጤና ጣቢያ ነፃ የአይንና የጥርስ ህክምና አገልግሎት እየሰጠ ነው። ግብረሰናይ ድርጅቱ ነፃ የህክምና አገልግሎቱን እየሰጣ ያለው በአዲስ አበባ ቀጨኔ አካባቢ በሚገኘው ህዳሴ ጤና ጣቢያ መሆኑ ታውቋል።

የጂዊሽ ቮይስ ሚኒስትሪ ኢንተርናሽናል ተወካይ ዶክተር አዳነ ቢረሳ ለኢዜአ እንደገለጹት በጤና ጣቢያዎች እንዲህ አይነት የህክምና አገልግሎት መስጠት ብዙዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል። በነፃ አገልግሎቱ አቅመ ደካሞችና መክፈል የማይችሉ እንዲሁም በቤት ውስጥ የዋሉ አዛውንቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑንም ገልጸዋል።

(ኢዜአ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ👌

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ የወልድያ ከተማ ወጣቶችና የአካባቢው ማህበረሰብ ወደ አርሶ አደሩ ማሳ ገብተው በተለያዩ ዘዴዎች የአንበጣ መንጋውን እየተከላከሉ ነው፡፡

PHOTO: ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ቲክቫህ ቤተሰቦች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መርሳና አካባቢው...

(የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ)

አርሶ አደሩ ጭስ በማጨስ ፣ ጅራፍ በማጮህ፣ ጥሩንባ በመንፋት ፣ ተማሪዎች ባዶ የውሃ ፕላስቲክ ጠጠር በማስገባትና በማንኳኳት፣ ዘፍላይ በመውጣት ዛፋን በማወዛወዝ መንጋውን ለመከላከል ጥረት እየተደረገ ነው፡፡

PHOTO: ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ቲክቫህ ቤተሰቦች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለወላይታ ኢንዱስትሪ አብዮት ማስፈጸሚያ የሚሆን ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ!

በመደመር ዕሳቤ ለ3 ቀናት ሲሰለጥኑ የቆዩ ከ1360 በላይ አጠቃላይ የወላይታ ዞን አመራሮች ለተጀመረው የኢንዱስትሪ አብዮት ንቅናቄ የሚሆን የ1 ወር ደመወዝ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ እንደገለጹት ለረዥም ጊዜ ከህብረተሰቡ ሲነሳ የቆየው የኢንዱስትሪ ፓርክ ጥያቄ ከሚመለከተው አካል እስካሁን ድረስ ምላሸ ያላገኘ ቢሆንም የህዝቡን የመልማት ጥያቄ ለመመለስ የዞኑ አስተዳደር ከመስከረም 2012 ዓ.ም ጀምሮ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-07-3
#JimmaUniversity

የጅማ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ ጥቅምት 20/2012 ዓ.ም ባካሄደው ልዩ ስብሰባ ለአራት ነባር መምህራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን ለኢፕድ በላከው መግለጫ አሳውቋል፡፡ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያገኙት ፕሮፌሰር ገመዳ አበበ በMolecular Medical Microbiology፣ ፕሮፌሰር ገዛኻን በሬቻ በ Applied Ecology፣ ፕሮፌሰር ሱልጣን ሱሌማን በPharmaceutical Analysis and Regulatory Affairs እና ፕሮፌሰር ዘለቀ መኮንን በMedical Parasitology ናቸው፡፡

(ኢፕድ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#GamoZone

የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ። የጋሞ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ረታ ተክሉ እንደተናገሩት ከሞያሌ ኮንሶ አድርጎ በአርባ ምንጭ ወደ ማዕከል ከተሞች የሚንቀሳቀሰው ኮንትሮባንድ እና ህገወጥ የጦር መሳሪያ በጸጥታው ስራ ላይ ጫና ከመፍጠሩም በላይ ህጋዊ ነጋዴዎች ከገበያ እንዲውጡ በማድረግ በሃገር እኮኖሚ ላይ አሉታዊ እየፈጠረ ነው፡፡

እንደ ኮማንደር ረታ ተክሉ ገለጻ ጥቅምት 23 /2012 ዓ/ም ከለሊቱ 6፡30 ገደማ የዞኑ ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት አርባ ሁለት ካርቶን ሶስት ዓይነት የሰው መድሀንት ፣ሰላሳ አንድ ቦንዳ ልባሽ ጨርቅ የጫነ ኮድ 3 አአ 43366 አይሱዙ መኪና ከነ አሽከርካሪው በህግ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራው እየተጣራ ይገኛል፡፡

የጋሞ ዞን ፖሊስ ኢንዶክትሪኔሽንና ህዝብ ግኑኝነት ሥራ ሂደት አስተባባሪ ኮማንደር አዳነ ኦኬ እንደገለጹት የኮንትሮባንድ ንግድ በህጋዊ መንገድ የሚሰሩትን ነጋደዎች ከውድድር ውጭ በማድረግ መንግስት ከንግዱ ዘርፍ የሚያገኘውን ገቢ ከማቀጨጭም ባሻገር ህገውጥነትን በማስፋፋት በሀገር ደህንነትና በጸጥታ ስራው ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ህብረተሰቡ በመረዳት ይህንን ህገወጥነት በመከላከል ረገድ ከፖሊስ ጎን እንድቆም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ከ2011 በጀት ዓመት ጀምሮ እስካሁን ከ19 ሚልዬን ብር በላይ የሚገመት የ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር መዋን ከዞኑ ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

(ጋሞ ዞን - ለቲክቫህ ኢትዮጵያ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ👌

የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በምስራቃዊ ዞን ወረዳ ጋንታ ኣፈሹም ሶስት ጣብያዎች የኣጨዳ ድጋፍ ኣደረጉ!

የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በምስራቃዊ ዞን ወረዳ ጋንታ ኣፈሹም ሶስት ጣብያዎች የኣጨዳ ድጋፍ ኣደረጉ።

እንደሚታወቀው በትግራይ ክልል በሰፊው የታየው የኣንበጣ ወረረሺኝ ለመከላከል የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች በክልሉ ደቡባዊ ዞን ኣላማጣ ኣከባቢ እንዲሁም በምስራቃዊ ዞን ፍረወይኒ ኣከባቢ ተገኝተው ለኣከባቢው ኣርሶኣደሮች ድጋፍ ኣድርግዋል።

በውስራቃዊ ዞን ወረዳ ጋንታ ኣፈሹም ሰብላቸው ያልሰበሰቡ ኣርሶኣደሮች ጋር በመሄድ የኣጨዳ እገዛ በማድረግ ኣርሶኣደሮቹ ሰብላቸው እንዲሰበስቡ ኣድርግዋል።

በዚ በጎ ስራ ሲሰሩ የነበሩ ከተለያዩ ክልሎች የመጡ ተማሪዎች ኣቅም ለሌላቸው ኣርሶኣደሮች ያደረጉት እገዛ ትልቅ ደስታ እንደፈጠረላቸውና በቀጣይም ከጎናቸው እንደሚሆኑ ገልፀዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው ኣርሶኣደሮችም በበኩላቸው የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ያደረጉላቸው እገዛ ከተለያዩ ወጪዎችና የኣንበጣ ወረረሽኝ እንተከላከለላቸው ገልፀው ለዩኒቨርስው ተማሪዎች ምስጋናቸው ኣቅርብዋል።

(ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር አሚር ስልጣናቸውን ሊለቁ ነው?

አዲስ ስታንዳርድ "በሰበር ዜናው" የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን ስልጣናቸውን ሊለቁ እንደሆነ ገልጿል። ለሚኒስትሩ ስልጣን መልቀቅ ግልፅ የሆነ ምክንያት እንደሌለም ዘገባው አክሏል።

ጉዳዩን እኛም ከጤና ሚኒስቴር ቤተሰቦቻችን ለማጣራት እየሞከርን ነው!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በ451 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እየተገነባ የሚገው የገናሌ ዳዋ ሶስት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በሁለት ወራት ውስጥ ኃይል ማመንጨት ሊጀምር እንደሆነ ተገለፀ፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር አብርሃም በላይ የፕሮጀክቱ አብዛኛው ስራ መጠናቀቁን ለኢዜአ ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ሳይንስ ለኢትዮጵያ ልማት እና ብልጽግና”

የኢትዮጵያ ሳይንስ ሳምንት “ሳይንስ ለኢትዮጵያ ልማት እና ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ነው። የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ከጥቅምት 25 እስከ ኅዳር 02 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ነው የሳይንስ ሳምንት የሚከበረው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Social Enterprise Challenge!!

Apply by Nov 8!
www.bluemoonethiopia.com

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎና - በድሬዳዋ እስከ ጅቡቲ ባለዉ መስመር የተከሰተዉን የአንበጣ ወረርሽኝ ለመከላከል ሁለት አውሮፕላኖችን ማሰማራቱን የምስራቅ አፍሪካ የበረሃ አንበጣ መከላከያ ድርጅት ገለፀ፡፡

(ዋልታ ቴሌቪዥን)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአንበጣ መንጋ...

እኛ ከተማ ያለነው የአንበጣ መንጋው እያደረሰ ያለው ጉዳት የማይደርስብን ከመሰለን እጅግ በጣም ተሳስተናል፤ የአምበጣ መንጋው ዛሬ ትኩረት ካልተሰጠው እና መከላከል ካልተቻለ የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ህይወት ማናጋቱ አይቀርም። ችግሩ በተዘዋዋሪ እያንዳንዳችን ቤት መግባቱም አይቀሬ ነው። ሁላችንም ከአርሶ አደሮቻችን ጎን ልንቆም ይገባል። የአንበጣ መንጋ የተከሰተባቸው አካባቢዎች እንዲሁም አቅራቢያ ከተሞች ላይ የምትገኙ ቤተሰቦቻችን አስፈላጊውን ሁሉ ከወገኖቻችን ጋር እንድታደርጉ፤ ለእገዛ ለሚቀርቡ ጥሪዎችንም ቀና ምላሽ በመመለስ የበሉላቹን እንድታደርጉ እንማፀናለን!!

ቲክቫህ ቤተሰቦች!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#attention

በደቡብ ወሎ ዞን በቃሉ ወረዳ እስካሁን ማለትም እስከ 27/02/2012 ዓ./ም ድረስ በ12 ቀበሌወች የአንበጣ መንጋ የተከሰተ መሆኑ ተገልጿል። በወረዳው በ013፣ 016፣ 017፣ 018፣ 019፣ 020፣ 021፣ 022፣ 023፣ 024፣ 026 እና 027 ቀበሌዎች የተከሰተ ሲሆን 16 ሺ ሄክታር መሬትንም ይሸፍናል። ከዚህም ውስጥ 4800 ሄክታር በማሽላና በሌሎች ሰብሎች የተሸፈነው በአንበጣ መንጋው የተጠቃ በመሆኑ ለጊዜው በአማካይ ከ15-20% ምርት ላይ #ጉዳት አድርሷል። ወረዳው ለበላይ አካል የድረሱልን ጥሪ ለማሰማት ጥረት ያደረገ ቢሆንም አካባቢው ለአውሮፕላን ርጭት ምቹነት የለውም በሚል ተጀምሮ ቀርቷል። በመሆኑም ወረዳው በራሱና ለድጋፍ ከሌሎች ወረዳወችና ተቋማት በመጡ አካላት እንድሁም በጎ ፈቃደኞች ሰፊ ርብርብ እያደረገ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE

ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የኢጋድ ዋና ጸሃፊነቱን ዛሬ በይፋ ከተሰናባቹ ዋና ጸሃፊ ከኬንያዊው አምባሳደር ሙሀቡብ ማሊም መረከባቸው ታውቋል፡፡ መረጃውን ዛሬ ከቀትር በኋላ በትዊተር ገጻቸው ያሰፈሩት፣ የኢጋድ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊ የሆኑት ኑር ሞሐመድ ሺክ ናቸው፡፡

(ዋዜማ ሬድዮ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ወጣቱ አሚር አማን ለምን የስራ መልቀቂያ እንዳስገባ አላውቅም ..." -- የጤና ሚኒስቴር የስራ ኃላፊ

(ጋዜጠኛ ተስፋዬ ጌትነት - ካፒታል)

ዶ/ር አሚን አማን ከወራቶች በፊት ነው የስራ መልቂያ ያስገቡት። ዶ/ር ሊዲያ ወይንም ዶ/ር ኤፍሪም የሳቸውን ቦታ ሊይዙ ይችላሉ። የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚን አማን የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ካስገቡ ሶስት ወር ያልፋቸዋል ሲሉ አንድ የሚኒስቲሩ የስራ ሀላፊ ተናግረዋል። "ወጣቱ አሚን ለምን የስራ መልቀቂያ እንዳስገባ አላውቅም። ትናንትም ቢሮ ሲሰራ ተመልክቸዋለው። እሱ ቦታውን ሲለቅ ሚኒስቴር ዴታዋ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ወይንም የቀድሞ የእናቶች ህፃናት ጤና ዳይሬክተር ወይንም የአሁኑ የስራ ፈጠራ ኮሚሽነር ዶ/ር ኤፍሬም ተክሌ ሊማንጎ ሊተኳቸው ይችላል የሚል ግምት በሰራተኞች ዘንድ አለ" ሲሉ እኚሁ የስራ ኃላፊ ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#MekelleUniversity

የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የመታወቂያ ደብተርን የሚተካ ሶፍትዌር በቅርቡ አዘጋጀተዋል። «ስማርት አይዲ» የተባለዉ ማንነትን መለያ መተግበርያ ወይም application የዜጎችን ዝርዝር መረጃዎች የሚይዝ፣ የወረቀት አሰራርን የሚያስቀር እና  ሕገ ወጥ መረጃን ለመለየት የሚያስችል ነው፡፡ አበልፃጊዎቹ የመቐለ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት የ2011 ዓ.ም የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምሩቃን የሆኑት ኪዳነ ገብረመድህን፣ አረጋዊ ሀይለየሱስና ሌሎች ባልደረቦቻቸው ሲሆኑ ከመታወቂያ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የሚገጥሙ ችግሮችን ለመፍታት አልመው እንደሰሩት ተናግረዋል፡፡ሶፍትዌሩ በሀገር ውስጥ ቋንቋዎች የሚሰራ መሆኑም አበልፃጊዎቹ ገልፀዋል።

(የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መልካም ዜና!

በባሌ ሮቤና አካባቢው ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት በኦሮሞ ባህል ለመፍታት የተካሄደው ውይይት ዛሬ በእርቀ ሰላም ተጠናቋል፡፡ የኦሮሚያ አባገዳዎች ኅብረት ኃላፊ አባገዳ ጎበና ሆላ በእርቀ ሰላም መድረኩ ላይ እንደተናገሩት የባሌ ሕዝብ ለቀረበው የእርቀ ሰላም ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽና ቀና ትብብር አመሰግነዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦብነግ ፓርቲ ልሆን ነው አለ!

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (#ኦብነግ) ወደ ፓርቲነት ራሱን ለመቀየር እየሰራሁ ነው አለ። ለአምስት ቀናት የሚቆየው የግንባሩ አራተኛ ድርጅታዊ ጉባዔ በጎዴ ከተማ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል።

የግንባሩ ሊቀመንበር  አድሚራል መሐመድ ዑመር ጉባዔውን ሲከፍቱ እንደተናገሩት ድርጅታቸው ከነጻ አውጪነት ወደ ፓርቲነት ራሱን በመቀየር ለመንቀሳቀስ ይፈልጋል። ለዚህም ጉባዔው የሕዝቡን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ የፖለቲካ አቅጣጫ የሚነድፍበት እንደሚሆንም አስታውቀዋል።

(ENA)

@tsegabwolde @tikvahethiopia