TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETHIOPIA

መንግስት በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ የሚያቀርበውን ፈሳሽ ዘይት ከውጪ ሊያስገባ ነው፡፡ ዘይቱ ወደ አገር እየተጓጓዘ መሆኑንና እስከ 15 ቀን ድረስ ገብቶ እንደሚከፋፈልም ይጠበቃል፡፡ በየወሩ 33 ሚሊየን ሊትር ፈሳሽ ዘይት እንዲያስገባና እንዲያከፋፍል የተፈቀደለት የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት (ኢግልድ) ዘይቱ ቀደም ብሎ ሲሰራጭ የነበረው እና የረጋው ዘይት በሚከፋፈልበት ዋጋ ለህብረተሰቡ እንደሚቀርብ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ተናግሯል፡፡

በድርጅቱ የሽያጭ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ደጀኑ ተክለ ማርያም እንደተናገሩት 1 455 ኮንቴነር ፈሳሽ ዘይት ከኢንዶኔዢያ ተገንዘቶ ወደ አገር እየተጓጓዘ ነው፡፡ 30 ሚሊየን ሊትሩ ከሚረጋው ዘይት በደረጃ ከፍ ያለና ፈሳሽ ሲሆን 3 ሚሊዮን ሊትሩ ደግሞ የተጣራ የሱፍ ዘይት መሆኑን ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል፡፡ ዘይቱ በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች እንደሚከፋፈልም ተሰምቷል፡፡

መንግስት በወሰነው መሰረት በየወሩ 40 ሚሊየን ሊትር ዘይት ከውጪ ተገዝቶ ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ይከፋፈላል፡፡ በቅርቡ 67 በመቶውን እንዲያስመጣና እንዲያከፋፍል የተፈቀደለት የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት ፈሳሽ ዘይት ብቻ እንደሚያስገባ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ተናግሯል፡፡

(ሸገር ኤፍ ኤም)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መልካም ዜና!

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች በ12 ወረዳዎች በ128 ቀበሌዎች ተከስቶ የነበረው የአንበጣ መነጋ በቁጥጥር ስር መዋሉን የክልሉ የግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ገለጸ። በቢሮው የችግኝ ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ ደጀኔ ሂርጳ እንዳሉት የአንበጣ መንጋው ከጎረቤት ሶማሊያ የመጣ ሲሆን በሁለቱ ዞኖች ውስጥ በ23 ሺህ 323 ሄክታር ሰብል ላይ ቢታይም የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር ተችሏል።

(የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)

@tsegawolde @tikvahethiopia
አቶ ገዱ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር እየተወያዩ ነው!

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከሱዳንና ከግብጽ አቻዎቻቸው ጋር በመሆን በነጩ ቤተ መንግስት ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ጋር እየተወያዩ ነው። ከዚህ በመቀጠልም የሶስቱ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ የአሜሪካ የገንዘብ ተቋም ኃላፊ ስቴቨን መንቺን እና የአለም ባንክ ፕሬዝዳንት በተገኙበት በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ። የኢፌዴሪ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለም በውይይቱ ይሳተፋሉ።

(Embassy Of Ethiopia, Washington DC.)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#EGYPT #SUDAN

ግብፅ ከሱዳን ጋር የሚያገናኛትን ስድስት ሺ ኪሎ ሜትር የባቡር መንገድ ልትገነባ መሆኗን በትራንስፖርት ሚኒስትሯ ካሚል ኢል-ዋዚር በኩል አስታውቃለች ሲል ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡ ፕሮጀክቱ  በግብፅ ደቡባዊ ክፍል ከሚገኘው አቡ ሲምበል ከተሰኘ አካባቢ የሚጀመር ሆኖ አቡ ሃማድ ወደተሰኘች የሱዳን አካባቢ የሚወስድ መንገድ መሆኑንም ዘገባው አመላክቷል፡፡

(ሚድል ኢስት ሞኒተር)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Washington DC

የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ገዱ አንዳርጋቸው ከሱዳን እና ግብፅ አቻዎቻቸው ጋር በመሆን ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በዋይት ሀውስ የተሳካ የጋራ ውይይት መካሄዱን አምባሳደር ፍፁም አረጋ አስታወቁ። ለዚህም ፕሬዝዳንት ትራምፕን አምባሳደሩ አመስግነዋል። አምባሳደር ፍፁም አረጋ ሶስቱ የናይል አገራት ፈጣሪ ለህዝባቸው የሰጣቸውን ይህን ፀጋ በብልሃት በመጠቀም አንዳችን ሌላችንን በማይጎዳ መልኩ ኑሯችን እንዲቀየርና በጋራ ድህነትን የምንሻገርበት መንገድ እዲሆን የኢትዮጵያ ፅኑ ፍላጎት ነው ሲሉ ከውይይቱ በኋላ በፌስ ቡክ ገጻቸው አስታውቀዋል። የሶስቱ አገራት ውጭ ሚኒስትሮች የጋራ ውይይትም በአሜሪካው የገንዘብ ሚንስትር በተገኙበት ቀጥሎ እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

(EBC)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቲክቫህ ኢትዮጵያ!

በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚማሩ እና በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ያላቸው፣ በመልካም ስነ ምግባር የታነፁ፣ ትምህርታቸውን እንደጨረሱም ይህቺን ምስኪን ሀገር እና ህዝቦቿን ለማገልግለ ትልቅ ህልም ያላቸው ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ለትምህርት የሚሆናቸውን እገዛ ማግኘት ያልቻሉ፤ ቤተሰቦቻቸው የአቅም ውስንነት ያለባቸውን ወንድምና እህቶቻችን በአቅማችን ለማገዝ ዝግጅታችንን አጠናቀናል።

ለጊዜው ተመራቂዎችን ብቻ ይመለከታል፦

•ላፕቶፕ(PC)
•መፅሄት ማሰሪያ የገንዘብ ችግር ያለባቸውን
•ሱፍ ለወንዶች(ለሴቶች ደግሞ ለምርቃታቸው የሚያስፈልጋቸው አልባሳት)


መልካም ስራ ከራስ ነውና የሚጀመረው እንደ መነሻ ከሁለት ዩኒቨርሲቲዎች ከሚማሩ ሁለት ተማሪዎች እገዛ(ስጦታ) የምንጀምር ይሆናል (አንድ አንድ እና አንድ ሴት)። የት ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ተማሪዎች እንደሆኑ በቅርቡ የምናሳውቅ ይሆናል። ተማሪዎቹን የመለየት ስራ ከተለያዩ አካላት ጋር ይሰራበታል። በምን መስፈርት ቲክቫህ ተማሪዎቹን እንደመረጠም ይገልፃል።

እገዛውን የምናደርገው (ስጦታውን የምናበረክተው) ቤተሰቦቻችን ከሚያስነግሯቸው ማስታወቂያዎች ላይ ከሚገኘው ገቢ ብቻ ነው። የትኛውም መንግስታዊ ሆነ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በዚህ ላይ እገዛ አያደርግልንም። (ቲክቫህ ከዚህ ቀደምም ቤተሰቦቹ በሚያስነግሩት ማስታዉቂያ የሚያገኘውን ገቢ ለተለያዩ በጎ አላማዎች ሲያውል እንደነበር አይዘነጋም)

ውድ ቤተሰቦቻችን ይህን እቅድ ከዓመት በፊት አጋርቻችሁ ነበር። በሀገራችን በነበረው ጥሩ ያልሆነ ሁኔታ እና በእኛ የአቅም ውስንነት😊ምክንያት እቅዱን ማሳካት ሳንችል ቀርተናል።

እኛ ሁለት ብለን ጀምረናል፤ ነገ ብዙ እንደምንሆን እናምናለን!!

ቲክቫህ ቤተሶቦች!!


አስተያየት መቀበያ👉 @tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
🔖እናስተዋዉቅዎ!
#Hot_Belt - ይጠቀሙ 0931081987
በሙቀት ውፍረት የሚቀንስ፤ ከልብስ ሰር የሚደረግ ሼፕ የሚያስዝ አና የሚያሳምር
የሰዊነትዎ ውፍረት ለመቀነስ! (👨ለወንድም) (ለሴትም👩) የሚሆን •ያሉበት ቦታ ድረስ ያለ ተጨማሪ ክፍያ እናደርሳለን (free delivery)🏍ዋጋ➡️1000 ብር
👉telegram @mastercomputers
👉Price 1000 birr .
አድራሻ- መገናኛ መተባበር ህንፃ 1ኛ ፎቅ 101A ወይም 101A ፊትለፊት
☀️መልካም ቀን ይሁንላችሁ! #ETHIOPIA☀️
🎬ቪዲዮ ኤዲቲንግ መማር ይፈልጋሉ? የራስዎትን ቪዲዮ ኢዲት ከማድረግ ጀምሮ ኣስከ ትላልቅ ዶክመንተሪዎች፣ ይህ የቪዲዮ ኢዲቲንግ ኮርስ አጫጭር ፊልም፣ ዶክመንተሪ፣ ሙዚቃዎችን... እንድትሰሩ ያደርጋቹሃል። ታዋቂ የኢዲቲንግ ሶፍዌሮችን በፕሮፌሽናል አስትማሪዎች ይሰጣሉ።

20 ቦታዎች ብቻ ስላሉን አሁኑኑ ይደውሉ እና ይመዝገቡ:
☎️ 0118633128 or +251991173014
🗓 ህዳር 1 ( November 11 ) ይጀምራል።
🚕 አድራሻ፣ ቦሌ መዳሃንያለም ፣ ከከቤ ፓስተሪ አጠገብ ፣ ዘውዱ ገሰሰ ህንጻ 2ተኛ ፎቅ።

በዚህ ወር የሚጀምሩ ሌሎች ስልጠናዎች፡
☑️Advance graphic design
☑️Autodesk revit essential
☑️Soial media marketing
☑️Website Development

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ https://t.iss.one/traingobeze ፌስቡክ ፣ ኢንስታግራም እና ትዊተር ላይ ያግኙን @traingobeze
በኅዳሴ ጉዳይ የጋራ መግለጫ ወጣ!

የግብፅ፣ የኢትዮጵያ፣ የሱዳን፣ የዩናይትድ ስቴትስና የዓለም ባንክ የጋራ መግለጫ፦

የግብፅ፣ የኢትዮጵያና የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ እንዲሁም ልዑኮቻቸው ከዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስትርና ከዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት ጋር ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ ጥቅምት 26/2012 ዓ.ም. ተገናኝተዋል።

በታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ አሞላል እና ማንቀሳቀስ (ኦፕሬሽን) ላይ አጠቃላይ፣ የትብብር፣ የተቀናጀ፣ ዘላቂና ሁሉም ተጠቃሚ ለሚሆኑበት ስምምነት እንዲሁም ይህንን ፅኑ አቋማቸውን በ2008 ዓ.ም. የመርኆች መግለጫ መሠረት ተግባራዊ የሚያደርጉበትን ግልፅ ሂደት ለመፍጠር ቁርጠኛነታቸውን ሚኒስትሮቹ በድጋሚ አረጋግጠዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በውኃ ሚኒስትሮቻቸው ደረጃ የሚካሄዱ አራት መንግሥታዊ የቴክኒክ ስብሰባዎችን ለማድረግ የደረሱበትን ስምምነት አስታውሰዋል። የዓለም ባንክና ዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ እንዲሰጡና በየስብሰባዎቹ ላይም በታዛቢነት እንዲገኙ ሚኒስትሮቹ ተስማምተዋል።

ሚኒስትሮቹ በተጨማሪም ስምምነቱን እስከ ጥር 6/2012 ዓ.ም. ለማጠናቀቅ ለመሥራት፣ እንዲሁም ኅዳር 28/2012 ዓ.ም. እና ጥር 4/2012 ዓ.ም. ሂደቱን ለመገምገምና ለመደገፍ ዋሺንግተን ዲሲ ላይ በሚደረጉ ሁለት ስብሰባዎች ላይ ለመገኘት ተስማምተዋል። እስከ ጥር 6/2012 ዓ.ም. ስምምነት ላይ የማይደረስ ከሆነ የ2008 ዓ.ምቱ የመርኆች መግለጫ አንቀፅ 10 ተግባራዊ እንዲሆን ሚኒስትሮቹ ተስማምተዋል።

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-07

(VOA)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በሲዳማ ዞን አርቤጎና ወረዳ ቀጠና ቀበሌ የመራጮች ምዝገባ በሠላም እየተካሄደ ይገኛል!" - አርቤጎና ቲክቫህ ቤተሰቦች

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዛይ ራይድ ታክሲ ከ40 ሆቴሎች ጋር ስምምነት ፈፀመ!

ዛይ ራይድ በአዲስ አበባ ሸራተንን ፣ራዲሰን ብሉን ጨምሮ በ40 ሆቴሎች ለሚስተናገዱ ደንበኞች የራይድ ታክሲ አገልግሎት ለመስጠት ስምምነት መፈረሙን የድርጅቱ መስራች አቶ ሀብታሙ ተናግረዋል። በስምምነቱ መሰረት ዛይ ራይድ ታክሲዎቹ ላይ ካሜራ የሚያሰገጥም ሲሆን ይሄም ሆቴሎች እነሱ ጋር አልጋ ይዘው በከተማው የሚንሸራሸሩት ደንበኛቻቸው አደጋ ወይንም ችግር ቢያጋጥማቸው ቶሎ ለማወቅ ይረዳቸዋል ተብሏል።

(ጋዜጠኛ ተስፋዬ ጌትነት-ካፒታል ጋዜጣ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ገበሬዎች የድረሡልኝ ጥሪ እያስተላለፉ ነው!

የክልሉ እና የፌደራል መንግሥት ዝምታ እስከመቼ?

በመርሳ ከተማ የተፈጠረው "የአንበጣ መንጋ" በደረሡ ሰብሎች ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው፡፡ ገበሬዎችም የድረሡልኝ ጥሪ እያስተላለፉ ነው፡፡ አንበጣውን ለማባረር የወጣው ማህበረሰብ አስተባባሪ እና መሪ ያስፈልገዋል።

(መርሳ ከተማ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#attention

አርሶ አደሮች የደረሰ እና በከፊል የደረሰ ሰብል እንዲሰበስቡ ጥሪ ተላለፈ!

ለቃሉ ወረዳ አርሶአደሮች በሙሉ የተላለፈ ጥሪ፦

ሰሞኑን በተከሰተው የአንበጣ መንጋ በርካታ ሰብሎች መውደማቸው ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ አሁን ላይ እስካሁን ካየነው በዓይነቱ የተለየ የአንበጣ መንጋ ከሗላ እየመጣ በመሆኑ ይህን ለመከላከል የማይቻልና ከቁጥጥር ውጭ በመሆኑ የደረሰውን ሰብል ብቻ ሳይሆን በከፊል የደረሰውን ሰብላችሁን እንድትሰበስቡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

የተለያዩ ድጋፍ የሚያደርጉ አካላትም በየማሳው እየተንቀሳቀሱ ስለሆነ በማሳችሁ ላይ ሆናችሁ ሰብሉን የመሰብሰብና አንበጣውን የመከላከል ስራ እንድታከናውኑ የቃሉ ወረዳ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

(የቃሉ ወረዳ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"...አሁን ላይ እስካሁን ካየነው በዓይነቱ የተለየ የአንበጣ መንጋ ከሗላ እየመጣ በመሆኑ ይህን ለመከላከል የማይቻልና ከቁጥጥር ውጭ በመሆኑ የደረሰውን ሰብል ብቻ ሳይሆን በከፊል የደረሰውን ሰብላችሁን እንድትሰበስቡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!"

(የቃሉ ወረዳ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን)

#ሼር #share

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በጉጂ ዞን በወዳራ ወረዳ ዛሬ ማለዳ 1፡35 አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተነገረ፡፡ በአደጋው የአንድ ሰው ሂወት ወዳዉኑ ሲያልፍ በበርካታ ተሳፋሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የዘገበው OBN ነው፡፡ ጉዳት የደረሰባቸው መንገደኞች በአዶላ ዋዩ አጠቃላይ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው ተብሏል፡፡

(OBN)

@tsehabwolde @tikvahethiopia
ከባድ የመግደል ሙከራ ያደረገዉ ተከሳሽ በፅኑ እስራት ተቀጣ!

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 27(1) እና 539(1)(ሀ) ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በመተላለፍ በፈፀመዉ ከባድ የሰዉ ግድያ ሙከራ ወንጀል ክስ ተመስርቶበት የክስ ሂደቱ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡

የወንጀል ዝርዝሩ እንደሚያስረዳዉ ተከሳሹ ሰዉን ለመግደል በማሰብ በቀን 27/10/2010 ዓ.ም በግምት ከሌሊቱ 7፡00 ሲሆን በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ክልል ዉስጥ ዘሚካኤል ይርጋሸዋ የተባለን የግል ተበዳይ ጭካኔን በተሞላበት ሁኔታ በመጥረቢያ 1 ጊዜ ጭንቅላቱን፣1ጊዜ ግንባሩንና በመጥረቢያዉ እጀታ እግሩን በመምታት የራስቅል አጥንት ስብራትና የአጥንት መሰርጎድ እንዲደርስበት አድርጓል፡፡

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-07-2

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ምዝገባ ሰላማዊ በሆነ መልኩ እየተከናወነ ይገኛል። እጅግ በርካታ ሰዎችም ምዝገባ እያከናወኑ እንደሚገኙ ከተለያዩ የሲዳማ ዞን ከተሞች ከሚኖሩ ቤተሰቦቻችን የሚመጡልን መልዕክቶች ያስረዳሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia