TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbeba

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች በአሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ምክንያት የውሃ ስርጭት መቋረጡ ተገለፀ፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች በተደጋጋሚ እየተፈጠረ ባለው የኤልክትሪክ ኃይል መቆራረጥ በውኃ ምርት ፣ አቅርቦትና ስርጭት ላይ ከፍተኛ መስተጓጎል እየፈጠረ መሆኑን የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ትላንት ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ በተፈጠረ የኤሌክትሪክ መቋረጥ ምክንያት በአቃቂ ከርሰ ምድር የተወሰነ ክፍል ውሃ ማምረት አልቻለም ነው የተባለው፡፡

በዚሁ ምክንያት አቃቂ ፣ በቃሊቲ ፣ በሳሪስ አቦ፣ ቦሌ ቡልቡላ፣ ጎተራ፣ ቦሌ ፣ ኦሎምፒያ፣ ስታዲየም፣ ለገሀር፣ ሜክሲኮ፣ ልደታ፣ ጦር ሀይሎች፣ መርካቶ(በከፊል)፣ ቀራኒዮ፣ ቤቴል፣ አለም ባንክ፣ አየር ጤና ፣በዘነበ ወርቅ፣ መከኒሳ ፣ካራ ቆሬ ፣በጀሞ ፣ለቡ፣ሀና ማሪያም፣ጎፋ እና ቄራ አከባቢዎች የውሃ ስርጭት ተቋረጧል፡፡

ችግሩን ለመፍታት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጥረት እያደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡ በተጠቀሱት አከባቢዎች የምትኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች በትዕግስት እንድትጠብቁን ጠይቋል፡፡

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባሁኑ ሰአት አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ውስጥ እንደሚገኝ ተገለፀ። ጋዜጠኛው በፖሊስ ኮሚሽኑ ውስጥ ለመገኘቱ እንደ ምክንያት የተባለው ደግሞ በምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት ስብሰባ አድርጎ ሲወጣ የተሰባሰቡ ቡድኖች ጉዳት ሊያደርሱበት ሲሞክሩ ፖሊስ ደርሶ ወደ ኮሚሽኑ ግቢ እንዳስገባው ነው ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ የገለፀው። የሪፖርተሩ ጋዜጠኛ ታምሩ ፅጌ ስለጉዳዩ የማጣራት ወደ ጋዜጠኛ እስክንድር ጋር ደውሎ ያገኘው ምላሽ፦ "አሁን ማናገር ስለማልችል መልሼ እደውልልሀለሁ" የሚል ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

በአዲስ አበባ የደቡብ ኢትዮጵያ ወጣቶች ማህበር 12ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ኮንፈረንስ መካሄድ የጀመረው ሰሞኑን በተከሰተው የጸጥታ መጓደል ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት በማድረግ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የደቡብ ኢትዮጵያ ወጣቶች ማህበር ሰብሳቢ ወጣት አብርሀም ፍቃዱ እንደገለጸው ማህበሩ በከተማዋ ለሚገኙ የደቡብ ተወላጆች ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የሚያችሉ ተግባራትን ሲየከናውን ቆይቷል፡፡ ለአብነትም በጌዲኦና ጎፋ ዞኖች የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመርዳት ከ500 ሺህ ብር በላይ እንዲሁም በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ የወጣት ማዕከላትን በቁሳቁስ ለማደራጀት ግምቱ ከ700 ሺህ ብር በላይ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-03-3

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

በመኖሪያ በቱ ብሬን (የመትረየስ ጠመንጃ) የሆነ የቡድን የጦር መሳሪያ ከመሰል 83 ጥይት እና 30 የሽጉጥ ጥይቶችን ሸሽጎ ለመሸጥ ሲያስማማ የነበረ ግለሰብ ተይዞ ምርመራ እያጠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ግለሰቡ እና የጦር መሳሪያው ሊያዝ የቻለው ከህብረተሰቡ የተገኘን መረጃ መነሻ በማድረግ ነው፡፡

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው ኮተቤ መሳለሚያ ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ አንድ ግለሰብ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ አንድ ብሬን (የመትረየስ ጠመንጃ) የቡድን የጦር መሳሪያ ከመሰል 83 ጥይቶች እና ከ30 የሽጉጥ ጥይቶች ጋር ደብቆ ገዥ በማፈላለግ ላይ እንዳለ መረጃ የደረሰው የፌዴራልና የአበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከሕብረተሰቡ ያገኘውን መረጃ መሰረት በማድረግ በተደረገው ብርቱ ክትትል ሁኔታውን ለቅርብ ኃላፊዎቻቸው አሳውቀው ለፖሊስ በቂ ማስረጃ በማሰባሰብ ግለሰቡ የጦር መሳሪያውን አሳልፎ ሳይ ሸጠው ከፍ/ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት በመኖሪያ ቤቱ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ የጦር መሳሪያውንና ጥይቶቹን ማግኘቱን የጉዳዩ መርማሪ ም/ሳጅን ጌታነህ ታረቀኝ ገልፀዋል፡፡

https://telegra.ph/ETH-11-05-6

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

ኢ/ር ታከለ ኡማ በሁለት ክፍለከተሞች ከ15 ዓመት በላይ ምላሽ ሳያገኙ ለቆዩ 874 ነዋሪዎች የቤት ባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ሰጥተዋል፡፡ ነዋሪዎቹ በተለያዩ አደጋዎችና በተለያዩ ምክንያቶች ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተነስተው የነበሩ ነዋሪዎች ናቸው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በነገው እለት ሶስት አዳዲስ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ግንባታ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በሚገኙበት በይፋ ያስጀምራል።

ፕሮጀክቶቹ ከቦሌ ሚካኤል ቀለበት መንገድ የላይና የታች መንገድ-ቡልቡላ ካባ መግቢያ የሚደርሰው 5.5 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው፣ ሁለተኛው ደግሞ ከአውቶቡስ ተራ-መሳለሚያ-18 ቁጥር ማዞሪያ አድርጎ ኮልፌ ቀለበት መንገድ ፕሮጀክት 3.4 ኪ.ሜ ርዝመትና 40 ሜትር የጎን ስፋት የሚኖረው ሲሆን ከአውቶቢስ ተራ-18 ቁጥር ማዞሪያ ያለው ነባር መንገድ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ያለበት እንደሆነ ይታወቃል።

በተያያዘም ከለገሀር በጥላሁን ገሰሰ አደባባይ እስከ ጋዜቦ አደባባይ የመንገድ ፕሮጀክት በባለስልጣኑ የራስ ሀይል የሚገነባ ሲሆን 1. 1 ኪሎ ሜትር ርዝመትና የእግረኛ መንገድን ጨምሮ የ 10 ሜትር ስፋት ይኖረዋል። የመንገድ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ከለገሀር በፍላሚንጎ ጀርባ አድርጎ ወደ ቦሌ ለመጓዝ አማራጭ መንገድ በመሆን በመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ ይደረግ የነበረውን የትራፊክ መጨናነቅ ችግር በከፍተኛ ደረጃ ይቀርፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው እነዚህን የመንገድ ፕሮጀክቶች በሁለት አመታት ለማጠናቀቅ በልዩ ትኩረት ይሰራል ተብሏል።

(EPA)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

"ሰው መሆን ይቀድማል!" ኪነ ኢትዮጵያ- አዲስ መንፈስ የተሰኘ የህዝብ ለህዝብ መድረክ የመክፈቻ ስነ ስርዓት በትላንትናው ዕለት በኤሊያና ግራንድ ሆቴል ተካሂዷል፡፡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሞያተኞች ጋር በጋራ በመሆን ያዘጋጀው ይህ መድረክ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ነበር የተከፈተው፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ ታዋቂና አንጋፋ አርቲስቶች፣ የክልል ርዕሰ መስትዳድሮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው ነበት፡፡ የህዝብ ለህዝብ መድረኩ ዓላማም ሀገራዊ አንድነትን፣ ሰላምን፣ ወንድማማችነትንና አብሮነትን በማጠናከር ኢትዮጵያዊ አንድነትን ማጎልበት መሆኑን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#AddisAbeba

ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ "አጠና ተራ አካባቢ" ከባድ የትራፊክ አደጋ መድረሱን የቤተሰባችን አባላት በቪድዮ በታገዘ መረጃ አሳውቀውናል። የደረሰውን ጉዳት በሚመለከት መረጃዎችን ለማግኘት ጥረት እናደርጋለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

ኢ/ር ታከለ ኡማ ከአፋን ኦሮሞ ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ የሆነውን ቡርቃ ዋዩ እንደኛ ደረጃ ት/ቤትን ተመልክተዋል። ጆሞ አካባቢ የሚገኘው ትምህርት ቤቱ ወደሥራ የገባው በዚህ ዓመት ሲሆን 5342 ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል።

በትምህርት ቤቱ ያለውን የትምህር አሰጣጥ ሂደት የተመለከቱት ኢ/ር ታከለ ኡማ ከመምህራን እና የተማሪ ወላጆች ጋር ቆይታ አድርገዋል። ወላጆችም በዩኒፎርም ስርጭት ወቅት በትምህርት ቤቱ ስላጋጠመው እጥረት እና ሌሎች ችግሮችን በተመለከተ ለኢ/ር ታከለ ጥያቄ አቅርበዋል።

ኢንጂነር ታከለ በበኩላቸው አስተዳደሩ ይህንን ት/ቤት ጨምሮ በሌሎች ትምህርት ቤቶች ያሉ ጥያቄዎች ላይ በአጭር ጊዜ ማስተካከያ እንደሚያደረግ ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

የአማራና የትግራይ ክልል ምሁራን ለሶስት ቀናት የሚቆይ ውይይት በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ ማካሄድ ጀምረዋል። የሁለቱን ክልሉች ምሁራን ጉባዔም የሰላም ሚኒስቴር ከሌሎች ተባባሪ አካላት ጋር በመሆን ማዘጋጀቱም ተገልጿል።

(EBC)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር ለኢ/ር ታከለ ኡማ በህጻናትና እናቶች በመደገፍ በኩል ላበረከቱት አስተዋጽኦ ስጦታ አበረከተ፡፡ ማህበሩ 7ኛውን መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል፡፡ በጉባኤው ላይ ኢ/ር ታከለ ኡማ ተገኝተዋል፡፡

የሴቶች ማህበሩ ኢ/ር ታከለ ኡማና የከተማ አስተዳደሩ በተያዘው አመት በስፋት የተጀመረው የተማሪዎች የምገባ መርሀግብር የመሪነት ሚና በመጫወታቸው ፤እንዲሁም የተማሪዎችን የመማሪያ ቁሳቁስና ዩኒፎርም አቅርቦት ላይ የከተማ አስተዳደሩ ያከናወነው ተግባር በማህበሩ አድናቆት ተችሮታል፡፡

ከዘህ በተጨማሪም በክረምቱ የአረጋውያንን ቤት በማደስ ከተማ አስተዳደሩ ያከናወነው ተግባር የሚመሰገንና መቀጠልም ያለበት ነው ተበሏል፡፡ ለእነዚህና የከተማ አስተዳደሩ ሴቶችና ሀጻናትን በሚመለከት ላከናወናቸው ተግባራት ምስጋና መገለጫ የሚሆን የ"ካባ" ስጦታ ለኢ/ር ታከለ ኡማ ተበርክቶላቸዋል፡፡

ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ -- የከተማ አስተዳደሩ ለሴቶችና ህጻናት የሚሰጠው ትኩረት ቀጣይነት ያለው መሆኑን ጠቅሰው"ለሴቶች ፣ህጻናትና አረጋውያን የማትመች ከተማን መፍጠር አንፈልግም " ብለዋል፡፡

(EPA)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

- በአዲስ አበባ ከተማ "ለአረንጓዴ ቦታነት" ተከልለው የነበሩ ቦታዎች ከግሉ ዘርፍ ጋር በጋራ በመሆን ፓርክ እንዲሰራባቸው ተወሰነ፡፡ በከተማዋ በተለያዩ ቦታዎች ለአረንጓዴ ቦታነት በሚል ለረጅም አመታት ተከልልው የነበሩ ቦታዎች ቢኖሩም ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጡ እንዳልነበረ የከንቲባ ፅህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

- በተጨማሪም አካባቢዎቹ ለህገወጥ የመሬት ወረራ የተጋለጡ እና ለቆሻሻ ማከማቻነት የዋሉ ሆነዋል፡፡ ይህንን የገመገመው የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔም ቦታዎቹ ከባለሃብቶች ጋር በመሆን የተሟላና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ያማከሉ መዝናኛ ያላቸው ፓርኮች እንዲሰራባቸው ወስኗል፡፡

- ፓርኮቹ ለነዋሪዎች ተጨማሪ የመዝናኛ አማራጭ እንደሚሆኑና የከተማዋ አረንጓዴ ሽፋን ለማሳደግም የካቢኔው ውሳኔ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ በከተማዋ የሚገኙ የህዝብ መዝናኛ ማእከሎችን ማሳደግ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝም ነው ፅህፈት ቤቱ ያስታወቀው፡፡

(Mayor Office AA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbeba

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል፡፡ ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ጉባኤ ምክር ቤቱ የ2012 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ያካሂዳል ተብሏል፡፡ በፌዴሬሽን ምክር ቤት አዳራሽ ከዛሬ ጀምሮ በሚካሄደው መደበኛ ጉባኤ ተደጋጋሚ የህዝብ ጥያቄዎች የሚነሱባቸውን አራት ተቋማት ማለትም ትምህርት ቢሮ፣ የቤቶችና ኮንስራክሽን ቢሮ፤ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ እንዲሁም የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ሪፖርታቸውን ለምክር ቤቱ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

(አዲስ ሚድያ ኔትወርክ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbeba #Lyon

ኢ/ር ታከለ ኡማ ከፈረንሳይዋ ሊዩን ከተማ ፕሬዝዳንት ዴቪድ ኬሚልፊልድ ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱ በአዲስ አበባ እና በሊዬን ከተማ መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር ሲሆን በተለያዩ መስኮችም በጋራ ለመስራት የሚያስችል ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ADDISABEBA

ማስታወሻ!

በነገው ዕለት (ታህሳስ 02/2012) ከለሊቱ 11:00 ሰዓት ለጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ የሚደረገው የአቀባበል ሥነ ሥርዓት እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ጀምሮ እስከ ብሔራዊ ቤተ-መንግስት ባሉት ግራና ቀኝ መንገዶች ላይ ተሸከርካሪን ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ማቆም የተከለከለ ነው።

አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገድ እንድትጠቀሙ፦

• ከኡራኤል ቤ/ክርስቲያን ወደ መስቀል አደባባይ

• ከቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ወደ መስቀል አደባባይ

• ከቦሌ ኤድናሞል ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ

• ከብሔራዊ ቤተ-መንግስት፤ ከፍል ውኃ፤ ከለገሀር፤ ከካሳንችስ፤ ከሳንጆሴፍ ትምህርት ቤት፤ ከስታዲየምንና ከሃራምቤ ሆቴል አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለጊዜው ዝግ ይሆናሉ።

የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘት እና መረጃ ለመስጠት የምትፈልጉ በስልክ ቁጥሮች ፡-
011-1-11-01-11
011-5-52-40-77
011-5-52-63-02
011-5-52-63-03 ወይም በነጻ ስልክ መስመር 991 እና 987 መጠቀም ይቻላል፡፡

(የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን)

@tikvahethiopiaBot @tikvagethiopia